አንድ ውል ሳይፈጸም በቀረ ጊዜ እንደውሉ አልተፈጸመልኝም የሚለው ተዋዋይ ወገን ሳይፈጸምልህ ቀርቷል በማለት ክርክር ለማቅረብ በቅድሚያ ውሉን ያልፈጸመው አካል ግድታውን እንዲፈጸምለት ለማድረግ አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ ላሰጠው የሚገባ ስለመሆኑና በዚህ መሰረት ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ወለድ የሚሰላበትን ጊዜ በመወሰን ረገድ ጠቀሜታ ያለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ህ/ቁ. 1772
No summary available.
ጥቅምት 29ቀን 2010 ዓ.ም.
ዳኞች- ዳኜ መላኩ ተፈሪ ገብሩ ቀነአ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራው ፀሃይ መንክር አመልካች- ኢትዮ ቴልኮም ጋምቤላ ሪጅን-ነ/ፈ ሰለሞን በንቲ ቀረቡ ተጠሪ- አዱራ ኮንስትራክሽን አነስተኛ እና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ-አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የጋምቤላ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ቅሬታ በማቅረቡ ሲሆን ክርክሩ የጀመረው የአሁን ተጠሪ በአመልካች ላይ በጋምቤላ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረበው ክስ ነው።
የክሱ ይዘት ባጭሩ አመልካች በጋምቤላ ከተማ 04 ቀበል ለሚያሰራው የኔትወርክ ታወር ማቆሚያ መሰረት ፎርም ዎርክ (Form work) ለማሰራት የግንባታ ውል ስምምነት ፈፅመን በገባነው ውልና በተሰጠን ትዕዛዝ መሰረት ግንባታውን ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ ርክክብ የተደረገ ቢሆንም ተከሳሽ በውላችን ከተስማማነው ክፍያ ውስጥ 70 በመቶ ከፍሎን ቀሪውን 30 በመቶ ክፍያ እንዲከፍለን ጥያቄ ብናቀርብም ለመክፈል ፈቃደኛ አይደለም። ስለሆነም ላከፍለን የሚገባውን ብር 284,471.03 ከህጋዊ ወለዱ ጋር እንዲከፈለን ይወሰንልን በማለት ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስ በመላ ጋምቤላ እና አካባቢዋ ለታወር ማቆሚያ ፎርም ወርክ ያስጠናው የዋጋ ተመን ለአንድ ሜትር ስኩዌር ነጠላ ዋጋ ብር 296.95 መሆኑን፤ ከውሉ ጋር በተያያዘ ቢል ኦፍ ኳንቲቲ ላይ ለኮንክሪት ሙላት ሥራ ተመን ለአንድ ሜትር ኩብ ነጠላ ዋጋ ብር 4112.11 የተቀመጠውን ዋጋ በስህተት ለታወር ማቆሚያ ፎርም ወርክ ብር 4112.11 እንዲሆን ተደርጎ በውሉ ላይ በመፃፉ ከተሰራው ስራ ዋጋ ውጪ ተሰልቶ የቀረበ የክፍያ ጥያቄ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም፤ በውሉ መሰረት የመጨረሻ ክፍያ የሚከፈለው አድ ሜጀርመንት (መሬት ላይ የተሰራ ስራ እየተለካ የሚከፈል) ሲሆን ከሳሾች የተሰራውን ሥራ እና ልኬት አስለክተው ማስረጃ ባላቀረቡበት ሁኔታ ቀሪ ክፍያ አልተከፈለንም በማለት ያቀረቡት ክስ ተገቢ አይደለም፤
በውሉም መሰረት ክፍያ የሚፈፀምላቸው ለተሰራው ሥራና ልኬት የሚገልፅ መረካከቢያ ሰነድ ተዘጋጅቶ ለተከሳሽ ሲቀርብ ሲሆን ይህን ሳያቀርቡ ክፍያ እና ወለድ መጠየቃቸው ከውሉ ውጪ ነው፤ በተሰራው ሥራ መያዣ የሚሆን የአንድ አመት ዋስታና እንደሚያዝ በውሉ አንቀጽ 52 ተመልክቶ እያለ በደፈናው ያቀረቡት ክስ ተቀባይነት የለውም፤ ከሳሽ የሰራው ሥራም በገለልተኛ ወገን ይታይልኝ በማለት ተከራክሯል።
ክርክሩ በዚህ መልኩ የቀረበለት የከፍተኛው ፍርድ ቤት ጉዳዩን መርምሮ ተከሳሽ ድርጅት ራሱ ባወጣው የዋጋ ተመን ብር 4112.11 የተዋዋለ በመሆኑና ውሉ በህግ የተመለከተው ሥርዓት ተጠብቆ የተደረገ በመሆኑ ተከሳሽ ከውሉ ውጪ በብር 296.95 እንዲከፈል ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት የለውም፤ ስራው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል ወይስ አልጀመረም? የሚለውን በተመለከተም ፍርድ ቤቱ ተጣርቶ ሪፖርት እንዲቀርብለት ያደረገ ሲሆን በሪፖርቱ ሙሉ በሙሉ እንደ ውሉ ሥራው ተጠናቆ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ የተረጋገጠ በመሆኑ ተከሳሽ አልተረከብኩም በማለት ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት የለውም፤ በልላ በኩል የሥራ ዋስትና መያዣውን በተመለከተ በውሉ አንቀጽ 52 መያዣ ወይም ጋራንቲ መተው እንዳለበት የተመለከተ በመሆኑ በዚህ ረገድ ተከሳሽ ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት ይኖረዋል በማለት በአጠቃላይ ተለክቶ ለቀረበው ዋጋውን ብር 233,498.99 ተከሳሽ ለከሳሽ እንዲከፍል፤ ከዚህ ገንዘብ ላይ የአንድ ዓመት ጋራንቲ ብር 15,792.82 እንዲቀነስ፤ እንዲሁም ቀሪውን ክፍያ መፈፀም ከነበረበት ዕለት አንስቶ የሚታሰብ 9% ወለድ እንዲከፈል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክርክራቸውን ከሰማ በኋላ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ አፅንቷል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ነው። አመልካች ጥቅምት 15/2009 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር ማመልከቻ ተጠሪ በገባው ውል መሰረት ግንባታውን አጠናቆ ባላስረከበበትና መረካከቢያ ሰነድ ቴክ ኦፍ ሽት (take off sheet) አዘጋጅቶ ባላቀረበበት ሁኔታ ቀሪ ክፍያ እንዲከፈለው መወሰኑ ውሉን ያላገናዘበ ነው፤ የሥር ፍርድ ቤት የባለሙያ ምስክርነት ሪፖርት ብቻ መሰረት በማድረግ የሰጠው ውሳኔ የህግ አግባብ የለውም፤
እንዲሁም ርክክብ ባልተደረገበት ሥራ ላይ ወለድ እንዲከፈል መወሰናቸው የህግ አግባብነት የለውም፤ ስለሆነም ውሳኔው ተሸሮ የተሰራው ሥራ ተለክቶና ርክክብ ተደርጎ በሚታወቀው መጠን እና ገለልተኛ ባለሙያ በጥልቀት አጥንቶ በሚያቀርበው መሰረት ተሰልቶ ቀሪ ክፍያ ካለ እንዲከፈል ተብሎ እንዲወሰን ጠይቋል።
ጉዳዩ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ እና ተጠሪ መልስ እንዲሰጥበት ታዞ ታህሳስ 25/2009 ዓ.ም በሰጠው መልስ አመልካች በውል የተመለከተውን አገልግሎት ማግኘቱ በተረጋገጠበት ሁኔታ፤ በውሉ ከተወሰነው እና አምኖ ሲከፍል ከቆየው መጠን በላይ ልላ ክፍያ ሳይጠየቅ በቂ ባልሆነ ምክንያት ላለመክፈል ሞክሮ በፍርድ ኃይል እንዲከፍል መደረጉ ተገቢ በመሆኑ ውሳኔው እንዲፀና በማለት ተከራክሯል። አመልካችም ክርክሩን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከፍሲል ባጭሩ የገለፅነው የክርክሩን አመጣጥና ግራ ቀኙ በሰበር ያደረጉትን ክርክር ሲሆን በበኩላችን በሥር ፍርድ ቤቶች በተሰጠው ውሳኔ የተፈፀመ የህግ ሥህተት መኖር አለመኖሩን መርምረናል።
ጉዳዩን እንደመረመርነው የሥር ፍርድ ቤት አከራካሪ የሆነው የግንባታ ስራ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል ወይስ አልጀመረም የሚለውን በተመለከተ በባለሙያ ተጣርቶ ሪፖርት እንዲቀርብለት በማድረግ ሙሉ በሙሉ እንደ ውሉ ሥራው ተጠናቆ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን በማረጋገጥ አመልካች በዚህ ረገድ ያቀረበውን ክርክር ውድቅ አድርጓል። የሥር ፍርድ ቤት እዚህ መደምደሚያ ላይ የደረሰው ፍሬ ጉዳዩን ለማጣራትና ማስረጃ ለመመርመርና ለመመዘን በህጉ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ነው።
በዚህ መልኩ የተደረሰበትን መደምደሚያ ይህ ፍርድ ቤት የሚቀበለው ይሆናል።
በልላም በኩል ከውሉ ጋር በተያያዘ ለኮንክሪት ሙላት ሥራ ተመን ለአንድ ሜትር ኩብ ነጠላ ዋጋ ብር 4112.11 የተቀመጠው ዋጋ በስህተት ለታወር ማቆሚያ ፎርም ወርክ እንዲሆን ተደርጎ በውሉ ላይ የተጻፈ በመሆኑ ዋጋው እንደገና ተሰልቶ ቀሪ ክፍያ ካለ እንዲከፈል እንዲደረግ አመልካች አጥብቆ የተከራከረ ቢሆንም ውሉ ጉድለት የልለበት መሆኑና አመልካችም ራሱ ባወጣው የዋጋ ተመን የተዋዋለ መሆኑ በሥር ፍርድ ቤቶች ተረጋግጦ ውሳኔ የተሰጠበት ከመሆኑም በላይ ግራቀኝ የተስማሙበት በውሉ የተመለከተ ዋጋ እያለ እንደገና ዋጋው እንዲተመን የሚደረግበት የህግ ምክንያት ባለመኖሩ በዚህም ረገድ በአመልካች የቀረበው ክርክር ተቀባይነት የለውም። በአጠቃላይ አመልካች በውሉ መሰረት ያልከፈለውን ቀሪ ክፍያ የተሰራው ሥራ ዋጋ 30% ለተጠሪዎች እንዲከፍል በተሰጠው ውሳኔ የተፈፀመ የህግ ስህተት የለም ብለናል።
በልላ በኩል ወለድን በተመለከተ የሥር ፍርድ ቤት ቀሪው ክፍያ መፈፀም ከነበረበት ዕለት አንስቶ የሚታሰብ 9% ወለድ እንዲከፈል የወሰነ ሲሆን አመልካች በሰበር ቅሬታው ርክክብ ባልተደረገበት ሥራ ላይ ወለድ እንዲከፈል መወሰኑ የህግ አግባብነት የለውም እንዲባል ጠይቋል። ተጠሪም በውሉ መሰረት አገልግሎት በማግኘታቸው እና ለመክፈልም ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በህጉ የተቀመጠውን ወለድ የማይከፍሉበት ምክንያት ስለልለ በዚህ ረገድ የቀረበው ቅሬታ ውድቅ እንዲደረግ ተከራክሯል። ባለዕዳው በውል ባይመለከት እንኳ ህጋዊውን 9% ወለድ እንዲከፍል የሚጠበቅ ቢሆንም ወለድ መታሰብ የሚኖርበትን ጊዜ በተመለከተ ቀሪው ክፍያ መፈፀም ከነበረበት ዕለት አንስቶ እንዲታሰብ መወሰኑ ህጉን የተከተለ ስለመሆኑ መርምረናል። በፍ/ብ/ህ/ቁ 1772 ሥር እንደተደነገገው እንደውሉ ሳይፈፀምልኝ ቀርቷል በማለት ክርክር ለማቅረብ የሚፈልገው አንደኛው ወገን ተዋዋይ የተዋዋለው ልላው አካል ግድታውን እንዲፈፅምለት ለማድረግ አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ ላሰጠው ይገባል። በዚህ መልኩ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱ ወለድ የሚሰላበትን ጊዜ በመወሰን ረገድ ጠቀሜታ ይኖረዋል። በተያዘው ጉዳይ ተጠሪ ማስጠንቀቂያ ስለመስጠቱ ወይም ማስጠንቀቂያ መስጠት የማያስፈልግ ስለመሆኑ በመግለፅ ያቀረበው ክርክር የለም። ይህ በሆነበት ሁኔታ ክፍያ መፈፀም ከነበረበት ዕለት አንስቶወለድ እንዲታሰብ የሚደረግበት የህግ ምክንያት አይኖርም። ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በዚህ ረገድ ላታረም ይገባል ብለናል። ተከታዩንም ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የጋምቤላ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰኔ 17 ቀን 2008 ዓ.ም ያሳለፈው ውሳኔ እንዲሁም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፍ/ይ/መ//08 መስከረም 1 ቀን 2009 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ተሻሽሐል።
ተለክቶ ለቀረበው የግንባታ ዋጋውን ብር 233,498.99 አመልካች ለተጠሪ እንዲከፍል፤
ከዚህ ገንዘብ ላይ የአንድ ዓመት ጋራንቲ ብር 15,792.82 እንዲቀነስ በተሰጠው ውሳኔ የተፈፀመ የህግ ስህተት ባለመኖሩ ይህ የውሳኔ ክፍል ፀንቷል።
ወለድ ክስ ከቀረበበት ከግንቦት 10 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ 9% ላከፈል ይገባል ብለናል።
አፈፃፀሙ ታግዶ እንዲቆይ በዚህ ፍርድ ቤት
No topics extracted.