የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች ውልን የሚመለከቱ ጉዳዮች በግልግል ዳኝነት (አርቢትሬተር) እንዳይዳኙ የተጣለው ገደብ ወይም ክልከላ ገላጋይ ዳኛ (አድጁዲኬተር) ጋር በተያያዘም ተፈጻሚነት ያላቸው ስለመሆኑ፡የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 315/2/፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1678/ለ፣3131 እና 3132/ለ/
No summary available.
መስከረም 23 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡- ዳኜ መላኩ ረታ ቶሎሳ ተኽላት ይመሰል ቀነአ ቂጣታ አብዬ ካሳሁን አመልካች፡- ጣና የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮና ኢንዱስትሪ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር
ጉዳዩ የቀረበው የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመዝገብ የካቲት 22 ቀን 2008 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ላታረምልኝ ይገባል በማለት አመልካች ሚያዚያ 26 ቀን 2008 ዓ.ም የተጻፈ 06 ገጽ የሰበር አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
በዚህ መዝገብ የተያዘው ጉዳይ የአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎች በአድጁዲኬሽን የሙግት መፍቻ ዘድ መዳኘት የሚችሉ መሆን አለመሆናቸውን የሚመለከት ነው።
ለጉዳዩ መነሻ ምክንያት የሆነው አመልካች ለተጠሪ 12 ውሃ ጉድጓድና 2 የውሃ ጉድጓድ መቆጣጠሪያ ለመገንባት፤ ተጠሪ ደግሞ ብር 59,922,705 /ሃምሳ ዘጠኝ ሚላዮን ዘጠኝ መቶ ሃያ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ አምስት ብር/ ለመክፈል ስምምነት አድርገው እንደነበር በመግለፅ በተጠሪ ጥፋት የተነሳ ሥራው በስምምነቱ መሰረት ላፈፀም ባለመቻሉ የውል ጊዜው ለተጨማሪ ስድስት ወራት እንዲራዘም፤ የዋጋ ለውጥ እንዲደረግ፤ ካሳና ወለድ ተጠሪ ለአመልካች እንዲከፍል በመጠየቅ የቀረበ ክስ ነበር።
ተጠሪም በበኩላቸው ጥፋት አለመኖሩን፤ችግሩ የተፈጠረው በአመልካች የቴክኒክ ብቃት ችግር መሆኑን በመጥቀስ የካሳ ክፍያም ሆነ የጊዜ ማራዘሚያ ጥያቄው ተቀባይነት የልለው በመሆኑ ክሱ ውድቅ እንዲሆን መልስ አቅርቧል።
ግራቀኙ ወገኖች አስቀድሞ ባደረጉት ውል አንቀጽ 24 መሰረት በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት የተመደበው አድጁዲኬተር ጉዳዩን እንዲዳኝ ተደርጎ በሰጠው ውሳኔ ስለጉዳዩ ተገቢውን ማጣራት ሲያደርግ ቆይቶ አመልካች በጠየቁት መሰረት የሥራ ማጠናቀቂያ ጊዜ በስድስት ወራት እንዲራዘም፤ተጠሪ ቅድመ ክፍያ ላዘገየበት ወለድ እንዲከፍሉ በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
ተጠሪው በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባቀረበው ይግባኝ በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገው ውል የአስተዳደር መስሪያ ቤት ውል መሆኑን ጠቅሶ የአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎችን በሚመለከቱ አለመግባባቶች የግልግል አካል ዳኝነት መስጠት እንዳይችል በህግ ክልከላ የተደረገ በመሆኑ በተያዘው ጉዳይ አድጁድኬተር ጉዳዩን ያየው ስልጣን ሳይኖረው ነው የሚልና ልሎች ዝርዝር የቅሬታ ነጥቦችን በማቅረባቸው ፍርድ ቤቱ ቅሬታው መልስ ሰጭን ያስቀርባል በማለት ግራ ቀኙን አከራከሮ ሲያበቃ በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገው ውል የአስተዳደር ውል ነው። የአስተዳደር ውሎች በግልግል ዳኝነት ላታዩ የማይገባቸው ለመሆናቸው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 315(2) ደንግጓል። ስለሆነም አድጁዲኬተር ጉዳዩን ያያው በህግ በተከለከለ ጉዳይ ላይ በተደረገው ውል መነሻነት በመሆኑ ሥልጣን ሳይኖረው ነው በማለት የአድጁዲኬተሩን ውሳኔ ሽሮታል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህንን ዳኝነት ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ የቀረበው የሥር ፍርድ ቤቶች ዳኝነት መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈፅሞበታል በሚል ሲሆን አቤቱታው በአጭሩ፡- አድጁዲኬሽን በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ዓለም አለመግባባቶችን ለመፍታት ጠቃሚ የሆነና ከግልግል ዳኝነት የተለየ የአለመግባባት መፍቻ መንገድ ሆኖ እያለ የፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አድጁዲኬሽንን ከግልግል ዳኝነት ጋር በማመሳሰል የተያዘውን ጉዳይ አድጁዲኬተር ማየት አይችልም በማለት መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ውሳኔ ነው የሚሉና ልሎችንም የቅሬታ ነጥቦች አጠቃሎ የያዘ ነው።
ሰበር አጣሪ ችሎቱም መዝገቡን መርምሮ በግራቀኙ ተከራካሪዎች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት በውላቸው አንቀጽ 24 መሰረት በአድጁዲኬተር መታየቱ ያላግባብ ነው ተብሎ የተወሰነበትን አግባብ ለማጣራት አቤቱታው ለሰበር ያስቀርባል በማለቱ ተጠሪ መልስ አቅርበዋል። አመልካችም የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ክርክሩ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ተጠናቋል። እኛም አቤቱታው ለሰበር ያስቀርባል ከተባለበት ነጥብ አንጻር ጉዳዩን እንደሚከተለው መርምረናል። እንደመረመርነውም አድጁዲኬተር (ገላጋይ ዳኛ) የአስተዳደር ውልን በተመለከተ የሚነሱ ክርክሮችን ለመዳኘት ይችላል ወይስ አይችልም? የሚለው ጭብጥ ምላሽ ማግኘት ያለበት መሆኑን ተገንዝበናል።
ከመዝገብ ምርመራው መገንዘብ እንደተቻለው በአመልካችና በተጠሪ መካከል እ.አ.አ አፕሪል 06 ቀን 2013 የተደረገ ውል ለመኖሩ በግራቀኙ ወገኖች የተካደ ጉዳይ አይደለም። በዚሁ ውል አንቀጽ 24 ሥር አለመግባባቶች የሚፈቱበትን አግባብ በተመለከተ አስቀድሞ በአድጁዲኬተር ወይም በገላጋይ ዳኛ ላታይ እንደሚገባው፤ይህ ገላጋይ ዳኛም በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ላመደብ የሚገባው መሆኑን እንዲሁም በገላጋይ ዳኛው ውሳኔ የቅሬታ አቀራረብ ሥርዓት ምን ላሆን እንደሚገባ ጭምር ስምምነት ተደርጓል።
ተጠሪ ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ሲሆን ለክርክሩ መነሻ የሆነው የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮም ለህዝብ ጥቅም ለመስጠጥ የታሰበ በመሆኑ ውሉ ለህዝብ ጥቅም የተደረገ ውል መሆኑ የሚያከራክር አይደለም። በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 3132(ለ) ሥር እንደተመለከተው ከህዝብ አግልግሎት ሥራ ጋር የተያያዙና ለውሉ አፈፃፀምም የተዋዋዩን የድሬዳዋ ውሃና ፍሳሸ ባለስልጣን ያልተቋረጠ ተካፋይነት የሚጠይቅ በመሆኑ ውሉ የአስተዳደር መስሪያ ቤት ውል ነው። ስለሆነም ተጠሪው ከአመልካች ጋር ያደረጉት ውል አስተዳደር መስሪያ ቤት ውል ነው መባሉ የሚነቀፍበት መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም።
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 315(2) ሥር በግልፅ እንደተመለከተው የአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎችን በግልግል ዳኝነት እንዳይታዩ ህግ ክልከላ አድርጓል። በተያዘው ጉዳይ አለመግባባትን ለመዳኘት በውል ሥልጣን የተሰጠው አድጁዲኬተር ወይም ገላጋይ ዳኛ ሲሆን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህጉ አንቀጽ 315(2) የአስተዳደር ውልን አስመልክቶ የሚነሳ አለመግባባትን ለመዳኘት የማይችለው የግልግል ዳኝነት አካል ወይም አርቢትሬተር ነው። እዚህ ላይ ላነሳ የሚገባው ዋናው ነጥብ የአድጁዲኬተር እና የአርቢትሬተር አንድነትና ልዩነታቸው ምንድን ነው አርቢትሬተር የአስተዳደር ውሎችን እንዳይዳኝ በህግ ክልከላ ከተደረገበት ዓላማ አንፃር አድጁዲኬተር የአስተዳደር ውሎችን እንዲዳኝ ላፈቀድለት ይገባል ወይ? ከዚህ አንፃር አመልካችና ተጠሪ ስለአለመግባባት አፈታት በውላቸው አንቀጽ 24 ያደረጉት ስምምነት በህግ ተቀባይነት ያለው ነው ማለት ይቻላል ወይ? የሚሉት ነጥቦች ናቸው።
በመሰረቱ አለመግባባቶችን ለመፍታት ከመደበኛ ፍርድ ቤቶች ውጭ የሆኑ የተለያዩ አማራጭ የሙግት መፍቻ ሥርዓቶች እንዳሉ የሚታወቅ ነው። ከእነዚህ አማራጭ የሙግት መፍቻ ስልቶች ውስጥ በአገራችን የሥነ ሥርዓት ህግ ዕውቅና ያገኙት ድርድር፤እርቅ፤ግልግል እና ስምምነት ሲሆኑ አድጁዲኬሽ ወይም ጉዳዩን በገላጋይ ዳኛ የመፍታት አሰራር በብዙ የዓለም ሀገሮች የሚሰራበት ከመሆኑም በላይ በንግዱ ህብረተሰብ መካከል የሚፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በኩል ደንብ ወጥቶለት እየተሰራበት ይገኛል።
አለመግባባት የተፈጠረበትን ጉዳይ መርምሮ ውሳኔ የመስጠት ሂደት አድጁዲኬሽን እንደሚባል የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ባወጣው ደንብ አንቀጽ 2 ሥር የተመለከተ ሲሆን ግልግል በግራቀኙ ወገኖች መካከል የሚፈፀም ውል ሲሆን ውሉን መሰረት በማድረግ የግልግል ዳኛ የሚሰጠው ውሳኔ አስገዳጅ ውጤት እንዳለው ከፍትሐብሕር ህግ አንቀጽ 3325 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች የምንገነዘበው ነው። ስለ ሁለቱ የሙግት መፍቻ ሥርዓቶች አንድነት ስንመለከት ውሳኔው አስገዳጅነት ያለው መሆኑ እና ከመደበኛ ፍርድ ቤቶች ውጭ በሆነ ሁኔታ አለመግባባት የሚፈታባቸው መሆኑ የሚያከራክር አይደለም።
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/አንቀጽ 315(2) ድንጋጌ በግልግል የዳኝነት ሥርዓት የአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎች ላዳኙ እንደማይገባ የደነገገበት አግባብ ፍትህ ከአማራጭ የሙግት መፍቻ የሚገኝ መሆኑን በመዘንጋት ሳይሆን የአስተዳደር ውሎች ጉዳይ የህግ የበላይነትን መርህ በአደረገው መደበኛ ፍርድ ቤት መታየቱ በውሎቹ ላደረስበት የታሰበውን ዓላማ ለማሳካት እንደሚያስችል ታምኖበት የተወሰደ የመንግስት ፖላሲ አማራጭ እንደሆነ መገንዘብ ተገቢ ነው። አማራጭ የሙግት መፍቻ መንገዶች የራሳቸው የሆነ ጠቀሜታ ያላቸው የመሆኑን ያህል የጎንዮሽ ጉዳትም ላኖራቸው እንደሚችል መገንዘብ ይገባል። በተለይም በአገራችን ሥርዓት ተበጅቶላቸው በጠነከረ አኳኋን የሚመሩ የመንግስትንና ህዝብን ጥቅም ላያስጠብቁ የሚችሉ የተሟላ ኃላፊነትና ተጠያቂነት የተሰጣቸው አማራጭ ሙግት መፍቻ ተቋማት ከአለመጠናከራቸው አንፃር የአስተዳደር ውሎች በግልግል ዳኝነት አካል እንዳይታዩ ህግ አውጭው አካል ለመምረጡ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/አንቀጽ 315 ይዘት መገንዘብ የሚቻል ነው።
የአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎች በግልግል ዳኝነት ላታዩ የማይገቡ ስለመሆኑ በህግ ከተመለከተና ዓላማውም የህግ የበላይነትን ለማስከበር ህግ አውጭው ለአስተዳደር ውሎች ዳኝነት የመረጠው ስለመሆኑ ግንዛቤ ከተወሰደ አድጁዲኬተር ማለትም የአርቢትሬተር ዓይነት አስገዳጅ ውሳኔ የሚሰጥ አካል የአስተዳደር ውሎችን እንዲዳኝ የሚያስችሉ ስምምነቶች የህግ ውጤታቸው ምን ይሆናል? የሚለውን ጥያቄ ምላሽ መስጠት ይጠይቃል። አርቢትሬተር የአስተዳደር ውሎችን በተመለከተ መዳኘት የማይችል ከሆነ አድጁዲኬተር ከሚሰጠው የዳኝነት ባህሪ አንፃር የአስተዳደር ውሎችን ላዳኝ የሚችል አይሆንም። ምክንያቱም አድጁዲኬተርም ሆነ አርቢትሬተር አስገዳጅ ውሳኔ የሚሰጡ አማራጭ የሙግት መፍቻ አካላት ስለሆኑ ነው።
ወደተያዘው ጉዳይ ስንመለስ አድጁዲኬተር ከአርቢትሬተር የተለየ አማራጭ የሙግት መፍቻ ተቋም ተደርጎ ላወሰድ ስለማይችል የሥር ፍርድ ቤቱ በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገ ውል የአስተዳደር መስሪያ ቤት ውል በመሆኑ በገላጋይ ዳኛ እንዲታይ ህጉ አይፈቅድም ሲል የደረሰበት ድምዳሜ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 315(2)ን፤የፍትሐ ብሕር ህጉን አንቀጽ 1678(ለ) 3131፤3132(ለ) ያገናዘበ በመሆኑ የሚነቀፍበት መሰረታዊ የህግ ስህተት አልተገኘም።
ለማጠቃለል ለሰበር አቤቱታው መቅረብ ምክንያት የሆነውን ዳኝነት የሰጠው ገላጋይ ዳኛ በተያዘው ጉዳይ ላይ የመወሰን ስልጣን የልለው ነው። ገላጋይ ዳኛ ሥልጣን አልነበረውም የሚል ድምዳሜ ላይ ከተደረሰ በአመልካች በኩል የሚቀርቡ ልሎች የቅሬታ ነጥቦችን በጭብጥነት ይዞ መወሰን ተገቢ አይሆንም። ስለሆነም ተከታዩን ወስነናል።
የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሲሚ ችሎት በመዝገብ የካቲት 22 ቀን 2008 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ባለመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ፀንቷል።
የአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎችን አስመልክቶ የሚነሳ አለመግባባትን አይቶ ለመወሰን ገላጋይ ዳኛ (Adjudicator) ሥልጣን የለውም በማለት ወስነናል።
በዚህ ችሎት ክርክር ለወጣ ወጭና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ።
No topics extracted.