አንድ ሰው ቀድሞ በቀረበ ክርክር ጣልቃ ገብ በመሆን ክርክር ያቀረበ ወይም በጉዳዩ ተሳታፊ የነበረ መሆኑ በጣልቃ ገብነት በቀረበበት ክርክር ግልጽ ዳኝነት ባልተጠየቀባቸው ጉዳዮች በልላ ጊዜ ክስ ለማቅረብ ወ/ሮ ጀምላ ጆብር እና አቶ ሶፊያ ጅማ XIV ስለመሆኑና በዚህ አግባብ የሚቀርብን ክስ በቀድሞው ክርክር ተጠቃሎ መቅረብ የነበረበትና ተከፋፍሎ ዳኝነት ላቀርብበት አይገባም በሚል አቤቱታን ዉድቅ በማድረግ የሚሰጥ ውሳኔ ተገቢነት የልለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 41፣216 እና 218
No summary available.
መስከረም 25 ቀን 2010 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ፀጋየ አስማማው አልማው ወል ሙስጠፋ አህመድ አብርሃ መሰለ ጳውሎስ ኦርሺሶ አመልካች፡- ሻምበል መሐመድ ብርሃን ረዳ -የቀረበ የለም ተጠሪ፡- ወ/ሮ ዘምዘም መኮንን-ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቶአል።
ጉዳዩ የፍቺ ውሳኔን ተከትሎ የተነሳ የንብረት ክፍያ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን አመልካች አቤቱታቸውን ለዚህ ችሎት ያቀረቡት በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ06/02/2006 ዓ.ም. ተሰጥቶ በፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ06/07/2008 ዓ.ም. በፍርድ የጸናው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ላታረም ይገባል በማለት ነው።
በንብረት ክፍያ ክርክሩ ፍርድ ካረፈባቸው ንብረቶች መካከል ለዚህ የሰበር ክርክር ምክንያት የሆነው ራዕይ 2001 ሁለገብ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር ውስጥ ግራ ቀኙ በአመልካች ስም ያላቸው ድርሻ ነው።በዚህ ማህበር ውስጥ በአመልካች ስም ያለው ድርሻ ተጣርቶ ክፍፍል እንዲፈጸምላቸው ጥያቄ ያቀረቡት ተጠሪዋ ሲሆኑ አመልካቹም የአባልነት ድርሻው የግራ ቀኙ የጋራ ሀብት መሆኑን አምነው መልስ በመስጠታቸው ፍርድ ቤቱ አመልካች ያላቸው ድርሻ ተጣርቶ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ከሰጠ በኃላ ከማህበሩ በጽሁፍ የተሰጠውን ምላሽ መሰረት አድርጎ አመልካች በማህበሩ ውስጥ እንዳላቸው ከተረጋገጠው ብር 174,412.65 (አንድ መቶ ሰባ አራት ሺህ አራት መቶ አስራ ሁለት ከስድሳ አምስት ሳንቲም) ውስጥ ግማሹ የተጠሪዋ ነው በማለት ውሳኔ ሰጥቶአል።
በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት አመልካች ባቀረቡት ይግባኝ ሳቢያ የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ እና አመልካች በማህበሩ ውስጥ ያላቸው ድርሻ መጠን በድጋሚ ተጣርቶ እንዲቀርብ ሁለት ጊዜ ትዕዛዝ ሰጥቶ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከተከናወነው ኦዲት ውስጥ በ23/05/2008 ዓ.ም. በተጻፈ መሸኛ የተላከለትን ሁለተኛ የኦዲት ሪፖርት መርምሮ በዚህኛው የኦዲት ሪፖርት ላይ የተገለጸው አመልካች ከማህበሩ ያገኙት ድርሻ በስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ ከተገለጸው መጠን በላይ ሆኖ መገኘቱን በምክንያትነት ይዞ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን በማጽናት ውሳኔ ሰጥቶአል።አመልካች ለዚህ ችሎት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በተከናወነው ኦዲት መሰረት የቀረበው ሪፖርት ማህበሩ ባለዕዳ መሆኑን የሚያመለክት ሆኖ ሳለ አመልካች ከማህበሩ ገንዘብ እንዳገኙ ተቆጥሮ ከተጠሪዋ ጋር እኩል ይከፋፈሉ ተብሎ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠውን ውሳኔ አግባብነት ተጠሪዋ ባሉበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዳዩ ለሰበር ክርክር እንዲቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም ክርክሩ የተስተናገደበትን የይግባኝ ሰሚውን ፍርድ ቤት መዝገብ በማስቀረብ ጭምር አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለክርክሩ ከተያዘው ነጥብ አንጻር መርምረናል።
በዚህም መሰረት አመልካች በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት ያቀረቡትን ይግባኝ በመቀበል ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት አመልካቹ በማህበሩ ውስጥ ያላቸውን ድርሻ ወይም ከማህበሩ ያገኙትን ትርፍ በተመለከተ ኦዲቱ በድጋሚ ተከናውኖ ሪፖርት እንዲቀርብለት በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ኦዲቱ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ተከናውኖ በ16/10/2007 ዓ.ም.
በተጻፈ መሸኛ ሰባት ገጽ የኦዲት ሪፖርት የተላከት መሆኑን፣በዚህ ሪፖርት ላይ ግራ ቀኙ አስተያየት እንዲያቀርቡ ተጠይቀው አመልካች በ02/11/2007ዓ.ም.፣ተጠሪዋ ደግሞ በ29/10/2007 ዓ.ም. የተጻፈ አስተያየት ማቅረባቸውን፣ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን አስተያየት በተለይ ደግሞ በተጠሪዋ የቀረበውን የተቃውሞ አስተያየት መሰረት በማድረግ ኦዲቱ አሁንም በድጋሚ ተከናውኖ ሪፖርት እንዲቀርብለት በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ኦዲቱ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ተከናውኖ በ23/05/2008 ዓ.ም. በተጻፈ መሸኛ ሶስት ገጽ የኦዲት ሪፖርት እና ስምንት ገጽ ደጋፊ ሰነድ የተላከት መሆኑን፣በዚህ ሪፖርት ላይ ግራ ቀኙ አስተያየት እንዲያቀርቡ ተጠይቀው አመልካች በ01/06/2008 ዓ.ም.፣ተጠሪዋም በተመሳሳይ ቀን በ01/06/2008 ዓ.ም. የተጻፈ አስተያየት ማቅረባቸውን፣በተጠሪዋ በኩል የቀረበው አስተያየት ሪፖርቱ ግልጽነት የልለው በመሆኑ ቢቻል ቀደም ሲል በስር ፍርድ ቤት በቀረበው የኦዲት ሪፖርት መሰረት ውሳኔ እንዲሰጣቸው፣ካልሆነም እንደገና እንዲጣራ እንዲደረግ የሚጠይቅ መሆኑን እና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ሪፖርቱን እና የግራ ቀኙን አስተያየት ከመረመረ በኃላ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን ያጸናው በመጨረሻ በቀረበው ሪፖርት መሰረት አመልካች ከማህበሩ ያገኙት ድርሻ በስር ፍርድ ቤት በቀረበው የኦዲት ሪፖርት ላይ ከተገለጸው መጠን በላይ ነው በሚል ምክንያት መሆኑን የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት መዝገብ ያመለክታል።
እንደሚታወቀው ማንኛውም ፍርድ ቤት ባለጉዳዮችን ማከራከር የሚገባው የተለያዩበት የሕግ ወይም የፍሬ ነገር አግባብ ምን እንደሆነ አረጋግጦ ለጉዳዩ ትክክለኛ ጭብጥ በመያዝ ስለመሆኑ፣የነገር ጭብጥ የሚመሰረተው አንደኛው ተከራካሪ ወገን ያመነውን የሕግ ወይም የነገር አግባብ ልላኛው ተከራካሪ ወገን በማስተባበል የካደ በሆነ ጊዜ ስለመሆኑ፣ፍርድ ቤቱ ጭብጥን ለመመስረት የሚችለውም ከግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር እና ማስረጃ እንዲሁም በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 241 መሰረት በሚደረግ ምርመራ በተከራካሪ ወገኖች የሚሰጠውን መልስ መሰረት በማድረግ ስለመሆኑ የጭብጥ አመሰራረትን በሚደነግጉ ከቁጥር 246 እስከ 248 በተመለከቱት የስነ ስርዓት ሕጉ ድንጋጌዎች እንዲሁም ፍርድ ቤቱ ውሳኔ በሚሰጥበት ጊዜ በክርክሩ የተያዘው ጭብጥ ምን እንደሆነ እና12010 ጭብጡ በአንድ ወይም በልላ አግባብ የተወሰነበትን ምክንያት በውሳኔው ላይ መግለጽ ያለበት ስለመሆኑ የፍርድ አጻጻፍን በሚመለከተው በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 182 (1) ተደንግጎ ይገኛል።
በተያዘው ጉዳይ በአመልካች ስም በማህበሩ ውስጥ ያለው ድርሻ የግራ ቀኙ የጋራ ሀብት መሆኑ በአመልካቹ የታመነ ሲሆን እያከራከረ ያለው በማህበሩ ውስጥ አመልካች ያላቸው ድርሻ ምን ያህል ነው? ማህበሩ ለአባላቱ ያስገኘው ትርፍ አለ ወይስ የለም?
አለ ከተባለ አመልካች ከማህበሩ ያገኙት ወይም ማግኘት የሚገባቸው ወይም የተካፈሉት ድርሻ ምን ያህል ነው? የሚሉ እና ተያያዥ ጥያቄዎች ናቸው።እነዚህ ጥያቄዎች ደግሞ በባህሪያቸው ፍርድ ቤቱ በራሱ ወይም ብቻውን የሚፈታቸው ሳይሆኑ የኦዲት ባለሙያ እገዛ የሚጠይቁ ናቸው።ፍርድ ቤቶች ሂሳብ የማጣራት ስራ በምትክ ዳኞች ወይም በልዩ አዋቂዎች /ኤክስፐርቶች/ ተከናውኖ ውጤቱ እንዲቀርብላቸው ትዕዛዝ መስጠት የሚችሉ ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 133 እስከ 136 ድንጋጌዎች የተመለከተ ሲሆን ሁለቱ የስር ፍርድ ቤቶች ኦዲቱን በተመለከተ የተለያየ ትዕዛዝ ሲሰጡ የነበረውም በዚሁ ስርዓት መሰረት ነው።በዚህ አግባብ በጽሁፍ ተዘጋጅተው በቀረቡት የኦዲት ሪፖርቶች ላይ ገልጽ ያልሆኑትን ወይም አሻሚ መስለው የታዩ ነጥቦችን ማጣራቱ አስፈላጊ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ፍርድ ቤቶች በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 133 (3) በተሰጣቸው ስልጣን መሰረት የኦዲት ስራውን አከናውነው ሪፖርቱን ያቀረቡ ልዩ አዋቂዎችን ምስከርነት መስማት ይጠበቅባቸዋል።
ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ኦዲቱ በድጋሚ ተከናውኖ ሪፖርት እንዲቀርብለት በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ኦዲቱ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ተከናውኖ በ23/05/2008 ዓ.ም. በተጻፈ መሸኛ የተላከው ሶስት ገጽ የኦዲት ሪፖርት እና ስምንት ገጽ ደጋፊ ሰነድ ማህበሩ በአንድ በኩል በኪሳራ ላይ እንደነበረ እና በልላ በኩል ደግሞ ትርፋማ እንደነበረ የሚያመላክት አሻሚ ይዘት ያለው መሆኑን ከመዝገቡ ተመልክተናል።ይህም የኦዲት ሪፖርቱ ግልጽነት የልለው ነው በማለት ተጠሪዋ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በሪፖርቱ ላይ የሰጡት አስተያየት ተገቢነት የነበረው መሆኑን መገንዘብ የሚያስችል ነው። እንዲህ ከሆነ ደግሞ ከላይ በተጠቀሰው የፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 133 (3) ድንጋጌ መሰረት በሪፖርቱ ላይ የሚያሻማ በሚመስል አገላለጽ የሰፈረውን ሀሳብ ይዘት እንዲያስረዱ ፍርድ ቤቱ ስማቸው በሪፖርቱ ላይ የተጠቀሰውን የሂሳብ ባለሙያዎች አስቀርቦ መስማት ይጠበቅበት ነበር። ኦዲቱን ያከናወኑ ኦዲተሮች በሪፖርቱ ላይ የሚያሻማ በሚመስል ሁኔታ የሰፈረውን ሀሳብ ለይተው እንዲያስረዱ ባልተደረገበት ሁኔታ ፍርድ ቤቶች የኦዲት ሪፖርቱን እራሳቸው በተረዱት አግባብ ተርጉመው የሚሰጡት ውሳኔ ስነ ስርዓታዊ ነው ላባል የሚችል ካለመሆኑም በላይ በጉዳዩ ላይ ትክክለኛ ፍትሕ ለመስጠት የሚያስችልም አይደለም።በመሆኑም በጉዳዩ ላይ ትክክለኛ ፍትሕ ለመስጠት ይረዳ ዘንድ ጉዳዩ ወደ ፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተመልሶ ኦዲቱን ያከናወኑት ባለሙያዎች ቀርበው ስለሪፖርቱ አጠቃላይ ይዘት ምስክርነታቸውን እንዲሰጡ ከተደረገ በኃላ ተገቢው ውሳኔ ላሰጥበት የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል።
ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ ተገኝቷል።
በፍርድ የጸናው ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348 (1) መሰረት ተሻሽሐል።
ራዕይ 2001 ሁለገብ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር ውስጥ ግራ ቀኙ በአመልካች ስም ያላቸውን ድርሻ በተመለከተ የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ተሽሯል።
የሆነውን የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መዝገብ አስቀርቦ ራዕይ 2001 ሁለገብ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር ውስጥ ግራ ቀኙ በአመልካች ስም ያላቸውን ድርሻ በተመለከተ ኦዲቱ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ተከናውኖ በ23/05/2008 ዓ.ም. በተጻፈ መሸኛ የተላከውን ሶስት ገጽ የኦዲት ሪፖርት እና ስምንት ገጽ ደጋፊ ሰነድ እንዲሁም በዚሁ የኦዲት ሪፖርት ላይ ግራ ቀኙ የሰጡትን አስተያየት ከመዝገቡ ውስጥ ከተመለከተ በኃላ በሪፖርቱ መጨረሻ ላይ ስማቸው የተጠቀሰውን ሶስት ኦዲተሮች፣እነዚህ ኦዲተሮች በቂ በሆነ ሕጋዊ ምክንያት ላገኙ እንደማይችሉ የሚረጋገጥ ከሆነም ሰለጉዳዩ ላያስረዱ የሚችሉ ልሎች ኦዲተሮችን ከዚያው ተቋም አስቀርቦ ስለሪፖርቱ አጠቃላይ ይዘት ምስክርነታቸውን ከሰማ በኃላ ተገቢውን ውሳኔ ይሰጥበት ዘንደ ጉዳዩ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 343 (1) መሰረት ለፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እንዲመለስ ወስነናል።
ከላይ በተራ ቁጥር ሁለት ከተመለከተው ውጪ ያለው የውሳኔ ክፍል አልተነካም።
የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ተገቢውን መፈጸም ያስችለው ዘንድ ለፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣እንዲያውቀው ደግሞ ለፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይላክ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ።
በዚህ መዝገብ በ14/03/2009 ዓ.ም. እና በ27/07/2009 ዓ.ም. ተሰጥቶ የነበረው የአፈጻጸም ዕግድ ተነስቷል።ይጻፍ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No specific laws extracted.
No topics extracted.