በአንድ ክርክር ውስጥ የከሳሾች ወይም የተከሳሾች ብዛት ከአንድ በላይ ሲሆንና ክርክሩም ከሳሾችን ወይም ተከሳሾችን በአንድ ዓይነት መልክ የሚመለከታቸው ሲሆን ከሳሾቹ ወይም ከተከሳሾቹ አንዱ በጠቅላላው ውሳኔ ላይ ይግባኝ ሲጠይቅና ይግባኙ የቀረበለት ፍርድ ቤት ፍርዱን በመለወጥ ያሻሻለው ወይም የለወጠው ወይም ያጸናው ፍርድ ይግባኙን ባላቀረቡት ከሳሾች ወይም ተከሳሾች ላይም በይግባኝ ደረጃም በቀረበው ጉዳዩ ከከሳሾቹ መካከል አንዱ ይግባኝ ጠይቆ የሚሰጠው ውሳኔ ልሎችንም አቶ ኃይሉ ሂንጌ እና አመርቲ ነሼ የፊንጫኣ ሀይል መመንጫ ፕሮጀክት XII ስለመሆኑ፡የፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 35 እና 331
No summary available.
ህዳር 20 ቀን 2010 ዓ/ም ዳኞች፡- ፀጋዬ አስማማው ሙስጠፋ አህመድ አብርሃ መሰለ ጰውሎስ ኦርሺሶ ሰናይት አድነው አመልካች፡- አቶ ኃይሉ ሂንጌ የቀረበ የለም ተጠሪ፡- አመርቲ ነሼ የፊንጫኣ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት ነገረ ፈጅ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
የክርክሩ መነሻ በጉዳት ካሳ ክርክር ላይ ተሳታፊ ለመሆን የቀረበ ነው። ለዚህ የሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነው የአሁን አመልካችን ጨምሮ አራት ከሳሾች የአሁን ተጠሪ ይዞታቸውን ለኤልክትሪክ ማመንጫ ስለወሰደባቸው የንብረት ጉዳት ካሳ እንዲከፍል ክስ አቅርበው ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 14442 በቀን 28/6/2006 ዓም የሰጠውን ውሳኔ ቅር በመሰኘት ከሥር ከሳሾች መካከል የአሁኑን አመልካች ጨምሮ ሶስቱ ይግባኝ ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምዕራብ ምድብ ችሎት አቅርበው ሲፀናባቸው ከይግባኝ ባዮች መካከል አቶ አመንቴ ደበሎ እና አቶ በላይ በየነ የሰበር አቤቱታ ለፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ሲያቀርቡ የአሁን አመልካች ተሳታፊ አልነበሩም። የተጠቀሱት ሁለቱ አመልካቾች ያቀረቡትን አቤቱታ የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ተቀብሎ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኃላ በሰበር መዝገብ የካቲት 17 ቀን 2008 ዓ/ም በዋለው ችሎት ላጣሩ የሚገባቸውን ነጥቦችን በመለየት በፍትሓብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 343 /1/ መሰረት ለሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ መልሶታል።
ጉዳዩ ከተመለሰ በኃላ የአሁኑ አመልካች በነጥብ የተመለሰው ጉዳይ እሳቸውንም የሚመለከት በመሆኑ ወደ ክርክሩ ለመግባት ጉዳዩን ለያዘው ፍርድ ቤት ሲያመለክቱ ፍርድ ቤቱ አስቀድሞ የተሰጠው ውሳኔ የተሻረው ሁለቱን ከሳሾች በሚመለከት በመሆኑ የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት የሰጠው ውሳኔ አመልካችን አይመለከታቸውም ሲል ትዕዛዘ ሰጥቷል።
ይህን ትዕዛዝ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምዕራብ ምድብ ችሎት አቅርበው ይግባኙን ተቀብሎ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኃላ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አጽንቷል። ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም የሥር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ ለማስለወጥ ሲሆን አመልካች በሥር ፍርድ ቤቶች ተፈጽመውብኛል ያሐቸውን ዝርዝር የቅሬታ ነጥቦችን አቅርበዋል።
የሰበር አቤቱታውን አጣሪው መርምሮ የአሁን አመልካች ከልሎች ሰዎች ጋር በመሆን በተጠሪ ላይ የካሳ ጥያቄ አቅርበው እስከ መጨረሻ ድረስ ተከራክረው ክርክራቸው ተቀባይነት በማጣቱ ከነሱ ጋር ተከራካሪ የነበሩ ሰዎች ለፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አቤቱታቸውን አቅርበው በፍትሓብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 343 /1/ መሰረት ተገቢው ማጣራት ተደርጎ እንዲወሰን በመመለሱ የአሁን አመልካች በተመለሰው ነጥብ መሰረት ለመከራከር የሚያስችል መብት አላቸው ወይስ የላቸውም?
የሚለውን ለማጣራት ለሰበር ችሎት ይቅረብ ብለናል ሲል ትዕዛዝ ሰጥቷል።
አመልካች ተጠሪን በአድራሻ ለውጥ ምክንያት ለማግኘት ያለመቻላቸውን ገልጸው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግ በጠየቁት መሰረት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጥሪ ተደርጎ ባለመቅረቡ ምክንያት መልስ የመስጠት መብቱ እንዲታለፍ ተደርጓል።
የነገሩ አመጣጥና የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ እንደተገለጸው ሲሆን ጉዳዩ ለዚህ ችሎት እንዲቀርብ ሲደረግ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር ጉዳዩን እንደሚከተለው መርምረናል። እንደመረመርነውም አስቀድሞ እስከዚህ ሰበር ችሎት ድረስ ደርሶ በነጥብ በተመለሰው ጉዳይ የአሁኑን አመልካችን ጨምሮ አራት ሰዎች በአንድ ላይ ሆነው እያንዳንዳቸው የሚገባቸውን የንብረት ጉዳት ካሳ ግምት በማቅረብ በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.14442 በሆነው ተከራክረዋል። ክስ ያቀረቡት በአንድ መዝገብ፣በአንድ ዓይነት ጉዳይ፣ በአንድ ላይ ነው። ይህም የፍትሓብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 35 ድንጋጌን የተከተለ እንደሆነ እንመለከታለን። በዚህ ሁኔታ ክስ አቅርበው ከተፈረደባቸው ሰዎች መካከል አንዱ ይግባኝ አቅርቦ ውሳኔው ከተሻረ ወይም ከተለወጠ ወይም ከተሻሻለ ይግባኝ ያልጠየቀው ሰው የፍርዱ ተጠቃሚ ላሆን ይችላል ወይስ አይችልም? የሚለውን መመልከት ተገቢ ይሆናል። የፍትሓብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 331 በአንድ ክርክር ውስጥ የከሳሾች ወይም የተከሳሾች ብዛት ከአንድ በላይ ሲሆንና ክርክሩም ከሳሾችን ወይም ተከሳሾችን በአንድ ዓይነት መልክ የሚመለከታቸው ሲሆን ከሳሾቹ ወይም ከተከሳሾቹ አንዱ በጠቅላላው ውሳኔ ላይ ይግባኝ ማለት ይችላል።
በዚህ ዓይነት ይግባኙ የቀረበለት ፍርድ ቤት እንደነገሩ አከባቢ ፍርዱን በማሻሻል ወይም በመለወጥ ያሻሻለው ወይም የለወጠው ወይም ያጸናው ፍርድ ይግባኙን ባላቀረቡት ከሳሾች ወይም ተከሳሾች ላይም ይፀናባቸዋል። ይህ ድንጋጌ በፍትሓብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 35 ላይ የተደነገጉትን ዝርዝር ነገሮችን ባሟላ መልኩ በአንድነት ሆነው ክስ ያቀረቡ ከሳሾች ከውሳኔ መልስ በይግባኝ ደረጃም በቀረበው ጉዳዩ ከከሳሾቹ መካከል አንዱ ይግባኝ ጠይቆ የሚሰጠው ውሳኔ ልሎችንም እንደሚያካትት በግልጽ ያስቀምጣል።
በተያዘው ጉዳይ ከላይ እንደተገለጸው የአሁኑን አመልካች ጨምሮ አራት ከሳሾች ክስ መስርተው በአንድ መዝገብ የተከራከሩ ናቸው። ጉዳዩ ንብረት ካሳን መሰረት ያደረገ ነው። እያንዳንዱ ከሳሽ ለራሱ የሚገባውን የካሳ መጠን ገምቶ ማቅረብ ማለት ግን ለየብቻው ክስ አቅርቧል ላያስብል አይችልም። የሆሮ ጉድሮ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ ሲያደርግ በትዕዛዙ ላይ የገለጸው ምንም እንኳን ከሳሾቹ በአንድ ላይ ክስ ቢያቀርቡም እያንዳንዳቸው የካሳውን መጠን ለይተው ያቀረቡ ስለሆነ ከፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በነጥብ በተመለሰው ጉዳይ አመልካች ላከራከሩ አይችሉም የሚል ሲሆን ይህም የፍትሓብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 35 እና 331 ድንጋጌን መንፈስና ዓላማ የተከተለ ሆኖ አላገኘነውም። በመሆኑም የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ትዕዛዝም ሆነ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ሲጠቃለልም የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
የሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.14442 በቀን 07/10/2008 ዓ/ም የሰጠው ትዕዛዝ እንዲሁም የኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁ.209044 በቀን 13/04/2009 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ በፍትሓብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 348 /1/ መሰረት ተሽሯል።
አመልካች ወደ ክርክሩ ውስጥ ገብተው ለመከራከር ያቀረቡት አቤቱታ የፍትሓብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 331 ድንጋጌን የተከተለ በመሆኑ ከፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰበር መዝገብ ላይ የሚጣሩ ነጥቦች ተይዘው በተመለሱት መሰረት በመ/ቁ. 14442 በሆነው ላይ የአመልካች ክርክር ቀጥሎ ፍርድ ቤቱ አከራክሮ የመሰለውን ውሳኔ እንዲሰጥበት በፍትሓብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 343 /1/ መሰረት መልሰንለታል።
ከፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በተመለሰው መሰረት የሁለቱ ከሳሾች ክርክር ውሳኔ አግኝቶ ከሆነም የአመልካች ክርክር በዚያው መዝገብ ታይቶ ውሳኔ ላያገኝ ይገባል ብለናል።
የዚህን ችሎት ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ።
የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይደረሳቸው።
መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.