ምንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ በማከማቸት የሙስና ወንጀል ፈጽሟል ተብሎ ክስ የቀረበበት ተከሳሽ የማስረዳት ግድታ ዐቃቤ ሕግ በክሱ ከገለፀውና በማስረጃ ካረጋገጠው ውጭ ተከሳሽ ልላ ገቢ የሚያገኝበት ስራ ወይም የገቢ ምንጭ ያለው መሆኑን ብቻ ለፍርድ ቤቱ በማሳየት የሚወሰን ሳይሆን፣በዓቃቤ ሕግ ክስና ማስረጃ ከተረጋገጠው ገቢ ውጭ በእጁ እንደተገኘ የተረጋገጠው ገንዘብና ሀብት ትክክለኛ ምንጭ ምን አንደሆነ የማስረዳት ግድታና ኃላፊነት ያለበት ስለመሆኑ፡የወንጀል ሕግ አንቀጽ 419 /1//ሀ/ እና /ለ/
No summary available.
ሕዳር 25 ቀን 2010 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዳኜ መላኩ ብርሃኑ አመነው በዕውቀት በላይ እንዳሻው አዳነ ኃይሉ ነጋሽ አመልካች፡- ብርሃነ ሀለፎም ገ/መድህን-ጠበቃ ገ/እግዚአብሕር ሙናቸው ተጠሪ፡- የፍደራል የሥነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዐቃቢ ህግ መዝገቡ የተቀጠረው መርምሮ ፍርድ ለመስጠት ነው። በመሆኑም መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የቻለው የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 18/02/2009 ዓ.ም ፍርድ እና በቀን 01/03/2009 ዓ.ም የቅጣት ውሳኔ የፍደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ጥር 10 ቀን 2009 ዓ.ም በማጽናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለታቸው ነው።
ጉዳዩ ምንጩ ያልታወቀ ንብረት ገንዘብ ማከማቸት የሙስና ወንጀልን የሚመለከት ነው። ተጠሪ በአመልካች ላይ በስር ፍርድ ቤት ባቀረበው ክሱ አመልካች የወንጀል ህግ አንቀጽ 419/1//ለ/ የተመለከተውን በመተላለፍ ከመስከረም 1982 ጀምሮ በተለያዩ የመንግስት መ/ቤቶች ተቀጥሮ ሲያገለግል በፍደራል አገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ከህዳር 1/1996-ሰኔ 30/1997 በብር 595 ደመወዝ መረጃ አገልግሎት ውሰጥ በክለርክነት፣ ከሰኔ 1/1999-ነሐሴ 30/1999 በብር 1145 ደመወዝ በተ.እ.ታ. መምሪያ የግብር ከፋዮች ምዝገባ ውስጥ ሱፐርቫይዘርነት፣ ከሰኔ 1/2006-ሐምል 2/2006 በብር 7284 ደመወዝ በኢ/ገ/ጉ/ባለስልጣን የአጠቃላይ ቅሬታ አስተናጋጅ ቡድን አስተባባሪ ሆኖ ሲሰራ በነበረበት ወቅት በመንግስት ሥራ ወይም በልላ መንገድ ወይም ከሚያገኘው ወይም ሲያገኝ ከነበረው ህጋዊ ገቢ ጋር በማይመጣጠን ሁኔታ በባለቤቱ ወ/ሮ አይናለም ጌታቸው ስም የተመዘገበ በአ.አ ኮልፍ ቀ/ክ/ከ ቀበል 02/03 የቤት ቁጥር 2244 የካቲት 26/2000 ዓ.ም የተገዙ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ቆሬ ኮንደሚኒየም የቤት ቁጥር ቢ51/54003 ሐምል 9/2004 ዓ.ም የተገዛ እና ከ10/03/2005 ጀምሮ የካፍቴሪያ አገልግሎት የሚሰጥ በባለቤቱ ስም የተመዘገበ ንግድ ፈቃድ፣ በአመልካች ስም የዳሽን ባንክ ሂሳብ 3553001 እስከ ሐምል 13 ቀን 2004 የነበረ .19፣ በባለቤቱ ወ/ሮ አይናለም ጌታቸው ዳሽን ባንክ ሂሳብ 3552001 እስከ ሐምል 13 ቀን 2004 የነበረ .28 ያለአግባብ ያከማቹ በመሆኑ ምንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ ማከማቸት ወንጀል ፈጽሟል የሚል ነው።
አመልካች የቀረበበትን ክስ በመካዱ በተጠሪ የቀረውን የሰነድ ማስረጃዎች ፍርድ ቤቱ ከመረመረ በኋላ የቀረበበትን ክስ እንዲከላከል በሰጠው ብይን በአመልካች 6 የሰው የመከላከያና የጽሁፍ ማስረጃዎች የቀረቡ መሆኑን ገልጾ ፍርድ ቤቱ ከመረመረ በኋላ ተጠሪ በአመልካች እና በባለቤቱ ስም ተመዝግበው የሚገኙት ንብረት እና ገንዘብ የአመልካች ገቢ ተብሎ ከተገለፁት በላይ መሆኑን የሚያስገነዝብ መሆኑን፤ የአመልካች አንደኛ ምስክር በብድር ለአመልካች ሁለት ጊዜ ሰጥቻለው ያሉትን በተመለከተ የመጀመሪያውን በ1999 ተሰጠ ውድቅ በማድረግ ሁለተኛው በ2004 ዓ.ም የተሰጠውን የብድር ውሉ ያረጋግጣል በማለት ተቀብሎታል፡ ሁለት የአመልካች ወንድሞችና መከላከያ ምስክሮች የአባታቸው የውርስ ድርሻ ተሸጦ ለአመልካች ቤት መግዢያ የሰጡት መሆኑን የገለጹ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ አልተቀበለውም፡ በልላ በኩል 4ኛ 5ኛ እና 6ኛ ምስክር በተመለከተም አመልካች በግል ያስተምር የነበረ መሆኑን ገቢው እንደማይታወቅ፤ ዕቁብ የደረሰው ስለመሆኑ የገለፁ መሆኑን ገልጾ አመልካች የመንግስት ሥራ ከጀመረበት 1982-1999 የነበረው አጠቃላይ የደመወዝ ገቢ የነበረና በአመልካች ባለቤት ስም ቤት የገዛው በመሆኑ ይህንን ለመግዛት የሚያስችል ገቢ የለውም በልዩነት የተገኘው ፣ አመልካች ጥቅምት 3/2003 ድረስ ያለው ጥቅል ገቢ ተሽከርካሪ ከገዛበት በልዩነት የተገኘ እና ሐምል 9/2004 የተገዛውን ቤት ጋር ገቢውና በብድር የተገኘው ሲነፃፀር ንብረቱን ለማፍራት የሚችልበት ነው፣ በባንክ ያለው ገንዘብ በወቅቱ ከነበረው ገቢ ጋር ሲነፃፀር ልዩነቱ .47 አመልካች አላስረዳም በአጠቃላይ አመልካች ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ይዞ ተገኝቷል ከተባለው ውስጥ .47 የሆነውን ብቻ ምንጩን ህጋዊ አመጣጡን ያላስረዳ ስለሆነ በቀረበበት ክስ የወንጀል ህግ አንቀጽ 419/1//ለ/ የተመለከተውን በመተላለፍ ጥፋተኛ ነው ብሎ በአንድ ዓመት ከሁለት ወር እስራት አና በብር 5000 የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ እና .47 ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ያቀረቡት ይግባኝ የፍደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሳይቀበል የስር ፍ/ቤት ውሳኔን አጽንቶታል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንን በመቃወም ሲሆን ይዘቱም የኮንደሚኒየም ቤት የተገዛበትን ገንዘብ ወጪ ሆኖ የተከፈለው ከቤትና ከባንክ ገንዘብ ሲሆን እንደተለያዩ ንብረት አድርጐ ወስዷል፣ የቀረበውን ክስ በመከላከያ ማስረጃዬ አስተባብያለሁ፣ የመከላከያ ምስክር የሰጠኝ ብድር አንዱን ተቀብሎ ልላውን ውድቅ ያደረገበት ምክንያት ተገቢ አይደለም፣ የአባቴን የውርስ ድርሻ ወንድሞቼ የሰጡኝ ስለመሆኑ ማረጋገጣቸው መተሳሰብና መፋቀር እንጂ ሀብትን አያመለክትም ፤አመልካች በግል የማስተምር እና የምነግድ መሆኑ ባለቤቴም ከመጋባታችን በፊት ጀምሮ ነጋድ መሆንዋ መጠኑ ባለመታወቁ መታለፍ የለባትም፣ የደረሰኝ ዕቁብ አልተያዘም፣ ለቤቱ መግዢያ ይኸው መዋሉን ገልጬ አልተያዘም የሚል ነው። የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ የስር ፍ/ቤት ሳይዝ ብቻ የያዘበት እና 2ኛ ምስክር የአመልካች ወንድምን እህት የሰጡትን ፍ/ቤቱ ውድቅ ያደረገበትን አግባብ ለመመርመር ተጠሪ ቀርቦ መልስ አንዲሰጥ በታዘዘው መሰረት በሰጠው መልሱ የአመልካች አቤቱታ መሰረታዊ የህግ ስህተት ሳይሆን የማስረጃ ምዘናን የሚጠይቅ ነው፡ ተቀባይነት የለውም፣ የገንዘብ ብድሩን በተመለከተ የስር ፍ/ቤት ተገቢውን ማጣራት አድርጐ የወሰነው ነው። የመከላከል ምስሮችም የተጠና ላሆን የሚችል እንጂ አልተከላከለውም፣ ሁለት ጊዜ የታሰበ የለም፣ የሚሉ ዝርዝር መልስ ሰጥተዋል። አመልካችም የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዳዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለዚህ ሰበር ምክንያት ከሆነው የስር ፍ/ቤት ውሳኔ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ለዚህ ሰበር ችሎት ያስቀርባል ሲባል ከተያዘው ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለው መርምረነዋል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የሚቻለው አመልካች የመንግስት ሰራተኛ በመሆን ያገኘውን ገቢ መሰረት በማድረግ አፍርቶታል የተባለውን ገንዘብ እና ንብረት .47 ልዩነት ያለው በመሆኑ ተመጣጣኝ አይደለም ምንጩንም ማስረዳት አልቻለም በማለት በተሰጠው ውሳኔ ላይ በማስረጃ ምዘና ወቅት በብድር ያገኘው እና የውርስ ንብረት ከወንድሞቹ የተላለፈለትን ውድቅ የተረገበትን አግባብ ለመመርመር ያስቀርባል መባሉን ነው።
ከወንጀል ሕግ አንቀጽ 419 ንዑስ አንቀጽ 1//ሀ/ እና /ለ/ ድንጋጌዎች ለመረዳት የሚቻለው ዐቃቤ ሕግ የመንግስት ሰራተኛ የሆነው ወይም የነበረው ሰው ያገኝ የነበረውና የሚያገኘው ገቢ ምን ያህል እንደሆነና የመንግስት ሰራተኛው በራሱ ስምም ሆነ በቤተሰቡ ስም ከሕጋዊ ገቢው ውጪ ይዞት የሚገኘውን የገንዘብና የንብረት ግምት የማስረዳት ግድታ ያለበት መሆኑን በመግልፅ ተደንግጓል። በልላ በኩል የመንግስት ሰራተኛ የነበረው ሰው ከነበረውና ከሚያገኘው ገቢ በላይ ይዞት የተገኘው ገንዘብ ወይም ሀብት ትክክለኛው ምንጭ ምን እንደሆነ የማስረዳት ግድታ እንዳለበት በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 419 ንዑስ አንቀጽ 1 ሶስተኛው ፓራግራፍ ፣ “… የዚህ አይነቱ የኑሮ ደረጃ እንድት ላኖረው እንደቻለ ወይም ያለው ንብረት ወይም የገንዘብ ምንጭ በእጁ እንድት እንደገባ ለፍርድ ቤቱ ካላስረዳ በስተቀር” ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ይዞ በመገኘቱ ጥፋተኛ ተብለው በሕጉ የተደነገገው ቅጣት ላጣልባቸው እንደሚችል በመግለፅ ይደነግጋሉ። ከዚህም የምንረዳው ዐቃቤ ሕግ በግልፅ ከሚታወቀው ሕጋዊ ገቢ በላይ ነው በማለት በክሱ የተገለፀውንና በማስረጃ ያረጋገጠውን ሀብት ትክክለኛ ምንጭ የማስረዳት ግድታ / Burden of Proof/ በተከሳሾች ላይ የሚወድቅ መሆኑን ነው።
የተከሳሾች የማስረዳት ግድታም ዐቃቤ ሕግ በክሱ ከገለፀውና በማስረጃ ካረጋገጠው ውጭ ተከሳሽ ልላ ገቢ የሚያገኝበት ስራ ወይም የገቢ ምንጭ ያለው መሆኑን ብቻ ለፍርድ ቤቱ በማሳየት የሚወሰን ሳይሆን፣ በዐቃቤ ሕግ ክስና ማስረጃ ከተረጋገጠው ገቢ ውጭ በእጁ እንደተገኘ የተረጋገጠው ገንዘብና ሀብት ትክክለኛ ምንጭ ምን እንደሆነ የማስረዳት ግድታና ኃላፊነት ያለበት መሆኑን ከወንጀል ሕግ አንቀፅ 419 ንዑስ አንቀጽ 1 ሶስተኛው ፓራግራፍ ድንገጌ አቀራረፅና ይዘት ለመረዳት ይቻላል።
ከዚህ አንጻር አመልካች የመንግስት ሰራተኛ ሆነው ካገኙት ህጋዊ ገቢ /ደመወዝ/ በተጨማሪ ያስቀርባል ሲባል የተያዙትን ከመከላከያ ምስክራቸው በብድር አግኝቼዋለሁ ያሉትን እና እህት እና ወንድማቸው የአባታቸውን ድርሻ ሰጥተውኛል ያሉት የስር ፍርድ ቤት ቢቀበላቸው በልዩነት ከገቢያቸው በላይ ለሆነው የገንዘቡን ምንጭ አላስረዱም ብሎ ጥፋተኛ ካለበት .47 አንጻር የሚያስተባብል አይደለም። በዋናነት ግን የስር ፍርድ እነዚህን በብድርና በስጦታ ተገኙ የተባሉትን የገንንዘብ ምንጮች ውድቅ ያደረገው በግራ ቀኙ የቀረቡትን ማስረጃዎች መርምሮና መዝኖ መሆኑ ሲሆን ይህ በፍሬ ጉዳይ ላይ የስር ፍርድ ቤት የደረሰበት ድምዳሜ የማስረጃ ምዘና ጉዳይ በመሆኑ በዚህ ሰበር ችሎት ላታይ የሚችልበት አግባብ የልለ ስለመሆኑ የኢ.ፍ.ድ.ሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 80/3//ሀ/ እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 ድንጋጌዎች ይዘት የሚያስገነዝብ ነው።
ስለሆነም የስር ፍርድ ቤት ማስረጃዎችን በመመዘን በደረሰበት ድምዳሜ ላይ የቀረበው አቤቱታ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት አልተቻለም። በዚህም መሰረት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 18/02/2009 ዓ.ም የሰጠውን ፍርድ በ01/03/2009 የቅጣት ውሳኔ እና የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 10/05/2009 ዓ.ም በማጽናት የሰጠው ትእዛዝ በወ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ 195/2/ /ለ/ /2/ መሰረት ፀንቷል።
No topics extracted.