ተሻሽሎ የቀረበ አንድ የወንጀል ክስ የተከሳሹ ያዕቆብ አብዱ ህዳር 29 184 XX መብት ላይ የሚኖረዉ አሉታዊ ተጽእኖ ጋር ተመዛዝኖ በስነስርዓት ህጉ የተጠበቀለት የመሰማት መብቱን በጥብቅ ተግባራዊ በማድረግ ክሱ እንደገና ተሰምቶ መወሰን ያለበት ስለመሆኑ በወ/መ/ስ/ስ/ህግ ቁ 118፤119/2/ ፤120 እና 121 እና የደቡብ ክልል አቃቤ ህግ ቀን 2010 ዓ.ም 37. የተከሰሰ ሰው የዓቃቤ ህግ ማስረጃ ሲሰማ በመገኘት የዓቃቤ ህግና ምስክሮች የመጠየቅና የመመርመር መብቱን በአግባቡ ከተጠቀመና መከላከያ ማስረጃ በማቅረብ እንዲከላከል ተፈቅዶለት ቀጠሮውን አክብሮ ያልቀረበ በሆነበት አግባብ ፍ/ቤቶች ጉዳዩ በልለበት የሚታይ አይደለም በማለት የሚሰጡት ውሳኔ አግባብነት የልለው ስለመሆኑ፡የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 161 እና 164 እና የህ/መ አንቀጽ 20/4/ XXI
No summary available.
መስከረም 22 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው በእውቀት በላይ እንዳሻው አዳነ ሃይሉ ነጋሽ እትመት አሰፋ አመልካች፡- የአ/ብ/ክ/መ/ፍ/ቢሮ ዓ/ህግ- አብርሃም በለጠ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ አንዱአለም ገናነው መላኩ - አልቀረቡም መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ነው ስለሆነም ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የአማራ ብ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። የጉዳዩን አመጣጥ ከመዝገቡ እንደተረዳነው አመልካች በስር ደጀን ወረዳ ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ ያቀረበው ክስ መነሻ ያደረገ ሲሆን የቀረበው ክስ ይዘት ተከሳሽ የወንጀል ህግ አንቀጽ 555(1(ለ)) በመተላለፍ የሰው አካል ላይ ጉዳት ማደረስ ወንጀል ተከሷል በማለት ክስ ቀርቦበታል። የሥር ተከሳሽ ፍ/ቤት ቀርቦ ክሱ ተነቦለት በሰጠው የእምነት ክህደት ቃል ድርጊቱን አልፈፀምኩም በማለት ክዶ ተከራክሯል። ከዚህ በኋላ ፍ/ቤቱ የዐ/ሕግ የሰዉ ምስክሮች በመስማትና በመመርመር ተከሳሽ ስለተመሰከረባቸው እንዲከላከሉ ብይን በሰጠዉ መሰረት ተከሳሽ መከላከያ ምስክሮች አስቀርቦ እንዲያሰማ ቀጠሮ ሰጥቷል። የተከሳሽ መከላከያ ምስክር ለመስማት ተደጋጋሚ ቀጠሮ የተሰጠ ሲሆን ተከሳሽ መከላከያ ምስክሩ በሚሰማበት ቀነ ቀጠሮ መከላከያ ምስክሩን ይዞ ባለመቅረቡ አመልካች ተከሳሽ መከላከያ የማቅረብ መብቱ ታልፎ ጉዳዩ በልለበት እንዲታይለት ለፍርድ ቤት አመልክቷል።
ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ የተከሰሰበት የህግ ድንጋጌ በወ/መ/ስ/ስ/ሕ/ቁጥር 161 መሰረት በልለበት ጉዳዩ ላታይ የሚቻል አይደለም በማለት ፖላስ ተከሳሽ ካለበት ቦታ አፈላልጎ እንዲያቀርብ ትእዛዝ በመስጠት መዝገቡን ዘግቷል። በዚሁ ውሳኔ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቤቱታውን ደግሞ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት እንደቅደም ተከተላቸው አቅርቦ አቤቱታውን ባለመቀበል ሰርዘውታል። አሁን የቀረበው ቅሬታ በዚሁ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በሰበር ችሎት ላታይ ይገባዋል በመባሉ ተጠሪ ቀርበው የጽሁፍ ክርክራቸው እንዲያቀርቡ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ባለመቅረባቸው በፅሁፍ መልስ የመስጠት መብታቸው ታልፏል።
የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ይህ ችሎትም የቀረበው ቅሬታ የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። ከመዝገቡ ይዘት ለመረዳት እንደተቻለው ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ተከሳሽ በመሆን የቀረበበት ክስ የወ/ህ/ቁጥር 555(1(ለ)) የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ሲሆን ተጠሪ ችሎት ቀርቦ የእምነት ክህደት ቃሉን ሲሰጥ ክዶ የተከራከረ መሆኑ የከሳሽ ዓ/ህግ ምስክሮች ሲሰሙ ችሎት ቀርቦ የተከራከረ እና እንዲከላከል ተነግሮት በተደጋጋሚ ቀጠሮ መከላከያ ማስረጃውን ይዞ ያልቀረበ መሆኑ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው ።አሁን ለቀረበው ጉዳይ የስር ፍርድ ቤቶች ተከሳሽ እንዲከላከል ትእዛዝ ተሰጥቶና አውቆ መከላከያ ምስክሩን ይዞ ባለመቅረቡ የመከላከል መብቱ ታልፎ ውሳኔ እንዲሰጥ የቀረበው የአመልካች አቤቱታ ጉዳዩ በልለበት የሚታይ አይደለም በማለት ውድቅ ማድረጋቸው ተገቢ ነው ወይስ አይደለም ? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዳዩን መርምረናል።
ጉዳዩን እንደመረመርነው ተጠሪ የወንጀል ክሱ በሚሰማበት ጊዜ ወንጀሉን ያልፈፀመ መሆኑን በመግለፅ የተከራከረ መሆኑ፣ተጠሪ ባለበት አመልካች ማስረጃዎቹን ያሰማ መሆኑንና ተጠሪም የመከላከል መብቱ ተጠብቆለት እንዲከላከል ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ሲሰጥ በችሎት የነበረ መሆኑ ተረጋግጧል።
ይህም ተጠሪ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 20 ንኡስ አንቀጽ 4 በተደነገገው መሰረት የአመልካችን ምስክሮች ቃል የመመርመርና የመጠየቅ መብቱ ሙሉ በሙሉ በተከበረበት ሁኔታ ተጠሪ በህገ መንግስት የተጠበቀለት የመከላከል መብት ፍርድ ቤት ቀርቦ ማሰማትና መጠቀም ሲገባው በራሱ ፍቃድ የተወው መሆኑ ከክርክሩ ይዘት ለመረዳት ችለናል።
በመርህ ደረጃ የወንጀል የክርክር ሂደት ተከሳሾች ባሉበት እንደሚደረግ በልዩ ሁኔታ ደግሞ የፈጸሙት ወንጀል ቀርበው መከራከር የማይፈልጉና ከፍትህ ስርዓቱ የሸሹ ግለሰቦች በፍትህ ስርዓቱ መጠየቅ ያለባቸው በመሆኑ በልሉበት ነገሩ ላሰማ እንደሚችል ከወ.ሥ.ሥ.ሕ.ቁ. 161(1) እና (2(ሀ) ድንጋጌ መሰረታዊ ይዘት ንባብ የምንረዳው ነው።
ፍርድ ቤቱም አንድን ጉዳይ ተከሳሽ በልለበት ለማየት እንዲችል ተከሳሹ በቀጠሮ ቀን ያለ በቂ ምክንያት መቅረቡ ሲረጋገጥ ብቻ መሆኑ የዚህ ድንጋጌ ንዑስ አንቀጽ 1 በግልጽ ያመለክታል። ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ በልለበት ነገሩ ለመስማት ትዕዛዝ ከሰጠ ጥሪው ተደራሽ በሆነ አግባብ ማስተላለፍ ይጠበቅበታል። በወ.ሥ.ሥ.ሕ.ቁ. 162 እንደተመለከተው ፍርድ ቤቱ የሚያስተላለፈው ጥሪ ተከሳሹ ስለተጠረጠረበት ጉዳይ ዝርዝር መግለጫ የያዘ እና ጥሪውም በጋዜጣ እንዲወጣ መታዘዝ እንዳለበት ከድንጋጌው ይዘት የምንገነዘበው ነው። በልላ በኩል ፍ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘም የመጥሪያ ማስታወቂያው በልላ መንገድ ማስተላለፍ እንደሚችል የዚህ ድንጋጌ ንዑስ አንቀጽ ሁለት ያሳያል።በያዝነው ጉዳይ ተጠሪ ክሱ በሚሰማበትና የከሳሽ ዓ/ህግ ምስክሮች በሚሰሙበት ጊዜ ችሎት ቀርቦ የተከራከረ በመሆኑ እና በተከሰሰበት የህግ ድንጋጌ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቶ አውቆ መከላከያ ማስረጃ ለመስማት ፍርድ ቤቱ ቀጠሮ በያዘበት ቀን ሳይገኝ መቅረቱ ጉዳዩ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 20 ንዑስ አንቀጽ (4) በወንጀል የተከሰሰሰው የዓቃቤ ህግ ማስረጃ ሲሰማ በመገኘት የዓቃቤ ህግን ምስክሮች የመጠየቅና የመመርመር መብቱን በአግባቡ ከተጠቀመና የመከላከያ ምስክሮችንና ማስረጃ እንዲያቀርብ የተሰጠውን መብት በራሱ ፍላጎት ካልተጠቀመ እና የመከላከል መብቱን ካልተጠቀመ ዳኞች የቀረበውን ክርክርና ማስረጃ በመመዘን ፍርድ ከመስጠት የሚገድባቸው ባለመሆኑ በህጉ ለተከሳሽ ከተሰጠው የመደመጥ መብት አንፃር ተከሳሹ መብቱ በራሱ ፍላጎት ባለመጠቀሙ ጉዳዩ ተከሳሹ በልለበት እንደሚታይ ጉዳይ ላታይ የሚችል ባለመሆኑ ፍርድ ቤቶች የቀረበውን ጉዳይ መርምረውና መዝነው ውሳኔ ከመስጠት የሚገድባቸው ጉዳይ አይሆንም። ከዚህ አንፃር ስንመለከተው ተጠሪ (የስር ተከሳሽ) መከላከያ ማስረጃ በማቅረብ እንዲከላከል ተፈቅዶለት ቀጠሮውን አክብሮ ባልቀረበበት ሁኔታ የስር ፍርድ ቤቶች ጉዳይ ከወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 161 ጋር በማያያዝ ጉዳዩ በልለበት የሚታይ አይደለም በማለት ውሳኔ መስጠታቸው፣ አንድ ጉዳይ ተከሳሽ በልለበት በ(defau|t procedure) ታየ የሚባለው መቼ ነው? ተከሳሽ በልለበት የወንጀል ክስ ስለሚታይበት ሁኔታ የሚደነግጉት ከወንጀለኛ መቅጫ ሥነስርዓት ሕግ ቁጥር 161 እስከ 164 የተደነገጉት ድንጋጌዎች ይዘት ትርጉምና ተፈፃሚነትና ውጤት እንደዚሁም በወንጀል የተከሰሰ ሰው በእነዚህ ድንጋጌዎች መሰረት በልለበት ታይቶ ከሚሰጥ ፍርድ ለእንድት አይነት ጉዳይ ነው የሚለውን የህገመንግስቱን አንቀጽ 20 ንዑስ አንቀጽ 4 እና የወንጀለኛ መቅጫ ስነስርዓት ሕግ ቁጥር 149 ንዑስ አንቀጽ 1 እና 4 ድንጋጌ ይዘት መንፈስና ዓላማ ያላገናዘበና የህግ መሰረት የልለው ሆኖ አግኝተነዋል።
በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች በጉዳዩ ላይ ውሳኔ የሰጡት የተረጋገጠው ፍሬ ነገር ከሕጉ ጋር ሳያገናዝቡ በመሆኑ የክርክሩ ሂደት በአግባቡ የተመራና የተሟላ ሁኖ አልተገኘም። የክርክሩ ሂደት በአግባቡ ያለመመራትና የተሟላ ፍሬ ነገር እንዲኖር ያለማድረግ የዳኝነት አሰጣጥ ሰርዓት የማይፈቅደው በመሆኑ የመሰረታዊ ሕግ ስህተት መመዘኛን የሚያሟላ ነው።
ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
መጋቢት 01 ቀን 2008 ዓ/ም በትእዛዝ የፀናው ውሳኔ በወ.መ.ሕ.ስ.ስ.ቁ.
195(2)(ለ)(1) መሰረት ተሽሯል።
ተጠሪ የክርክሩ ሙሉ ሂደት ተከታትሎ ለተከሰሰበት ወንጀል እንዲከላከል ትእዛዝ መሰጠቱን አውቆ የጠፋ ስለሆነ ይህ ጉዳይ በልለበት ላባል የሚችል ስላልሆነ ፍርድ ቤቱ ተጠሪ የመከላከል መብቱን ለመጠቀም እንዳልፈለገ ቆጥሮ ተገቢውን እንዲወስን ለክልሉ ደጀን ወረዳ ፍርድ ቤት ተመልሶለታል።ይፃፍ።
እንዲያውቁት የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍ/ቤቶች ይላክ።
No topics extracted.