አንድ ጉዳይ በማንኛውም የክርክር ደረጃ ላይ በሚገኝበት ወቅት ተከራካሪ ወገኞች በእርቅ ወይም በግልግል ስምምነት የመጨረስ መብት ያላቸው ቢሆንም፤ ክሱን በእርቅ ለመጨረስ ቀጠሮ ያስለወጠ ወገን እነ ሕጻን ቤተልሄም ሰለሞን (ሁለት ሰዎች) እና እነ አቶ ጌታቸዉ XI በተሰጠበት ቀን ፍ/ቤትን ቀርቦ የተደረሰበትን ደረጃ ያለማሳወቅ እና ለረጅም ጊዜ ጉዳዩን ያለመከታተል ኪሳራ እንዲከፈል ላወሰንበት ከመቻሉ በላይ አዲስ ክስ መመስረት የማይቻል ስለመሆኑ፡የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ. 69 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ፣ የፍ/ሥ/ሥ/ቁ. 275 እና 79/1/ ገ/መስቀል(3 ሰዎች)
No summary available.
መስከረም 23 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ በዕዉቀት በላይ እንዳሻዉ አዳነ ኃይሉ ነጋሽ እትመት አሰፋ አመልካቾች:- 1ኛ. ሕጻን ቤተልሄም ሰለሞን ሞግዚት ወ/ሮ አዜብ እንግዳ 2ኛ. ሕጻን ቃለአብ ሰለሞን ሞግዚት አዜብ እንግዳ ተጠሪዎች፡- 1ኛ. አቶ ጌታቸዉ ገ/መስቀል 2ኛ. ወ/ሮ ንግስት ሃይሉ ጠበቃ ሀብታም ስብሀቱ ቀረቡ 3ኛ. ወ/ሮ ትርሐስ ሃይሉ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
አመልካቾች በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በዕርቅ ጉዳዩን ለመጨረሰ ጠይቀዉ የተጠሪዎች ወንድም ወደ ዉጭ በመሄዱ ዛሬ ነገ ይመጣል እያሉ ላሰበሰቡ ስላልቻሉ ፍ/ቤቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 73 መሰረት የዘጋዉ መዝገብ ተንቀሳቅሶ ጉዳዩ ይታይልን በማለት ያቀረቡት አቤቱታ ለተጠሪዎች እንዲደርሳቸዉ ተደርጎ በሰጡት መልስ ጉዳዩን በእርቅ እጨርሳለሁ ብለዉ በእርቅ መጨረስ ካልተቻለ ይህንኑ ለፍ/ቤቱ በቀጠሮ እለት ቀርቦ በማስረዳት ጉዳዩ እንዲቀጥል መጠየቅ ሲገባቸዉ የአመልካቾች ጠበቃ ባለመቅረቡ መዝገቡ ተዘግቷል። መዝገቡ ከተዘጋም ሁለት ዓመት ከ6 ወር ሆኖታል። መዝገቡ የተዘጋዉ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 69 ሆነ 73 ለዉጥ የልለዉ በመሆኑ መዝገቡ ላንቀሳቀስ አይገባም በማለት ተከራክረዋል።
የስር ፍ/ቤት ጉዳዩን መርምሮ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 73 መሰረት ከሳሾች ጉዳዩን በዕርቅ ለመጨረስ ከሄዱ በኃላ ባለመቅረባቸዉ መዝገቡ መዘጋቱ ተገቢ ሲሆን መዝገቡ ከተዘጋ ከ2 ዓመት ከ6 ወር በኃላ የሚከፈትበት አግባብ የለም፤ በቀጠሮ ቀን እርቁን አልጨረስንም ቀጠሮ ይሰጠን ብለዉ መጠየቅ እየተገባቸዉ ይህን አላደረጉም በማለት የአመልካቾችን መዝገብ ይንቀሳቀስልን አቤቱታ ዉድቅ በማድረግ ብይን ሰጥቷል።
አመልካቾች በዚህ ብይን ቅር ተሰኝተዉ ለክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ይግባኝ ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኘም። የሰበር አቤቱታዉ የቀረበዉ ይህን ብይን በመቃወም ለማስለወጥ ነዉ።
የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ይዘት፡- የስር ከፍተኛ ፍ/ቤት መዝገቡን በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ በሰጠዉ ብይን በቀን 06/10/2005 ዓ.ም መዝገቡን የዘጋዉ ሲሆን ይግባኝ ሰሚዉ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በቀን 22/12/2005 ዓ.ም ብይኑን በመሻር ወደ ፍሬ ጉዳዩ ገብቶ እንዲያከራክር ወስኖ መልሶለታል። ከዚያም መዝገቡ እንዲንቀሳቀስ ጠይቀን በቀን 11/02/2006 ዓ.ም ለቀን 28/02/2006 ዓ.ም ተጠሪዎች እንዲቀርቡ ያዘዘ ሲሆን ሳይቀርቡ በሽማግል እንድንጨርስ ጊዜ ይሰጠን ስላሉ እኛም ለፍ/ቤቱ ይህን አሳዉቀን ሂደናል። ፍ/ቤቱ ራሱ በቀን 23/03/2006 ዓ.ም ቀጠሮ ግራቀኙ ሳንቀርብ መዝገቡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 73 መሰረት ዘግቶታል። ግራቀኛችን ጉዳዩን በእርቅ እንጨርሳለን ብለን ያቀረብነዉ በልለንበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 69 መሰረት ለጊዜዉ መዝጋት ሲገባዉ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 73 መሰረት መዝጋቱ የሕግ ስህተት ነዉ። የስር ፍ/ቤት ግራቀኛችን በማናዉቀዉ እኛ ተስማምተን እንመጣለን ብለን የሄድነዉ በማስመሰል 2 ዓመት ከ6 ወር ሆኖታል መዝገቡ ላንቀሳቀስ አይገባም ማለቱ አግባብ አይደለም። ምክንያቱም የተጠሪዎች ወንድም ወደ ዉጪ አገር በመሄዱ እየጠበቅን ቆይተን እያለ መዝገቡ የተዘጋዉ በምን ምክንያት መሆኑን ሳናዉቅ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 73 መሰረት መዘጋቱ አግባብ ስላልሆነ የስር ፍ/ቤትን ብይን በመሻር መዝገቡ እንዲንቀሳቀስ ይወሰንልን የሚል ነዉ።
የአመልካቾች አቤቱታ ተመርምሮ ተከራካሪ ወገኖች ጉዳዩን በእርቅ ለመጨረስ ከፍ/ቤት የሄዱ ቢሆኑም የተከሳሽ ወገን በተለያየ ምክንያት ለእርቁ ዝግጁ ባለመሆናቸዉ የአሁኑ አመልካቾች ጉዳዩ እንዲንቀሳቀስ ሲያመለክቱ ከ1 ወር በላይ ጊዜዉ ያለፈ ስለሆነ የተዘጋዉ መዝገብ ላንቀሳቀስ አይገባም ተብሎ የተወሰነበትን አግባብነት ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 69-73 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች እንዲሁም ልሎች አግባብነት ካላቸዉ ሕጎች መሰረት ለማጣራት ሲባል ለሰበር ያስቀርባል የተባለ ሲሆን ግራቀኙ መልስና የመልስ መልስ በጽሁፍ በመቀባበል ተከራክረዋል።
የተጠሪዎች መልስ ይዘት፡- የስር ፍ/ቤት አመልካቾች ጉዳዩ በእርቅ ባያልቅም ለ23/03/2006 ዓ.ም በሰጠዉ ቀጠሮ መቅረብ ሲገባቸዉ ባለመቅረባቸዉ መዝገቡን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.73 መሰረት መዝጋቱም ሆነ ይንቀሳቀስልን አቤቱታ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 74(2) መሰረት በአንድ ወር ዉስጥ የቀረበ ባለመሆኑ ዉድቅ መደረጉ ሕጉን መሰረት ያደረገ ነዉ። ስለሆነም ይጽናልን የሚል ነዉ።
የጉዳዩ አመጣጥ ከላይ ባጭሩ የተገለጸዉን የሚመስል ሲሆን ግራ ቀኙ በዚህ ችሎት ያደረጉትን የጽሁፍ ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ብይን እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምረናል።
ከክርክሩ መገንዘብ የተቻለዉ ጉዳዩ በክርክር ሂደት ላይ እያለ የአሁን አመልካቾች ጉዳዩን በእርቅ ለመጨረስ በተጠሪዎች መጠየቃቸዉን ለፍ/ቤቱ በማስታወቃቸዉ ፍ/ቤቱ ቀጠሮ ለሕዳር 23 ቀን 2006 ዓ.ም ለዉጧል። በዚህ ቀጠሮ ግራቀኙ ባለመቅረባቸዉ ፍ/ቤቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 73 መሰረት መዝገቡን መዝጋቱን ገልጾ ተመላሽ አድርጓል። ከ2 ዓመት ከ6 ወር በኋላ ግንቦት 17 ቀን 2008 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የተዘጋዉ መዝገብ እንዲንቀሳቀስላቸዉ መጠየቃቸዉን ተገንዝበናል። አመልካቾች ለሕዳር 23 ቀን 2006 ዓ.ም ቀጠሮ የተያዘዉ ግራቀኛችን በልለንበት ነዉ የሚለዉ ክርክር ለቀጣይ 2 ዓመት ከ6 ወር ጉዳዩን ያልተከታተሉ በመሆናቸዉ የሚያመጣዉ ለዉጥ የለም። አመልካቾች መዝገቡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 69 መሰረት ላዘጋ እየተገባዉ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 73 መሰረት መዘጋቱ ስህተት ነዉ በማለት ያቀረቡትን ቅሬታ በተመለከተ መዝገቡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 73 መሰረት የተዘጋዉ ሐምል 01 ቀን 2008 ዓ.ም በተሰጠዉ ብይን ሳይሆን 2 ዓመት ከ6 ወር በፊት ሕዳር 23 ቀን 2006 ዓ.ም በመሆኑ በዚህ ረገድ የቀረበዉ ቅሬታ በዚህ መዝገብ ላታይ አይችልም።
በመሰረቱ አንድ ከሳሽ የሆነ ወገን በአንድ ሰዉ ላይ ክስ ከመሰረተ በኃላ በመጀመሪያዉ ቀጠሮ ይሁን ክርክር ላይ ባለበት ወቅት በተሰጠ ቀጠሮ ቀጠሮን አክብሮ በራሱ ወይም ወክሎት ላከራከር የሚችል ሰዉ አለመቅረብ ዋጋ እንደሚያስከፍል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጋችን ስለተከራካሪ ወገኖች መቅረብና አለመቅረብ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
69 እና ተከታዮቹ ቁጥሮች፣ ስለቀጠሮ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.197 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች እንዲሁም ክስን መተዉ አስመልክቶ ከተደነገጉ ጥብቅ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ መገንዘብ ይቻላል። በተለይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 275 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት አንድ ጉዳይ በማንኛዉም የክርክር ደረጃ ላይ በሚገኝበት ወቅት ተከራካሪ ወገኖች በእርቅ ወይም በግልግል ስምምነት የመጨረስ መብት ያላቸዉ ቢሆንም ክሱን ከሳሽ ወገን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 279(1) መሰረት ፍርድ ቤትን ሳያስፈቅድ ያቀረበዉን ክስ የተወ ከሳሽ ኪሳራ እንዲከፍል ላወሰንበት ከመቻሉም በላይ በተወዉ ክስ አዲስ ክስ መመስረት እንደማይችል በግልጽ ተመልክቷል።
በተያዘዉ ጉዳይ አመልካቾች በክርክር ላይ ያለዉን ጉዳያቸዉን በእርቅ ለመጨረሰ ቀጠሮ እንዲለወጥላቸዉ ጠይቀዉ ተለዉጦላቸዉ በተሰጠዉ ቀጠሮ ቀርበዉ የደረሱበትን ደረጃ ለፍ/ቤቱ አላሳወቁም። ከዚህ አልፎ ለ2 ዓመት ከ6 ወር ጉዳያቸዉን አልተከታተሉም።
ይህ በሆነበት ሁኔታ በቀጠሮ ዕለት ላለመቅረባቸዉ ያቀረቡት ምክንያት ምንም ይሁን ከ2 ዓመት ከ6 ወር በኃላ የተዘጋዉን መዝገብ እንዲንቀሳቀስላቸዉ የሚደረግበት የሕግ አግባብ የለም። በመሆኑም የስር ፍ/ቤት የተዘጋዉ መዝገብ 2 ዓመት ከ6 ወር በኃላ የሚንቀሳቀስበት የሕግ አግባብ የለም በማለት የአመልካቾችን አቤቱታ ዉድቅ ማድረጉ የሚነቀፍበት የሕግ ምክንያት የለም።
ሲጠቃለል የስር ፍ/ቤት የተዘጋዉ መዝገብ አይንቀሳቀስም በማለት የአመልካቾችን አቤቱታ ዉድቅ በማድረግ የሰጠዉ ብይን የስነ ስርዓት ሕጉን ድንጋጌዎች አላማ የተከተለ ነው ከሚባል በቀር የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አልተገኘም። በመሆኑም ተከታዩ በአብላጫ ድምጽ ተወስኗል።
በትግራይ ክልል በማዕከላዊ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 1631 ሐምል 01 ቀን 2008 ዓ.ም ተሰጥቶ፤ በክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ ጥቅምት 21 ቀን 2009 ዓ.ም በተሰጠ ትዕዛዝ የጸናዉ ብይን መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል ለማለት ባለመቻሉ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348/1/ መሰረት ጸንቷል።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።
No topics extracted.