በወንጀል ህግ አንቀጽ 620/3/ ስር የጥፋተኝነት ውሳኔ ለመስጠት በግል ተበዳይ ላይ ከባድ የአካል ወይም የአይምሮ ጉዳት ወይም ሞት የደረሰ መሆኑ ላረጋገጥ የሚገባ ስለመሆኑ እና አንድ የወንጀል ክስ የወ/ህ/አንቀጽ ቁጥር 620/2/መ/ መሰረት በማድረግ በቀረበበት ሁኔታ ፍ/ቤቶች የጥፋተኝነት ውሳኔ ሲሰጡ የክስ መሰረት የሆነውን አንቀጽ ወደ አንቀጽ ቁጥር 620/3 በመቀየር ውሳኔ ለመስጠት የማይችሉ ስለመሆኑ፣ የወንጀል አፈጻጸሙ አፀያፊነት ከወንጀል ፈጻሚው እነ ሀይላይ ወ/ገብርኤል እና የት/ብ/ክ/መ/ፍትህ ዐ/ህግ XXV ከተረጋገጠና በቅጣት አወሳሰን መመሪያው በወጣው ደረጃ መሰረት ቅጣቱ ቢወሰን የወንጀል ህጉን የቅጣት አላማና ግብ የሚያሳካ የማይሆንበት ሁኔታ ሲኖር ቅጣቱን ከቅጣት አወሳሰን መመሪያ ውጪ መወሰን የሚቻል ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/ቁ. 620/2/ መ፣ 620/3/ እና የወ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 113/2/ የወ/ህ/ቅ/አ/መ/ቁ.2/2006 27/1/ እና 4/9/ የወ/ህ/ቁ. 539/1/2//ሀ/፣ የወ/ህ ቁ. 82
No summary available.
መስከረም 26 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡ ብርሃኑ አመነው በዕውቀት በላይ እንዳሻው አዳነ ሃይሉ ነጋሽ እትመት አሰፋ አመልካቾች፡-
መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የወንጀል ጉዳይ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በትግራይ ብሕራዊ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ ፍ/ቤት በአክሱም ምድብ ችሎት ነው። ተጠሪ በአሁን አመልካቾች ላይ በሥር ፍ/ቤት ያቀረበው የተሻሻለ ክስ ይዘት አመልካቾች የወንጀል ሕግ አንቀጽ 620/3 ድንጋጌን በመተላለፍ ሚያዝያ 10 ቀን 2007 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት አባሪ ተባባሪ በመሆን በአክሱም ከተማ በማዕበል ቀበል ቀጠና 4 በተባለ ቦታ የግል ተበዳይ ወ/ት ሐጎሳ ሀይሉን በመምታት በተለያየ የሰውነት አካሐ ላይ 1 × 1 ሳ.ሜ፤
በጭንቅላትዋ ላይ 2 × 1 ሳ.ሜ፤በምላሷ ላይ 2 × 2 ሳ.ሜ ጉዳት ካደረሱባት እና ራሷን እንድትስት ካደረጉ በኋላ ለብሳው የነበረውን ልብስ በመቅደድ አውልቀው እርቃንዋን በማድረግ 1ኛ አመልካች ክብረንጽህናዋን በመድፈሩ፤2ኛ አመልካችም ተባብሮ ክብረንጽሕናዋን በመድፈር ቀጥቅጠው ራሷን እንድትስት በማድረግ አስገድዶ የመድፈር ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ነው። አመልካቾች ክሱ ተነቦላቸው መቃወሚያ የልላቸው መሆኑን ከገለጹ በኋላ የእምነት ክሕደት ቃላቸውን ሲጠየቁ ድርጊቱን አልፈጸምንም በማለት ክደው የተከራከሩ በመሆኑ የተጠሪ ማስረጃዎች ተሰምተዋል።
የቀረበ የለም 1ኛ የተጠሪ ምስክር የግል ተበዳይ ለፍ/ቤቱ በሰጠችው የምስክርነት ቃል አመልካቾች በዕለቱ በሐሙስ ገበያ በኩል ወደ ቤታቸው አብረው እንሂድ ያልዋት መሆኑን፤ምሽት ነው አልሕድም ስትላቸው ሞባይል እናበራለን ያልዋት መሆኑን፤2ኛ አመልካች ወደኋላ ቀርቶ ስለነበር 1ኛ አመልካች እንጠብቀው ያላት መሆኑን፤ብርሃን ያለበት ቦታ እንጠብቀው ብትለውም ልብስሽን አውልቂ ያላት መሆኑን፤እንደማትፈልግ በመግለጽ ተው ብትለውም ደጋግሞ አፍንጫዋን በመምታት እያንዳንዱ የለበሰችውን ልብስ ቀዶ የጣለው ፓንት ሳይቀር የወረወረ መሆኑን፤ለሕይወትሽ ሳሳሽላት ሲላት የመጣ ይምጣ ለሕይወቴ አልሳሳም ያለችው መሆኑን፤እንዳልገልሽ ሲላት ግደለኝ ስትለው እንዳታይ በማለት በድንጋይ ዓይኗን ጭንቅላትዋን አንገትዋን እጇን የመታት መሆኑን፤ድንግልናዋን የደፈረ እና ማሕጸኗ የተሰነጠቀ መሆኑን፤ሁለተኛ አመልካችም መጥቶ የደፈራት መሆኑን፤በምላጭ፤በሚስማር ወይም በቢላዋ መሆኑን ባልለየችው ሁኔታ እንደእባብ ሲቀጠቅጧት ያደሩ መሆኑን፤ባሕር ውስጥ እንከትሻለን ያልዋት መሆኑን፤በጀርባዋ ወድቃ እያለ በእግራቸው ሆድዋን ረግጠው ከእግርዋ እስከ ጸጉርዋ ድርስ የሸኑባት መሆኑን፤ምራቃቸውን ከተፉባት በኋላ ሞታለች አልሞተችም እያሉ ሹራብ ሸፍነዋት የሄዱ መሆኑን፤በረሃ ላይ ራቁትዋን ያደረች መሆኑን፤ከፍላጎትዋ ውጪ አስገድደው የእርቅ ውል ያስፈረሟት መሆኑን፤ በደረሰባት አደጋ ምክንያት ሆድዋን የሚቆርጣት፤ የሚነፋት ፤የሚያቃጥላት ፤የሚያዞራት፤ የሚሞቃት እና የሚያሰቃያት መሆኑን በመግለጽ መስክራለች ።
ሁለተኛ የተጠሪ ምስክር ለፍ/ቤቱ በሰጡት የምስክርነት ቃል ሚያዝያ 10 ቀን 2007 ዓ.ም ከልላቱ በ 6፡00 ሰዓት በራቸው የተንኳኳ መሆኑን፤ማነው ሲሉ የግል ተበዳይ ክፈችልኝ ያለቻቸው እና ፈርተው ያልከፈቱላት መሆኑን፤ጠዋት በሩን ሲከፍቱ የግል ተበዳይ ራቁትዋን በር ሥር ቁጭ ብላ ያገኟት መሆኑን፤ሰውነትዋ ተመትቶ የነበረ እና 1ኛ አመልካች መትቶኝ ነው ያለቻቸው መሆኑን፤ልብሶቿ ተቀዳድው ሜዳ ላይ ተጥለው የተገኙ መሆኑን እና ለቤተሰቦቿ ስልክ የደወሉ መሆኑን በመግለጽ መስክረዋል።
3ኛ የተጠሪ ምስክር ለፍ/ቤቱ በሰጡት የምስክርነት ቃል በእለቱ ስልክ ተደውሎላቸው መጥተው የግል ተበዳይን ሕክምና ቦታ የወሰዷት መሆኑን፤የተመታችበትን አካባቢ ያዩ እና ልብሶቿ ተቀዳደው ተጥለው ከባድ ጉዳት ደርሶባት የነበረ እና አመልካቾች መቱኝ ብላ የነገረቻቸው መሆኑን በመግለጽ መስክረዋል። 4ኛ ምስክር በሰጡት የምስክርነት ቃል አመልካቾች በእለቱ ከግል ተበዳይ ጋር የግል ተበዳይ ተመታሁ ባለችበት አካባቢ ሲሄዱ ያይዋቸው መሆኑን በመግለጽ መስክሯል። 5ኛ ምስክርም በሰጡት የምሥክርነት ቃል በእለቱ አመልካቾችን ያዩ እና የግል ተበዳይ መቱኝ ብላ የነገረቻቸው መሆኑን በመግለጽ መስክረዋል። በግል ተበዳይ ላይ አዲስ የሆነ የክብረንጽሕና መገርሰስ እንደደረሰባት፤ማሕጸንዋ እንደተሰነጠቀ እና እንደተሰፋ ፤በተለያየ አካሐ ላይ ጉዳት እንደደረሰ የሚያሳይ የተለያየ የሰነድ ማስረጃም ቀርቧል።
ጉዳዩ በቀጥታ የቀረበለት ፍ/ቤት በተጠሪ በኩል የቀረቡትን ማስረጃዎች ከመረመረ በኋላ ተጠሪ እንደክሱ አስረድቷል በማለት አመልካቾች በተከሰሱበት የሕግ አንቀጽ እንዲከላከሉ በማለት በሰጠው ብይን መሰረት አመልካቾች ድርጊቱ ተፈጸመ በተባለበት ቦታ ላይ እንዳልነበሩ የሚያስረዱ መከላከያ ምሥክሮችን በማቅረብ አሰምተዋል፤የሰነድ ማሥረጃዎችም አቅርበዋል።
ፍ/ቤቱ የግራቀኙን ማስረጃዎች ከመረመረ በኋላ አመልካቾች ድርጊቱን የፈጸሙ ለመሆኑ በሚገባ ስለተመሰከረባቸው እና ባቀረቡት መከላከያ ማሥረጃ ክሱን ስላላስተባበሉ በተከሰሱበት የሕግ አንቀጽ ጥፋተኛ ናቸው በማለት የጥፋተኝነት ውሳኔ ሰጥቷል። የቅጣት ውሳኔን በተመለከተም በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 02/2006 መሰረት ቅጣቱን በማስላት የወንጀሉን ደረጃ ደረጃ ሐ እርከን የቅጣት መነሻ እርከን 38 በመያዝ ፤ተጠሪ ድርጊቱ በጭካኔ ስለተፈጸመ በማክበጃነት ይያዝልን በማለት ያቀረበውን የቅጣት ማክበጃ ባለመቀበል፤ተጠሪ ድርጊቱ በጨለማ የተፈጸመ ስለሆነ በማክበጃነት ይያዝ በማለት ያቀረበውን ማክበጃ በመቀበል ወደ እርከን 39 በማሳረፍ፤አመልካቾች ድርጊቱን በሥምምነት የፈጸሙት ስለሆነ በቅጣት ማክበጃነት ላያዝ የሚገባው ቢሆንም ከእርከን 39 በላይ የሚወጣ በመሆኑ ማክበድ አይቻልም በማለት፤አመልካቾች የወንጀል ሪከርድ የለባቸውም የሚለውን በቅጣት ማቅለያነት በመያዝ፤አመልካቾች የቤተሰብ አስተዳዳሪ ነን ከተበዳይ ጋር ታርቀናል በማለት ያቀረቡትን የቅጣት ማቅለያ ባለመቀበል አመልካቾች በዕድሜ ልክ ጽኑ እሥራት እንዲቀጡ በማለት ወስኗል። አመልካቾች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት በየደረጃው ላሉ የክልሉ ፍ/ቤቶች አቤቱታ ያቀረቡ ቢሆንም አቤቱታቸው ተቀባይነት አላገኘም።የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም ነው።
የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- በግል ተበዳይ ላይ ከባድ የሆነ የአካል እና የአእምሮ ጉዳት ወይም ሞት ባልደረሰበት ሁኔታ የተከሰስንበት የሕግ አንቀጽ መቀየሩ፤የተጠሪ ማሥረጃዎች በአግባቡ ባላስረዱበት ሁኔታ እና አመልካቾች ክሱን በተከላከልንበት ሁኔታ የበታች ፍ/ቤቶች የጥፋተኝነት ውሳኔ መስጠታቸው እና የወንጀል ሪከርድ የልለን እና ወጣቶች ሆነን ሳለ በቅጣት ማቅለያነት ሳይያዝ የተሰጠው የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ላታረም ይገባል የሚል ነው። የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካቾች የተከሰሱት የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 620/2/መ የተመለከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል በሚል ሆኖ የሥር ፍ/ቤት ወደ ወንጀል ሕግ አንቀጽ 620/3 በመለወጥ የጥፋተኝነት ውሳኔ መስጠቱ፤ተፈጸመ ከተባለው የወንጀል ድርጊት በሁለቱ ድንጋጌዎች ላይ ከተመለከተው የቅጣት መጠን እንዲሁም ከወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 113/2 ጋር በማገናዘብ ለመመርመር ሲባል ጉዳዩ በዚህ ችሎት እንዲታይ ተደርጓል።ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል።
የጉዳዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው።እኛም እንዲጣራ የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር እና ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረነዋል። በሰበር አጣሪው እንዲጣራ የተያዘው ነጥብ አመልካቾች የተከሰሱት የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 620/2/መ የተመለከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል በሚል ሆኖ የሥር ፍ/ቤት ወደ ወንጀል ሕግ አንቀጽ 620/3 በመለወጥ የጥፋተኝነት ውሳኔ መስጠቱ፤ተፈጸመ ከተባለው የወንጀል ድርጊት በሁለቱ ድንጋጌዎች ላይ ከተመለከተው የቅጣት መጠን እንዲሁም ከወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 113/2 ጋር በማገናዘብ ለመመርመር ሲባል የሚል ቢሆንም ተጠሪ አሻሽሎ ባቀረበው ክስ አመልካቾች የወንጀል ሕግ አንቀጽ 620/3 ድንጋጌን ተላልፈው ወንጀል ፈጽመዋል በማለት ክስ ያቀረበባቸው በመሆኑ የሰበር አጣሪው አመልካቾች የተከሰሱት በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 620/2/መ መሰረት ሆኖ ሳለ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 620/3 ጥፋተኛ መባላቸው ከወንጀል ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 113/2 ጋር በማገናዘብ ለመመርመር በማለት የያዘውን ማጣሪያ ነጥብ መመርመር አስፈላጊ ሆኖ አላገኘነውም። በልላ በኩል የበታች ፍ/ቤቶች አመልካቾችን በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 620/3 መሰረት ጥፋተኛ የማለታቸውን አግባብነት እንደሚከተለው መርምረነዋል።
የኢ.ፍ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 620/3 ድንጋጌ አስገድዶ መድፈሩ ከባድ የአካል ወይም የአዕምሮ ጉዳት ወይም ሞትን ያስከተለ ሲሆን ቅጣቱ የዕድሜ ልክ እሥራት እንደሚሆን ይደነግጋል። በበታች ፍ/ቤቶች ከተረጋገጠው ፍሬነገር የግል ተበዳይ የተደበደበች ቢሆንም በዚሁ ድንጋጌ በተጠቀሰው ሁኔታ በግል ተበዳይ ላይ ከባድ የአካል ወይም የአዕምሮ ጉዳት ወይም ሞት የደረሰባት መሆኑ በበታች ፍ/ቤቶች የተረጋገጠው ፍሬነገር አያሳይም። በመሆኑም የበታች ፍ/ቤቶች በግል ተበዳይ ላይ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 620/3 በተመለከተው መሰረት ጉዳት እንደደረሰባት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ አመልካቾችን በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 620/3 መሰረት ጥፋተኛ ናቸው በማለት የሰጡት የጥፋተኝነት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
በልላ በኩል አመልካቾች ድርጊቱን የፈጸሙት ሁለት ሆነው በጭካኔ እና የግል ተበዳይን በማሰቃየት መሆኑን ፍሬነገርን የማጣራት እና ማሥረጃን የመመዘን ሥልጣን ባላቸው የበታች ፍ/ቤቶች ተረጋግጧል። የኢ.ፍ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 620/2/መ አስገድዶ መድፈሩ የተፈጸመው በጭካኔ ወይም በማሰቃየት ወይም ቁጥራቸው ከአንድ በላይ በሆኑ ወንዶች ሕብረት ሲሆን ወንጀል ፈጻሚው ቅጣቱ ከአምስት አመት እስከ ሀያ አመት ለመድረስ በሚችል ጽኑ እሥራት እንደሚቀጣ ይደነግጋል። አመልካቾች ድርጊቱን የፈጸሙት ሁለት ሆነው በጭካኔ እና የግል ተበዳይን በማሰቃየት መሆኑን ፍሬነገርን የማጣራት እና ማስረጃን የመመዘን ሥልጣን ባላቸው የበታች ፍ/ቤቶች የተረጋገጠ በመሆኑ አመልካቾች የተከሰሱበትን የሕግ አንቀጽ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 113/2 መሰረት በመቀየር አመልካቾች ጥፋተኛ መባል ያለባቸው በወንጀል ሕግ አንቀጽ 620/2/መ መሰረት ነው ብለናል።
የኢ.ፍ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 1 የወንጀል ህግ ግብ ወንጀል እንዳይፈፀም መከላከል ሲሆን ይህንን የሚያደርገው ስለወንጀሎችና ስለቅጣታቸው በቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት፤ ማስጠንቀቂያነቱ በቂ ባልሆነበት ጊዜ ወንጀል አድራጊዎቹ ተቀጥተው ልላ ወንጀል ከመፈፀም እንዲቆጠቡና ለልሎች ማስተማሪያ እንዲሆኑ ወይም እንዲታረሙ በማድረግ ወይም ተጨማሪ ወንጀሎች እንዳይፈፀሙ እርምጃዎች እንዲወሰዱባቸው በማድረግ መሆኑን ይደነግጋል።
የዚሁ ሕግ አንቀጽ 87 እና 88 ድንጋጌም ቅጣቶች እና የጥንቃቄ እርምጃዎች ሕጉ ላደርስበት ያሰበበትን ዓላማ ለማረጋገጥ በሚቻልበት ሁኔታ በሕጉ መንፈስ መሰረት መፈጸም እንዳለባቸው እና ሰብአዊ ክብርን በሚጠብቅ መንገድ መፈጸም እንደሚኖርባቸው፤ፍርድ ቤቱ ቅጣቶችንና የጥንቃቄ እርምጃዎችን የሚወሰነው የወንጀል ህጉን ጠቅላላ ክፍል ድንጋጌዎችን እንዲሁም ስለወንጀሎችና ስለቅጣታቸው የሚደነግጉትን የልዩ ክፍሉ ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ መሆኑን፣ ቅጣት ላወሰን የሚገባው የወንጀል አድራጊውን ግላዊ የአደገኛነት መጠን ያለፈ የህይወት ታሪኩን ወንጀል ለማድረግ ያነሣሡትን ምክንያቶችና የሀሣቡን ዓላማ የግል ኑሮውን ሁኔታ፣ የትምህርቱን ደረጃ፣ እንዲሁም የወንጀሉን ከባድነትና የአፈፃፀሙን ሁኔታዎች በማመዛዘን መሆኑን፣ የወንጀል ህጉ ልዩ ክፍል ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ፍርድ ቤቱ እጅግ ቀላል ከሆነው ቅጣት አንስቶ እስከ ከባዱ ድረስ ያለውን በጥንቃቄ በመመርመር ለእያንዳንዱ ጉዳይ ተገቢ የሆነውን ቅጣት እንደሚወስን ይደነግጋል።
የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 02/2006 አንቀጽ 4/9 መመሪያው በወንጀል ሕጉ ስለቅጣት አወሳሰን ከተቀመጡት ድንጋጌዎች ጋር ተጣጥሞ መተርጎም እንደሚገባው ይደነግጋል።
አመልካቾች ጥፋተኛ የተባሉበት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 620/2/መ ድንጋጌ ከአምስት ዓመት እስከ ሀያ ዓመት ለመድረስ በሚችል ጽኑ እሥራት የሚያስቀጣ ሲሆን በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 02/2006 መሰረት ደረጃ እና እርከን የወጣለት ነው።
አመልካቾች ድርጊቱን የፈጸሙት የግል ተበዳይን አልባሳት በሙሉ በመቀዳደድ፤በድንጋይ የተለያዩ አካላትዋን ደጋግመው በመምታት፤ድርጊቱን እንዳታይ በድንጋይ ዓይኗን ጭንቅላትዋን አንገትዋን እጇን በመታት በመሆኑ እና ድንግልናዋን ከደፈሩ በኋላም እንደእባብ ሲቀጠቅጧት ያደሩ እና በጀርባዋ ወድቃ እያለ በእግራቸው ሆድዋን ረግጠው ከእግርዋ እስከ ጸጉርዋ ድርስ የሸኑባት፤ምራቃቸውን የተፉባት በመሆኑ የአመልካቾች ድርጊት አፈጻጸም አጸያፊ እና በቅጣት አወሳሰን መመሪያው ለወንጀሉ በወጣው ደረጃ መሰረት ላወከል የማይችል እና ቅጣቱ በቅጣት አወሳሰን መመሪያው መሰረት ቢወሰን የወንጀል ሕጉን የቅጣት ዓላማ እና ግብ የማያሳካ ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም ቅጣቱ በቅጣት አወሳሰን መመሪያው ቁጥር 02/2006 አንቀጽ 27/1 መሰረት ከቅጣት አወሳሰን መመሪያ ውጪ ላወሰን ይገባል ብለናል። አመልካቾች አጸያፊ በሆነ ሁኔታ የግል ተበዳይን አልባሳት በመቀዳደድ እና የተለያዩ የሰውነት ክፍሐን በድንጋይ በመምታት አካላትዋን በመርገጥ ድርጊቱን የፈጸሙ እና ድርጊቱን ከፈጸሙ በኋላም በግል ተበዳይ ላይ ምራቃቸውን በመትፋት እና ሽንታቸውን በመሽናት ጥለዋት የሕዱ በመሆኑ አመልካቾች በሀያ ዓመት ጽኑ እሥራት ላቀጡ ይገባል በማለት ወስነናል።በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በትግራይ ብሕራዊ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ ፍ/ቤት በአክሱም ምድብ ችሎት በመ. ግንቦት 17 ቀን 2008 ዓ.ም የተሰጠው የጥፋተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ፤የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ. ሐምል 28 ቀን 2008 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በመ. ታሕሣሥ 19 ቀን 2009 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 195/2/ለ/2 መሰረት ተሻሽሐል።
አመልካቾች ጥፋተኛ ላባሉ የሚገባው በወንጀል ሕግ አንቀጽ 620/2/መ መሰረት ነው ብለናል።
የበታች ፍ/ቤቶች በአመልካቾች ላይ ያስተላለፉትን የቅጣት ውሳኔ በማሻሻል አመልካቾች በሀያ ዓመት ጽኑ እሥራት ላቀጡ ይገባል በማለት ወስነናል።
-የሚመለከተው ማረሚያ ቤት በተሻሻለው የቅጣት ውሳኔ መሰረት እንዲያስፈጽም ታዟል።
-በተሻሻለው የቅጣት ውሳኔ መሰረት እንዲፈጸም የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ለሚመለከተው ማረሚያ ቤት እንዲደርሰው ታዟል።
-በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 02/2006 አንቀጽ 27/2 መሰረት የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ለፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት እንዲተላለፍ ታዟል።
-መዝገቡ ተዘግቷል።ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.