የማይፀናና ህገ ወጥ የሆነ የቤት ሽያጭ ውል ፈራሽ ሆኖ ግራ ቀኙ ወገኖች ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ ውሳኔ ሲሰጥ በህገ ወጥ በመንገድ በተገኘው ባዶ ቦታ ላይ ቤት የገነባው ወገን ቤቱን በራሱ ወጪ በማፍረስ ለባለይዞታው እንዲያስረክብ ከማድረግ ባለፈ ለግንባታው ያወጣውን ወጪ ባለይዞታ የሆነው ወገን እንዲከፍለው ላደረግ የማይገባ ስለመሆኑ፡የኢ.ፍ.ድ.ሪ ሕ/መ አንቀፅ 40(3) እና የፍ/ብ/ህ ቁ 1815
No summary available.
መስከረም 26 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡ ...1.ረታ ቶለሳ 2. ተኽላት ይመሰል 3. ተፈሪ ገብሩ 4. ቀነዓ ቂጣታ 5. ፀሐይ መንክር አመልካች፡- ወ/ሮ እቴናት አድማሱ - ቀርበዋል ።
ተጠሪ፡- አቶ ደመቀ ይዘንጋዉ - የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድተሰጥቷል።
ይህ የሰበር ጉዳይ የመኖሪያ ቤት ክርክርን መነሻ ያደረገ ሲሆን፣ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ላቀርብ የቻለዉ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.45202 በ20/07/2008 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልኝ በማለት የአሁን አመልካች ያቀረበችዉን የሰበር አቤቱታ መርምሮ ለመወሰን ነዉ።
የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ በቢቡኝ ወረዳ ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪ ከሳሽ፣የአሁን አመልካች ተከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር።ከሳሽ ባቀረበዉ ክስ በ26/2/1999 ዓ.ም በተደረገዉ ዉል ተከሳሽ 8 ሜትር በ 12 ሜትር የሆነዉ ቦታና ቤት በብር 1,800.00 ሸጠዉልኝ በቦታዉ ላይ 37 ቆርቆሮ ቤት ከሰራሁኝ በኋላ ስመ ሀብቱን አዛዉርልኝ ካርታና ፕላን ላሰራበት ሲላት ፈቃደኛ ካለመሆንዋም በላይ በስሟ ካርታና ፕላን አሰርታ ከይዞታዋ ጋር ስላከተተች ቤቱን የገዛሁበትን ብር 1,800.00 ዉል ላፈረሰችበት ብር 5,000.00፣ 37 ቅጠል ቆርቆሮ ለማሰራት ያወጣሁትን ወጪ በአጠቃላይ ብር 27,198 /ሀያ ሰባት ሺህ አንድ መቶ ዘጠና ስምነት/ እንዲትከፍለኝ በማለት ከሷል።
ይህን ክስ በተመለከተ ተከሳሽ ባቀረበችዉ መልስ በተባለዉ ዉል ቤቱንና ቦታዉን አልሸጥኩም፣ በ26/2/1999 ዓ.ም በተጻፈ ዉል 5 ሜትር በ 5 ሜትር ባዶ ቦታ በብር 1,800.00 ሸጨለት በዉሉ ቀን ብር 50.00 ሰጥቶኝ ቀሪዉን ዉሉ በቀበል ሲጸድቅ ላሰጠኝ ተስማምተን ነገር ግን ባዶ ቦታ አይሸጥም ስለተባለ ብሩን መልሸለታለሁ እኔ ለቅሶ በሄድኩበት በልለሁበት 32 ቆርቆሮ በጉልበት ባልሸጥኩለት ቦታ ሁሉ ቤት ሰርቷል፣ ባዶ ቦታ አይሸጥም፣ ቤቱን ለመስራት የተባለዉን ወጪ አያወጣም፣ ስለዚህ ቤቱን በራሱ ወጪ አፍርሶ እንዲያነሳ በማለት ተከራክሯል።
ከዚህ በኋላ ፍ/ቤቱ የሰዉ ምስክሮችን በመስማት በሰጠዉ ዉሳኔ የሽያጭ ዉሉ የተደረገዉ ባዶ ቦታ ላይ ስለሆነ የሚጸና የቤት ሽያጭ ዉል የለም፣ ዉሉ ፈርሶ ተዋዋይ ወገኖች ወደ ነበሩበት ላመለሱ ይገባል፣ ከሳሽ በተከሳሽ ቦታ ላይ 33 ቆርቆሮ የሰራዉ ተከሳሽ እያወቀች ቢሆንም ከሳሽ ቤቱን አፍርሰዉ ከሚያነሳ በቀር ግምቱንም ሆነ ቤቱ የተሰራበትን ወጪ ለመክፈል የሚትገደድበት የሕግ አግባብ የለም፤ ነገር ግን ከሳሽ ቤቱን አፍርሶ ለመዉሰድ የጠየቀዉ ዳኝነት ስለልለ ታልፏል፣ በዚህ በሕገ ወጥ ዉል ምክንያት ከሳሽ ለተከሳሽ የከፈላት ብር 1,800.0 /አንድ ሺህ ስምንት መቶ/ ተከሳሽ ለከሳሽ እንዲትከፍለዉ በማለት ወስኗል። የምስራቅ ጎጀም አስተዳደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዳዩን በይግባኝ አይቶ የሥር ዉሳኔ አንጽቷል።
የሥር ከሳሽ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታ ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረበ ሲሆን ችሎቱ ግራ ቀኛቸዉን በማከራከር በሰጠዉ ዉሳኔ የሽያጭ ዉሉ ሕገ ወጥ ስለሆነ ተጠሪ ለአመልካች ብር 1,800.00 /አንድ ሺህ ስምንት መቶ/ እንድትመልስ መባሉ በአግባቡ ነዉ፣ የሥር ፍ/ቤት ዉሉ ሕገ ወጥ ቢሆንም መኖሩን እስካመነበት ድረስ አመልካች ቤቱን ለመሥራት ያወጣዉን ወጪ ተጠሪ ልትከፍለዉ አይገባም በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነዉ፣ አመልካች ቤቱን ለመሥራት ያወጣዉን ወጪ ተጠሪ ልትከፍለዉ ይገባል፣ የወጪዉን መጠን ግን የሥር ፍ/ቤት በማስረጃ አጣርቶ እንዲወስን በማለት ወደ ሥር ፍ/ቤት መልሶታል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ ይህን ዉሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካች በ16/09/2008 ዓ.ም የተጻፈ ሁለት ገጽ አቤቱታ አቅርቧል።
የአቤቱታዉ ይዘት በአጭሩ፡--የአሁን አመልካች ከተጠሪ ጋር የፈጸምነዉ ረቂቅ ዉል ሲሆን የሽያጭ ዉሉ ባዶ ቦታ የሚመለከት በመሆኑ በወቅቱም ዉሉን ለማዞር ስንጠይቅ የባዶ ቦታ ሽያጭ ዉል አይዞርም በመባላችን ረቂቅ ዉሉ ቀሪ ወይም ፈራሽ ያደረግነዉ ሆኖ ሳለ ቤቱንም ያለ እኔ ፈቃድ የሰራዉ መሆኑን ምስክሮች ከማረጋገጣቸዉም በላይ የቀበልዉ ዋና አስተዳደሪ በችሎት ቀርቦ ያስረዳ በመሆኑ መክፈል የሚገባዉ ስለረቂቅ ዉሉ የተባልኩትን ገንዘብ ብቻ እንጂ ያለ እኔ ፈቃድ ከሳሽ ስለሰራዉ ቤት ግምት ለመክፈል የምገደድበት ምክንያት የለም፣ ቤቱ የተሰራበትም ተቃዉሜአለሁ ስለዚህ የክልል ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠዉ ዉሳኔ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ላታረምልኝ ይገባል በማስረጃ ተመልሶ እንዲጣራልኝ ወጪና ኪሳራ እንዲከፈለኝ በማለት በዝርዝር አመልክቷል።
የሰበር አጣሪ ችሎት ጉዳዩን በማየት ፣የሥር ፍ/ቤት የአሁን አመልካች ዉሉ ሕገ ወጥ እንደሆነ እና ቤቱ የተሰራዉ በልለሁበት ነዉ በማለት ያቀረቡት ክርክር ታልፎ ተጠሪ ቤቱን ለመስራት ያወጡት ወጪ አመልካች እንዲከፍሉ የመባሉን አግባብነት፣ ለመመርመር ሲባል አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዲያቀርብ ቢታዘዝም ተጠሪ መጥሪያ ተቀብለዉ ባለመቅረባቸዉ መልስ የመስጠት መብታቸዉ ታልፏል።
የጉዳዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸዉ ሲሆን ይህ ችሎት የግራ ቀኛቸዉን ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንዲሁም አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል ከተያዘዉ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመርነዉ የአሁን አመልካች እና ተጠሪ በ26/2/1999 ዓ.ም በተደረገ የሽያጭ ዉል ቦታና ቤት እንደሚመለከት ቢገለጽም፣ የሥር ፍ/ቤት ባደረገዉ ማጣራት ግራ ቀኛቸዉ የተሻሻጡት ባዶ ቦታ ብቻ መሆኑን ባቀረበዉ ማስረጃ አረጋግጧል። ስለሆነም ግራ ቀኛቸዉ የተሻሻጡት ባዶ ቦታ በመሆኑ የሥር ፍ/ቤቶች የሚጸና የቤት ሽያጭ ዉል እንደልለ እና ዉሉ ሕገ ወጥ መሆኑን ድምዳሜ ላይ በመድረስ ወስኗል። በኢ.ፍ.ድ.ሪ.ሕገ መንግስት አንቀጽ 40 /3/ መሰረት ‹‹የገጠርም ሆነ የከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሀብት ባለቤትነት መብት የመንግስትና የሕዝብ ብቻ ነዉ። መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሕር ብሕረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ንብረት ነዉ። በማለት ደንግጓታል። ይህን ድንጋጌ ተግባራዊ ለማድረግ ከወጡት ዝርዝር ሕጎች መካከል የከተማ ቦታ በላዝ ስለመያዝን እንደገና ለመደንገግ የወጣዉ አዋጅ ቁጥር 272/1994 እና ይህን አዋጅ የሻረ የከተማ ቦታን በላዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ ቁጥር 721/2004 ተጠቃሾች ናቸዉ። እነዚህ እና ልሎች ዝርዝር ሕጎችን ማየት እንደሚቻለዉ የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት በሕጉ በተዘረጋዉ ሥርዓት ተከትሎ ስልጣን ያለዉን አካል ጠይቆ ከማግኘት ዉጭ በሽያጭ ገዝቶ መያዝ እንደማይቻል ያስገነዝባሉ። የከተማ ቦታ በሽያጭ ዉል ተሽጦ ከሆነ ዉሉ ሕገ መንግስቱንም ሆነ ዝርዝር ሕጎቹን የሚጥስ ስለሆነ ሕገ ወጥና ፈራሽ ዉል ነዉ።
በዚህ መሰረት አሁን ወደ ተያዘዉ ጉዳይ ስንመለስ የአሁን ተጠሪ ባዶ ቦታ ከአመልካች ገዝቶ ቤት የሰራ መሆኑ በሥር ፍ/ቤት የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ። የሥር ፍ/ቤቶች በዉሳኔዎቻቸዉ እንዳመለከቱት ይህ ዉል ሕገ ወጥ እና ፈረሽ ዉል ነዉ። ይህ ከሆነ ደግሞ ግራ ቀኛቸዉ ወደ ነበሩበት ላመለሱ ይገባል። በዚህ ረገድ የፍ/ብ/ሕ/ቁ.1815 ማየት ይቻላል። ግራ ቀኛቸዉ ወደ ነበሩበት ላመለሱ ይገባል ሲባል ግን የባለይዞታነት መብት ያለዉን ሰዉ/አካል ላይ እዳ በመጫን መሬቱን ላያጣዉ የሚችል የገንዘብ ክፍያ ላጣልበት አይገባም። በመሆኑም ይህ ዉል ሕገ ወጥ በመሆኑ እስከፈረሰ ድረስ የአሁን አመልካች ለተጠሪ ልትከፍለዉ የሚገባት ብር 1,800 /አንድ ሺህ ስምንት መቶ/ ብቻ ላሆን ይገባል እንጂ የአሁን ተጠሪ በሕገ ወጥ ዉል በያዘዉ ቦታ ላይ የሰራዉን ቤት ለማሰራት ያወጣዉን ወጪ አመልካች የምትከፍልበት የሕግ አግባብ የለም። ስለሆነም የአሁን ተጠሪ በአመልካች ቦታ ላይ የሰራዉን ቤት በራሱ ወጪ በማፍረስ ቦታዉን ለተጠሪ ለማስረከብ ግድታ አለበት። ነገር ግን ግራ ቀኛቸዉ ከተስማሙ የአሁን አመልካች የቤቱን ግምት ለተጠሪ ከፍለዉ ቤቱን ለመዉሰድ ይህ ዉሳኔ የሚያግዳቸዉ አይሆንም ብለናል።
ሲጠቃለል የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በግራ ቀኛቸዉ መካከል የተደረገዉ ዉል ሕገ ወጥ ስለሆነ አመልካች የተቀበሉትን ገንዘብ ብር 1,800.00 /አንድ ሺህ ስምንት መቶ/ ለተጠሪ እንድትመልስ ያለዉ ተገቢ ቢሆንም ተጠሪ በአመልካች ቦታ ላይ ቤት ለመስራት ያወጣዉን ወጪ እንድትከፍል በማለት የሰጠዉ የዉሳኔ ክፍል መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ የሚከተለዉ ተወስኗል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠው ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 /1/ መሰረት ተሻሽሐል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የአሁን ተጠሪ በአመልካች ቦታ ላይ ቤት ለመስራት ያወጣዉን ወጪ የመክፈል ኃላፊነት አለባት በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ ክፍል ተሽሯል። የአሁን ተጠሪ በራሱ ወጪ ቤቱን ከአመልካች ቦታ ላይ አፈርሶ በማንሳት ቦታዉን ለአመልካች ላለቅ ይገባል። አመልካች ቤቱን ለመስራት ተጠሪ ያወጣዉን ወጪ ለመክፈል አይገደዱም ብለናል። ነገር ግን ግራ ቀኛቸዉ ከተስማሙ እና የአሁን አመልካች ከፈለጉ የቤቱን ግምት ለተጠሪ ከፍለዉ ቤቱን ለመዉሰድ ይችላሉ ብለናል።
የቢቡኝ ወረዳ ፍ/ቤት በመ.ቁ.07213 በ17/3/2007 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና ይህን ዉሳኔ በማጽናት የምስራቅ ጎጀም አስተዳደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.0120127 በ7/4/2007 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ በዉጤት ደረጃ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያልተፈጸመባቸዉ ስለሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.348 /1/ መሰረት ጸንቷል።
የሥር ፍ/ቤቶች የአሁን አመልካች በዉል ምክንያት ከተጠሪ የተቀበሉትን ብር 1,800.00 /አንድ ሺህ ስምንት መቶ/ ለተጠሪ እንዲመልሱ በማለት የሰጡት የዉሳኔ ክፍል ጸንቷል።
የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይደረስ። ግራ ቀኛቸዉ በዚህ ችሎት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻሉ።
በ8/10/2008 ዓ.ም የተሰጠዉ የእግድ ትዕዛዝ በዚህ ዉሳኔ ተነስቷል።
No topics extracted.