በመርህ ደረጃ አንድ ዉል ለአንደኛው ወገን የበለጠ ሼህ አደም ፋረስ የካቲት 44 V ይሰጣል በሚል እንደማይፈርስ ነገር ግን ፈቃድ የተገኘዉ በዕድሜ መግፋት ወይም የንግድ ልምድ ዕዉቀቱ ማነስ ካለና በሕላና ግፍ መስሎ ከታየ ዉሉ የሚሰርዝበት ሁኔታ ስለመኖሩ፡አንድ ተዋዋይ የዉል ይሰረዝልኝ ክስ ዉሉ የማይረጋበት ምክንያት ከቀረበት ጊዜ ጀምሮ በሁለት ዓመት ዉስጥ ማቅረብ ያለበት ስለመሆኑ ፡የፍ/ሕ/ቁ. 1710(1)እና(2) ፤ የፍ/ሕ/ቁ.1810(1) እና ሼህ ሙስጠፋ ፍላ 27/2010 ዓ.ም 10. ዉል እንዲፈርስ ጥያቄ የሚያቀርብ ወገን ዉሉ ላፈርስ የሚችልበት በህግ ተቀባይነት ያለዉ ምክንያት ስለመኖሩ የማስረዳት ግድታ ያለበት ሲሆን የዉል ይፍረስልኝ ጥያቄ የሚቀርብለት ፍርድ ቤትም ለዉሉ መፍረስ በምክንያትነት የተጠቀሰዉ ሁኔታ ዉሉ እንዲፈርስ ለማድረግ በህግ ተቀባይነት ያለዉ እና በቂ ምክንያት መሆን አለመሆኑን ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸዉ የህጉ ድንጋጌዎች እነ አቶ ረጋሣ ጉርሙ (2 ሰዎች) እና እነ አቶ ተሾመ አፈወርቅ (2 ሰዎች) VI ጋር አገናዝቦ የማጣራት ግድታ ያለበት ስለመሆኑ፡የፍ/ብ ህግ አንቀጽ 347(1)፣ 347(2) እና ፍ/ህ አንቀጽ 1710(2)
No summary available.
የሰ/መ/ቁ/ -138386 ቀን - 26/06/2010 ዓ.ም ዳኞች፡- ዳኜ መላኩ ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራዉ ፀሐይ መንክር አመልካቾች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ የዉል ይፍረስልኝ ጥያቄን መሰረት በማድረግ የተሰጠዉን ፍርድ በመቃወም የቀረበን የሰበር አቤቱታ የሚመለከት ነዉ። ክርክሩ የተጀመረዉ በፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን፣ ተጠሪዎች ከሳሽ አመልካቾች ደግሞ ተከሳሾች በመሆን ተከራክረዋል።
ተጠሪዎች በቀን 20/08/05 ዓ.ም ጽፈዉ ለፍርድ ቤቱ ያቀረቡት ክስ ይዘትም በአጭሩ፤
አመልካቾች የማይገባቸዉን ጥቅም ለማግኘት የተጠሪዎችን በዕድሜ መግፋትና ነገሮችን የማመዛዘን አቅማቸዉ እየቀነሰ መሄድን በተለይም 1ኛ ተጠሪ ከ1994 ዓ.ም ጀምሮ ፓርኪንሰስ በሚባል የማስታወስ አቅምን በሚያሳጣ በሽታ በመጠቃቱ የአእምሮ እና የነርቭ በሽተኛ መሆኑን በመጠቀም እና 2ኛ ተጠሪን ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ በማሳመን እና በማግባባት በቂ/ክ/ከተማ ወረዳ 2 ዉስጥ የሚገኘዉን የቤ/ቁ/047/26 የሆነዉን ቤት ነሐሴ 06 ቀን 1996 ዓ.ም እራሳቸዉ ባዘጋጁት የሽያጭ ዉል ላይ ተጠሪዎችን አስፈርመዉ ግን በዉሉ ላይ የተጠቀሰዉን ገንዘብ ሳይከፍሉ የቤቱን ካርታ እና ተያያዥ ሰነዶችን መቀበላቸዉን ጠቅሰዉ በተንኮል፣ያልተገባ ተስፋ በመስጠት ዉል ለመዋዋል ችሎታ በልላቸዉ ሰዎች መካከል የተደረገዉ ዉል ፈራሽ ነዉ ተብሎ ይወሰንልን የሚል ነዉ።
አመልካቾች ለቀረበባቸዉ ክስ በሰጡት መልስ፤ ዉሉ ተደርጎ ከሁለት ዓመት በኋላ የቀረበዉ የዉል ይፍረስልን ጥያቄ በይርጋ የሚታገድ መሆኑን ጠቅሰዉ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አንስተዉ የተከራከሩ ሲሆን፣ ፍሬ ነገሩን በተመለከተም ቀደም ሲል በመንደር የተፃፈዉን የሽያጭ ዉል ህጋዊ ለማድረግ በዉልና ሰነዶች ማረጋገጫ ምዝገባ ጽ/ቤት መመዝገቡን እና ተጠሪዎች ገንዘቡን መቀበላቸዉን እና 1ኛ ተጠሪ የአእምሮ በሽተኛ ነዉ በሚል ዉሉ እንዲፈርስ የቀረበዉም ዳኝነት ተቀባይነት የልለዉ መሆኑን በመጥቀስ ክሱ ዉድቅ ሆኖ ይወሰንላቸዉ ዘንድ ተከራክረዋል።
ጉዳዩ በመጀመሪያ የቀረበለት የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በዚህ መልኩ ከግራ ቀኝ የቀረበዉን ክርክር እና ማስረጃ ከሰማ በኋላ፤ 1ኛ ተጠሪ ዉሉ በተደረገበት ወቅት ነገሮችን የማገናዘብ እና የማስተዋል ችግር በሚያስከትል ፓርክንስንስ በሚባል በሽታ መጠቃታቸዉ በሕክምና ማስረጃ መረጋገጡን እና በወቅቱ ዕድሜያቸዉ በ90 ዓመት የሚጠጋ መሆኑ ሲታይ 1ኛ ተጠሪ ዉሉን ያደረጉት ህጋዊ ዉጤቱን ለማወቅ የሚያስችል ጤነኛ የአእምሮ ሁኔታ እና አቅም ሳይኖራቸዉ መሆኑን ጠቅሶ ዉሉ ፈራሽ ነዉ በማለት ተጠሪዎች በዉሉ ምክንያት የተቀበሉትን ብር 700,000.00 ለአመልካቾች እንዲመልሱ፣አመልካቾችም ለዉሉ መነሻ የሆነዉን ቤት ለተጠሪዎች እንዲያስረክቡ ሲል ወስኗል። የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ይህኑን አጽንቷል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበዉም በዚሁ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ሲሆን፣ አመልካቾች በቀን 21/06/09 ዓ.ም ተዘጋጅቶ በጠበቆቻቸዉ አማካይነት ባቀረቡት 5 ገጽ የሰበር አቤቱታ፤ 1ኛ ተጠሪ በዕድሜ መጃጃታቸዉ እንዲሁም የአእምሮ ጤና ችግር ያለባቸዉ እና ዉሉም በጫና የተደረገ ስለመሆኑ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ፣ በልላ በኩል ተጠሪዎች የሽያጭ ዉሉን ያደረጉት ወደዉ እና ፈቅደዉ በሰነዶች ምዝገባ እና ማረጋገጫ ጽ/ቤት በተረጋገጠ ዉል ሆኖ እያለ ዉሉ ተደርጎ ከሁለት ዓመት በኋላ የቀረበን የዉል ይፍረስልኝ ጥያቄ በመቀበል ዉሉ እንዲፈርስ በሚል በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመባቸዉ በመሆኑ ተሽረዉ ይወሰንላቸዉ ዘንድ ዳኝነት ጠይቀዋል።
አቤቱታዉ ተመርምሮ ዉሉ የተደረገዉ ተጠሪዎች በዕድሜ መጃጃት እና አእምሮ መታወክ ላይ በነበሩበት ወቅት ነዉ በሚል ምክንያት ዉሉ ተደርጎ ከሁለት ዓመት በኋላ የቀረበዉን የዉል ይፍረስልኝ ጥያቄ በመቀበል ዉሉ እንዲፈርስ የተሰጠዉን ዉሳኔ አግባብነት ግራ ቀኝ በተገኙበት አከራክሮ ለመወሰን ሲባል መዝገቡ ለሰበር ችሎት የስቀርባል በመባሉ፣ ተጠሪዎች ቀርበዉ በቀን 15/09/09 ዓ.ም ተዘጋጅቶ በጠበቃቸዉ አማካይነት ባቀረቡት 9 ገጽ የጽሑፍ መልስ፤ 1ኛ ተጠሪ የማሰብ እና የማስታወስ አቅም በሚያሳጣ ፓርክንሰስ በሚባል የአእምሮ ህመም ተጠቅቶ ባሉበት ወቅት ዉሉ መደረጉ በመረጋገጡ በፍቃድ ጉድለት ምክንያት ዉሉ እንዲፈርስ መደረጉ እና ክሱም በሁለት ዓመት ይርጋ ቀሪ ላሆን የማይገባዉ መሆኑን በመጥቀስ የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ ፀንቶ ይወሰንላቸዉ ዘንድ ዳኝነት ጠይቀዋል። አመልካቾች በቀን 12/10/09 ዓ.ም ጽፈዉ ባቀረቡት የመልስ መልስ ቀርቦ ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል።
የጉዳዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኝ ክርክር ይዘት በአጭሩ ከላይ የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችሎትም ለሰበር አቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉን ዉሳኔ መዝገቡን ለማስቀረብ ከተያዘዉ ጭብጥ እና ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል። ከግራ ቀኝ ክርክር ሂደት መገንዘብ የተቻለዉ ተጠሪዎች በስር ፍርድ ቤት ላቀረቡት ክስ መሰረት ያደረጉት ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ የቤት ሽያጭ ዉል የተደረገዉ ተጠሪዎች በዕድሜ ጃጅተዉ ባሉበት ወቅት በተለይም 1ኛ ተጠሪ ፓርክንስንስ በሚባል አእምሮን በሚያጠቃ በሽታ ተጠቅተዉ የዉሉን ህጋዊ ዉጤት ለማወቅ በሚያስችል ጤነኛ የአእምሮ ሁኔታ እና አቅም ሳይኖራቸዉ በመሆኑ ዉሉ ላፈርስ ይገባል በማለት ሲሆን፣ አመልካቾች በበኩላቸዉ ዉሉ በህግ አግባብ የተደረገ በመሆኑ ላፈርስ አይገባም በማለት የሚከራከሩ መሆኑን ነዉ።
በመሰረቱ ዉል እንዲፈርስ ጥያቄ የሚያቀርብ ወገን ዉሉ ላፈርስ የሚችልበት በህግ ተቀባይነት ያለዉ ምክንያት ስለመኖሩ የማስረዳት ግድታ ያለበት ሲሆን የዉል ይፍረስልኝ ጥያቄ የሚቀርብለት ፍርድ ቤትም ለዉሉ መፍረስ በምክንያትነት የተጠቀሰዉ ሁኔታ ዉሉ እንዲፈርስ ለማድረግ በህግ ተቀባይነት ያለዉ እና በቂ ምክንያት መሆን አለመሆኑን ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸዉ የፍትሐብሕር ህጉ ድንጋጌዎች ጋር አገናዝቦ የማጣራት ግድታ እንዳለበት ይታወቃል። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት ተጠሪዎች ያቀረቡትን የዉል ይፍረስልኝ ጥያቄ በመቀበል ዉሉ እንዲፈርስ የመወሰኑን አግባብነት መመርመሩ ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል።
ከክሳቸዉ አጠቃላይ ይዘት መረዳት የሚቻለዉ ተጠሪዎች ለዉሉ መፍረስ የጠቀሱት መሰረታዊ ምክንያት ዉሉ በተደረገበት ወቅት ዉል ለማድረግ የሚያስችል ችሎታ የልላቸዉ መሆኑን ነዉ። የስር ፍርድ ቤትም ዉሉ እንዲፈርስ ሲል ለደረሰበት ድምዳሜ በመሰረታዊነት የጠቀሰዉ ምክንያት ይህኑን ስለመሆኑ ተመልክተናል። በርግጥ ህጋዊ ዉልን ለማቋቋም አስፈላጊ ከሆኑት ሁኔታዎች ዉስጥ አንዱ ዉሉ ዉል ለማዋዋል ችሎታ ባላቸዉ ሰዎች መካከል የተደረገ መሆኑ ስለመሆኑ በህጉ አንቀጽ 1678(ሀ) ተመልክቷል። አንድ ሰዉ ዉል መዋዋልን ጨምሮ ልሎች ህጋዉያን ተግባራትን (juridical acts) ለማከናወን ችሎታ የለዉም ማለት ስለሚቻልባቸዉ ሁኔታዎች የፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 2 ስለ ችሎታ በሚል ርዕስ ከአንቀጽ 192 ጀምሮ ባሉት አንቀፆቹ የሚደነግግ ሲሆን፤ ከአእምሮ ችግር ጋር በተያያዘ በህጉ አንቀጽ 339 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ስር ተመልክቷል። በዚህም መሰረት አንድ ዉል ከአእምሮ ጉድለት ጋር በተያያዘ ምክንያት ላፈርስ የሚችለዉ የአእምሮ ጉድለቱ በግልጽ የታወቀ ሲሆን (notorious insanity) ወይም በፍርድ ክልከላ (judicially interdicted) ሲደረግ ስለመሆኑ በህጉ አንቀጽ 347 (1) እና 372 ስር ከተመለከቱት ድንጋጌዎች መረዳት ይቻላል።
የተያዘዉን ጉዳይ በተመለከተ 1ኛ ተጠሪ በግልጽ የታወቀ የአእምሮ ጉድለት ያለበት ስለመሆኑ ወይም የአእምሮ ጉድለት ያለበት መሆኑ ታዉቆ በፍርድ ክልከላ የተደረገ ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ሕጉ አንቀጽ 339፣ 340 እና 351 ስር በተመለከቱት ድንጋጌዎች አግባብ የቀረበ ክርክርም ሆነ ማስረጃ የለም። በርግጥ ዉሉ በሚደረግበት ወቅት በነበረበት የአእምሮ ችግር (ህጉ “እብድ” በሚል ይገልፀዋል) የነበረበት በመሆኑ ምክንያት ጉድለት የልለበትን ፍቃድ ለመስጠት በማይችልበት ሁኔታ ላይ እንደነበረ ለማስረዳት ከቻለ ዉሉን ማስፈረስ የሚችል ስለመሆኑ በህጉ አንቀጽ 347(2) ስር ተመልክቷል። ይሁንና ይህ ድንጋጌ፣ የአእምሮ ችግሩ በግልጽ የታወቀ ካልሆነ በስተቀር ወይም በፍርድ ካልተከለከለ በስተቀር የአእምሮ ችግር መኖሩ መረጋገጡ ብቻዉን ዉልን ለማፍረስ ምክንያት እንደማይሆን በህጉ አንቀጽ 347(1) ስር ለተመለከተዉ ድንጋጌ ልዩ ሁኔታ (exception) በመሆኑ፣ በጠባቡ መተርጎም እንደሚገባዉ ይታመናል።
በመሆኑም ተዋዋዩ ዉሉን ያደረገዉ ነፃ ፍቃድ መስጠት በማይችልበት ሁኔታ ላይ መሆኑን በማስረዳት ዉሉ እንዲፈርስ መጠየቅ የሚቻለዉ ዉሉ በተደረገበት ወቅት ተዋዋዩ እብድ (የአእምሮ ችግር ያለበት) መሆኑን እና ዉሉም የተደረገዉ ተዋዋዩ በዚህ የአእምሮ ሁኔታ ዉስጥ ሆኖ ባለበት ወቅት ስለመሆኑ በማያጠራጥር አኳያ በማስረጃ ማረጋገጥን እንደሚጠይቅ ከፍ ሲል ከተመለከቱት ድንጋጌዎች አጠቃላይ ዓላማ እና መንፈስ መረዳት ይቻላል። ይሁንና 1ኛ ተጠሪን በተመለከተ በስር ፍርድ ቤት የቀረበ የህክምና ማስረጃ ግለሰቡ አእምሮን ላያጠቃ በሚችል በሽታ መያዛቸዉን እንጂ በርግጥም ዉሉ በተደረገበት ወቅት በህጉ አጠራር እብድ በመሆን አእምሮአቸዉን መቆጣጠር በማያስችል ደረጃ ላይ የነበሩ መሆናቸዉን አያሳይም።
ከፍ ሲል እንደተመለከተዉ ተጠሪዎች ዉሉ እንዲፈርስ በምክንያትነት ከጠቀሱት ዉስጥ አንዱ በዕድሜያቸዉ የገፉ ወይም የጃጁ መሆናቸዉን በመግለጽ ነዉ። በርግጥ መጃጀት ለዉል መፍረስ አንዱ ምክንያት ላሆን እንደሚችል በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 1710(2) ስር ተመልክቷል። ይሁንና መጃጀት ለዉል መፍረስ ምክንያት ላሆን የሚችለዉ ዉሉ ለአንደኛዉ ወገን የበለጠ ጥቅም የሚሰጥ ሆኖ ይህም ላሆን የቻለዉ የአንደኛዉን ወገን (የተጎጂዉን) መጃጀት ወይም በዕድሜ መግፋቱን መሰረት በማድረግ የተደረገ መሆኑ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ በህጉ አንቀጽ 1710 (1 እና 2) ስር ከተመለከቱት ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ መረዳት ይቻላል። በመሆኑም በዕድሜ መግፋትን ወይም መጃጀትን መሰረት በማድረግ ዉል እንዲፈርስ ጥያቄ የሚያቀርብ ወገን በዕድሜ መግፋቱ ወይም መጃጀቱ መኖሩን ብቻ ሳይሆን ዉሉም ለተከሳሽ የበለጠ ጥቅም በሚሰጥ መልኩ የተደረገ ስለመሆኑ ጭምር የማረጋገጥ ግድታ አለበት። ከዚህ አንፃር የተያዘዉን ጉዳይ ስንመለከት ተጠሪዎች ዉሉ አመልካቾችን በይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርግ ስለመሆኑ ለማሳየት ቤቱ 10,000,000.00 እንደሚያወጣ በክሳቸዉ ያመለከቱ ቢሆንም ይህ ግምት መሰረት የሚያደርገዉ ክሱ በተመሰረተበት ወቅት፣ በ2005 ዓ.ም፣ ያለዉን የቤቱን ዋጋ እንጂ ዉሉ በተደረገበት ወቅት በ1996 ዓ.ም የነበረዉን ዋጋ አለመሆኑን ከክሱ ይዘት መረዳት ይቻላል። በመሆኑም ዉሉ አመልካቾችን በይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርግ ስለመሆኑ ባላሳዩበት ሁኔታ የተጠሪዎችን መጃጀት ወይም በዕድሜ መግፋት ብቻ መሰረት በማድረግ ዉሉ እንዲፈርስ ተጠሪዎች ያቀረቡት ጥያቄም ተቀባይነት ያለዉ አይደለም።
በአጠቃላይ በግራ ቀኝ መካከል የተደረገዉ ዉል ላፈርስ የሚችልበትን እና በህግ ተቀባይነት ያለዉ ተጠሪዎች ምክንያት በማቅረብ ባላስረዱበት ሁኔታ ያዉም ዉሉ ዉልን ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠዉ አካል ማለትም በዉል እና ሰነዶች ማረጋገጫ የተደረገ ሆኖ እያለ፣ ዉሉ ተደርጎ ከ9 ዓመት በኋላ እንዲፈርስ ያቀረቡትን ክስ ተቀብሎ ዉሉ እንዲፈርስ በፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፀንቶ የተወሰነዉ ዉሳኔ ዉል ላፈርስ የሚችልበትን ሁኔታ በተመለከተ ከላይ በፍትሐብሕር ህጉ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ያላገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ብለናል። በመሆኑም ተከታዩ ተወስኗል።
የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.128919 በቀን 24/04/09 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት፣ የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 03/08/08 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት የሰተዉን ዉሳኔ በማጽናት፣ የሰጠዉ ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ዉል ላፈርስ የሚችልበት ህጋዊ ምክንያት የለም ብለናል።
በዚህ ችሎት በተደረገ ክርክር ምክንያት የወጣዉን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻሉ ብለናል።
እግድ ተነስቷል፤ይፃፍ።
No topics extracted.