የሙከራ ጊዜ ቅጥር ሲፈጸም ሰራተኛው ኤልያስ ባርና ሬስቶራንት መስከረም 232 XXVI እንዲያውቀው ሳይደረግና ስምምነት ሲደረግም በጽሁፍ ተደርጎ በሁለት ምስክሮች ባልተረጋገጠበት አሰሪው ሰራተኛው ለተቀጠረበት የሥራ መደብ ተስማሚ ሆኖ አልተገኘም በሚል የቅጥር ውሉን ያለምንም ማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ በህጉ መብት ያልተሰጠው ስለመሆኑ፣ የአ/ቁ. 377/96 አንቀጽ 1/1/ /2/ እና /3/ እና እነወ/ሮ ምርትነሽ አጥናፉ 26 ቀን 2010 ዓ.ም 46. አንድ ሰራተኛ የፕሮቪደንት ፈንድ ወይም የጡረታ መብት ተጠቃሚ ከሆነ አሰሪው የስራ ስንብት ክፍያ በተደራቢነት የመክፈል ግድታ የልለበት ሲሆን በራሱ ፍላጎት እና ፈቃደኝነት የስራ ስንብት ክፍያን በተደራቢነት እንዳይከፍል ክልከላ የሚያደርግ ስላለመሆኑ፡አዋጅ ቁጥር 494/1998 አንቀጽ 2 (ሰ)
No summary available.
መጋቢት 14 ቀን 2010 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አልማው ወል ሙስጠፋ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውሎስ ኦርሺሶ አመልካች፡- ቦሰት የሕጻናትና ቤተሰብ በጎ አድራጎት ድርጅት ጠበቃ ድሬሳ በዳዳ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ዓለም ሽመልስ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዳዩ አዋጅ ቁጥር 377/1996 “ን” መሰረት አድርጎ የተነሳ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን አመልካች የሰበር አቤቱታውን ለዚህ ችሎት ያቀረበው ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የምስራቅ ኦሮሚያ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቋሚ ቦርድ የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኃላ የቅነሳ እርምጃው የተወሰደው በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 28፣29 (3) እና 42 የተመለከተውን ስርዓት ተከትሎ አለመሆኑ እና ድርጅቱ በ2002 ዓ.ም. ባወጣው የሰው ኃይል መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የመስሪያ ቤቱ ቦርድ ሳያጸድቀው መሆኑ ስለተረጋገጠ እርምጃው ሕገወጥ ነው፣ ሕገወጥ ስንብት የሚያስከትላቸውን እና ተያያዥ ክፍያዎችን አመልካች ለተጠሪዋ ላከፍል ይገባል በማለት በመዝገብ ቁጥር 867/01/2008 በ29/07/2009 ዓ.ም.የሰጠው እና በኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ችሎቶች እንደቅደም ተከተላቸው በመዝገብ በ21/02/2010 ዓ.ም.እና በመዝገብ በ16/04/2010 ዓ.ም. በተመሳሳይ ሁኔታ በፍርድ የጸናው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ላታረም ይገባል በማለት ነው።
የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ ጉዳዩ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ የመታየቱን አግባብነት፣ቅነሳው የተከናወነው ሰራተኞችን የስራ አፈጻጸም መሰረት በማድረግ ሆኖ ሳለ ስንብቱ ሕገወጥ ነው የመባሉን አግባነት፣የህክምና ወጪ ከኢንሹራንስ ድርጅት ለተጠሪዋ የተከፈለ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ አመልካች እንዲከፍል የመወሰኑን አግባብነት እና ተጠሪዋ የፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ ሆነው እያለ የስራ ስንብት ክፍያ በተደራቢነት እንዲከፈል የመወሰኑን አግባብነት ከአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 29 (3) እንዲሁም የዚሁ አዋጅ ማሻሻያ ከሆነው አዋጅ ቁጥር 494/1998 አንቀጽ (2) (ሰ) እና በመዝገብ ከተሰጠው የሰበር ችሎት ገዥ ውሳኔ አንጻር ተጠሪዋ ባሉበት ለማጣራት እንዲቻል ጉዳዩ ለሰበር ክርክር እንዲቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም በጉዳዩ እልባት ማግኘት የሚገባቸው፡-
ጉዳዩ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ የስረ ነገር ስልጣን ስር የሚወድቅ አይደለም በማለት አመልካች የሚያቀርበው ክርክር ተቀባይነት ያለው ነው ወይስ አይደለም?
የቅነሳ እርምጃው የተከናወነው አግባብነት ባላቸው የአዋጅ ቁጥር 377/1996 ድንጋጌዎች የተዘረጋውን ስርዓት መሰረት አድርጎ አይደለም በማለት በስር ፍርድ ቤቶች የተደረሰበት ድምዳሜ የሚነቀፍበት ሕጋዊ ምክንያት አለ ወይስ የለም?
ያልተከፈለው የሕክምና ወጪ ታስቦ አመልካች ለተጠሪዋ ላከፍል ይገባል በሚል የተሰጠው የውሳኔ ክፍል የሚነቀፍበት ሕጋዊ ምክንያት አለ ወይስ የለም?
ተጠሪዋ የፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ ሆነው እያለ አመልካች የስራ ስንብት ክፍያ በተደራቢነት እንዲከፍል የተሰጠው የውሳኔ ክፍል አዋጅ ቁጥር 494/1998 አንቀጽ (2) (ሰ) ድንጋጌን እና በዚህ ረገድ የተሰጠውን የሰበር ገዥ ውሳኔ የሚጻረር ነው በማለት አመልካች የሚያቀርበው ክርክር በመዝገቡ የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮች መሰረት ያደረገ ነው ወይስ አይደለም?
የሚሉ መሆናቸውን በመገንዘብ አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ከእነዚሁ ነጥቦች አንጻር መርምረናል።
የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ አዋጅ ቁጥር 377 1996 "ን" መሰረት አድርገው የሚነሱ የስራ ክርክር ጉዳዮች የሚታዩት እንደየጉዳዩ ዓይነት በክልል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ወይም በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በከልል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሚታዩት በአዋጁ አንቀጽ 138 (1) ስር ከፊደል (ሀ) እስከ (ረ) የተዘረዘሩት እና ልሎች ተመሳሳይ የግል የስራ ክርክር ጉዳዮች መሆናቸውን እና በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቋሚ ቦርድ የሚታዩት ደግሞ በአዋጁ አንቀጽ 142 (1) ከፊደል (ለ) እስከ (ሸ) የተዘረዘሩት እና ልሎች ተመሳሳይ የወል የስራ ክርክር ጉዳዮች መሆናቸውን የተጠቀሱት የአዋጁ ድንጋጌዎች እንዲሁም የአዋጁ አንቀጽ 147 (1) (ሀ) ድንጋጌ ያመለክታሉ።በሁለቱ ድንጋጌዎች ስር ከተመለከቱት የግል እና የወል የስራ ክርክር ዓይነቶች አንዳንዶቹ በስያሜም ሆነ በይዘት የመመሳሰል ባህርይ ያላቸው በመሆኑ የትኛው ክርክር በግል፣የትኛው ደግሞ በወል የስራ ክርክር ስር እንደሚወድቅ መለየቱ በተግባር ሲያስቸግር ይታያል።ከዚህም በመነሳት እና አግባብነት ያላቸውን የአዋጁን ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ የግል የስራ ክርክርን ከወል የስራ ክርክር ለመለየት ስለሚያስችሉ መስፈርቶች በመዘርዘር የፍ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት በመ.ቁ.18180 በ29/11/1997 ዓ.ም. እና በልሎችም በርካታ መዝገቦች አስገዳጅ የህግ ትርጉም የሰጠ መሆኑ የሚታወቅ ጉዳይ ነው።በዚህ አስገዳጅ የህግ ትርጉምም ሕጉ የስራ ክርክር ጉዳዮችን የወል ወይም የግል ብሎ ለመለየት የተከራካሪ ሰራተኞችን ቁጥር እንደመስፈርት መወሰድ እንዳለበት የማያመለክት መሆኑ፣አንድ የስራ ክርክር የወል ነው የሚባለው ጉዳዩ የጋራ በሆነ የሰራተኞች መብትና ጥቅም ላይ አዎንታዊ ወይም አሉታዊ ውጤት የሚያስከትል ሆኖ ሲገኝ ብቻ መሆኑ፣አንድን የስራ ክርክር ጉዳይ የግል የስራ ክርክር የሚያደርገው ደግሞ ጉዳዩ ከግል አልፎ በጋራ መብት ላይ የሚያስከትለው ውጤት የልለ በሆነ ጊዜ መሆኑ እና መሰል ጉዳዮች በዝርዝር ተመልክተዋል።
በልላ በኩል በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቋሚ ቦርድ የስረ ነገር ስልጣን ስር ከሚወድቁ ጉዳዮች አንዱ የሰራተኞች ቅነሳ ጉዳይ ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 142 (1) (ሸ) እና አንቀጽ 147 (1) (ሀ) ድንጋጌዎች ስር ተመልክቷል።ይህ ማለት ግን ከቅነሳ ጋር የተያያዘ ማናቸውም ጉዳይ በቦርዱ የስረ ነገር ስልጣን ስር የሚወድቅ ነው ከሚል ድምዳሜ ላይ ለመድረስ የሚያስችል አይደለም።በቦርዱ የስረ ነገር ስልጣን የሚወድቅ ነው ለማለት የሚቻለው ከላይ በተጠቀሰው የሰበር ገዥ ውሳኔ መሰረት ጉዳዩ የወል ባህርይ ያለው መሆኑ ሲረጋገጥ ነው።
በተያዘው ጉዳይ ተጠሪዋ ለክሳቸው ምክንያት ካደረጓቸው ነጥቦች አንዱ ተጠሪዋ በሕመም ፈቃድ እና ቀጥሎም በወላድ ፈቃድ ምክንያት በስራ ላይ ላልነበሩበት ጊዜ የስራ አፈጻጸማቸውን ሞልቶ ለቅነሳው መሰረት በማድረግ አመልካች ድርጅት የዘረጋው የቅነሳ ስርዓት ተገቢነት የለውም የሚል መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።ይህ ደግሞ የድርጅቱ ሰራተኞች በተለያዩ ምክንያቶች በስራ ገበታ ላይ ባልነበሩበት ጊዜ በልላ አነጋገር ስራ ባልሰሩበት ጊዜ የስራ አፈጻጸማቸውን በመሙላት አመልካች ድርጅት ለቅነሳ ተግባር ላጠቀምበት ይችላል ወይም አይችልም? የሚል ጥያቄ የሚያስነሳ በመሆኑ በዚህ ጥያቄ ዙሪያ ጉዳዩ በቀረበለት አካል በአንድ ወይም በልላ አግባብ የሚሰጠው ውሳኔ በተጠሪዋ ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሳይሆን በልሎችም ሰራተኞች መብት ላይ አዎንታዊ ወይም አሉታዊ ውጤት የሚያስከትል በመሆኑ ክርክሩ የወል ባህርይ እንዲኖረው የሚያደርግ ነው።እንዲህ ከሆነ ደግሞ ጉዳዩ በቦርድ የስረ ነገር ስልጣን ስር የማይወድቅበት ሕጋዊ ምክንያት አይኖርም።በመሆኑም ጉዳዩ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ የስረ ነገር ስልጣን ስር የሚወድቅ አይደለም በማለት አመልካች የሚያቀርበው ክርክር ተቀባይነት ያለው ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም።
ሁለተኛውን ነጥብ በተመለከተ አመልካች ድርጅት የቅነሳ እርምጃውን የወሰድኩት የ30% በ70% ቀመር በትክክል ተገባራዊ እንዳደርግ ከኢ.ፍ.ዲ.ሪ. የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት ኤጀንሲ በተሰጠኝ መመሪያ መሰረት ነው በማለት የተከራከረ ቢሆንም ይህንን የክርክር ነጥብ በማስረጃ ማስደገፍ ያልቻለ መሆኑ፣የቅነሳ እርምጃው የተከናወነውም በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 29 (3) የተመለከቱትን ግልጽ መስፈርቶች መሰረት በማድረግ አለመሆኑ፣ይልቁንም ተጠሪዋን ከስራ ያሰናበተው በሕመም ምክንያት ለረዥም ጊዜ በስራ ላይ ያልነበሩ መሆኑን በስንብት ደብዳቤው ላይ በመግለጽ መሆኑ፣በተጠሪዋ ላይ የስንብት እርምጃ የወሰደውም ተጠሪዋ ስራ ላይ ባልነበሩበት ጊዜ የተሞላላቸውን የስራ አፈጻጸም ውጤት ጭምር በመጠቀም መሆኑ በቦርዱ የተረጋገጡ እና በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ተቀባይነት ያገኙ ፍሬ ነገሮች መሆናቸውን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።አመልካቹም በዚህ ረገድ በሰበር አቤቱታው ላይ ያቀረበው የማስተባበያ ክርክር የለም።እንዲህ ከሆነ ደግሞ አመልካች የወሰደው እርምጃ ሕጋዊ ላሆን አይችልም።በመሆኑም የቅነሳ እርምጃው የተከናወነው አግባብነት ባላቸው የአዋጅ ቁጥር 377/1996 ድንጋጌዎች የተዘረጋውን ስርዓት መሰረት አድርጎ አይደለም በማለት በስር ፍርድ ቤቶች የተደረሰበት ድምዳሜ የሚነቀፍበት ሕጋዊ ምክንያት አልተገኘም።
ሶስተኛውን ነጥብ በተመለከተ አመልካች አጥብቆ የሚከራከረው ለተጠሪዋ እና ለቤተሰባቸው አባላት የህክምና ወጪ አመልካች በጥቅል የገባውን የመድን ሽፋን ብር 7,000 /ሰባት ሺህ/ ተጠሪዋ እና የቤተሰባቸው አባላት ተጠቅመው ያጠናቀቁ ስለመሆኑ የመድን ሽፋን ከሰጠው ድርጅት በተጻፈ ደብዳቤ ተረጋግጦ እያለ አመልካች ለተጠሪዋ ተጨማሪ የህክምና ወጪ እንዲተካ ውሳኔ የተሰጠው አለአግባብ ነው በማለት ሲሆን ቦርዱ እና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ የቀረበውን ክርክር ሳይቀበሉ የቀሩት በግራ ቀኙ መካከል ባለው ውል መሰረት አመልካች የብር 7,000 /ሰባት ሺህ/ የህክምና ወጪ የመሸፈን ግድታ ያለበት ለተጠሪዋ እና ለቤተሰባቸው አባላት በጥቅል ሳይሆን በነፍስ ወከፍ ነው በማለት ነው።አመልካች የመድን ሽፋን ከገባበት የገንዘብ መጠን ብር 7000 /ሰባት ሺህ/ ውስጥ ከአዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ ለተጠሪዋ በግል የብር 4,236 /አራት ሺህ ሁለት መቶ ሰላሳ ስድስት/ የህክምና ወጪ የተተካላቸው መሆኑ እና ቀሪው ብር 2,764 /ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ስድሳ አራት/ የህክምና ወጪ የተተካው ደግሞ ለተጠሪዋ የቤተሰብ አባላት መሆኑ በተጠሪዋም ያልተካደ ሲሆን በቦርዱ ውሳኔ መሰረት አመልካች ለተጠሪ መተካት የሚጠበቅበት የህክምና ወጪ ብር 2,764 /ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ስድሳ አራት/ መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።አመልካች በእያንዳንዱ የበጀት ዓመት ውስጥ ለተጠሪዋ እና ለቤተሰባቸው አባላት በጥቅል ሳይሆን በነፍስ ወከፍ የብር 7,000 /ሰባት ሺህ/ የህክምና ወጪ የመሸፈን ግድታ የተጣለበት በየትኛው ደንብ እና ድንጋጌ መሰረት እንደሆነ ለይተው በመጥቀስ ተጠሪዋ በሰበር መልሳቸው ላቀረቡት ክርክር አመልካቹ በመልስ መልሱ የሰጠው ማስተባበያ የለም።አመልካች ድርጅት ለተጠሪዋ እና ለቤተሰባቸው አባላት በጥቅል የብር 7,000 /ሰባት ሺህ/ የመድን ሽፋን መግባቱ በግራ ቀኙ መካከል የተደረገውን ውል መሰረት ያደረገ ካልሆነ ደግሞ ልዩነቱን እራሱ የመሸፈን የውል ግድታ ይኖርበታል።በመሆኑም ያልተከፈለው የሕክምና ወጪ ታስቦ አመልካች ለተጠሪዋ ላከፍል ይገባል በሚል የተሰጠው የውሳኔ ክፍል የሚነቀፍበት ሕጋዊ ምክንያት አልተገኘም።
አራተኛውን እና የመጨረሻውን ነጥብ በተመለከተ አመልካች አጥብቆ የሚከራከረው ተጠሪዋ የፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ መሆናቸው ተረጋግጦ እያለ የስራ ስንብት ክፍያ በተደራቢነት እንዲከፈላቸው የተሰጠው ውሳኔ አዋጅ ቁጥር 494/1998 አንቀጽ (2) (ሰ) ድንጋጌን እና በዚህ ረገድ የተሰጠውን የሰበር ገዥ ውሳኔ መሰረት ያደረገ ባለመሆኑ ላሻር ይገባዋል በማለት ነው።እንደተባለው የስራ ውሉ በሕገ ወጥ መንገድ የተቋረጠበት ሰራተኛ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 በአንቀጽ 39 ( 1) (ለ) በተመለከተው መሰረት የስራ ስንብት ክፍያ የማግኘት መብት ካላቸው ሰራተኞች ወስጥ የሚካተት ቢሆንም የፕሮቪደንት ፈንድ ወይም የጡረታ መብት ተጠቃሚ የሆነ ሰራተኛ የስራ ውሉ በተቋረጠ ጊዜ በተደራቢነት የስራ ስንብት ክፍያ የማግኘት መብት እንደማይኖረው የአዋጅ ቁጥር 377/1996 ማሻሻያ በሆነው አዋጅ ቁጥር 494/1998 በአንቀጽ 2 (ሰ) ስር ተደንግጎ ይገኛል።የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት አግባብነት ያላቸውን የሁለቱን አዋጆች ድንጋጌዎች አገናዝቦ በመተርጎም የፕሮቪደንት ፈንድ ወይም የጡረታ መብት ተጠቃሚ የሆነ ሰራተኛ የስራ ስንብት ክፍያ የማግኘት መብት የማይኖረው ስለመሆኑ ቀደም ሲል በቀረቡ ተመሳሳይ ጉዳዮች ላይ በመዝገብ ፣37048 እና በልሎችም መዝገቦች አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል።
ተጠሪዋ የፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ መሆናቸው ያልተካደ ሲሆን የስር ፍርድ ቤቶች ከላይ በተጠቀሰው አዋጅ እና የሰበር ገዥ ውሳኔ መሰረት የፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ የሆነ ሰራተኛ የስራ ስንብት ክፍያ በተደራቢነት የማግኘት መብት የማይኖረው መሆኑን ተቀብለው ነገር ግን ለተጠሪዋ የስራ ስንብት ክፍያ እንዲከፈል የወሰኑት አመልካች ድርጅት ለተጠሪዋ በጻፈው የስንብት ደብዳቤ ላይ ከፕሮቪደንት ፈንድ በተጨማሪ የስራ ስንብት ክፍያ እንደሚከፈላቸው የገለጸ መሆኑን መሰረት በማድረግ እንደሆነ የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል። ውሳኔው አዋጁን እና የሰበር ገዥ ውሳኔን የሚጻረር ነው በሚል በጥቅሉ ከመከራከር በቀር የስንብት ደብዳቤው አነጋገር እና ይዘት ከላይ የተገለጸው ስላለመሆኑ አመልካች በሰበር ደረጃ ያቀረበው የማስተባበያ ክርክር የለም።
አመልካች በአስረጂነት ጠቅሶ የሚከራከርባቸው የአዋጁ ድንጋጌ እና የሰበር ገዥ ውሳኔዎች ደግሞ አሰሪው የፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ ለሆነ ሰራተኛ የስራ ስንብት ክፍያ በተደራቢነት የመክፈል ግድታ እንደልለበት የሚያመለክቱ ከመሆናቸው በቀር አሰሪው በራሱ ፍላጎት የስራ ስንብት ክፍያውን በተደራቢነት እንዳይከፍል የሚከለክሉ አይደሉም።አመልካች የስንብት ክፍያው በተደራቢነት እንደሚከፈል ክርክር ከመጀመሩ በፊት በስንብት ደብዳቤው ላይ በግልጽ ፈቅዶ እያለ ተጠሪዋ ክስ ካቀረቡ በኃላ የስራ ስንብት ክፍያው ላከፈል የማይችልበት ሕጋዊ ምክንያት ስለመኖሩ ያቀረበው ሕጋዊ ምክንያት ሳይኖር የስራ ስንብት ክፍያው እንዲከፈል የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ከላይ የተጠቀሰውን አዋጅ እና የሰበር ገዥ ውሳኔ የሚጻረር ነው በማለት በደፈናው የሚያቀርበው ክርክር ተቀባይነት ላሰጠው የሚገባ አይደለም። በመሆኑም ተጠሪዋ የፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ ሆነው እያለ አመልካች የስራ ስንብት ክፍያ በተደራቢነት እንዲከፍል የተሰጠው የውሳኔ ክፍል አዋጅ ቁጥር 494/1998 አንቀጽ (2) (ሰ) ድንጋጌን እና በዚህ ረገድ የተሰጠውን የሰበር ገዥ ውሳኔ የሚጻረር ነው በማለት አመልካች የሚያቀርበው ክርክር በመዝገቡ የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮች መሰረት ያደረገ ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም።ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ ስላልተገኘ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
በምስራቅ ኦሮሚያ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቋሚ ቦርድ በመዝገብ ቁጥር 867/01/2008 በ29/07/2009 ዓ.ም. ተሰጥቶ በኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ችሎቶች እንደቅደም ተከተላቸው በመዝገብ በ21/02/2010 ዓ.ም. እና በመዝገብ በ16/04/2010 ዓ.ም. በተመሳሳይ ሁኔታ በፍርድ የጸናው ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348 (1) መሰረት ፀንቷል።
በምስራቅ ኦሮሚያ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቋሚ ቦርድ በመዝገብ ቁጥር Mr/290/01/2009/3 የተያዘው አፈጻጸም ታግዶ እንዲቆይ በዚህ መዝገብ በ26/04/2010 ዓ.ም. ተሰጥቶ የነበረው ትዕዛዝ ተነስቷል።ይጻፍ፡
የውሳኔው ቅጂ ለስር ፍርድ ቤቶች ይላክ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.