አንድ ውል በይዘቱ የአስተዳደር ውል ሲሆን የአስተዳደር አካል ወይም መንግስት ውሉን ለመሰረዝ መብት ያለው ስለመሆኑና ልላኛው ወገን በውሉ መፍረስ የደረሰበት ጉዳት ካለ ከመጠየቅ በስተቀር ውሉ እንዲሻሻል ሆነ ለስራ ማስኬጃ የተቀበለውን ቅድመ ክፍያ ላለመመለስ የሚያቀርበው መከራከሪያ ተቀባይነት የልለው ስለመሆኑ፡የፍ/ብ/ ህ/ቁጥር 1815፣3180 እና 3181 129534 የላቦከምከም ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት እና እነ ወ/ሮ እናትነሽ ዘለቀ (2 ሰዎች) መስከረም ቀን2010 ዓ.ም 28. የኦዲት ሪፖርት የሚያሻማና ግልጽነት የልለው በሆነበትና በሪፖርቱ የቀረበውን ሀሳብ ይዘት እንዲያስረዱ ሪፖርቱን ያዘጋጁ የሂሳብ ባለሙያዎች ቀርበው ሻምበል መሐመድ ብርሃን ረዳ እና መስከረም2 5 ቀን 2010 XV ባልተደረገበት ሁኔታ ፍርድ ቤቶች የኦዲት ሪፖርቱን ራሳቸው በተረዱት አግባብ ተርጉመው የሚሰጡት ውሳኔ ስነ ስርዓታዊ ነው ላባል የማይችል ስለመሆኑ የፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 133 (3) ወ/ሮ ዘምዘም መኮንን ዓ.ም. 29. በቀድሞ ክርክር ጊዜ በግልጽ ዳኝነት ተጠይቆበት በዝምታ የታለፈ ጉዳይ በልላ ጊዜ የክስ እና የክርክር ምክንያት ላሆን አይችልም ማለት እንጂ ፍ/ቤቶች በተከራካሪ ወገኖች በግልጽ ዳኝነት የተጠየቀበትን ጉዳይ በዝምታ ማለፍ የማይችሉ ስለመሆኑ የፍ/ስ/ስ/ሕ ቁጥር 5 (3) ፤182 (1)
No summary available.
መስከረም 30 ቀን 2010 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አልማው ወል ሙስጠፋ አህመድ አብርሃ መሰለ ጳውሎስ ኦርሺሶ ሰናይት አድነው አመልካች፡- ወ/ሮ የሺመቤት ገ/ፃዲቅ - ጠበቃ ተፈሪ ከበደ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ፋንታዬ ሽጉልቱ - ተወካይ ወ/ሮ ንጋቷ ባየህ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቶአል።
ጉዳዩ በፍቺ እና የንብረት ክፍፍል ስምምነት መነሻ አለአግባብ የተወሰደ ነው የተባለን ንብረት ለማስመለስ ከቀረበ ክስ ጋር ተያይዞ የተነሳ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን አመልካች የሰበር አቤቱታቸውን ለዚህ ችሎት ያቀረቡት በባሶና ወራና ወረዳ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ27/03/2008 ዓ.ም. የተሰጠው እና በሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ 0 በ13/05/2008 ዓ.ም. ተሻሽሎ በአማራ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በመዝገብ ቁጥር 030- 7079 02/10/2008 ዓ.ም. በትዕዛዝ የጸናው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ላታረም ይገባል በማለት ነው።
የጉዳዩን አመጣጥ በተመለከተ፡-አቶ ደምሴ ባየህ የተባሉ የተጠሪዋ ልጅ እና አመልካቿ ከሃያ ዓመታት በላይ በጋብቻ ተሳስረው ከቆዩ በኃላ በመካከላቸው በተፈጠረው አለመግባባት መነሻ የፍቺ እና የንብረት ክፍፍል ስምምነት አድርገው ይኸው ስምምነት በወረዳው ፍርድ ቤት በመዝገብ በ08/09/2007 ዓ.ም.የተመዘገበ እና ንብረቶቹንም የተከፋፈሉ መሆኑን፣ከዚህ በኃላ የንብረት ክፍፍል ስምምነቱ የተደረገው ተጋቢዎቹ በጋራ ባፈሩት ንብረት ላይ ሳይሆን በእኔ ንብረት ላይ ነው በማለት የአሁኗ ተጠሪ በ24/09/2007 ዓ.ም. በተጻፈ ማመልከቻ 1ኛ ተከሳሽ በነበሩት የአሁኗ አመልካች እና 2ኛ ተከሳሽ በነበሩት የተጠሪዋ ልጅ /የአመልካቿ የቀድሞ ባለቤት/ ላይ የንብረት ያስረክቡኝ ክስ ማቅረባቸውን፣አመልካቿ ለክሱ በሰጡት መልስ ክሱ አስቀድሞ በፍርድ ያለቀ ነው፣ስምምነቱ እንዲፈርስ ባልተደረገበት ሁኔታ አዲስ ክስ ላቀርብ አይገባውም፣ የንብረት ክፍፍሉ ሲደረግ ተጠሪዋ በቦታው እያሉ ባልተቃወሙበት ሁኔታ አዲስ ክስ ማቅረባቸው ተቀባይነት ላኖረው አይገባም የሚሉ የመጀመሪያ ደረጃ የመቃወሚያ ነጥቦችን ካስቀደሙ በኃላ ፍሬ ጉዳዩን በተመለከተ በፍርድ ቤት በጸደቀው ስምምነት መሰረት ክፍፍል የተደረገባቸው ንብረቶች በጋብቻው ውስጥ የተፈሩ በመሆኑ ክሱ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት የተከራከሩ መሆኑን፣የስር 2ኛ ተከሳሽን በተመለከተ በእጃቸው የነበረውን 0.5 ጥማድ የእርሻ ይዞታ መልሰውልኛል በማለት ተጠሪዋ ክሱ እንዲቋረጥ ያደረጉ መሆኑን፣ፍርድ ቤቱም የመጀመሪያ ደረጃ የመቃወሚያ ነጥቦቸን በብይን አልፎ በተጠሪዋ እና በአመልካቿ መካከል ክሱን እና የግራ ቀኙን እንዲሁም የማጣሪያ ምስክሮችን ከሰማ እና ከወረዳው መሬት እና አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ተገቢውን ማጣራት ካደረገ በኃላ የግራ ቀኙን አጠቃላይ ክርክር እና ማስረጃ መርምሮ ክርክር ያስነሳው 0.5 ጥማድ የእርሻ መሬት የተጠሪዋ ልጅ እና አመልካቿ በመጋዞ ሲጠቀሙበት እንደነበረ የተገለጸ ቢሆንም የይዞታ ባለመብትነቱ ግን የተጠሪዋ እንደሆነ ከሚመከተው አካል በቀረበ ማስረጃ የተረጋገጠ መሆኑን እና ክፍፍል የተደረገባቸው ከብቶች እና የተለያዩ እህሎችም የተጠሪዋ እንደሆነ መረጋገጡን ገልጾ አመልካቿ በክፍፍሉ የወሰዷቸውን ከብቶች እና በውሳኔው ላይ መጠናቸው እና ዓይነታቸው በዝርዝር የተገለጸውን የተለያዩ እህሎች ለተጠሪዋ እንዲመልሱ ውሳኔ መስጠቱን፣ይግባኙን የተመለከተው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በበኩሉ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ ክፍፍል የተደረገባቸው ከብቶች እና የተለያዩ እህሎች የተጠሪዋ ስለመሆናቸው በማስረጃ አልተረጋገጠም በማለት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን አሻሽሎ ከብቶቹን እና እህሎቹን አመልካቿ የመመለስ ግድታ የለባቸውም በማለት ውሳኔ የሰጠ መሆኑን እና በክልሉ ሰበር ችሎት በትዕዛዝ የጸናውም ይኸው ውሳኔ መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።
አመልካቿ ለዚህ ችሎት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች ከስር 2ኛ ተከሳሽ ጋር ለ24 ዓመታት ሲጠቀሙበት የኖሩትን የእርሻ መሬት የስር 2ኛ ተከሳሽ ያገኙት ከእናታቸው ነው በማለት የስር ፍርድ ቤቶች አመልካቿን መብት የማሳጣታቸውን አግባብነት ተጠሪዋ ባሉበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዳዩ ለሰበር ክርክር እንዲቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም በጉዳዩ እልባት ማግኘት የሚገባው ይግባኝ ሰሚ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን በማሻሻል የሰጠው ውሳኔ በስነ ስርዓት ሕጉ የተመለከተውን የውሳኔ አሰጣጥ ስርዓት መሰረት ያደረገ ነው ወይስ አይደለም? የሚል ነጥብ መሆኑን በመገንዘብ አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ከዚሁ ነጥብ አንጻር መርምረናል።
በዚህም መሰረት አመልካቿ ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረቡት ከብቶቹን እና እህሎቹን ይመልሱ መባሉን በመቃወም ብቻ ሳይሆን በ0.5 ጥማድ መሬት ላይ መብት የላቸውም መባሉን በመቃወም ጭምር ስለመሆኑ ለዚህ ችሎት ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ ላይ የገለጹ ሲሆን መሬቱ ጭምር የይግባኝ ምክንያት የነበረ ስለመሆኑ ተጠሪዋም በሰበር መልሳቸው ላይ ገልጸዋል። በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 339 ድንጋጌ መሰረት ይግባኙ በተሰማበት ጊዜም ግራ ቀኙ በመሬት ይገባኛል ጉዳይ ላይ ጭምር የተከራከሩ መሆኑን የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውሳኔ ያመለክታል።ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ክርክሩን የሰማው በመሬት ይገባኛል ጉዳይ ላይ ጭምር ቢሆንም በመጨረሻ ግን የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን በልሎች ነጥቦች ረገድ ሲያሻሽል በመሬት ይገባኛል ክርክሩ ረገድ ግን ውሳኔ ሳይሰጥ በዚህ ረገድ በአመልካቿ የቀረበውን ቅሬታ በዝምታ አልፎታል።በመሰረቱ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በሚሰጠው የፍርድ ውሳኔ የመጀመሪያውን ደረጃ ፍርድ ቤት ፍርድ ያሻሻለው ወይም የለወጠው እንደሆነ በትችቱ ላይ ለይግባኝ ባዩ የሚገባውን ዳኝነት ዘርዝሮ መግለጽ ያለበት ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 182 (1) ድንጋጌ ስር የተመለከተ ሲሆን ይግባኝ በተባለበት ፍርድ ቤት መዝገብ ውስጥ የሰፈረው ማስረጃ በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ግምት በቂ ሆኖ ሲገኝ የነገሩን ጭብጥ በማሻሻል ወይም በመለወጥ ተገቢ መስሎ የታየውን የመጨረሻ ፍርድ ላሰጥ የሚችል ስለመሆኑ እና ይግባኝ የተባለበት ፍርድ ቤት ፍርዱን የሰጠው በልላ ምክንያት ቢሆንም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በመዝገቡ ላይ በተረዳው መሰረት ጭብጡን ለውጦ ከመፍረድ የማይታገድ ስለመሆኑ በዚሁ ሕግ በቁጥር 242 ስር ተመልክቶአል። በመሆኑም አመልካቿ የይግባኝ ቅሬታ ባቀረቡበት የ0.5 ጥማድ መሬት ክፍያ ጥያቄ ላይ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር እንደሰማ ሁሉ በአንድ ወይም በልላ አግባብ ተገቢ ነው የሚለውን ውሳኔ ላያሳርፍበት ሲገባው በዝምታ ማለፉ ስነ ስርዓታዊ ነው ላባል የሚችል ሆኖ አልተገኘም።
በእርግጥ በአንድ ክርክር እና ሙግት ላይ በግልጽ ዳኝነት ተጠይቆበት ጥያቄው ተቀባይነትን ሳያገኝ የታለፈ እንደሆነ የተጠየቀው ዳኝነት እንደተከለከለ የሚቆጠር ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 5 (3) ድንጋጌ ስር ተመልክቶአል።ይህ ማለት ግን በቀድሞ ክርክር ጊዜ በግልጽ ዳኝነት ተጠይቆበት በዝምታ የታለፈ ጉዳይ በልላ ጊዜ የክስ እና የክርክር ምክንያት ላሆን አይችልም ማለት እንጂ በተከራካሪ ወገኖች በግልጽ ዳኝነት የተጠየቀበትን ጉዳይ ፍርድ ቤቶች በዝምታ ማለፍ ይችላሉ ማለት አይደለም።ይህ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በዝምታ የታለፈው የዳኝነት ጥያቄ ተገቢ ፍሬ ነገሮችን ማጣራትን እና ማስረጃ መመዘንን ጭምር የሚመለከት በመሆኑ ጉዳዩ ወደ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተመልሶ ተገቢው ውሳኔ እንዲሰጥበት ከሚደረግ በቀር በዚህ ሰበር ደረጃ ውሳኔ ላሰጥበት የሚችል ሆኖ አልተገኘም።
ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ በከፊል መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቶአል።
የተሰጠው እና በሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ 0 በ13/05/2008 ዓ.ም. ተሻሽሎ በአማራ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በመዝገብ ቁጥር 030-7079 02/10/2008 ዓ.ም.
በትዕዛዝ የጸናው ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348 (1) መሰረት ተሻሽሎአል።
አመልካቿ የይግባኝ ቅሬታ ያቀረቡበትን የ0.5 ጥማድ መሬት ክፍያ ጥያቄ ጉዳይ በዝምታ በማለፍ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በክልሉ ሰበር ችሎት በትዕዛዝ የጸናው የውሳኔ ክፍል ተሽሮአል።
ከላይ በተራ ቁጥር ሁለት የተጠቀሰውን የይግባኝ ቅሬታ ነጥብ በተመለከተ የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ መርምሮ ተገቢውን ውሳኔ ይሰጥበት ዘንድ ጉዳዩ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 343 (1) መሰረት ለሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዲመለስ ወስነናል።
የውሳኔው ግልባጭ ተገቢውን መፈጸም ያስችለው ዘንድ ለሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣እንዲያውቁት ደግሞ ለባሶና ወራና ወረዳ ፍርድ ቤት እና ለአማራ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ይላክ።
ከላይ በተራ ቁጥር ሁለት ከተጠቀሰው ውጪ ያለው የውሳኔው ክፍል አልተነካም።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቶአል።