“…ማናቸውም የግል አቤቱታ በቀረበ ጊዜ ይቀጣል..” የሚል አገላለጽ በውስጣቸው የሚገኙ ድንጋጌዎችን በመተላለፍ ወንጀል በተፈጸመ ጊዜ በግል አቤቱታ እንዲያቀርብ ከተፈቀደለት ሰው በቀር በልላ በማንም ሰው የክስ ጉዳይ ላንቀሳቀስ የማይችል ስለመሆኑና የግል ከሳሽ የሆነው ሰውም የማመልከቻውን አዘገጃጀት በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 150-153 መሰረት መምራት የሚኖርበት ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 556/2/ እና 575/2/ሀ/ መሰረት ተደርጎ የቀረበ የወንጀል ክስ በግል ተበዳይ ወይም ህጋዊ ወኪሉ አማካይነት የሚቀርብ እና በግል አቤት ባይ የቀረበ ክስ በሚመራበት ስነ-ስርዓት የሚመራ ሳይሆን በዓቃቤ የፍ.ጠ.ዓ/ህግ እና እዮኤል ተስፋዬ የሺጥላ XVIII ወይም በመንግስት የሚቀርቡ የወንጀል ክሶች በሚመሩበት ስርዓት የሚስተናገዱ እና በግል ተበዳይ ፍላጎት መሰረት ላቋረጡ የማይችሉ ወንጀሎች ስለመሆናቸው፣ የወ/ህ/ስ/ስ/ህ/ቁ 150-153 እና የወ/ህ/ቁ. 559/2/ እና 575/2/ሀ/፣ በወ/ህ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.
No summary available.
መስከረም 30 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው በዕውቀት በላይ እንዳሻው አዳነ ሃይሉ ነጋሽ እትመት አሰፋ አመልካች፡- አቶ አሸብር መለስ ተጠሪ፡- የፍድራል ዓቃቤ ሕግ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ ወንጀል ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው።
ተጠሪ በሥር ፍ/ቤት በአመልካች ላይ ያቀረበው ክስ ይዘት በአጭሩ አመልካች የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 626/4/ሀ በመተላለፍ ከእርሱ ጋር ተቃራኒ ጾታ ካላት ዕድሜዋ አሥራ ሥምንት ዓመት ካልሞላት ልጅ ጋር የግብረሥጋ ግንኙነት ለመፈጸም በማሰብ በቀን 10/08/07 ዓ.ም በግምት ከጠዋቱ 12፡30 ሲሆን በየካ ክፍለ ከተማ ቀበል 16/17 ክልል ልዩ ቦታው ላምበረት አካባቢ የቤት ሰራተኛ የሆነችው እና እድሜዋ ከ15/16 ዓመት የሚገመተውን የግል ተበዳይ ዓይናለም አየነው ጋር የግብረሥጋ ግንኙነት የፈጸመ በመሆኑ ዕድሜያቸው አሥራ ሦስት ዓመት በሆነ እና አሥራ ሥምንት ዓመት ባልሞላቸው ልጆች ላይ የሚፈጸም የግብረሥጋ ድፍረት በደል ወንጀል ፈጽሟል የሚል ነው።
ለአመልካች ክሱ ተነቦለት መቃወሚያ አቅርቦ መቃወሚያው በብይን ውድቅ ከተደረገ በኋላ የእምነት ክሕደት ቃሉን ሲጠየቅ ድርጊቱን አልፈጸምኩም በማለት ክዶ በመከራከሩ ፍ/ቤቱ የተጠሪ ምስክሮች እንዲሰሙ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት የተጠሪ ምስክሮች ተሰምተዋል።
የተጠሪ 1ኛ ምስክር የሆነችው የግል ተበዳይ ለፍ/ቤቱ በሰጠችው የምስክርነት ቃል በአመልካች ቤት በቤት ሰራተኛነት የተቀጠረች መሆኑን፤አመልካች ጠዋት ሚስቱ ወደ ሥራ ስትወጣ ቀኑን በማታስታውሰው ዕለት አመልካች የግብረሥጋ ግንኙነት የፈጸመባት መሆኑን፤ድርጊቱን የፈጸመችው በፍላጎት መሆኑን፤አመልካች የወርአበባ መምጫ ጊዜዋን የሚያውቅ እና የሚቆጣጠር መሆኑን፤ከአመልካች ቤት ከወጣች በኋላ ልላ ሰው ቤት የገባች መሆኑን፤ለአመልካች ስልክ ደውላ አርግዣለሁ ስትለው የሰደባት እና አላውቅልሽም ብሎ ስልኩን የዘጋው መሆኑን፤በአመልካች ቤት ያስቀጠረቻት ትዝታ የተባለች ግለሰብ መሆንዋን፤ድርጊቱ እንደተፈጸመ ለማንም ያልተናገረች መሆኑን፤ድርጊቱ ከተፈጸመ ከተወሰነ ቀን በኋላ ከቤቱ የወጣች እና ወደ ትዝታ ቤት የሕደች መሆኑን፤ትዝታ ሰው ቤት ካስቀጠረቻት በኋላ አርግዣለሁ ብላ ለአመልካች ስልክ ስትደውልለት ሲሰድባት ለትዝታ አርግዣለሁ ብላ የነገረቻት መሆኑን፤አርግዣለሁ ያለችው ገንዘቧን ስለከለከላት ተናዳ መሆኑን፤የአመልካች ባለቤት ደውላ የጠየቀቻት እና ሁሉንም ነገር የነገረቻት መሆኑን፤የአመልካች ባለቤት ጋንዲ ሆስፒታል ወስዳ ያስመረመረቻት መሆኑን በመግለጽ መሥክራለች።
የተጠሪ 2ኛ ምስክር ለፍ/ቤቱ በሰጠችው የምስክርነት ቃል የግል ተበዳይ አመልካች ደፍሮኛል ስትላት ማመን ስላቃታት ስልክ ደውይለት ያለቻት መሆኑን፤የግል ተበዳይ ለአመልካች አርግዣለሁ ብላ ስልክ ስትደውልለት የሰደባት መሆኑን፤የአመልካች ባለቤት ስለድርጊቱ ለማወቅ የግል ተበዳይ መመርመር አለባት በማለት ስልክ የደወለችላት መሆኑን፤ከአመልካች ባለቤት ጋር በመሆን የግል ተበዳይን ሆስፒታል ወስደው ያስመረመሯት መሆኑን በመግለጽ መስክራለች። የግል ተበዳይ በ25/10/07 ዓ.ም የተመረመረች እና በክብረንጽሕና መገለጫ አካሐ ላይ የቆየ የክብረንጽህና መገርሰስ መኖሩን እና ልላ አካላዊ ጉዳት ያልተገኘባት መሆኑን የሚያሳይ ከጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል የቀረበው የሕክምና ማስረጃ እና የግል ተበዳይ ዕድሜ ከ15-16 ዓመት መሆኑን የሚያሳይ ከዳግማዊ ምኒላክ ሆስፒታል የተጻፈ የሕክምና ማሥረጃም ቀርቧል።
ፍ/ቤቱ ተጠሪ ባቀረበው የሰው ምስክር እና የሰነድ ማሥረጃ እንደክሱ አስረድቷል በማለት አመልካች እንዲከላከል ብይን ሰጥቷል። 1ኛ የአመልካች መከላከያ ምስክር ለፍ/ቤቱ በሰጠችው የምስክርነት ቃል አመልካች ድርጊቱ ተፈጸመ በተባለበት ሰዓት በቤት ውስጥ ያልነበረ መሆኑን፤የግል ተበዳይ ለአመልካች ሥልክ ደውላ አርግዣለሁ ያለች መሆኑን እና እውነት መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ ጋንዲ ሆስፒታል ወስደው ያስመረመረቻት መሆኑን በመግለጽ መስክራለች።
2ኛ የአመልካች መከላከያ ምሥክር የግል ተበዳይ ስትሆን ለፍ/ቤቱ በሰጠችው የምሰክርነት ቃል በአመልካች ቤት ተቀጥራ ስትሰራ የነበረ እና ልላ ሰው ቤት ለመስራት ብላ ከአመልካች ቤት በፍላጎትዋ የለቀቀች መሆኑን፤ከአመልካች ቤት ከለቀቀች በኋላ የተቀጠረችበት ቤት ባለቤት አስቀድሞ ስትሰሪበት የነበረው ቤት አሰሪዎች ገንዘብሽን ከፍለውሻል ወይ ብላ ስትጠይቃት ገንዘቤን አልሰጡኝም ስትላት ገንዘብሽን እንዲሰጡሽ ክሰሽው አስፈራሪያቸው ስላለቻት ክሱን የመሰረተች መሆኑን እንጂ ከአመልካች ጋር የግብረሥጋ ግንኙነት ፈጽማ የማታውቅ መሆኑን፤አመልካችን ያለአግባብ በመክሰሷ የጸጸታት መሆኑን፤በዚህም ምክንያት አመልካችንና ባለቤቱን ይቅርታ የጠየቀቻቸው መሆኑን እና ክሱን እንደምታነሳ የነገረቻቸው መሆኑን፤ይቅርታ ጠይቂ ብሎ የነገራት ወይም የመከራት ሰው የልለ መሆኑን፤በራሷ ተነሳሽነት ይቅርታ የጠየቀች መሆኑን እና በዚህም ምክንያት ከአመልካች ወይም ከባለቤቱ የተከፈላት ገንዘብ የልለ መሆኑን በመግለጽ መሥክራለች።
የአመልካች 3ኛ መከላከያ ምስክርነት ቃል ለፍ/ቤቱ በሰጠው የምሥክርነት ቃል ድርጊቱ ተፈጸመ በተባለበት ዕለት አመልካች ቤት ምሳ ተጠርተው ሄደው እንደነበረ እና ተበዳይ በወቅቱ ጤናማ እንደነበረች እና ሰኔ 21 ቀን 2007 ዓ.ም ልጁን ሲያስመርቅ አመልካችን እና ባለቤቱን ጠርቷቸው ተበዳይ ለአመልካች ስልክ ደውላ ደፍሮኛል ብየ እከስሃለሁ ያለችው መሆኑን በመግለጽ መሥክሯል። ፍ/ቤቱ በግራቀኙ የቀረቡትን ማሥረጃዎች ከመረመረ በኋላ አመልካች የግል ተበዳይን በመከላከያ ምሥክርነት አቅርቦ ያሰማ ቢሆንም የግል ተበዳይ የአመልካች መከላከያ ምሥክር ሆና በሰጠችው ቃል አመልካችን እንድከሰው የገፋፋችኝ አመልካችን የማታውቅ እና ከግል ተበዳይ ጋርም ዝምድና የልላት እና አንድ ሣምንት ብቻ የሰራችባት አሰሪ ነች ያለች በመሆኑ በምንም ሁኔታ ላሆን የሚችል አይደለም፤ምስክሯ አመልካች አንድ ደፍሮኛል ልላ ጊዜ ደግሞ አልደፈረኝም በማለት የሰጠችው ቃል እምነት የሚጣልበት አይደለም፤የአመልካች ምስክሮች ቃልም እርስ በእርስ የሚደጋገፍ አይደለም በማለት አመልካች በተከሰሰበት የሕግ አንቀጽ ጥፋተኛ ነው ብሎ በሦስት ዓመት ከሰባት ወር ቀላል እሥራት እንዲቀጣ በማለት ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ይግባኝ ያቀረበ ቢሆንም አቤቱታው ተቀባይነት አላገኘም።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡-የግል ተበዳይ የአመልካች የመከላከያ ምስክር ሆና ለፍ/ቤቱ በሰጠችው የምሥክርነት ቃል አመልካች በክሱ የተጠቀሰውን ድርጊት አልፈጸመብኝም የግብረሥጋ ግንኙነት ፈጽሞብኛል ያልኩት ገንዘቤን ስለከለከለኝ እና አሰሪዬ አመልካች ገንዘብሽን እንዲሰጥሽ ክሰሽው ስላለችኝ ነው በማለት በመሰከረችበት ሁኔታ የበታች ፍ/ቤቶች አመልካችን ጥፋተኛ በማለት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ላታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የግል ተበዳይ በአመልካች የመከላከያ ምሥክርነት ቀርባ ከአመልካች ጋር የግብረሥጋ ግንኙነት አልፈጸምንም፤የግብረሥጋ ግንኙነት ፈጽመናል ብዬ የከሰስኩት የሰራሁበትን ደመወዜን እንዲከፍለኝ ነው በማለት በመሰከረችበት ሁኔታ አመልካች ጥፋተኛ የመባሉን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎ ግራቀኙ በጽሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል።
የጉዳዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው። እኛም እንዲጣራ የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር እና ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምረነዋል። የግል ተበዳይ የተጠሪ ምስክር ሆነ በመቅረብ አመልካች በክሱ በተገለጸው ሁኔታ ድርጊቱን የፈጸመባት ስለመሆኑ የመሰከረች ቢሆንም የአመልካች መከላከያ ምስክር ሆና ስትቀርብ ከአመልካች ቤት በፍላጎትዋ የለቀቀች መሆኑን፤አመልካች በክሱ የተገለጸውን ድርጊት ፈጽሟል ያለችው ከአመልካች ቤት ከለቀቀች በኋላ የተቀጠረችበት ቤት አሰሪ አመልካች ገንዘብሽን እንዲሰጥሽ ክሰሽው አስፈራሪያቸው ስላለቻች እንጂ ከአመልካች ጋር የግብረሥጋ ግንኙነት ፈጽማ የማታውቅ መሆኑን፤አመልካችን ያለአግባብ በመክሰሷ የጸጸታት መሆኑን፤አመልካችንና ባለቤቱን ይቅርታ የጠየቀቻቸው መሆኑን እና በዚህም ምክንያት ከአመልካች ወይም ከባለቤቱ የተከፈላት ገንዘብ የልለ መሆኑን በመግለጽ መሥክራለች።
ተከሳሽ በቀረበበት ማሥረጃ መሰረት የተመሰከረበት እንደሆነ ተከሳሽ የቀረበበትን ክስ እንዲከላከል ብይን የሚሰጥ መሆኑ ከወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 142/1 መሰረት መገንዘብ ይቻላል። ጉዳዩ የቀረበለት ፍ/ቤት አመልካች በቀረበበት ማስረጃ መሰረት የተመሰከረበት ሆኖ ስላገኘው አመልካች እንዲከላከል ብይን የሰጠ ቢሆንም የግል ተበዳይ የአመልካች መከላከያ ምሥክር ሆና ቀርባ አመልካች ድርጊቱን ያልፈጸመባት መሆኑን፤ድርጊቱ ተፈጽሞብኛል ያለችው ገንዘብዋን ስላልከፈላት ተናዳ እና አሰሪዋ ክሰሽው ስላለቻት መሆኑን፤በዚህም ምክንያት ተጸጽታ አመልካችን እና ባለቤቱን ይቅርታ የጠየቀቻቸው መሆኑን እና ይህንንም በማድረግዋ ከአመልካች ወይም ከባለቤቱ የተከፈላት ገንዘብ የልለ መሆኑን በማያሻማ ቃል ለፍ/ቤቱ ገልጻለች። ከዚህም በላይ የግል ተበዳይ የዓቃቤሕግ ቀጥተኛ ምስክር በመሆን ለፍ/ቤቱ በሰጠችው የምስክርነት ቃል አርግዣለሁ ያለችው አመልካች ገንዘቧን ስለከለከላት ተናዳ መሆኑን በመግለጽ የሰጠችው የምስክርነት ቃል የአመልካች መከላከያ ምስክር በመሆን ከሰጠችው የምሰክርነት ቃል ጋር ተገናዝቦ ሲታይ የግል ተበዳይ ከመነሻውም ቢሆን አመልካች የግብረሥጋ ግንኙነት ፈጽሞብኛል በማለት የሰጠችው የምሰክርነት ቃል ሐሰት እንደሆነ የሚያመላክት ነው።
በአጠቃላይ የተጠሪ ቀጥተኛ ምስክር የሆነችው የግል ተበዳይ ለፍ/ቤቱ በሰጠችው የምስክርነት ቃል አመልካች ድርጊቱን አልፈጸመብኝም፤አመልካች የግብረሥጋ ግንኙነት ፈጽሞብኛል ያልኩት ገንዘቤን ስለከለከለኝ ነው፤ ይህንንም በማድረጌ ስለተጸጸትኩ አመልካችን እና ባለቤቱን ይቅርታ ጠይቄያቸዋለሁ፤ይህንንም በማድረጌ የተከፈለኝ ገንዘብ የለም በማለት የመሰከረች በመሆኑ እና ተጠሪ የግል ተበዳይ የአመልካች የመከላከያ ምስክር በመሆን የሰጠችው የምሥክርነት ቃል ተደልላ ወይም ጥቅም አግኝታ የሰጠችው ቃል መሆኑን ያላረጋገጠ በመሆኑ አመልካች የተጠሪን ማስረጃ የጉዳዩ ባለቤት በሆነችው የግል ተበዳይ በበቂ ሁኔታ አስተባብሐል። አመልካች የቀረበበትን ክስ እስካስተባበለ ድረስ ፍ/ቤቱ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 149/2 መሰረት አመልካችን በነጻ መልቀቅ ይገባዋል። በመሆኑም የበታች ፍ/ቤቶች አመልካች የጉዳዩ ባለቤት የሆነችውን የግል ተበዳይ በመከላከያ ምስክርነት አቅርቦ የቀረበበትን ክስ በበቂ ሁኔታ ባስተባበለበት ሁኔታ አመልካችን ጥፋተኛ በማለት በሦስት ዓመት ከሰባት ወር ቀላል እሥራት ላቀጣ ይገባል በማለት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል። በዚህም ምክንያት በአብላጫ ድምጽ ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ. ሕዳር 26 ቀን 2009 ዓ.ም የሰጠው የጥፋተኝነት ውሳኔ እና ሕዳር 28 ቀን 2009 ዓ.ም የሰጠው የቅጣት ውሳኔ፤የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ. ጥር 23 ቀን 2009 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 195/2/ለ/2 መሰረት በአብላጫ ድምጽ ተሽሯል።
የተጠሪ ቀጥተኛ ምስክር የሆነችው የግል ተበዳይ አመልካች ድርጊቱን እንዳልፈጸመ በመግለጽ የአመልካች መከላከያ ምሥክር በመሆን የመሰከረች በመሆኑ አመልካች የቀረበበትን ክስ ተከላክሐል በማለት አመልካች በነጻ እንዲሰናበት በአብላጫ ድምጽ ወስነናል።
-የሚመለከተው ማረሚያ ቤት የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔ የተሻረ መሆኑ አውቆ አመልካችን ከእሥር እንዲፈታው የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ይላክለት።
-የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የመ. የሆነው መዝገብ ወደመጣበት ይመለስ።
-መዝገቡ ተዘግቷል። ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
የልዩነት ሃሳብ ስማችን በተራ ቁጥር 3 እና 4 የተመለከተው ዳኞች በአብላጫው ድምፅ ከሰጠው ውሳኔ በሚከተለው ምክንያት በሃሳብ ተለይተናል። የአሁኑ አመልካች በስር ፍርድ ቤት በተጠሪ የቀረበው ክስ ሲታይ፡- አመልካች የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 626/4//ሀ/ በመተላለፍ ከእርሱ ጋር ተቃራኒ ጾታ ካላት ዕድሜዋ አሥራ ስምንት ዓመት ካልሞላት ልጅ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ለመፈጸም በማሰብ በቀን 10/08/07 ዓ.ም በግምት ከጠዋቱ 12፡30 ሲሆን በየካ ክፍለከተማ ቀበል 16/17 ክልል ልዩ ቦታው ላምበረት አካባቢ የቤት ሰራተኛ የሆነችው እና እድሜዋ ከ15/16 ዓመት የሚገመተውን የግል ተበዳይ ዓይናለም አየነው ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የፈጸመ በመሆኑ ዕድሜአቸው አሥራ ሦስት ዓመት በሆነ እና አሥራ ስምንት ዓመት ባልሞላቸው ልጆች ላይ የሚፈጸም የግብረ ሥጋ ድፍረት በደል ወንጀል ፈጽሟል የሚል ነው።
አመልካች የእምነት ክህደት ቃል ሲጠየቅ ድርጊቱን አለመፈፀሙና ጥፋተኛ አለመሆኑ ገልፆ የተከራከረ ቢሆንም በወቅቱ የስር ፍርድ ቤት አመልካች በቀረበበት ክስ የወንጀል ህግ አንቀፅ 626/4/ሀ ጥፋተኛ በማለት ድምዳሜ ላይ የደረሰው የቀረቡት የዓ/ህግ ምስክሮች በአመልካች በቤት ሰራተኛነት ተቀጥራ ስትሰራ የነበረችው ተበዳይ አይናለም አየነው አመልካች ጠዋት ሚስቱ ወደ ሥራ ስትወጣ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የፈጸመባት መሆኑን፤ድርጊቱን የፈጸመችው በፍላጎት መሆኑን፤የግል ተበዳይ በልላ ጊዜ ለአመልካች ስልክ ደውላ አርግዣለሁ ስትለው የሰደባት እና አላውቅልሽም ብሎ ስልኩን የዘጋው መሆኑን፤2ኛ የዓ/ህግ ምስክር ደግሞ ለፍ/ቤቱ በሰጠችው የምስክርነት ቃል የግል ተበዳይ አመልካች ደፍሮኛል በማለት ከነገረቻት በኋላ ስልክ ደውይለት ያለቻት መሆኑን፤የግል ተበዳይ ለአመልካች አርግዣለሁ ብላ ስልክ ስትደውልለት የሰደባት መሆኑን መስክራለች፣ በተጨማሪ የግል ተበዳይ ጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል በመሄድ የተመረመረች ሲሆን በክብረንጽሕና መገለጫ አካሐ ላይ የቆየ የክብረንጽህና መገርሰስ መኖሩን እና ልላ አካላዊ ጉዳት ያልተገኘባት መሆኑን ፣እንዲሁም የግል ተበዳይ ዕድሜ ከ15-16 ዓመት መሆኑን የሚያሳይ ከዳግማዊ ምኒላክ ሆስፒታል የተጻፈ የሕክምና ማስረጃ በመቅረቡና በቀረበው ማስረጃ ተረጋግጧል በማለት ስለመሆኑ መዝገቡ ያመለክታል።
አመልካች የተከሰሱት የወንጀል ህግ አንቀፅ 626/4/ሀ በመሆኑ ይኸው የወንጀል ህግ አንቀፅ 626/4/ሀ/ “ ማንም ሰው ተቃራኒ ፆታ ካላት ፣ዕድሜዋ አሥራ ሦስት ዓመት በላይ ሆኖ አሥራ ስምንት ዓመት ካልሞላት ልጅ ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት የፈፀመ ወይም ይህችው ልጅ እንዲህ አይነቱን ድርጊት ከእርሱ ጋር እንድትፈፅም ያደረገ እንደሆነ …“ ስለመሆኑ ተደንግጓል:: ወደተያዘው ጉዳይ ስንመለስ የግል ተበዳይ አካለመጠን ያልደረሰች እድሜዋ ከ16 አመት በታች ሆና በአመልካች ቁጥጥር ስር የቤት ሰራተኛ የነበረች በመሆንዋ ከክርክሩ ይዘት ለመረዳት ችለናል። ስለሆነም አመልካች ፈፅሞታል የተባለው ወንጀል የግል ተበዳይ ፍቃድ መኖሩ ተበዳይ አካለመጠን ያልደረሰች ስለሆነች ፍቃደኛ ነበረች ተብሎ አመልካች ከጥፋተኝነት ላድን የሚችልበት የሕግ ምክንያት ላኖር ካለመቻሉም በላይ የነበራቸው የአሰሪና የቤት ሰራተኛ ግንኙነት ተበዳይን በተጽዕኖው ስር ያዋላት መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው ።
እንግዲህ የበታች ፍርድ ቤት አመልካች ድርጊቱን ፈፀመ በማለት ድምዳሜ የደረሱት አመልካች ድርጊቱን ስለመፈፀሙ የአቃቤ ሕግ ምስክሮች እና የፅሁፍ ማስረጃዎች በሚገባ ተረጋግጧል ፣አመልካች በመከላከያ ማስረጃው አልተደገፉም በሚል ምክንያት ነው።አመልካች ከሚከራከርባቸው ነጥቦች ውስጥ የአመልካችን የድርጊት ፈጻሚነት በተገቢው መንገድ አቃቤ ሕግ በማስረጃ ያለማስደገፉንና የአቃቤ ሕግ ማስረጃዎችን አመልካች በመከላከያ ምስክሮች የማስተባበላቸው ሁኔታን በተለይ የግል ተበዳይ መከላከያ ምስክር ሆና አልተደፈርኩም በማለት መስክራለች በማለት ሲሆን፤ የበታች ፍርድ ቤት በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 141 ስር የተመለከተውን የማስረጃ ምዘና መርህ ተከትለው የግል ተበዳይ አካለ መጠን ያልደረሰችና መጀመሪያ የዓ/ህግ ምስክር በመሆን ቀርባ መደፈርዋ በተመለከተ የሰጠችው የምስክርነት ቃል በቀረበው የሃኪም ማስረጃም ጭምር የተረጋገጠ በመሆኑ ተአማኒነት ያለው መጀመሪያ የሰጠችው የምስክርነት ቃል ነው በማለት የስር ፍርድ ቤቶች ባላቸው ማስረጃ የመመዘን ስልጣን ተጠቅመው ማስረጃውን መዝነው አመልካችን ጥፋተኛ ያደረጉ ስለመሆኑ የክርክሩ ሂደት የሚያሳየን እና በአመልካችና ተበዳይ የነበረው ግንኙነትም የአሰሪና የቤት ሰራተኛ መሆን በራሱ ግምት ውስጥ አስገብቶ ተመዝኖ የተስጠ በመሆኑ ተገቢና ህጋዊ ሆኖ አግኝተነዋል።
በመሆኑም ከዚሁ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መገንዘብ የሚቻለውም አመልካች ጥፋተኛ የተባሉት በጉዳዩ ላይ የቀረቡት ማስረጃዎቸ ተመዝነው መሆኑን ነው።
በተያዘው ጉዳይም አብላጫው ድምፅ አመልካች በነፃ እንዲሰናበት እንደ ምክንያትነት የገለፁት የተከሳሽ 2ኛ መከላከያ ምስክር በመሆን የቀረቡት የግል ተበዳይ በዓ/ህግ ምስክር ሆና የሰጠችው ምስክርነት በመቀየር አመልካችን የከሰስኩት የሰራሁበት ገንዘብ ስላልሰጠኝ እንጂ ከአመልካች ጋር የግብረሥጋ ግንኙነት ፈጽሜ አላውቅም በማለት በመመስከርዋ የዓ/ህግ ምስክር ሆና የሰጠችው ምስክርነት ቃል ተአማኒነት የለውም በማለት መሆኑ ውሳኔው ያመለክታል እዚህ ላይ መታየት ያለበት ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት አንድ የመጨረሻ ፍርድ ያገኘን ጉዳይ ማረም የሚችለው በውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት መኖሩ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ በኢ.ፍ.ዲ.ሪ. ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3(ሀ)) እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 ተመልክቷል። ከእነዚህ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ መገንዘብ የሚቻለው ደግሞ ይህ ሰበር ችሎት ፍሬ ነገርን የማጣራት ወይም ማስረጃን የመመዘን ስልጣን የልለው መሆኑን ነው።በተመሳሳይ ጉዳይ ይህ ችሎት በሰ/መ/ቁ/ 41526 እና ልሎች በርካታ መዛግብት የሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም አቤቱታ የቀረበበት ጉዳይ ከማስረጃ ምዘና ጋር የተያያዘና የፍሬ ነገር ክርክር ላይ ያተኮረ እንደሆነ በሰበር ችሎት ላስተናገድ የማይችል ስለመሆኑ በየትኛውም ፍርድ ቤት፤ይህ ሰበር ሰሚ ችሎትንም ጨምሮ የሚያስገድድ በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀፅ 2 መሰረት አስገዳጅነት ያለው ትርጉም የሰጠበት ጉዳይ ነው።ስለሆነም የግል ተበዳይ በአመልካች ላይ ክስ መስርታ የከሳሽነት ቃል ከሰጠች በኋላ ፍርድ ቤት ቀርባም መደፈርዋን አረጋግጣ እያለ ፤መጀመሪያ የሰጠችው የምስክርነት ቃል ቀይራለች እና ተአማኒነት ያለው በኋላ የተሰጠው ምስክርነት ነው በማለት በአብላጫው ድምፅ መወሰኑ የግል ተበዳይ አካለመጠን ያልደረሰች ከመሆኑዋና የአመልካች የቤት ሰራተኛ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ በሃኪም ማስረጃም ጭምር የተረጋገጠ ጉዳይ በመሆኑ፣የዓ/ህግ ማስረጃ ከነሙሉ ይዘቱ መመዘን እንዳለበት ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ የሰጠው ትርጉም ያላገናዘበና የስር ፍርድ ቤቶች ባላቸው ማስረጃ የመመዘን ስልጣን አመልካች ወንጀል መፈፀሙ በሰውና በሃኪም ማስረጃ ተረጋግጧል አመልካች የአቃቤ ሕግ ማስረጃዎች በመከላከያ ማሰረጃው አላስተባበለም በማለት የገለጸዉ ሲታይ ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በአዋጅ ቁ.25/1988 አንቀጽ 10 መሰረት ከተሰጠዉ ስልጣን አንጻር ይህን በማስረጃ የተረጋገጠዉን ፍሬ ነገር ከመቀበል ዉጭ ድጋሚ ለማጣራት የሚያስችለዉ የህግ አግባብ የለም። ስለሆነም አመልካች ለድርጊቱ ኃላፊነት አለበት ተብሎ የተወሰነው ወንጀሉ መሰራቱ ወይም መፈጸሙና ተሰራ ወይም ተፈጸመ የተባለው ወንጀል ደግሞ በአመልካች በበቂና በአሳማኝ ሁኔታ ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያላቸው ፍርድ ቤቶች በተረጋገጠበት ሁኔታ በመሆኑና ይህም በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 23(4) እና 626(4(ሀ)) ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የሚያሟላ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች አመልካች ጥፋተኛ በማለት የሰጡት ውሳኔ ላፀና ይገባል በማለት አብላጫው ድምፅ ከሰጠው ውሳኔ በሃሳብ ተለይተናል ።
No topics extracted.