በትግራይ ክልል ገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ መሰረት ባለይዞታ አርሶ አደር ይዞታውን የመሸጥ መብት የልለውና የኸው ተፈፅሞ ሲገኝ ይህ ውል እንዳይረጋ በማንኛውም ጊዜ ተቃውሞ ላነሳና ጉዳዩ የቀረበለትም ፍ/ቤትም ውሉ ከጅምሩ ህገወጥ መሆኑን አውቆ ውሉ ህጋዊና ተፈፃሚነት የለውም በማለት ላወሰን የሚገባ ስለመሆኑ የትግራይ የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ ቁ. 55/1994፣ አዲሱ አዋጅ ቁ. 236/2006 የፍ/ሕ/ቁ. 1678፣1716፣1718፣1195 እና 1196
No summary available.
ቀን የካቲት 16 ቀን 2008 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማዉ ወል ዓላ መሐመድ ተኽላት ይመሰል እንዳሻዉ አዳነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- ማንአህሎህ አንተነህ ተወካይ ቀረቡ ተጠሪ፡- የማቻካል ወረዳ አካባቢ ጥበቃ መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት ተወካይ የክልሉ ዓ/ሕግ ቀረቡ መዝገቡ መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል ።
ጉዳዩ የመሬት ይዞታ እና የሰብል ግምት ክርክር የሚመለከት ሲሆን ጉዳዩ የተጀመረው በአብኪመ የማቻኮል ወረዳ ፍ/ቤት የአሁኑ ተጠሪ በዓቃቤ ህግ በኩል በአሁኑ አመልካች ላይ ባቀረበው ክስ መነሻነት ነው።
የአሁኑ ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ ባጭሩ ፡- አመልካች ከማንም ሕጋዊ መብት ካለው አካል ሳይሰጠው በመቻከል ወረዳ በሸይ ቀበል ልዩ ስሙ ገለቦ በተባለው ቦታ በምስራቅ መንገድ በምዕራብ ተምጫ ወንዝ፣ በሰሜን የኔወርቅ ለቀው በደቡብ አሚጋ የሚያዋስነው የህዝብ ግጦሽ መሬት በወርድ 50 ሜትር በቁመት 80 ሜትር የሆነውን የመስኖ መሬት በመያዝ በ2004፣2005 እና 2006 እህል በመዝራት፤ አትክልት በማፍራት ገቢ በማግኘቱ የሰብል ግምት በመክፈል የህዝብና የመንግስት ይዘት ለቆ እንዲያሰረክብ ዳኝነት መጠየቁን የሚያሰይ ነው፡፤
የአሁኑ አመልካች የመከለከያ መልስ ያቀረበ ሲሆን ዋና ፍሬ ነገሩ የሰብል ግምት መቅረብ ያለበት በመሬት ይዞታው ላይ ውሳኔ ከተሰጠ በኃላ መሆን እንዳለበት፤ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን መሬት በ1994 ኣ/ም የቀበል አመራር ኮሚቴዎች ለወፍጮ መትክያ የተሰጠው ስለመሆኑ በመግለጽ መልስ አቅርበዋል፡፤
የስር ወረዳ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙ ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኃላ የአሁን አመልካች መሬቱ ከ1994 ዓ/ም የያዝኩት ስለሆነ ጉዳዩ በይርጋ ቀሪ ይሆናል በማለት ያቀረበው ክርክር በተመለከተ በዚህ ጉዳይ በ1999 ዓ/ም በወንጀል ተከሶ ጥፋተኛ የተበለ በመሆኑ በይርጋ የሚቋረጥ አይደለም ። አመልካች መሬቱን በቀበል የአመራር አካላት የተሰጠኝ ነው በማለት የተከራከረ ቢሆንም መሬት የማስተዳደር ስልጣን የወረዳው መሬት አስተዳደር አጠቃቀም ጽ/ቤት እንጅ የቀበል አመራር አይደለም። አመልካች በመሬቱ ላይ የዘራው ሰብል ግምት በድምሩ 11,474/ አስራ አንድ ሺህ አራት መቶ ሰባ አራት ብር ይክፈል ይዞታውም ይልቀቅ በማለት ፍርድ ሰጥቷል።
የአሁኑ አመልካች የስር ወረዳ ፍ/ቤት ውሳኔ በመቃወም ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙ ከከራከረ በኃላ አመልከች ለክርክሩ መነሻ የሆነውን መሬት ለወፍጮ ተጠቃሚ ህብረተሰብ አህያ እንዲያስርበት በቀበል አስተዳደር የተሰጠው መሆኑ በወቅቱ የቀበል አስተዳደር ኃላፍዎች የነበሩ ቀርበው የመስከሩ ቢሆንም መሬት የመስጠት ስልጣን የወረዳ አስተዳደር መሆኑ በክልሉ የገጠር መሬት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 133/98 ተመልክቷል።
በመሆኑም አመልካች መሬቱን ያገኘው ህጋዊ ሥልጣን ከልለው የቀበል አስተዳደር ጽ/ቤት በመሆኑ ይልቀቅ መባሉ በአግባብ ነው። የሰብል ግምት በተመለከተ አመልካች መሬቱን ያረሰው መብት ያለው መስሎት በመሆኑ በፍ/ህ/ቁ/1173 (2) መስራት ላሻሸል እንደሚገባው የጤፍ ሰብል ግምት ዳኝነት ያልተጠየቀበት በመሆኑ የዚህን ግምት መጠን ተቀንሶ ብር 7,726.5 ይክፈል ሲል ወስኗል። አመልካች ይህንን ውሳኔ በመቃወም ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረበው አቤቱታ ውድቅ ተደርጓል የአሁን ሰበር አቤቱታ የቀረበውም የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ ለሰበር ይቅረብ በመባሉ ተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦ ግራ ቀኙ የጽሑፍ ክርክር አደርጓል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘት መሬቱ በ1994 ዓ/ም የተሰጠው በመሆኑ በ10 ዓመት ይርጋ ቀሪ እንንደሚሆን ለክርክሩ መነሻ የሆነውን መሬት የሰጡት የቀበል አስተዳደር በመሆኑ የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ እንዲሻር መጠየቁን የሚያሰይ ነው።
ተጠሪ በበኩሉ አመልካች የህዝብና የመንግስት ንብረት በህገወጥ የያዘ በመሆኑ ጉዳዩ በይርጋ ህግ ቀሪ የሚሆን አይደለም መሬቱም ሥልጣን በልለው የቀበል አስተዳደር የተሰጠው በመሆኑ ይልቀቅ መባሉ በህጉ አግባብ ነው የሚል መልስ አቅርበዋል፡፤ አመልካች የሰበር አቤቱታው የሚያጠናክር የመልስ መልስ አቅርበዋል። የጉዳዩ አመጠጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችሎት የስር ፍርድ ቤቶች በሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት መፈጸም ያለመፈፀሙን መርምረዋል። እንደመረመርናውም የአሁኑ አመልካች አጥብቆ የሚከራከራው የመሬት ይዞታው በቀበል አስተዳደር እንደተሰጠው እና ለረጅም ዓመት ሲጠቀምበት እንደነበር ነው። ተጠሪ በበኩሉ የቀበል አስተዳደር መሬት የመስጠት ስልጣን እንደልለው እና ሰብል በማምረት ያገኘው ህገወጥ ጥቅም ገቢ እንዲያደርግ መወሰኑ በአግባቡ ነው የሚል ክርክር አቅርበዋል።
በስር ፍርድ ቤት በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠው አመልካች ከዚህ መሬት ጋር በተያየዘ በ1999 ዓ/ም በወንጀል ተከሶ እንደተቀጣ መሬት የመስጠት ስልጣን በልለው የቀበል አስተዳደር የተመራው ስለመሆኑ ነው። አመልካች የመሬት ይዞታው በቀበል አስተዳደር ተሰጠኝ ይበል እንጂ የቀበል አስተዳደር መሬት የመስጠት ኃላፊነት እንደነበራቸው በህግ የተደገፈ ክርክር አላቀረበም፡፤
በህጉ አግባብ ሥልጣን ባለው አካል የመሬት ይዞታው ማግኘቱ ካልተረጋገጠ ደግሞ የህዝብና የመንግስት ይዞታ ላለቅ ይገባል መባሉ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ጉዳይ አይደለም።
አመልካች ያቀረበው የይርጋ ክርክር የህግ ድጋፍ የለውም ብለናል።
አመልካች በህገ ወጥ መንገድ በያዘው መሬት ላይ ሰብል ዘርቶ ገዚ በማግኘቱ ምክንያት ከፍተኛ ፍርድ ቤት የስር ወረዳ ፍ/ቤት ውሳኔ በማሻሸል 7,726 ብር የሰብል ግምት እንዲከፍል ወስኗል።
አመልካች ሰብሉን የዘራበት አግባብ ሲታይ የመሬት ይዞታው በቀበል አስተዳደር የተሰጠው ስለመሆኑ እምነት በመያዝ ነው። በስር ፍርድ ቤት ቀርበው የተሰሙ የቀበል የስራ ኃላፊዎች የነበሩ ግለሰቦች መሬት ሰጥተው እንደነበረ አስረድቷል። ይህ ሲታይ አመልካች መሬቱ ስልጣን ባለው አካል ተሰጥቶኛል ከሚል እምነት በመነጨ በቅን ልቦና ሰብል ያመረተ መሆኑን መረዳት ይቻላል ተጠሪም መሬቱ ሥልጣን ባለው አካል አልተሰጠውም በማለት ተከራከረ እንጅ የቀበል አስተዳደር ያልሰጠው ስለመሆኑ ክዶ አልተከራከረም። ይህ ከሆነ አመልካች ሰብል በመዝራት አገኘው የተበለው ግምት 7,726 ብር ይክፈል መባሉ በህጉ አግባብ ሆኖ አላገኘነውም።
በመሆኑም አመልካች መሬቱ እንዲለቅ የተሰጠው ውሳኔ በአግባቡ ሆኖ የሰብል ግምት ይክፈል ተብሎ የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ግን ላሻሻል የሚገባው ነው፡፤ በዚህም ተከታዩን ወስነናል፡፤
የምስራቅ ስደሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 011806 በ 24/06/2007 ዓ/ም የመቻከል ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 11475 በ2/08/2006 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ በማሻሸል የሰጠው ውሳኔ ተሻሽሐል፡፤
አመልካች ለክርክሩ ምክንያት የሆኑትን መሬቶች እንዲያሰረክብ መወሰኑ በአግባቡ ነው ብለናል።
አመልካች የሰብል ግምት 7726 /ሰባት ሺህ ሰባት መቶ ሃያ ሰድስት ብር 50/100 የሆነውን ለመልስ ሰጭው ላከፍል ይገባል ተብሎ የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ተሸሯል
የወጪና ኪሰራ ይቻቻሉ ብለናል።
No topics extracted.