ሰራተኛ በህይወቱ ላይ አደጋ ላደርስበት በሚችል አኳኋን እንዲሰራ ማድረግ ህገወጥ ድርጊት ስለመሆኑና ሰራተኛው ያለማስጠንቀቂያ ውል እንዲያቋርጥ በቂ ምክንያት ስለመሆኑ፣ የአ/ቁ. 14/ሰ/ እና አንቀጽ 32/1/ እድገት ተስፋ ሁለገብ ሀ/የተ/የህ/ ስራ ማህበር እና እነ አቦዬ ለሜሳ
No summary available.
መስከረም 29 ቀን 2010ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወል ሙስጠፋ አህመድ አብርሃ መሰለ ጳውሎስ ኦርሺሶ ሰናይት አድነው አመልካች፡- እድገት ተስፋ ሁለገብ ሸ/ኃ/የተ/የህ/ሥ/ማህበር - የስራ አመራር ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ታመነ መኮንን ቀረቡ።
ተጠሪ፡- አቦዬ ለሜሳ/ባለቤታቸው አቶ ሐይሉ አስፋውና ወራሾች እነ አሉላ ሀይሉ - ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልን በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዳዩ በመጀመሪያ የታየው በፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። የሥር ከሳሽ የአሁን ተጠሪ ከአመልካች ድርጅት ጋር ከሐምል 28 ቀን 1978 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 11 ቀን 2008 ዓ.ም በተለያዩ የስራ መደቦች 1,300.00/አንድ ሺህ ሶስት መቶ ብር/ እየተከፈላቸው ሲሰሩ እንደነበረ ነገር ግን አመልካች ከሚሰሩበት የነበረ የስራ መደብ ሳይፈልጉ በማንሳት ፤ምክንያቱ ሳይነገራቸው፤የውድድር ስርዓት ሳያደርጉ፤የተመደቡት የስራ መደብ ለማታ ስራ የማይመችና ሞያቸው ወዳልሆነ የስራ መደብ የስራ ዝውውር ደብዳቤ የሚገልፅ ደብዳቤ የደረሳቸው መሆኑን፤በዚሁ ምክንያት ዝውውሩ ላይ ቅሬታ አቅርበው እያሉ አመልካች የስራ ውሉ ያለአግባብ ስላቆረጠብኝ የካሳ፤የስራ ስንብት ክፍያ፤ ክፍያ ለዘገየበት ክፍያ እንዲከፈላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል።
የአሁን አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስ የስራ ዝውውሩን ያደረገበት ምክንያት ተጠሪ የተዛወሩበት የስራ መደብ ላይ ለረጅም አመታት የሰሩበት እንደሆነ እስከ ምሽቱ 4፡00 ሰዓት የሚያሰራው የመዝናኛ ክበቡ የስራ ባህሪ መሆኑን ፤የተጠሪ ዋናው ምክንያታቸው ትምህርት ስለምማር አይመቸኝም የሚል መሆኑን፤ስራ እየሰሩ ምላሽ መጠበቅ ሲችሉ ከ14/03/08 ዓ.ም እስከ 11/04/08 ዓ.ም ስራ ትተው ቤታቸው መቀመጣቸው ትክክል እንዳልሆነ ያቀረቡት የክፍያ ጥያቄም ጡረታ የሚዋጣላቸው በመሆኑ ላከፈላቸው እንደማይገባ በመግለፅ የመከላከያ መልሳቸውን አቅርበዋል።
ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም ተጠሪ የተመደቡት በሙያቸው መሆኑን፣ የተመደቡት የስራ መደብ ለህይወታቸው አስጊ አለመሆኑን፤ተጠሪ ወደተመደቡበት ስራ ሄደው አለመስራታቸው፤በትምህርት ምክንያት ዝውውሩን የሚቃወሙ ስለመሆኑ እንደማያሳይ፤ ተጠሪ ቅሬታ አቅርበው ከስራ መቅረታቸው፣ ከስራ የቀሩበት በበቂ ምክንያት ነው የሚያስብል አለመሆኑን በምክንያትነት ጠቅሶ ተጠሪ ከ5 ተከታታይ ቀናት በላይ ከስራ መቅረታቸው በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 27/1/ለ/ መሰረት ስንብቱን ህጋዊ ያደርገዋል፤በተጠሪ የተጠየቁት ክፍያዎች የህግ ድጋፍ የልላቸው ናቸው በማለት ውሳኔ ሰጥተዋል። የአሁን ተጠሪ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ በመቃወም ለፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ተጠሪ እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት እንዲሰሩ መደረጉ አግባብ አለመሆኑን፤ተጠሪ ላቀረቡት ቅሬታ ምላሽ ጠብቅ ሲባሉ ወደስራ ገበታቸው ያልገቡት ተጠሪ ላይ ጫና በሚያሳድር ሁኔታና መብታቸውን ባላከበረ መልኩ በመሆኑ ከስራ ገበታቸው ያለበቂ ምክንያት ቀርተዋል አያሰኘም በማለት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ በመሻር ስንብቱ ህገወጥ ነው፤ ስለሆነም የህገወጥ ስንብት ውጤት ክፍያዎቹ በተመለከተ የግራ ቀኙን ማስረጃ በማየት ውሳኔ እንዲሰጥበት ለስር ፍርድ ቤት መልሶታል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበውም ይህንኑ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። አመልካች ጥር 12 ቀን 2009 ዓ.ም በፃፉት አቤቱታ በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ተፈጽሟል የሚሉባቸውን ምክንያቶችን ዘርዝረው አቅርበዋል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ በመደረጉ ተጠሪ መልስ እንዲሰጡበት በታዘዘው መሰረት ሐምል 21 ቀን 2009 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርበዋል። የአመልካች የመልስ መልስ መስጠት መብታቸው በመታለፉ የቀረበ የመልስ መልስ የለም።
የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ይህ ችሎትም አቤቱታ የቀረበበትን ውሳኔ ከግራ ቀኙ ክርክርና ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የዚህን ችሎት ምላሽ የሚያስፈልገው ነጥብ በጉዳዩ ላይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ሆኖ ተገኝቷል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ ይሰሩበት ከነበረው የስራ መደብ ወደልላ የስራ መደብ የተዛወሩ መሆናቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ እንደደረሳቸው ስራው በምሽት የሚሰራ በመሆኑ ለህይወታቸው አስጊ እንደሆነና ልሎች ምክንያቶች በመግለፅ እንዲስተካከል አቤቱታ አቅርበው ምላሽ በመጠባበቅ እያሉ ከ5 በላይ ተከታታይ የስራ ቀናት ከስራ ቀርተዋል በማለት አመልካች የስራ ውሉ የተቋረጠ መሆኑን ከውሳኔ ግልባጭ ተገንዝበናል። በመሰረቱ የስራ ውል ላቋረጥ የሚችልባቸው መንገዶች በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 23 ስር ተመልክቷል። አንደኛው መንገድ በአሰሪው አነሳሽነት የሚደረግ የስራ ውል መቋረጥ እንደሁኔታው በማስጠንቀቂያ ወይም ያለማስጠንቀቂያ ላደረግ የሚችል ሆኖ የምክንያቶቹ ዝርዝር እና አፈፃፀሙ ከአንቀፅ 26 እስከ 30 ተደንግገው ይገኛሉ። በተጨማሪም በሕብረት ስምምነት ያለማስጠንቀቂያ ውሉን ለማቋረጥ የሚያበቃ ምክንያት ተደርጎ የተወሰደ ጉዳይም በአሰሪው አነሳሽነት ያለማስጠንቀቂያ ውሉን ላያቋርጥ የሚችል መሆኑ በአንቀጽ 27/1/ተ/ ተደንግጎ ይገኛል። ስለዚህ በአዋጁ በተደነገጉ ምክንያቶችና ሁኔታዎች የሚፈፀም የስራ ውል ማቋረጥ ህጋዊ የስራ ማቋረጥ ሲሆን ከነዚህ ውጭ የሚደረጉ የስራ ውል ማቋረጥ ህገወጥ መሆኑን ከአንቀጽ 42 ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል።
በአመልካችና ተጠሪ መካከል የተደረገው የስራ ውል በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/1996 መሰረት መብትና ግድታ ያቋቁማል። በህጉ አንቀጽ 12 የአሰሪው ግድታ በአንቀጽ 13 ደግሞ የሰራተኛው በግልፅ ተደንግጎ ይገኛል። ህገወጥ ድርጊት የተባሉት የአሰሪና ሰራተኛ ቅደም ተከተል በአንቀጽ 14/1/ እና 14/2/ በዝርዝር ሰፍረው ይገኛሉ።
የአሰሪው ግድታ ከተገለፁት ከስራው ጋር በተያያዘ የሰራተኛውን ደህንነትና ጤንነት ለመጠበቅና ከአደጋ ለመከላከል የሚያስፈልጉትን እርምጃዎች ሁሉ የመውሰድና እነዚሁንም እርምጃዎችን በሚመለከት ረገድ አግባብ ባላቸው ባለስልጣኖች የሚሰጡትን ደረጃዎች መመሪያዎች የመከተል በአሰሪው ላይ የተጣለ ግድታ ነው። በልላ በኩል አሰሪውና ሰራተኛው ህገወጥ ድርጊት ተብለው ከተገለፁት ውስጥ በህጉ አንቀጽ 14/1/ሰ/ በአሰሪው ሰራተኛውን በህይወቱ ላይ አደጋ ላያደርስበት በሚችል አኳኋን እንዲሰራ ማድረግ ህገወጥ ድርጊት መሆኑን የተመለከተ ነው። አሰሪው ግድታው ካልፈፀመና ህገ ወጥ ድርጊት መፈፀሙ ከተረጋገጠ ሰራተኛው ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውሉን ማቋረጥ በቂ ምክንያት ይሆናል በማለት በአንቀጽ 32/1/ለ ይደነግጋል። ይህ ከተረጋገጠ ደግሞ ሰራተኛው በአዋጁ መሰረት የተለያዩ ክፍያዎችን ከአሰሪው የማግኘት መብት አለው።
ስለሆነም ከላይ እንደተጠቀሰው ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የአመልካች አድራጎት የተጠሪን ህይወት ለአደጋ ያጋለጠ ስለመሆኑ አረጋግጧል። ይህ ስለመሆኑም ይህ የሰበር ችሎት በ
በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀፅ 2/1/ መሰረት በየትኛውም እርከን የሚገኝ ፍ/ቤትን የማስገደድ ኃይል ያለውን ህግ ትርጉም ስጥቷል።
ለዚህም አመልካች ዝውውሩን ተግባራዊ ያደረገው ትራንስፖርት አገልግሎት የማሟላት ግድታውን ሳይወጣ ስለመሆኑ በማረጋገጥ የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ ስላልተገኘ ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በፍድራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ መጋቢት 27 ቀን 2008 ዓ/ም ተሰጥቶ በፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ታህሳስ 14 ቀን 2009 ዓ/ም በመሻር የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
ከዚህ ፍርድ ቤት