አንድ የመሬት ሽያጭ ውል ህገ ወጥ ውል መሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ ገዥ ወገን በመሬቱ ላይ የሰራው ቤት በሻጭ ፈቃድ እንደተሰራ ተደርጎ የህግ ግምት የሚወሰድበት አግባብ የማይኖር ስለመሆኑ የኢፍድሪ ህ/መ አንቀፅ 40 (3) እና የፍ/ብ/ህ ቁጥር 1678 (ለ) እና 1716 141606 አቶ ማሞ ቱሉ እና አቶ አበበ አበራ መስከረም 25/2010 ዓ.ም III 5. የዕቃ ማጓጓዝ ውል በማጓጓዣ ሰነድ ወይም መሰል ሰነዶች ላረጋገጥ የሚችል ስለመሆኑ፣ በየብስ የዕቃ ማጓጓዝ ስራን ለመደንገግ ተሻሽሎ የወጣ አዋጅ ቁጥር 547/99 አንቀጽ 4፤8 130676 ጅቡቲ ድንበር ተሻጋሪ ደረጃ 3-ለ የደ/ጭ/ማ/ባ/ማህበር እና አቶ ሞላደርጎ ጥቅምት 27/2010 6. አንድ ሥራን ለመስራት የመተባበርና የመተጋገዝ ስምምነት ማድረግ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ስምምነት ነው ከሚባል በስተቀር አስገዳጅነት ያለው በሕግ ፊት ግድታን የሚፈጥር ውል አለ ለማለት የሚያስችል ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1678፤1731፤1771
No summary available.
ጥቅምት 27ቀን 2010 ዓ.ም.
ዳኞች- ዳኜ መላኩ ተፈሪ ገብሩ ቀነአ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራው ፀሃይ መንክር አመልካች- ጅቡቲ ድንበር ተሻጋሪ ደረጃ 3-ለ የደ/ጭ/ማ/ባ/ማህበር ጠ/ግርማ ስላሴ አርአያ ቀረቡ ተጠሪ- አቶ ሞላ ደርጎ ከደነው ጠበቃ /ሳሙኤል አስፋው ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ መጋቢት 6/2008 ዓ.ም ተሰጥቶ በፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ ሰኔ 23/2008 ዓ.ም የፀናውን ውሳኔ በመቃወም ሲሆን ክርክሩ የጀመረው የአሁን ተጠሪ በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ ነው።
የክሱ ይዘት፡- ከሳሽ ከተከሳሽ ጋር ባደረጉት ውል ንብረትነቱ የአረብ ኮንስትራክሽን የሆነ አንድ ኮንቴነር ከጅቡቲ ወደብ ወደ ይርጋ ጨፍ እንዲያጓጉዝላቸው በተስማሙት መሰረት ከሳሽ አጓጉዠ አስረክቤያለሁ፤ ተከሳሽ ይህን ያዘዘው በ16/04/07 ዓ.ም ሲሆን በቀን 29/05/07 ዓ.ም በርክክብ ሰነዱ ላይ ፈርሞ የክፍያ ቀጠሮ ሰጥቷል፤ ነገር ግን ክፍያ ለመፈፀም ፈቃደኛ ስላልሆነ ጭነቱ ለተጓጓዘበት ለ300 ኩንታል በብር 150.00 ሂሳብ ብር 450.00.00፣ ኮንቴነር መመለሻ ብር 8.000.00፤ እና ጭነት ለዘገየበት ዲመሬጅ ክፍያ ብር 20.400.00፤ በአጠቃላይ ብር 73,400.00 (ሰባ ሶስት ሺህ አራት መቶ) ከነወለዱ እንዲከፍል እንዲወሰን መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስ ከሳሽ ዕቃዎቹን ከጂቡቲ ወደብ ለማጓጓዝና የማጓጓዣውን ሰነድ (Way Bill) የተቀበለው ከአረብ ኮንትራክተር ኃ/የተ/የግ/ማህበር መሆኑን ሰነዱ ያስረዳል፤ ከሳሽ እቃዎቹን አጓጉዞ ያስረከበው ለዚሁ ድርጅት ነው፤
ስለሆነም ተከሳሽ የተጓጓዙትን ዕቃዎች ያልተረከበ በመሆኑ በንግድ ህጉ አንቀፅ 581 እና 582 መሰረት ተከሳሽን ለመጓጓዣው ላጠይቅ አይችልም፤ በተከሳሽ ትዕዛዝ ተሰጥቷል እንዲሁም ርክክቡም መፈፀሙን ያስረዳሉ ተብሎ የቀረቡት ሰነዶችም የማጓጓዣውን ሂሳብ እኔ የምከፍል ስለመሆኑም ሆነ ከከሳሽ ጋር ውል መግባቴን የሚያረጋግጡ አይደሉም በማለት ተከራክሯል።
ክርክሩ በዚህ መልኩ የቀረበለት የስር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃውን ከመረመረ በኋላ በከሳሽ በኩል የቀረቡት ምስክር ከሳሽ ከጂቡቲ ዕቃ ጭነው ይርጋጨፍ አጓጉዘው ያስረከቡት ከተከሳሽ ጋር ባላቸው ስምምነት መሆኑን፤ ስለማጓጓዙና ክፍያውን በተመለከተ የተነጋገሩትም ከተከሳሽ ጋር መሆኑን ማስረዳታቸውን እና ይህ ምስክርነት በተከሳሽ በኩል አለመስተባበሉን፤ በሰነድ ማስረጃነት የቀረቡት ሰነዶች ሲታዩም የጭነት ሰነዶችን የተረከበው ተከሳሽ መሆኑን፤ ተከሳሹ ከሳሽ አጓጉዘው ያስረከቡ መሆናቸውን ገልጾ ተከሳሽ ክፍያ ለመክፈል ቀጠሮ መስጠቱን የሚያስረዳ መሆኑን፤ በተለይ ክፍያ ለመክፈል የሰጠው ሰነድ የማጓጓዣ ውልን የሚተካ ደረሰኝ መሰል ነገር ላባል እንደሚችል፤ በአጠቃላይ ከሳሽ የመጓጓዣ ውል መኖሩን ለማስረዳት ስለቻሉ ፍርድ ቤቱ በግራ ቀኙ መካከል የመጓጓዣ ውል አለ የሚል መደምደሚያ ላይ መድረሱን በመግለፅ ተከሳሽ ገንዘቡን ከነወለዱ ለከሳሽ እንዲከፍል ወስኗል።
በዚህ ውሳኔ ላይ ይግባኙ የቀረበለት የከፍተኛው ፍርድ ቤት በበኩሉ ክርክራቸውን ሰምቶ የቀረቡት ሰነዶች እና የሰው ማስረጃዎች እንዲሁም ክርክሩ የሚያሳየው ተጠሪ የማጓጓዝ ውል ያላቸው ከአመልካች ጋር መሆኑን ነው፤ ይህ ከሆነ ደግሞ አመልካች በአሰራር አስጫኙ ክፍያ ሲከፍለን ብቻ ነው ለተጠሪ የምንከፍለው በማለት ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት የለውም፤ ተጠሪ ውል ያላቸው ከአመልካች ጋር በመሆኑ አረብ ኮንትራክተርስ ከፈለም አልከፈለም ተጠሪን የሚመለከት አይደለም፤ እንዲሁም አመልካች ተጠሪን ወክሎ ገንዘብ ለመቀበል ሳይሆን ሰነዱን የተቀበለው እራሱ ለመክፈል ስለሆነ ተጠሪ ያጓጓዘበትን ክፍያ ይክፈል ተብሎ የተሰጠው ውሳኔ በአግባቡ ነው በማለት የሥር ፍርድ ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ አፅንቷል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ነው። አመልካች ሀምል 18/2008 ዓ.ም ባቀረበው የሰበር ማመልከቻ ተመርምሮ ጉዳዩ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ እና ተጠሪ መልስ እንዲሰጡበት ተደርጓል። በዚህ መሰረት ግራ ቀኙ የስር ክርክራቸውን በማጠናከር በፅሁፍ ተለዋውጠዋል።
ከፍ ሲል ባጭሩ የገለፅነው የጉዳዩን አመጣጥ ሲሆን በበኩላችን ቅሬታ በቀረበበት ውሳኔ የተፈፀመ የህግ ሥህተት መኖር አለመኖሩን መርምረናል። እንደመረመርነው ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ ከአመልካች ጋር ባደረጉት ስምምነት መሰረት ንብረትነቱ የአረብ ኮንስትራክሽን የሆነ ዕቃ ከጅቡቲ ይርጋ ጨፍ አጓጉዘው ማስረከባቸውንና ተጠሪም በርክክብ ሰነዱ ላይ ፈርሞ ገንዘቡን ለመክፈል የክፍያ ቀጠሮ መስጠቱን ገልፀው ገንዘቡ እንዲከፈላቸው የጠየቁ ሲሆን አመልካች በበኩሉ የማጓጓዣ ውል አለማድረጉን፤ ተጠሪ የማጓጓዣውን ሰነድ የተቀበለው ከአረብ ኮንትራክተር መሆኑንና እቃዎቹም ተጓጉዘውለት የተረከበው ይኸው ድርጅት መሆኑን በመግለፅ ላጠየቅ እንደማይገባ ተከራክሯል።
ግራ ቀኙ በተጠቀሰው መልኩ ያቀረቡትን ክርክር በቅድሚያ የመረመረው የሥር ፍርድ ቤት የተለያዩበትን ፍሬ ነገር በማስረጃ በማጣራት የጭነት ሰነዶችን የተረከበው አመልካች መሆኑን፤ አመልካች ተጠሪ አጓጉዘው ያስረከቡ መሆናቸውን ገልጾ ክፍያ ለመክፈል ቀጠሮ መስጠቱ በሰነድ ማስረጃ መረጋገጡን፤ ክፍያ ለመክፈል የሰጠው ሰነድ የማጓጓዣ ውልን የሚተካ ደረሰኝ ላባል እንደሚችል፤ በዚህም ምክንያት በግራ ቀኙ መካከል የመጓጓዣ ውል መኖሩ መረጋገጡን ወስኗል። ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም አመልካች አጓጓዥ እንጂ አረብ ኮንስትራክሽንን ወክሎ ስራ የሚሰራ ወይም ትራንዚተር አለመሆኑን በማረጋገጥ የሥር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አፅንቷል።
ከክርክሩ መገንዘብ እንደሚቻለው ተጠሪ ውል ስለመደረጉ በማስረጃነት ያቀረቡት የሰነድ ማስረጃ የጭነት ማጓጓዣ ሰነዱን እና አመልካች ክፍያ ለመክፈል ቀጠሮ መስጠቱን ለማስረዳት የቀረበውን ነው። በየብስ የዕቃ ማጓጓዝ ስራን ለመደንገግ ተሻሽሎ የወጣው አዋጅ ቁጥር 547/99 በንግድ ሕግ አማካኝነት በ1952 ዓ.ም ወጥቶ በሥራ ላይ ያለውን ሕግ በተለይም የአጓጓዦችን የኃላፊነት መሰረት፣የኃላፊነት መጠንወሰንና ልሎች መብቶችና ግድታዎችን አስመልክቶ ዓለም ዓቀፍ ይዘት ካለውና ወጥ የሆነና የተቀላጠፈ አግልግሎት መስጠት በሚያስችል መልኩ አሻሽሎ መደንገግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ተሻሽሎ መደንገጉን በአዋጁ መግቢያ ከተመለከተው መገንዘብ ይቻላል።
በዚህ መልኩ ተሻሽሎ በወጣው አዋጅ ቁጥር 547/99 በአንቀጽ 4 ሥር እንደተመለከተው የእቃ ማጓጓዝ ውል የሚረጋገጠው በማጓጓዣ ሰነድ መሆኑን፤ ነገር ግን ይህ ሰነድ አለመኖሩን ወይም ያልተሟላ መሆኑ ወይም መጥፋቱ ዕቃዎችን ለማጓጓዝ የተደረገውን ውል ዋጋ አልባ ላያደርገው እንደማይችልና ላያስቀረው እንደማይችል የሚደነግግ ሲሆን በአዋጁ አንቀፅ 8 ሥር እንደተመለከተው ደግሞ ላኪው እና አጓጓዡ ከተስማሙ የማጓጓዣው ሰነድ አጓጓዡ በሚሰጠውና ላኪው ተገቢ የሆኑትን ፅሁፎች በሚያሰፍርበት እንደ ደረሰኝ ባሉ ሰነዶች ላተካ እንደሚችል ይደነግጋል።
ስለሆነም የእቃ ማጓጓዝ ውል በማጓጓዣ ሰነድ ወይም መሰል ሰነዶች ላረጋገጥ እንደሚችል ከተሻሻለው የአዋጁ ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል።
በተያዘው ጉዳይ ፍሬ ነገሩን የማጣራት ሥልጣን በህጉ የተሰጣቸው የሥር ፍርድ ቤቶች በግራ ቀኙ የቀረበውን ክርክር እና ማስረጃ ተመልክተው ከፍ ሲል እንደተገለፀው የጭነት ሰነዶችን የተረከበው አመልካች መሆኑን፤ አመልካች ተጠሪ አጓጉዘው ያስረከቡ መሆናቸውን ገልጾ ክፍያ ለመክፈል ቀጠሮ መስጠቱን፤ እንዲሁም አመልካች አጓጓዥ እንጂ አረብ ኮንስትራክሽንን ወክሎ ስራ የሚሰራ ወይም ትራንዚተር አለመሆኑ አረጋግጠዋል። ይህ በማስረጃ የተረጋገጠው ፍሬ ነገር ከፍ ሲል ከተጠቀሰው የህጉ ግልፅ ድንጋጌ አንፃር ተገናዝቦ ሲታይ የሥር ፍርድ ቤቶች በግራ ቀኙ መካከል የመጓጓዣ ውል አለ የሚል መደምደሚያ ላይ በመድረስ አመልካች ገንዘቡን ከነወለዱ ለተጠሪ እንዲከፍል መወሰናቸው ህጉን የተከተለ ነው ከሚባል በቀር ውሳኔው የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው የሚባል ሆኖ አላገኘነውም። ስለሆነምተከታዩንወስነናል።
በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ መጋቢት 6/2008 ዓ.ም ተሰጥቶ በፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ ሰኔ 23/2008 ዓ.ም የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችሎት ስለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሳራ ይቻቻሉ።
ሰ/ጌ የሰ.መ.
መስከረም 23/2010 ዓ.ም ዳኞች 1. ዳኜ መላኩ 2. ረታ ቶለሳ 3. ተኸላት ይመስል 4. ቀነዓ ቂጣታ 5. ፀሐይ መንክር አመልካች……… አቶ ገ/እግዚአብሕር ገ/ክርስቶስ ከጠበቃ አቶ ዝናቡ ይርጋ ጋር ቀረበዋል።
ተጠሪ ……………… አቶ ሐረጎት ገ/እግዚአብሕር ቀረበዋል።
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር ጉዳይ ቤት ለመስራት የወጣውን የጉልበት ዋጋና የገንዘብ ወጪ ለማስከፈል የቀረበ ክስን መነሻ ያደረገ ሲሆን፣ ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ላቀርብ የቻለው የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ በ11/2/2008 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልኝ በማለት የአሁን አመልካች ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ መርምሮ ለመወሰን ነው።
የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ በናዕድር ዓድት ወረዳ ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪ ከሳሽ፣ የአሁን አመልካች ተከሳሽ ሁኖ ሲከራከሩ ነበር። ከሳሽ ባቀረበው ክስ ከሳሽ እና ተከሳሽ በ1995 ዓ.ም በጹሑፍ በተደረገ ውል ተከሳሽ በሰመማ ከተማ በስሙ በተሰጠው ቦታ እኔ እንዳሰራው እና ለእኔም እንደሚሰራ ተስማምተን፣ በዚህ መሰረት አጥር እና ሁለት ክፍል ቤት በብር 80,000.00 /ሰማኒያ ሺህ/ የሚገመት ሰርቼ የእኔን አሰራኝ ስለው እምቤ ስላለ የጉልበቴን ዋጋ እና ለሰራሁት ግንብ ለሚሆኑት ዕቃዎች ዋጋ ድርሻዬን ብር 40,000 እንዲከፍለኝ በማለት ከሷል። ተከሳሽ የጽሁፍ መልስ ባለማቅረቡ ታልፏል። ግራ ቀኛቸው በቃል ባደረጉት ክርክር ከሳሽ ሁለት ክፍል ቤት እና አጥር የስራሁበትን ገንዘብ እንዲከፍለኝ በማለት ሲጠይቅ፣ ተከሳሽ ደግሞ ከሳሽ የስራው ቤት የለም፣ የ1995 ዓ.ም አሁን ላጠይቀኝ አይችልም በማለት ተከራክሯል።
ከዚህ በኋላ ፍ/ቤቱ የከሳሽን የሰው ምስክሮች በመስማት በሰጠው ውሳኔ ከሳሽ እና ተከሳሽ ተባብረው ለሰሩት ሁለት ክፍል ቤት ተከሳሽ ለከሳሽ ብር 40,000 / አርባ ሺህ/ እንዲከፍለው በማለት ወስኗል። የሥር ተከሳሽ በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለማዕከላዊ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት አክሱም ምድብ ችሎት እና የሰበር አቤቱታ ለትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የቀረበ ቢሆንም ቅሬታው ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቶ የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ ጸንቷል። አሁን የቀረበው የሰበር አቤቱታ ይህን ትዕዛዝ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአሁን አመልካች በ27/3/2008 ዓ.ም የተጻፈ ሶስት ገጽ አቤቱታ አቅርቧል።
የአቤቱታው ይዘት በአጭሩ፡- የአሁን ተጠሪ በውሉ መሰረት ቤት ተሰርቷል ያለው በ1995 ዓ.ም ሲሆን ገንዘብ እንዲከፈለው የጠየቀው 10 ዓመት ካለፈው በኋለ ስለሆነ ክሱ በይርጋ የሚቋረጥ ነው። በዚህ ጉዳይ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት የወረዳ ፍ/ቤት የተዘጋው መዝገብ ይከፈት አይከፈት የሚለውን በተመለከተ ግራ ቀኛቸውን አከራክሮ እንዲወስን መልሶለት እያለ ይህን ሳያደርግ የሰጠው ውሳኔ የሕግ ስህተት ስለሆነ እንዲታረምልኝ፤ ተጠሪ ባቀረበው ክስ በመካከላችን ያለው የመተጋገዝ ውል እንዳለ የገለጸ ሲሆን ይህ ደግሞ ስምምነት እንጂ በሕግ ፊት አሰገዳጅነት ውጤት ያለው ውል አይደለም፣ ተጠሪ የጽሑፍ ውል አለ እያለ ስለሆነ በዚህ አግባብ ማስረዳት ሲገባው የሰው ምስክሮች ብቻ በመስማት የተጠየቀው 40,000 መኖሩን አግባብነት ባለው ማስረጃ ሳያስረዳ የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲሻርልኝ ወጪና ኪሳራ እንዲከፈለኝ በማለት አመልክቷል።
ይህ ችሎት አቤቱታው ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዲያቀርብ በታዘዘው መሰረት ጥር 16 ቀን 2008 ዓ.ም የተጻፈ አራት ገጽ መልስ አቅርቧል። የመልሱም ይዘት በአጭሩ፡- የአሁን አመልካች ቀርበው መልስ እንዲሰጡ መጥሪያ ቢላክላቸውም እምቢ አልቀበልም ማለታቸው በምስክሮች የተረጋገጠ ስለሆነ ጉዳዩን እንዳመኑበት የሚያስቆጥር ነው። የሥር ፍ/ቤት በአመልካች በኩል የቀረበውን የይርጋ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ የሰጠው ውሳኔ በአግባቡ ነው። መዝገብ ማስከፈት በተመለከተ የይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በመለሰለት መሰረት የወረዳው ፍ/ቤት እንደገና አጣርቶ የአሁን አመልካች በቀጠሮ ቀን ያልቀረቡት በበቂ ምክንያት እንዳልሆነ አይቶ የሰጠው ውሳኔ አግባብነት ያለው ነው። በአመልካች እና ተጠሪ መካከል ያለው ውል የመተጋገዝ ውል ሳይሆን ሁለታችን በቤቱ ላይ ያለን መብት የሚያስረዳ ስለሆነ የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ አግባብነት ያለው ነው። ተጠሪ ውል ስለመኖሩ በሰው ምስክሮች ያስረዳ ሲሆን አመልካች ውል መኖሩን ስላልካደ፣ ተጠሪ ውል በጽሑፍ አላስረዳም በማለት ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት የለውም የሥር ውሳኔ አግባብነት ያለው ስለሆነ እንዲጸናልኝ ወጪና ኪሳራ እንዲወሰንልኝ በማለት በዝርዝር ተከራክሯል። የአሁን አመልካች የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርቧል። ይህ ችሎት ለትክክለኛ ፍርድ አሰጣጥ ይረዳ ዘንድ የሥር መዝገብ የመ. አስቀርቦ ከዚህ መዝገብ ጋር ተያይዟል እንዲሁም ግራ ቀኛቸውን በቃል ሰምቷቸዋል።
የጉዳዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተው ሲሆን ይህ ችሎት የግራ ቀኛቸውን ክርክር አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል። እንደመረመርነው በዚህ ጉዳይ እልባት ማግኘት ያለበት በአመልካች እና ተጠሪ መካከል በሕግ ፊት ግድታን የሚፈጥር ውል አለ ወይስ የለም? የሚለው ነጥብ እንደሆነ ተገንዝበናል።
በዚህ መሰረት ተዋዋይ ወገኖች ውልን በሚያደርጉበት ጊዜ በሕጉ የተመለከተውን የውል አመስራረት ሥርዓት ተከትሎ መሆን እንዳለበት የሚያከራክር አይደለም። የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1678 ሥር እንደተመለከተው በሕግ ፊት የሚጸና ውል ለማቋቋም መሟላት ያለባቸው ሁኔታዎች ተዘርዝሮ እናገኛለን። ከእነዚህ መሰረታዊ ሁኔታዎች መካከል አንዱ ውል መደረግ ያለበት “በቂ የሆነ እርግጠኛነት ያለው የሚቻልና ሕጋዊ የሆነ ጉዳይ” በተመለከተ መሆን እንዳለበት ነው። ተዋዋይ ወገኖች በሕግ የተመለከቱትን አስገዳጅ የሕግ ድንጋጌዎች በጠበቀ መልክ እና ፈቃጅ የሆኑ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ በመሰላቸው ተነጻጻሪ መብትና ግድታ በማስቀመጥ መዋዋል እንደሚችሉ ይታመናል።
ተዋዋይ ወገኖች በዚህ አግባብ ያቋቋሙት ውል ያንን ጉዳይ በተመለከተ በመካከላቸው ሕግ እንደሆነ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1731 ድንጋጌ የሚያስገናዝበው ጉዳይ ነው። ይህ ከሆነ ተዋዋይ ወገኖች በውሉ በተፈጠረው መብት ተጠቃሚ የሚሆኑበት እና በግድታው ደግሞ የሚገደዱበት ሁኔታ ይፈጠራል ማለት ነው። በዚህ ውል መሻነትም ግድታውን የተወጣው ወገን ልላኛው ወገን ደግሞ ግድታውን እንዲወጣ የመጠየቅ መብት እንደሚሰጠው ግልጽ ነው። በዚህ አግባብ አሁን ወደ ተያዘው ጉዳይ ስንመለሰ የአሁን ተጠሪ ባቀረበው ክስ የአሁን አመልካች ቤቴን አስራኝ የአንተን ደግሞ አሰራአለሁ ብሎ በራሱ ይዞታ ላይ በሰማኒያ ሺህ ብር ቤት ሰርተን በውሉ መሰረት የእኔን ቤት አሰራኝ ቢለው እምቢ ስላለ የጉልበቴን ዋጋ እና ለስራሁት ግንብ የሚሆነውን ዕቃዎች ዋጋ እንዲከፍለኝ የሚል ነው። ከዚህ ክስ መገንዘብ እንደሚቻለው ተጠሪ እና አመልካች አንዱ የልላውን ቤት ለመስራት ለመተጋገዝ ያደረጉት ውል እንደሆነ ያሳያል። የአሁን ተጠሪ ባቀረበው የዳኝነት ጥያቄ አመልካች በዚህ አግባብ ስላልሰራልኝ ገንዘብ እንዲከፍለኝ የሚል ነው። ተጠሪው የጉልበቱን ዋጋ እና ዕቃዎቹን በምን አግባብ ገምቶ እንዳቀረበ የሚያመለክት ነገር መኖሩን የሥር ውሳኔ የሚያመለክተው ነገር የለም።
በዚህ ረገድ የአሁን አመልካች የቀረበው የጽሁፍ መልስ ባይኖርም በቃል ባቀረበው ክርክር ከሳሽን ያሰራሁት ቤት የለም ያቀረበው ክስ በይርጋ የሚታገድ ነው የሚል ነው።
ይህ ማለት አመልካች ውል መኖሩን የካደ መሆኑን ያመለክታል። በወረዳው ፍ/ቤት የተሰሙት የሰው ምስክሮች በሰጡት የምስክርነት ቃል 1ኛ ምስክር አመልካች እና ተጠሪ ሚያዚያ ወር 1995 ዓ.ም ሁለት ክፍል ቤት አብረው በአመልካች ይዞታ ለይ እንደሰሩ፣ 2ኛ ምስክር በ1995 ዓ.ም ተጠሪ በአመልካች ይዞታ ላይ ሁለት ክፍል ቤት እንደሰራ፣ 3ኛ ምስክር በ1995 ዓ.ም በሰመማ ከተማ በአመልካች ቦታ ላይ አመልካች እና ተጠሪ ሁለት ክፍል ቤት እንደሰሩ ተጠሪ ገንዘቤን አካፍለኝ ሲለው እምቢ እንዳለው መመስከራቸውን የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ ያሳያል። ከእነዚህ የምስክሮች ቃል መገንዘብ እንደሚቻለው ተጠሪ ለሰራው ሥራ የጉልበት ዋጋ በስንት ብር እንደተስማሙ፣ ምን ምን ዕቃዎችን ለቤቱ ግንባታ እንዳቀረበ እና ግምታቸው ምን ያህል እንደሆነ የመሰከሩት ነገር የለም። የወረዳው ፍ/ቤት የግራ ቀኛቸውን ክርክር እና የምስክሮች ቃል መነሻ በማድረግ በደረሰበት ድምዳሜ በአመልካችና በተጠሪ መካከል በትብብር ቤት የመስራት ስምምነት እንዳለ ማረጋገጡን አመልክቷል። የአሁን ተጠሪ በዚህ ችሎት በቃል ባቀረበው ክርክር ከአመልካች ጋር ተባብረው ቤት ለመስራት እንደተስማሙ የአመልካች ቤት ከሰሩ በኋላ አመልካች የተጠሪን ለመስራት ፈቃደኛ ባለመሆኑ፣ የጉልበቱን ዋጋ እና ያቀረባቸውን ዕቃዎች ዋጋ እንደጠየቀ ገልጾ ተከራክሯል። አመልካች በበኩሉ ተጠሪ እንደሚለው አብረን ቤት ለመስራት በቃልም ሆነ በጽሑፍ ያደረግነው ስምምነት የለም፣ ቤቱን በገንዘቤ የሰራሁት እኔ ራሴ ነኝ ተጠሪ በሰራተኝነት ለስራው ሥራ በአካባቢ ዋጋ ተከፍሎታል በማለት ተከራክሯል።
ከዚህ ሁሉ መገንዘብ እንደሚቻለው በአመልካች እና ተጠሪ መካከል አንዱ ቤት ሲሰራ ልላው ላያግዘው እንደዚሁም ልለው ቤት ሲሰራ መጀመሪያ የተሰራለት ሰው አብረው ላሰራ እና ላያግዘው መስማማታቸውን በዚህ ረገድ የመተባባርና የመተጋገዝ ስምምነት ማድረጋቸውን ያመለክታል። ይህ የመተጋገዝ ወይም የመተባበር ስምምነት በአካባቢው ልማድ ተቀባይነት ያለው ቢሆንም ከሕግ አንጻር ግን አንዱ ወገን ልላውን ወገን ግድታውን አልፈጸመልኝም እና እንዲፈጽምልኝ በማለት ለማስገደድ የሚያስችል አይደለም። አንዱ ወገን በዚህ በመተባበር ስምምነት መሰረት ሥራው ተሰርቶለት ልላውን ያለገዘ እንደሆነ ምናልባት በአካባቢው ልማድ የሚያመጣው ትጽእኖ ላኖር ቢችልም ይህ ስምምነት ከሕግ አንጻር የግራ ቀኛቸዉን ተነጻጻሪ መብትና ግድታ የፈጠረ ነው እና አንዱ ወገን ልላውን ወገን እንደውሉ እንዲፈጽምልኝ በማለት የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1771 በሚደነግገው አግባብ ለመጠየቅ የሚያስችለው የሕግ መሰረት የለም። ይህ ማለት በግራ ቀኛቸው መካከል የተደረገው የመተባበር የመተጋገዝ ስምምነት በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ነው ከሚባል በስተቀር አስገዳጅነት ያለው በሕግ ፊት ግድታን የሚፈጥር ውል አለ ለማለት የሚያስችል ሁኔታ የለም። ከዚህም በላይ የአሁን ተጠሪ የጉልበት ዋጋ በስንት ብር እንደተስማሙ እና ያቀረባቸው ዕቃዎች ምን እንደሆኑ እና ግምታቸው በማስረጃ ማረጋገጡን የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ የሚያመለክተው ነገር የለም። ይህ በሆነበት ሁኔታ የአሁን ተጠሪ እንደውሉ ገንዘብ እንዲከፍለኝ በማለት አመልካችን ለመጠየቅ የሚያስችለው የሕግ አግባብ አላገኘነውም።
ሲጠቃለል የሥር ፍ/ቤቶች በግራ ቀኛቸው መካከል የመተባበርና የመተጋገዝ ስምምነት እንጂ ግድታን የሚፈጥር ውል በልለበት ተጠሪ ደግሞ የጉልበት ዋጋ በስንት ብር እንደተስማሙ እና ያቀረባቸው ዕቃዎች ዓይነት እና ግምት በማስረጃ ባላረጋገጠበት ያቀረበውን ክስ ውድቅ ማድረግ ሲገባቸው ክሱን በመቀበል አመልካች ብር 40,000 / አርባ ሺህ/ እንዲከፍል መወሰናቸው ከላይ የተመለከቱትን የውል ሕግ ድንጋጌዎችን ያላገናዘብ ስለሆነ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ የሚከተለው ተወስኗል።
የናዕድር ዓድት ወረዳ ፍ/ቤት በመ. በ1/10/2007 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና ይህን ውሳኔ በማጽናት የማዕከላዊ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት አክሱም ምድብ ችሎት በመ.ቁ. 20724 በ5/12/2007 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ እና የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ. 78992 በ11/2/2008 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመባቸው ስለሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
በተጠሪ እና በአመልካች መካከል የነበረው ስምምነት በመተጋገዝና በመተባበር ቤት ከመስራት ውጭ በሕግ ፊት መብትና ግድታን የሚፈጥር ውል ስላልሆነ አመልካች ለተጠሪ ብር 40,000 / አርባ ሺህ/ ለመክፈል የሚገደድበት የሕግ አግባብ የለም ብለናል።
የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
ግራ ቀኛቸው በዚህ ችሎት የደረሰባቸውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻሉ።
የመ.ቁ. 02823 ለናዕድር ዓድት ወረዳ ፍ/ቤት ይመለስ።
No topics extracted.