ለቀጠሮ ምክንያት የሆነ ጉዳይ ሳይፈፀም የቀረው ከተከራካሪዎቹ ወገኖች በአንደኛው ጉድለት የሆነ እንደሆነ መፈፀም ይገባው የነበረው ጉዳይ ያልተፈፀመ ወ/ሮ ሸዋዬ ገ/እግዚአብሕር እና **ተጠሪ-** ወ/ሮ ብርሃኔ VII እንኳ ፍርድ ቤቱ የጉዳዩን መፈፀም ሳይጠብቅ የመሰለውን ውሳኔ መስጠት ስለመቻሉ፡የፍ/ብ/ስ/ሥ/ህ/ቁ 199(1) ፀአዱ
No summary available.
የካቲት 26 ቀን 2010 ዓ.ም.
ዳኞች- ዳኜ መላኩ ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነአ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራው ፀሃይ መንክር አመልካች- ወ/ሮ ሸዋዬ ገ/እግዚአብሕር - ጠበቃ ወይንሸት መንግስቱ ቀረቡ ተጠሪ- ወ/ሮ ብርሃኔ ፀአዱ - ጠበቃ ቅድስት የበቃ- ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የፍድራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ስላመለከቱ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁን አመልካች በተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ነው።
አመልካች ያቀረቡት ክስ ይዘት ተጠሪ በአዲስ አበባ ከተማ ወረዳ 20 ቀበል 38 ክልል ውስጥ ቁጥሩ 426 የሆነ ቤት ያላቸው ሲሆን ባለቤቴ ሟች አቶ ኃይለ ስልጣን ፀአዱ በህይወት በነበሩበት ወቅት በራስህ ጉልበትና ገንዘብ ቤት ሰርተህ በመኖሪያነት ተገልገልበት በማለት ውክልና ጭምር ሰጥተውት በቤታቸው ግቢ ውስጥ ተጠሪ ከልለው በሰጡት ቦታ ላይ ግምቱ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ) የሆነ ከእንጨትና ጭቃ የተሰራ አንድ ክፍል ቤት ከነመፀዳጃው ሰርተዋል፤ የሟችን ሞት ተከትሎ ተከሳሽ ቤቱን እየተገለገሉበት ሲሆን በዚሁ ቤት ውስጥ የነበሩ ግምታቸው ብር 11,766.00 (አስራ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ስድሳ ስድስት) የሆኑ የተለያዩ ንብረቶች ይዘው ስለከለከሉኝ ንብረቶቹን በአይነት ያስረክቡኝ ወይም ግምቱን እንዲከፍሉ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
ተጠሪ በሰጡት መልስ የቤት ቁጥር 426 የሆነው ቤት በተጠሪ እና በባለቤታቸው ሻምበል አረዳ በኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት በ1965 ዓ.ም የተሰራ ሲሆን ከዚያ ወዲህ በግቢው ውስጥ የተሰራ ቤት የለም፤ የአመልካች ባለቤት በተጠሪ ግቢ ቦታ ተሰጥቶት የሰራው ቤት የለም፤ ሟች የተጠሪ ወንድም በመሆኑ በእንግድነት መጥቶ ሲኖር ነበር፤
በመታመሙ ምክንያት ተጠሪ ሳስታምመው ቆይቶ ከዚህ አለም በሞት የተለየ ሲሆን አመልካች ለቅሶ ከመምጣት ውጪ አላስታመሙም፤ የቤት ቁሳቁስ በማለት ዘርዝረው ያቀረቡት አንድም ዕቃ የለም፤ በአጠቃላይ ክሱ አላግባብ ለመበልፀግ የቀረበ በመሆኑ ውድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክረዋል።
ጉዳዩ በዚህ መልኩ የቀረበለት የሥር ፍርድ ቤት ግራ ቀኙ ምስክሮቻቸውን እንዲያቀርቡ ያዘዘ ሲሆን ከሳሽ ምስክር በቀጠሮ ቀን አቅርበው ባለማሰማታቸው መብታቸው የታለፈ ሲሆን የተከሳሽ ምስክሮች ቀርበው እንደመልሳቸው ማስረዳታቸውን፤ ምስክር ከተሰማ በኋላ የአመልካች ጠበቃ በዕለቱ ልላ ቦታ ቀጠሮ ስለነበረኝ ምስክሮችን ፍርድ ቤቱ አስቀርቦ ይስማልኝ በማለት ቢጠይቁም በመጀመሪያ ምስክር ለመስማት ሲቀጠር ግራ ቀኙ በተገኙበት መታዘዙን መዝገቡ የሚያሳይ በመሆኑና ከሳሽ ሆነ ጠበቃቸው በቀጠሮው ምስክር እንደሚሰማ እያወቁ ልላ ቦታ ቀጠሮ ተደርቦ ቢሆን እንኳ ቢያንስ ጠበቃው ከቀጠሮ ቀን በፊት ይህንን ለችሎቱ ማሳወቅ ሲገባቸው ካለማሳወቃቸውም በላይ ለምስክሮች መጥሪያ ስለማድረሳቸው እንኳ አልተረጋገጠም፤ በመሆኑም ከሳሽ በራሳቸው ቸልተኝነት ምስክር አላሰሙም፤ በሰነድ ረገድም ያቀረቡት ማስረጃ የለም፤ ስለሆነም ክሱ በተከሳሽ የተካደ በመሆኑና ከሳሽም በሰነድም ይሁን በሰው ማስረጃ እንደክሱ ያላስረዱ በመሆኑ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ወስኗል።
አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም የይግባኝ ቅሬታቸውን ለፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ነው። አመልካች የካቲት 3/2009 ዓ.ም ያቀረቡት የሰበር ማመልከቻ ተመርምሮ አመልካች ጠበቃቸው ባለመገኘታቸው ብቻ ምስክር የማሰማት መብታቸው ታልፎ ክሱን አላስረዱም ተብሎ የመወሰኑን አግባብ ለማጣራት ሲባል ጉዳዩ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ እና ተጠሪ መልስ እንዲሰጡበት ተደርጓል። ተጠሪ መስከረም 23/2010 ዓ.ም በተፃፈ መልስ አመልካች ለምስክሮች የተጻፈውን መጥሪያ እንኳን ሳይወስዱ እርሳቸውም ሆነ ጠበቃቸው በቀጠሮው እለት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በመቅረታቸው በሥነ ሥርዓት ህጉ መሰረት ምስክር የማሰማት መብታቸው የታለፈው በህጉ አግባብ በመሆኑ የሚነቀፍበት አንዳችም ምክንያት ካለመኖሩም በላይ ይህን የታለፈ መብታቸውን ለማስነሳት የሚያበቃ በቂ ምክንያት ያላቀረቡ በመሆኑ ውሳኔው ላፃና ይገባል በማለት ተከራክረዋል። አመልካችም ክርክራቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
ከፍ ሲል ባጭሩ የገለፅነው የጉዳዩን አመጣጥ እና በሰበር የተደረገውን ክርክር ሲሆን በበኩላችን በሥር ፍርድ ቤቶች በተላለፈው ውሳኔ የተፈፀመ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን መርምረናል።
ክርክሩ በሚመራበት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 199(1) ሥር እንደተደነገገው ለቀጠሮ ምክንያት የሆነው ጉዳይ ሳይፈፀም የቀረው ከተከራካሪዎቹ ወገኖች በአንደኛው ጉድለት ሆኖ እንደሆነ መፈፀም ይገባው የነበረው ጉዳይ ያልተፈፀመ ቢሆንም እንኳ ፍርድ ቤቱ የጉዳዩን መፈፀም ሳይጠብቅ የመሰለውን ውሳኔ መስጠት እንደሚችል ተመልክቷል።
ከተያዘው ጉዳይ መገንዘብ እንደሚቻለው የስር ፍርድ ቤቶች የአመልካችን ክስ ውደቅ በማድረግ የወሰኑት አመልካች ሆኑ ጠበቃቸው በቀጠሮው ምስክር እንደሚሰማ እያወቁ ባለመቅረባቸውና ጠበቃው ልላ ቦታ ቀጠሮ ተደርቦባቸው ቢሆን እንኳ ቢያንስ ከቀጠሮ ቀን በፊት ይህን ለፍርድ ቤቱ ካለማሳወቃቸውም በላይ ለምስክሮች መጥሪያ ማድረሳቸው እንኳ አልተረጋገጠም፤ በመሆኑም ከሳሽ በራሳቸው ቸልተኝነት ምስክር አቅርበው ያላስረዱ በመሆኑ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በሚል ነው። አመልካች በዚህ መልኩ መብታቸው የታለፈው ከህግ ውጪ ነው ላባል የሚችልበት በህግ የተደገፈ ምክንያት አላቀረቡም።
ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤቶች ከፍ ሲል በተጠቀሰው መልኩ የደረሱበት መደምደሚያ እና ያሳለፉት ውሳኔ ክርክሩ የሚመራበትን የሥነ ሥርዓት ህግ መሰረት ያደረገ ነው ከሚባል በቀር የተከተሉት የክርክር አመራር ሥርዓት የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው የሚሰኝ ሆኖ አላገኘነውም። ስለሆነም ተከታዩን ወስነናል።
በፍድራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ ጥር 20/2007 ዓ.ም ተሰጥቶ በከፍተኛው ፍርድ ቤት በኮ/መ/ ህዳር 6/2009 ዓ.ም የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ፀንቷል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ።
No topics extracted.