No summary available.
የሰ/መ/ ቀን 24/01/2010 ዓ.ም ዳኞች፡- ረታ ቶሎሳ ተኽላት ይመስል ተፈሪ ገብሩ ቀነአ ቂጣታ አብዬ ካሳሁን አመልካች፡- የላቦ ከምከም ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት - ዓ/ህግ አበበ ሙሉ ቀረቡ ተጠሪዎች፡- 1ኛ ወ/ሮ እናትነሽ ዘለቀ ጠበቃ በላይ መሸሻ ቀረቡ 2ኛ አቶ አበባው ክብረት መዝገቡ መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል ።
2ኛ ተጠሪም ሥራውን ለመስራት ውክልና የወሰዱ ቢሆንም በ10 ቀን ውስጥ ምንም ዕቃ አላስቀመጡም ። በመሆኑም ውሉ እንዲሰረዝ በቅድመ ክፍያ የተወሰደውን ገንዘብ እንዲመልሱ ይወሰን ዘንድ ዳኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው ።
የስር ተከሳሾች /ተጠሪዎች/ ባቀረቡት የመከላከያ መልስ 2ኛ ተጠሪ ላከሰሱ እንደማይገባ የተከራከሩ ሲሆን 1ኛ ተጠሪ በበኩላቸው ውሉ የሚሰረዝበት ህጋዊ ምክንያት አይኖርም ፤ውሉ ላይ የተጠቀሰው ሥራ እና ሳይት ፕላኑ ላይ የተቀመጠው ሥራ መሰረታዊ ልዩነት ያለው ስለመሆኑ የሚፈጀው ገንዘብና ጊዜ ልዩነት የሚያመጣ በመሆኑ ውሉ እንዲሻሻል በመጠየቅ በቅድሚያ ክፍያ መልክ የወሰደው ገንዘብ ግን የሚመለስበት አግባብ እንደልለ በመጥቀስ ክሱ ውድቅ እንዲደረግ ጠይቋል ።
በዚህ መልክ ክርክሩ ያቀረበለት የስር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን አጠቃላይ ክርክር ከመረመረ እና ለጉዳዩ አወሳሰን ተገቢነው ያለው ጭብጥ ከመሰረተ በኋላ የአሁኑ ተጠሪ ቅድመ ክፍያ የግንባታው አጠቃላይ ዋጋ 30% መቀበሉን የስራ ዝርዝር እና ሳይት ፕላኑ የማይጣጣም ስለመሆኑ ፤የስራ ዝርዝሩ OPd የሚል ሲሆን ፕላኑ ላይ ደግሞ IPd የሚል ስለመሆኑ፤ ይህ ደግሞ የዋጋ ልዩነት እንደሚያስከትል አመልካች ተጠሪዎችን ማስገደድ የሚችለው ፕላኑ በማስተካከል ወይም የሚያስፈልገው ወጪ በባለሙያ አስገምቶ በማስተካከል ብቻ ስለመሆኑ ፤ አመልካች ውሉ በማቋረጡ የሚከፈለው ኪሳራ ካለ ተጠሪዎች የመጠየቅ መብት እንደላቸው በመግለጽ ክሱን ውድቅ በማድረግ ወሰኗል ።የአሁኑ አመልካች በዚህ ውሳኔ ላይ ቅሬታውን ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመቀጠልም ለክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረበ ቢሆንም ተቀባይነት አላገኘም ። አመልካች የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔና ትዕዛዝ በመቃወም የአሁኑ ሰበር አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን የአቤቱታው መሰረታዊ ይዘት ሲታይም ፡- የስር ፍርድ ቤቶች ግራቀኙ ያደረጉት ውል አይፈርስም በማለት የቅድመ ክፍያው እጣ ፋንታ ሳይወሰኑ ማለፋቸው ተገቢ አለመሆኑን ፤1ኛ ተጠሪ ልዩነት እንዳለው እያወቁ ወደ ውል የገቡ በመሆኑ ውሉ ተሻሽሎ መቀጠል አለበት ተብሎ የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ ባለመሆኑ ላሻር ይገባል በማለት መከራከሩን የሚያሳይ ነው። የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ ለክሱ ምክንያት የሆነው ግንባታ ሳይጀመር የቀረው በአሁኑ አመልካች ምክንያት ነው የሚባል ቢሆን ተጠሪ በቅድሚያ የወሰዱት የውለታውን ገንዘብ 30% እንዲመልሱ የተጠየቀው ዳኝነት የመታለፋ አግባብነት ተጠሪዎች ባሉበት ማጣራት ይቻላል ዘንድ ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ይቅረብ ተብሐል ። ተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው ባቀረቡት የጽሑፍ መልስ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲጸና ጠይቋል ።
አመልካች አቤቱታውን የሚያጠናክር የመልስ መልስ አቅርቧል ።
የጉዳዩ አመጣጥና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከትነው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበትን የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት መሆን አለመሆኑን ለጉዳዩ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር መርምረናል ።
እንደመረመረነውም አመልካች ከ1ኛ ተጠሪ ጋር የግንባታ ውል ስምምነት በማድረግ ቅድመ ክፍያ 30% ወይም ብር 137,931.50 የወሰዱ ስለመሆኑ ያከራከረ ጉዳይ አይደለም ። አመልካች ባቀረበው ክስ ያደረጉት ውል ተሰረዞ በቅድመ ክፍያ የተወሰደው ገንዘብ እንዲመለሰለት ጠይቋል ። 1ኛ ተጠሪ በበኩላቸው ውሉ ተሻሽሎ የፕሮጀክቱ ገንዘብ ተጨምሮ ሥራውን ከሚቀጥል በቀር በቅድመ ክፍያ መልክ የወሰደው ገንዘብ ለመመለስ የሚገደድበት አግባብ አለመኖሩን በመግለጽ ተከራክሯል ። ጉዳዩን ያጣራው የስር ፍርድ ቤት በግንባታ ውሉ ያለው የስራ ዝርዝር እና ሳይት ፕላኑ የማይጣጣም ስለመሆኑ ሥራውን ተጨማሪ ውጪ የሚያስፈልገው ስለመሆኑ የአሁኑ 1ኛ ተጠሪ ሥራውን መቀጠል የሚችለው ፕላኑ በማስተካከል የሚያስፈልገው ወጪ በባለሙያ አስገምቶ በማስተካከል ብቻ ስለመሆኑ በመግለጽ ክሱን ውድቅ ማድረጉን መዝገቡ ያሳያል ። ከመዝገቡ እንደተረዳነው አመልካች የቅድመ ክፍያ 30% ከከፈለ በኋላ ከተጠሪዎች ጋር በተነሳው አለመግባባት ሥራውን አለመሰራቱን ነው ። የስር ፍርድ ቤት የአመልካች ክስ ውድቅ በማድረግ የወሰነ ቢሆንም በቅድመ ክፍያ ተወሰደ የተባለው ገንዘብ በተመለከተ ግን ያለው ነገር የለም ። አመልካች እና ተጠሪዎች ያደረጉት የግንባታ ውል ግራቀኙ ባደረጉት ስምምነት መሰረት የማይፈጸም ከሆነ ላኖር የሚችለው ህጋዊ ውጤት ከፍ/ሕ/ቁ 1815 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ማየቱ ተገቢ ይሆናል ። በዚህ ድንጋጌ መሰረት አንድ ውል የተሰረዘ ወይም የፈረሰ ከሆነ ግራቀኙ ውለታ ከመደረጉ በፊት ወደነበሩበት ሁኔታ ላመለሱ እንደሚገባ በግልጽ ተመልክቷል።
No specific laws extracted.
No topics extracted.
አመልካች ከ1ኛ ተጠሪ ጋር ያደረገው ውል ባህሪ ሲታይም አስተዳደራዊ ውል ስለመሆኑ መረዳት ይቻላል። በአመልካች እና 1ኛ ተጠሪ የተደረገው የጤና ጣቢያ ግንባታ ውል ከመሆኑ አንፃር የአስተዳደር አካሉ ውለታ የማፍረስ መብት ያለው ስለመሆኑ ተጠሪም ውሉ በመፍረሱ ምክንያት ጉዳት ያደረሰበት ቢሆን ካሳ የመጠየቅ መብት እንዳለው የፍ/ሕ/ቁ 3180 እና 3181 ድንጋጌዎች መሰረታዊ ይዘት ያስገነዝቡናል ። በመሆኑም የአሁኑ 1ኛ ተጠሪ ከአመልካች ጋር ያደረገው የግንባታ ውል በተፈጠረው አለመግባባት የማይቀጥል ስለመሆኑ ግልጽ በሆነበት ሁኔታ የስር ፍርድ ቤት በቅድመ ክፍያ የተወሰደውን ገንዘብ በተመለከተ ምንም ሳይል ማለፉ በሕጉ አግባብ ሆኖ አልተገኘም። በልላ በኩል አመልካች ከ1ኛ ተጠሪ ጋር ያደረገው ውል አስተዳደራዊ ውል ከመሆኑ አንፃር መንግስት ውሉን የመሰረዝ መብት አለው። የአሁኑ ተጠሪዎች የደረሰባቸው ጉዳት ካለ ካሳ ከሚጠይቁ በቀር መንግስት ውል እንዲያሻሽል የማስገደድ ወይም በቅድመ ክፍያ የተወሰደውን ገንዘብ ያለመመለስ መብት የላቸውም ብለናል ። በዚህ ሁሉ ምክንያት የስር ፍርድ ቤቶች የአመልካች ክስ የቅድሚያ ክፍያ ይመለስልኝ የሚል ሆኖ ሳለ እና ውሉም የሚቀጥልበት የህግ ምክንያት በልለበት ሁኔታ ክሱን ውድቅ ማድረጋቸው የፍ/ሕ/ቁ 1815 ፤ 3180 እና 3181 ያላገናዘበ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል ። በዚህም ተከታዩን ወስነናል ።
በደቡብ ጎንደር መስተዳደር የላቦ ከምከም ወረዳ ፍርድ ቤት በመዝገብ 6 በ16/02/2008 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ01/04/2008 ዓ.ም የሰጠው ብይን የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/አ/መ/ በ08/09/2008 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ ተሻሽሐል ።
የአሁኑ ተጠሪዎች ከአመልካች በቅድመ ክፍያ የወሰዱት ከፕሮጀክቱ አጠቃላይ ዋጋ 30% ወይም ብር 137,931.50 /አንድ መቶ ሰላሳ ሰባት ሺ ዘጠኝ መቶ ሰላሳ አንድ ከሀምሳ ሳንቲም / ላመለሱ ይገባል በማለት ወስነናል ።
ተጠሪዎች ከውሉ አፈፃፀም ጋር በተያያዘ የደረሰባቸው ኪሳራ ካለ በሕጉ አግባብ ክስ አቅርበው የመጠየቅ መብታቸው ይህ ውሳኔ አያግዳቸውም ብለናል ።
የዚህ ፍርድ ቤት ክርክር ያስከተለው ወጪና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል ።