በፍርድ ባለመብት አማካኝነት የተፈረደን ፍርድ ለማስፈጸም የቀረበው የአፈጻጸም የክስ ማመልከቻ ይፈጸም የተባለውን ፍርድ ብቻ መሰረት ላያደርግ የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 378 ልዩ ልዩ
No summary available.
ቀን ታህሳስ 21/2008ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ ፈይሳ ወርቁ አመልካች፡- የኢት/ያ ገ/ጉ/ባለስልጣን ሚል ቅ/ጽ/ቤት -ዓ/ሕግ መለስ ማእከል ተጠሪ፡- ፉአድ ደኑር ሁሴን -ወኪል ጠይብ አህመድ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን፤ መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዳይ በግራቀኙ መካከል በፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ ምክንያት ያቀረቡትን ክርክር የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ አመራርም ሆነ በጉዳዩ ላይ የሚሰጠው ዳኝነት አፈጻጸም ፍርድን መሰረት ላያደርግ እንደሚገባ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች ጋር አገናዝቦ ተገቢውን ዳኝነት ለመስጠት በሚል ነው።
የአሁን ተጠሪ በአሁን አመልካች ላይ ያቀረበው የአፈጻጸም ክስ በአፋር ብ/ክ/መንግስት የአውሲረሱ ከፍተኛ ፍ/ቤት በፍ/መ/ቁ. 4043 ታህሳስ 28ቀን 2006ዓ.ም የተሰጠውን ውሳኔ ለማስፈጸም እንደሆነ ግራቀኙን ያከራከረ ጉዳይ አይደለም።
በዚህም ውሳኔ የአሁን ተጠሪን ባለመብት፤ የአሁን አመልካችን ባለዕዳ ለማድረግ የሚያስችለው በዚሁ በፍ/መ/ቁ. 4043 ታህሳስ 28ቀን 2006ዓ.ም የተሰጠው የፍርድ ክፍል የአሁን ተጠሪ ወደ አገር ውስጥ እንዲያስገባቸው ፈቃድ አግኝቶ በዲክላራሲዮን ለተዘረዘሩት 9አይነት እቃዎች 5አይነት እቃዎች ካርታ ከተፈቀደ እቃዎች ውጭ በመሆናቸው ወደ ሃገር ውስጥ ላገቡ የሚችሉ አይደለም። ስለሆነም አሁን አመልካች በህግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ተጠቅሞ ተገቢ የሆነውን አስተዳደራዊ ውሳኔ እንዲሰጥ ይህንን የማይፈጽም ከሆነ ደግሞ ቀደም ሲል ለእቃዎቹ ከተከፈለው ቀረጥና ታክስ 5% ተቀጥቶ እቃዎች ወደ መጡበት ሃገር እንዲመለሱ የአሁን ተጠሪ በዲክላራሲዮኑ መሰረት ያስገባቸው በዲክላራሲዮኑ የተዘረዘሩት ህጋዊ እቃዎች ደግሞ ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገቡ በሚል የተሰጠው ውሳኔ ነው።
ይህ ውሳኔ እስከ ፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ደርሶ ያልተለወጠ ስለመሆኑም ግራቀኙ የተማመኑበት ጉዳይ ነው።
እንግዲህ ለዚህ ሰበር መነሻ ለሆነው በአፈጻጸም መ/ቁ. 4043 ለሆነው የአፈጻጸም ጉዳይ ምክንያት የሆነው ይህንኑ ከላይ የተመለከተውን ፍርድ ለማፈጸም እስከሆነ ድረስ በዚሁ ፍርድ የፍርድ ባለመብት የሆነው የአሁን ተጠሪ የፍርድ ባለእዳ ሆኖ በተሰየመው በአሁን አመልካች ላይ ላያቀርብ የሚገባው የፍርድ ማስፈጸሚያ አቤቱታ ይዘት ይህንኑ ከላይ የተጠቀሰውን ፍርድ ለማስፈጸም የፍርዱን ይዘት በአፈጻጸም ማመልከቻው ላይ በመግለጽና የፍርዱንም ግልባጭ በማስረጃነት በማያያዝ ላሆን እንደሚገባው የአፈጻጸም ክስ አዘጋጀጀት እና የአፈጻጸም ክስ ጉዳይ አጀማመርን አስመልቶ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 378 የተመለከተው ድንጋጌ አስረጂ ነው።
ይሁን እንጂ በአፈጻ/መ/ቁ. 4043 ተሰይሞ ለቀረበው የአፈጻጸም ጉዳይ መነሻ ይሆን ዘንድ የአሁን ተጠሪ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 378 በሚያዘው መሰረት ታህሳስ 04ቀን 2006ዓ.ም በተጻፈ የአፈጻጸም ክስ ማመልከቻ ያቀረበው የአፈጻጸም ክስ አቤቱታ ይዘት ወይም ፍሬ ቃሉ በአፈጻጸም ክሱ ምክንያት የሆነውን ፍርድ ይዘት የሚጠቅስ፤ በማስረጃነትም ይህንኑ የፍርድ ግልባጭ አባሪ በማድረግ መሆን ሲገባው በዚሁ ታህሳስ 04ቀን 2006ዓ.ም በተጻፈው የአፈጻጸም የክስ ማመልከቻ የተገለጸው ከፍርዱ ውጭ በፍርድ ያልተካተተውን ሁሉ በመጨመር <<በስህተት ወደ አገር ውስጥ ለገቡት እቃዎች የተከፈለው 5% ቀረጥና ታክስ የፍርድ ባለመብት ተቀጥቶ እቃዎቹ ወደመጡበት አገር እንዲመለሱ እንዲሁም የአሁን አመልካች በሰጠው ፈቃድ (declaration) መሰረት ቀሪ ህጋዊ እቃዎችን ወደ ሃገር ውስጥ እንዲያስገባ የተወሰነልን ቢሆንም በስህተት ወደ ሃገር ውስጥ የገቡት እቃዎች በተከሳሽ እምቢተኛነት በአፋጣኝ ወደ መጡበት ሃገር ባለመመለሳቸው። በፍርድ ባለዕዳ እጅ የሚገኙት እቃዎች የተበላሹ በመሆኑ የወቅቱ የእቃዎች ዋጋ ተገምቶ ገንዘቡን እንዲከፍል ይታዘዝልኝ>> በማለት የቀረበ ስለመሆኑ ተገንዝበናል።
በፍርድ ባለመብት አማካኝነት የተፈረደን ፍርድ ለማስፈጸም የቀረበው የአፈጻጸም የክስ ማመልከቻ ይፈጸም የተባለውን ፍርድ መሰረት ላያደርግ እንደሚገባ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 378 ተደንግጓል።
ስለሆነም ይኸው ፍርዱን መሰረት ያላደረገ የአፈጻጸም ማመልከቻ መቅረቡን እንደተረዳ የአፈጻጸም ችሎቱ የፍርድ ባለእዳን ከመጥራቱ በፊት ይህንኑ አግባብነት ያለውን ድንጋጌ መሰረት ያደረገ የአፈጻጸም ማመልከቻ ተስተካክሎ እንዲቀርብ ማድረግ ይገባው ነበር።
ይህም ታልፎ የአሁን አመልካች በፍርድ ባለእዳነቱ መልስ እንዲሰጥ እንደተጣራ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 386 እንደተመለከተው እቃዎቹ ያልተበላሹ፣ እንዲሁም እቃዎች ወደ መጡበት ሃገር አንዲመልሱ እንጂ በፍርድ ባለመብት እንዲወሰዱ በሚል ባልተወሰነበት ሁኔታ የእቃዎችን ግምት መጠየቃቸው ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ማሰባቸውን የሚያመለክት ነው የሚለውን ሁሉ ጨምሮ መልሱን በይዘቱ የአፈጻጸም ማመልከቻው ፍርዱን መሰረት ያደረገ ስላልሆነ እንደጥያቄው እንዲፈጸም አልገደድም በማለት መልሱን የሰጠ መሆኑንም የስር ፍ/ቤቱ እንደተረዳ የአፈጻጸም ማመልከቻውን፤ ለማመልከቻው በፍርድ ባለእዳው የተሰጠውን መልስ፣ በአፈጻጸሙ ጉዳይ ምክንያት ከሆነው በመ/ቁ. 4043 ታህሳስ 28ቀን 2006ዓ.ም ከተሰጠው የፍርድ ይዘት ጋር በማገናዘብ ክርክሩ በደረሰበት ደረጃም ቢሆን የፍርድ ባለመብት በአፈጻጸም ችሎቱ እገዛ እንዲፈጸምላቸው በክስ ማመልከቻው ያቀረቡት ዝርዝር እና የጠየቁት ዳኝነት ለፍርዱ አፈጻጸም መነሻ የሆነውን ፍርድ ምርኩዝ ያላደረገ መሆኑን ገልጾ ዳኝነት መስጠት ሲገባው ከፍርዱ አድማስ ውጭ በመውጣት እቃዎች ተበላሽተው የተገኙ ከሆነ የፍርድ ባለእዳ በምትኩ የእቃዎችን ግምት ዋጋ ላከፍል ይገባል በሚል በአማራጭ ፍርድ ያረፈበት በማስመሰል አሁን የአሁን አመልካች የእቃዎችን ግምት ዋጋ ብር 4,732,278.64 /አራት ሚላዮን ሰባት መቶ ሰላሳ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሰባ ስምንት ከ64%/ እና በዚሁ የገንዘብ ግምት ልክ 10% የጠበቃ አበል የአሁን አመልካች ለአሁን ተጠሪ ላከፍል ይገባል በማለት የሰጠው ውሳኔ ስለፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ አመራር ከተዘረጉት ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 378,386,391 አንጻር ሲታይ ህጋዊ መሰረት ያለው ዳኝነት ሆኖ አላገኘነውም።
ምናልባት የአሁን ተጠሪ በመ/ቁ. 4043 ታህሳስ 28ቀን 2006ዓ.ም በተወሰነበት ውሳኔ መሰረት እቃዎችን ወደመጡበት ሃገር ለማስመለስ በፍርድ አፈጻጸም ችሎት እገዛ ጥያቄ አቅርቦ እንደፍርዱ ለማስፈጸም ጥረት ሲደረግ ወደ መጡበት ሃገር ይመለሱ የተባሉት እቃዎች ተበላሽተዋል ካለ፤ የፍርድ ባለእዳም ለአፈጻጸም ክሱ በሰጠው መልስ ላይ አልተበላሹም በማለቱ እቃዎች ተበላሽተዋል ወይስ አልተበላሹም? የሚለውን ጭብጥ የስር ፍ/ቤት በአፈጻጸም ጉዳዩ እንደሰጠው ዳኝነት እቃዎችን በማስፈተሽ እምቢተኛ እስከሆነ ድረስ እቃዎቹ እንደተበላሹ ይቆጠራሉ እንኳ ቢባል እቃዎቹ ተበላሽተው የተገኙ እንደሆነ የሚለውን ታሳቢ በማድረግ አማራጭ ክስ ያልቀረበበት፤ በዋናው ፍርድም እቃዎቹ ተበላሽተው የተገኙ እንደሆነ የአሁን አመልካች የእቃዎችን ዋጋ ግምት እንዲከፍል ይገደዳል በሚል ፍርድ ያላረፈበት በመሆኑ ፍርድ ያላረፈበትን ጉዳይ በአፈጻጸም ክስ አስታኮ በአፈጻጸም ጉዳይ ላይ እንደአዲስ ፍርድ ለመስጠት የሚያስችል የህግ መሰረት የለም።
ለአፈጻጸሙ መነሻ የሆነው ፍርድ ከተሰጠ በኋላ ለአሁን አመልካች እንደፍርዱ እቃዎችን ወደ መጣበት ሃገር እንዲመለሱ ለማድረግ እምቢተኛ በመሆኑ የተነሳ እቃዎቹ ተበላሽተው ከሆነ ይኸው ስህተት የአሁን አመልካች ከህግ ወይም ከውል በመነጨ ለመክሰስ የሚያስችል ግድታ ያለበት ከሆነ እራሱን ከቻለ ክስ የክስ ምክንያት ላሆን ከሚቻል በቀር ከቶውንም ቢሆን እንደአሁን ተጠሪ አቀራረብ በፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ ለመወሰን የሚቻል አይደለም።
በዚህ ሁሉ ምክንያት የአሁን ተጠሪ ታህሳስ 04 ቀን 2006ዓ.ም አዘጋጅቶ በቀረበው የአፈጻጸም የክስ ማመልከቻ መሰረት የስር ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈጻጸምን የጉዳይ ሂደት ለፍርድ አፈጻጸም አንኳር እና መሰረት የሆነውን አፈጻጸም እንደፍርዱ ላፈጸም እንደሚገባ በፍርድ አፈጻጸም ስርዓት የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ጥሰው ለአፈጻጸም ክሱ መነሻ ከሆነው ፍርድ ይዘት በመውጣት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
በአፋር ብ/ክ/መንግስት የአውሲረሱ ከፍተኛ ፍ/ቤት በአፈ/መ/ቁ. 4043 መጋቢት 12ቀን 2007ዓ.ም የሰጠው ፍርድ፤ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በአፈጻጸሙ 4,732,278.64 /አራት ሚላዮን ሰባት መቶ ሺህ ሰላሳ ሁለት ሺ ሁለት መቶ ከሰባ ስምንት ከ64%/ ሳንቲም እና በዚሁ ልክ የጠበቃ አበል 10% ጨምሮ በድምሩ ብር 5,205,504.00 /አምስት ሚላዮን ሁለት መቶ አምስት ሺህ አምስት መቶ አራት ብር/ የመክፈል ግድታ ስለመሆኑ ለተጠሪ እንዲከፍል አይገደድም ብለናል።
ወደ መጡበት ሃገር ይመለሱ የተባሉት እቃዎች በመበላሸታቸው ምክንያት እንደፍርዱ ለመፈጸም የሚቻል አይደለም ከሚል መነሻ የአሁን ተጠሪ መብቱን በማረጋገጥ ረገድ ወደ ፊት ክስ የሚያቀርብ ቢሆን ይህ ፍርድ የሚያግደው አይሆንም ብለናል።
በዚሁ የሰበር ጉዳይ ምክንያት ግራቀኙ ባደረጉት ክርክር ላስከተለው ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻሉ።
No topics extracted.