በአፈጻጸም ወቅት አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት በሐራጅ ተሸጦ ከእዳ መክፈያ /ከግራ ቀኙ/ ይካፈሉ በተባለበት ጊዜ የሐራጅ ማስታወቂያ የፍ/ባለመብትን ጥቅም ላይ በቀጥታ ጉዳት እስካላደረሰ ወይም ወ/ሮ ሃዋ ጆሬ ተወካይ ታጅጂሆ እና አቶ አብዲ ቀንጨራ XXI መሆኑ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ የሐራጅ ማስታወቂያው ተገቢ ለሆነ ቀን በአየር ላይ አልዋለም ወይም በጨረታው ለሚሳተፉ ሰዎች በቂ ጊዜ አልተሰጠም የሚባልበት ሁኔታ አለመኖሩ፣ የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. አንቀጽ 445
No summary available.
ቀን 08/04/2008 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ ፈይሳ ወርቁ አመልካች፡- ወ/ሮ ሀዋ ጀሬ ተወካይ ታጁ ጀሬ ተጠሪ፡- አቶ አብዲ ቀንጨራ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ሰጥተናል
ጉዳዩ አፈጻጸምን የሚመለከት ሲሆን ቀደም ሲል በአመልካች እና ተጠሪ መካከል የነበረውን የባልና ሚስት ክርክር ተከትሎ የተሰጠውን የፍቺ እና የንብረት ክፍፍል ውሳኔ መሰረት በማድረግ ተጠሪ በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ሞያል ወ/ፍ/ቤት የንብረት ከፍፍል ውሳኔን ለማስፈጸም የአፈጻጸም አቤቱታ አቅርበው የአፈጻጸም መዝገብ አስከፈተዋለው። የአፈጻጸም ችሎቱ የቤቱን ደርሻ ክፍፍል በተመለከተ ግራ ቀኙ ስላልተሰማሙ ቤቱ በግልጽ ጨረታ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ በሚፈቅድው መሰረት ተገቢው ማስታወቂያ ተደርጎ በጨረታ ተሸጦ እኩል እንዲካፈሉ ትዕዛዝ ሰጥቷል። የጨረታውን ውጤት ለመጠባበቅ በተያዘው ቀጠሮ በቀን 21/01/2007 ዓ/ም ጨረታውን እንዲያስፈጽም የታዘዘው የከተማው አስተዳደር መሐንዲስ ፍ/ቤት በአካል ቀርቦ ለጨረታ በተሰጠው ጊዜ ውስጥ ብዙ ተወዳዳሪዎች ስላልቀረቡ እና በስህተት የጨረታ መነሻ ዋጋ ስላላወጣን ልላ ቀጠሮ ይሰጠን በማለት ለአፈጻጸም ችሎቱ ሲያመለከት ችሎቱ የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 140,500 (አንድ መቶ አርባ አምስት መቶ ብር) ሆኖ ግልጽ ጨረታ በማወጣት ለ10 ቀን ማስታወቂያ አየር ላይ አቆይቶ ቤቱን በጨረታ በመሸጥ ውጤቱ በቀን 21/01/2007 ዓ/ም እንዲቀርብ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ቤቱ በጨረታ በብር 210,000 (ሁለት መቶ አስር ሺህ ብር) አሸናፊ ለሆኑት አቶ መሐመድ ጀሎ መሸጡን የጨረታ ኮሚቴም በቀን 16/3/07 ዓ/ም በተጻፈ ቃለ ጉባኤ ለፍ/ቤቱ አስታወቋል። በቃለ ጉባኤው ላይ የአሁኑ አመልካችን ጨምሮ 3 ተወዳዳሪዎች ቀርበው አቶ መሐመድ ጀሎ በብር 210,000 ያሸነፉ መሆኑ የተመለከት ሲሆን ተጠሪ ደርሻቸውን ብር 105,000 በማመልከቻ ላይ ፈርሞ መወሰዱን እና የአሁኑ አመልካች ድርሻ ገንዘባቸው ልሎች እኩል ተከፈሉ የተባሉ ዕቃዎች ግምት እስከከፈለኝ ድረስ ይህን ገንዘብ አልወሰደም ማለታቸው ስር ፍ/ቤት ውሳኔ ላይ ተመልከቷል። ቤቱን በጨረታ በአሸናፊው አቶ መሐመድ ጀሎ ስም እንዲዛወር ችሎቱ ተዕዛዝ ሰጥቷል።
አመልካች (የስር የአፈጻጸም ከሳሽ) በዚህ አፈጻጸም ላይ ያላቸውን ቅሬታ ለማሳረም ለቦረና ዞን ከፍ/ፍ/ቤት አቅርበው ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን ካከራካረ በኋላ የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ አጽንቷል።
አመልካች አቤቱታቸውን ለኦሮሚያ ክልል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት አቅርበው የስር ፍ/ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት አይደለም በማለት አቤቱታውን አልተቀበለውም።
አመልካች በስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ላይ ቅሬታቸውን በመዘርዘር አቤቱታ አቅርበዋል የአቤቱታው ይዘት በጨረታው ለማስተፍ ለስር ፍ/ቤት አመልካች ፍ/ቤቱ ፈቅደልኝ ተሳትፈያላው የሞያል ወ/ፍ/ቤት የጨረታ ማስታወቂያ ካወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አንድ ወር ድረስ ቆይቶ የጨረታው ሽያጭ እንዲካሄድ ማዘዝ ሲገባው ለ10 ቀን ብቻ አየር ላይ ማሲታወቂያው እንዲቆይ የሰጠው ትእዛዝ ከፍ/ብ/ስ/ስ/ቁ.426 ውሳኔ ነው አመልካች ከጨረታ መነሻ ዋጋ ላይ በመጨመር 300,000 ብር ግምት የተጠሪን ድርሻ ብር 150,000 ካፍዬ ቤቱን እንዳሰቀር ለሐራጀ ሻጩ የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ከማወጣቱ በፊት አስቀደሜ አስወቄው እያለ ያለ ምንም የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ በጨረታ ተወዳዳሮ ለአሸነፈው ሰው በብር 210,000 መሸጡ የጨረታ ሽያጭ ሂደቱ ስነ ስርዓቱን ያልተከተለ እና የተጭበረበረ በመሆኑ መብቴን የሚጎዳ ነው። የተጠሪን ድርሻ ብር 150,000 ከፍዬ ብር 300,000 ግምት ቤቱን ለማስቀርት ጨረታው ይፍረስልኝ ብዬ ያቀረብኩትን መቃወሚያ ያለበቂ ምክንያት ውድቅ ማድረጉ ተገቢ አይደለም የሚል ነው።
የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ የማይነቀሳቀስ ንብረት የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ለ30 ቀናት አየር ላይ እንዲቆ መደረግ እንዳለበት በፍ/ብ/ስ/ስ/ቁ.426 አስገዳጅ ደንጋጌ እያለ የስር ፍ/ቤት ማስታወቂያው ለ 10 ቀን አየር ላይ እንዲቆይ ማደረጉ ተገቢ መሆን አለመሆኑን ለማጣራት ተጠሪ መልስ እንዲሰጡበት ተደርጓል።
የተጠሪ መልስ ይዘት የቤቱ የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ከአንድ ወር በላይ አየር ላይ ቆይቷል።
አመልካች በጨረታው ለመወዳደር ያቀረበችው ብር 150,000 ብቻ ነው የሚል ሲሆን አመልካች በመልስ መልሳቸው አመልካች ብር 150,000 በጨረታው ላይ የጠቀሰኩት የተጠሪን ድርሻ እንጂ ሙሉውን የጨረታ ዋጋ አይደለም። የመጀመሪያው ጨረታ ማስታወቂያ የቆየው ለ15 ቀን ሲሆን የሞያል ከተማ መሀንዲስ ተለዋጭ ትእዛዝ እንዲሰጠው ለስር ፍ/ቤት በጠየቀው መሰረት የጨረታ ማስታወቂያው ለ10 ቀን አየር ላይ እንደወል ትእዛዝ የሰጠ መሆኑን የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ላይ ተመልክቷል በማለት ተከራከረዋል።
የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው የሰር ፍ/ቤቶች ውሳኔ እና ትእዛዝ ጋር በማገናዘብ የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ እንዲጣራ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር የስር ፍ/ቤት ውሳኔ እና ትእዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን መርምረናል።
እንደመረመርነውም ለክርክር ምክንያት በሆነው የቤት ሽያጭ ጨረታ ላይ አመልካች ፍ/ቤቱን አስፈቅደው በጨረታው የተሳተፉ ሲሆን በጨረታው ከተሳተፉ ተጨርቶች መካከል አቶ መሐመድ ጅሎ የተባሉ ተጨራች በብር 210,000 ጨረታውን ያሸነፉ መሆኑን እና አመልካቿ በጨረታው ሲሰተፉ ቤቱን በጨረታ ለመግዛት የገለጹት ዋጋ ብር 300,000 ሳይሆን ብር 150,000 ብር ነው ብር 150,000 የጠቀሱት የተጠረን ድርሻ እንደሆነ በመልስ መልሳቸው የገለጹ ቢሆንም በእርግጥም ቤቱን በ300,000 ብር በጨረታ አሸንፈው የተጠሪን ድርሻ ብር 150,000 ለመከፈል አሰበው ቢሆን በጨረታው ለመወዳደር መጥቀሰ የነበረባቸው ብር እንጂ 150,000 ባለመሆኑ በዚህ ረገድ ያነሱት መከራከሪያ ተቀባይነት ያለው አይደለም። የአፈጻጸም ሂደቱ በተካሄደበት የስር ፍ/ቤት ከጨረታው ውጤት በኋላ አመልካች ከቤቱ ሽያጭ ድርሻቸውም ብር 105,000 ለመወሰድ ፈቃደኛ ያልሆኑ በሰበር አቤቱታቸው ላይ እንደገለጹት ሳይሆን ልሎች ከተጠሪ ጋር እንዲከፍሉ ውሳኔ የተሰጠባቸው ዕቃዎች ግምት እንዲከፍላቸው ድርስ ገንዘቡን አልቀበልም ማለታቸው በስር ፍ/ቤት ውሳኔ ላይ ተመልክቷል አመልካች ለቦረና ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ያቀረቡት የይግባኝ አቤቱታ የጨረታ ማስታወቂያ ለአንድ ወር አየር ላይ ሳይቆይ መሸጡን በመቃወም ሳይሆነ በጨረታው እና ብር 300,000 አቅርቤ እያለ በብር 210,000 መሸጡ ተገቢ አይደለም የተጠሪን (የመልስ ሰጪን) ድርሻ ብር 150,000 ካፍዬ ቤቱን እንድወሰድ የወሰንልኝ የሚል መሆኑን ከስር ፍ/ቤት ውሳኔ ተመልክቷል።
አመልካች አፈጻጸሙ በተጀመረበት ቦረና ዞን የሞያል ወረዳ ፍ/ቤት የጨረታ ማስታወቂያው ለአንደ ወር አየር ላይ አልቆየም በማለት የተቃወመ መሆኑን በይግባኝ ሰሚው የዞኑ ከፍ/ፍ/ቤት ይህን መቃወመያ ያነሱ መሆኑ በውሳኔው ላይ አልተመለከተም።
አመልካች በስር ፍ/ቤት በጨረታው እንዲሳተፉ ተፈቀደላቸው በጨረታው በብር 150,000 ተወዳደረው ከአመልካች ጋር ተወዳደርው አሸናፊ ለሆነው ተጨራች በብር 210,000 መሸጡን አረጋግጠናል አመልካች በስር ፍ/ቤቶች በነበራቸው ክርክር የጨረታ ማስታወቂያ ለአንድ ወር አየር ላይ አልቆየም በማለት ያነሱት መቃወሚያ በስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ላይ የተመለከተ ባይሆንም አንሰተወት እንኳ ቢሆን በአመልካቿ መብት ላይ ቀጥታ ጉዳት ያደረሰ ወይም የሚያደርስ መሆኑ አልተረጋገጠም በመሆኑም በፍ/ብ/ስ/ስ/ቁ.445 መሰረት ጨረታ ሽያጩ ላፈርስ አይገባም የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ በአግባቡ በመሆኑ የሚከተለው ተወስኗል።
በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን የሞያል ወ/ፍ/ቤት በፋ/ቁ. 04295 ከፍ/ፍ/ቤት በፋ/ቁ.10915 በቀን 25/04/2007 ዓ/ም በዋለ ችሎት የሰጠው ውሳኔ እና የኦሮሚያ ክልል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት በፋ/ በቀን 17/06/07 በዋለ ችሎት የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ቁ.348 (1) መሰረት ጸንቷል።
ግራ ቀኙ በዚህ ሰበር ችሎት ላደረጉት ክርክር ያወጡትን ወጪ የየራሳቸው ይቻሉ ብለናል።
መዝገብ ዕልባት ያገኘ በመሆኑ በቀን 8/07/2007 ዓ/ም በዋለ ችሎት የተሰጠው ዕግድ ተነስቷል ይጻፍ ብለናል መዝገቡ ዕልባት ያገኘ በመሆኑ መ/ቤት ይመለስ።
No topics extracted.