በኦሮሚያ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ መሰረት ይዞታን የመጠቀም መብት የሚተላለፈው በውርስ ሕግ መሰረት በይዞታው የመጠቀም መብት ላለው የቤተሰብ አባል ሲሆን በዚሁ አግባብ ቅድሚያ የውርስ መብት የሚሰጠው ከመሬቱ በሚያገኙት ገቢ ለሚተዳደሩ(ልላ መተዳደሪያ)ገቢ ለልላቸው ወራሾች ሥለመሆኑ የኦሮሚያ የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ ቁ. 130/1999 አንቀፅ 9(1)(2) አዋጁን ለማስፈፀም የወጣው ደንብ ቁጥር 151/2005 አንቀፅ 10(1) XIX
No summary available.
የሰ/መ/ቁ.
.. የካቲት 4 ቀን 2008 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብረሃ መሰለ አመልካቾች፡-
ጉዳዩ በገጠር የእርሻ ይዞታ ላይ የተነሳ የውርስ ይገባኛል ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም ከሳሾች የነበሩት የአሁኖቹ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ያሉት ተጠሪዎች በደብረ ላባኖስ ወረዳ ፍርድ ቤት ተከሳሽ በነበሩት የአሁኑ 1ኛ አመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ ነው።የአሁኗ 2ኛ አመልካች በዋናው ክርክር ጊዜ በጉዳዩ በጣልቃ ገብነት የተከራከሩ ሲሆኑ የአሁኖቹ 5ኛ እና 6ኛ ተጠሪዎች ደግሞ በጉዳዩ ላይ የወረዳ ፍርድ ቤቱ በ27/07/2006 ዓ.ም. ውሳኔ ከሰጠ በኃላ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 358 ድንጋጌ መሰረት ወደ ጉዳዩ የገቡ ናቸው።
ፍርድ ቤቱ በከሳሾች እና በተከሳሽ፣እንደሁም በጣልቃ ገቧ የአሁኗ 2ኛ አመልካች መካከል የነበረውን ክርክር መርምሮ ክርክር ያስነሳውን የእርሻ መሬት፣ እንዲሁም የእንስሳት ግምት ብር 7,000 (ሰባት ሺህ) ከሳሾች እና ተከሳሽ እኩል ይካፈሉ በማለት በመዝገብ በ27/07/2006 ዓ.ም. ውሳኔ ሰጥቶአል።ከዚህ በኃላ የእርሻ ይዞታው እና የከብቶቹ ግምት በውርስ ላተላለፍ የሚገባው ለከሳሾች እና ለተከሳሹ ብቻ ሳይሆን ለእኛም ጭምር በመሆኑ ውሳኔው ላሻሻል ይገባል በማለት የአሁኖቹ 5ኛ እና 6ኛ ተጠሪዎች በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 358 ድንጋጌ መሰረት በ24/10/2006 ዓ.ም. የተጻፈ የመቃወም አቤቱታ በማቅረባቸው መዝገቡ ተንቀሳቅሶ የስር ከሳሾች ውሳኔው መቃወሚያ አቅራቢዎቹ በጠየቁት አግባብ ቢሻሻል ተቃውሞ እንደልላቸው በመግለጽ መልስ የሰጡ ሲሆን የስር ተከሳሽ በበኩላቸው በሰጡት መልስ መቃወሚያ አቅራቢዎቹ ከሟች ስሜ ደገፋ የሚወለዱ ቢሆንም በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ እና በደመወዝ የሚተዳደሩ በመሆናቸው እና የሟች የቤተሰብ አባል ከሳሽ ብቻ በመሆናቸው ጥያቄአቸው ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት የተከራከሩ መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።
ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር መርመሮ መቃወሚ አቅራቢዎቹ የሟች ስሜ ደገፋ ልጆች እና ወራሾች መሆናቸው አልተካደም በማለት የቀድሞውን ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 360 (2) መሰረት አሻሽሎ ክርክር ያስነሳውን የእርሻ መሬት፣እንዲሁም የእንስሳት ግምት ብር 7,000 (ሰባት ሺህ) ከሳሾች፣ተከሳሽ እና መቃወሚያ አቅራቢዎቹ እኩል ላካፈሉ ይገባል በማለት በ09/11/2006 ዓ.ም.ውሳኔ ሰጥቷል። በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት የአሁኖቹ አመልካቾች ባቀረቡት ይግባኝ ሳቢያ የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የወረዳው ፍርድ ቤት ውሳኔን አጽንቷል።
አመልካቾቹ አቤቱታቸውን ለዚህ ችሎት ያቀረቡት የክልሉ ሰበር ችሎት የቀረበለትን አቤቱታ ዘግቶ በማሰናበቱ ሲሆን ለዚህ ችሎት የቀረበው አቤቱታ ተመርምሮ የአሁኖቹ 5ኛ እና 6ኛ ተጠሪዎች በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ እና በደመወዝ የሚተዳደሩ በመሆናቸው የገጠር የእርሻ ይዞታን የመውረስ መብት የላቸውም በማለት የአሁኑ 1ኛ አመልካች ያቀረቡት ክርክር በስር ፍርድ ቤቶች ውድቅ የመደረጉን አግባብነት ተጠሪዎቹ ባሉበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዳዩ ለሰበር ክርክር እንዲቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም በጉዳዩ እልባት ማግኘት የሚገባቸው፡-
2ኛ ተጠሪ በዚህ መዝገብ በአመልካችነት የመከራከር መብት አላቸው ወይስ የላቸውም?
1ኛ አመልካች በ27/07/2006 ዓ.ም. በወረዳው ፍርድ ቤት በተሰጠው ውሳኔ ላይ በዚህ መዝገብ ያቀረቡት የክርክር ነጥብ በዚህ መዝገብ ላስተናገድ የሚችል ነው ወይስ አይደለም?
የቀድሞውን ውሳኔ በማሻሻል በወረዳው ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በክልሉ የበላይ ፍርድ ቤቶች ተቀባይነት ያገኘው ውሳኔ የተሰጠው ለጉዳዩ አግባብነት ያላቸው ፍሬ ነገሮች በአግባቡ እንዲጣሩ ከተደረገ በኃላ ነው ወይስ አይደለም?
የሚሉ መሆናቸውን በመገንዘብ አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ከእነዚሁ ነጥቦች አንጻር መርምረናል።
የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ 2ኛ አመልካች በወረዳው ፍርድ ቤት በጣልቃ ገብነት የክርክሩ ተካፋይ የነበሩት የመቃወም አቤቱታ ከመቅረቡ በፊት በነበረው ሂደት ነው።የመቃወም አቤቱታው ከቀረበ በኃላ 2ኛ አመልካች የክርክሩ ተካፋይ የነበሩ ስለመሆኑ የመዝገቡ ግልባጭ አያመለክትም።ቀደም ሲል እንደተገለጸው የመቃወም አቤቱታው ከመቅረቡ በፊት ውሳኔ የተሰጠው በ27/07/2006 ዓ.ም. ሲሆን የመቃወም አቤቱታ ከቀረበ በኃላ ውሳኔ የተሰጠው ደግሞ በ09/11/2006 ዓ.ም. ነው።2ኛ አመልካች በ27/07/2006 ዓ.ም. በተሰጠባቸው ውሳኔ ላይ ቅሬታ ካላቸው በውሳኔው ላይ ያላቸውን ይግባኝ እና አቤቱታ ስርዓቱን ጠብቀው ማቅረብ ይችሉ የነበረ ከመሆኑ ውጪ ተካፋይ ባልተደረጉበት ክርክር በ09/11/2006 ዓ.ም. በተሰጠው ውሳኔ ላይ ይግባኝ እና አቤቱታ ማቅረብ የሚችሉበት ስነ ስርዓታዊ አግባብ የለም።በመሆኑም 2ኛ ተጠሪ በዚህ መዝገብ በአመልካችነት የመከራከር መብት አላቸው ማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም።
ሁለተኛውን ነጥብ በተመለከተ ለዚህ ሰበር ክርክር መነሻ የሆነው የመቃወም አቤቱታ ከቀረበ በኃላ በ09/11/2006 ዓ.ም. የተሰጠው ውሳኔ በመሆኑ 1ኛ አመልካች ይግባኝ እና አቤቱታ ማቅረብ የሚገባቸው ይህንኑ በ09/11/2006 ዓ.ም. የተሰጠውን ውሳኔ መሰረት በማድረግ ከሚሆን በቀር የኃለኛውን ውሳኔ አስታከው የመቃወም አቤቱታ ከመቅረቡ አስቀድሞ በ27/07/2006 ዓ.ም.በተሰጠው ውሳኔ ላይ ይግባኝ እና አቤቱታ ላያቀርቡ የሚችሉበት አግባብ የለም።በመሆኑም 2ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች ጭምር የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በመሆናቸው የእርሻ መሬት የመውረስ መብት የላቸውም፣በ3ኛ ተጠሪ እጅ የሚገኝ የውርስ ንብረት ጭምር መኖሩን በመጥቀስ ያቀረበኩት የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ የታለፈብኝ አላግባብ ነው በማለት 1ኛ አመልካች ያቀረቡት ክርክር በዚህ መዝገብ ላስተናገድ የሚችል ሆኖ አልተገኘም።
ሶስተኛውን ነጥብ በተመለከተ 1ኛ አመልካችም ሆኑ ተጠሪዎቹ የሟች ስሜ ደገፋ ልጆች እና ወራሾች መሆናቸው በግራ ቀኙ ያልተካደ ሲሆን የአንድ አርሶ አደር ወይም አርብቶ አደር በመሬት ይዞታ የመጠቀም መብት በውርስ የሚተላለፈው በውርስ ሕግ መሰረት በይዞታው የመጠቀም መብቱን የመውረስ መብት ላለው የቤተሰብ አባል ስለመሆኑ በክልሉ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/1999 አንቀጽ 9 (1) ስር የተመለከተው ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ቅድሚያ የውርስ መብት የሚሰጠው ከመሬቱ በሚያገኙት ገቢ ለሚተዳደሩ ወይም ልላ መተዳደሪያ ገቢ ለልላቸው ወራሾች እንደሆነ በአዋጁ አንቀጽ 9 (2) ስር ተመልክቶአል።አዋጁን ለማስፈጸም በወጣው ደንብ ቁጥር 151/2005 አንቀጽ 10 (1) ስር ያለው ድንጋጌም ተመሳሳይ ይዘት ያለው ነው። የአሁኖቹ 5ኛ እና 6ኛ ተጠሪዎች በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ እና በደመወዝ የሚተዳደሩ በመሆናቸው የገጠር የእርሻ ይዞታን የመውረስ ቀዳሚ መብት ያላቸው የሟች ቤተሰብ አባል ሆነው ከእርሻ መሬቱ በሚገኘው ገቢ የሚተዳደሩ የአሁኑ 1ኛ አመልካች መሆናቸውን በመግለጽ የአሁኑ 1ኛ አመልካች መከራከራቸውን እና 5ኛ እና 6ኛ ተጠሪዎች ደግሞ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ሳይሆኑ የእርሻ መሬቱ የሚገኝበት ቀበል ነዋሪዎች መሆናቸውን በመግለጽ የተከራከሩ መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል። የስር ፍርድ ቤቶች ይህንን መከራከሪያ ሳይቀበሉ የቀሩት ሁሉም ወራሾች በእርሻ መሬት አወራረስ ላይ እኩል መብት እንዳላቸው በመቁጠር እንደሆነ የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።በመሆኑም በአንድ በኩል በ1ኛ አመልካች አና በልላ በኩል ደግሞ በ5ኛ እና 6ኛ ተጠሪዎች መካከል የተነሳውን ክርክር በማስረጃ ሳያጣራ ሁሉም ወራሾች በእርሻ መሬት ላይ እኩል መብት እንዳላቸው በመቁጠር መሬቱን እኩል እንዲካፈሉ በወረዳው ፍርድ ቤት የተሰጠው እና በክልሉ የበላይ ፍርድ ቤቶች ተቀባይነት ያገኘው ውሳኔ በስነ ስርዓት ሕጉ የተመለከተውን የክርክር አመራር ስርዓት መሰረት ያላደረገ በመሆኑ ሕጋዊ ተቀባይነት ላሰጠው የሚገባ ሆኖ አልተገኘም።ከእርሻ ይዞታው ውርስ ጋር ተያይዞ በተነሳው ክርክር ከሟች የተላለፉት እንስሳት ውርስ ጉዳይ የሚገዛው ውርስን በሚመለከቱ የፍትሐብሕር ሕጉ ድንጋጌዎች መሰረት በመሆኑ የእንስሳቱን ግምት ብር 7,000 (ሰባት ሺህ) ከሳሾች፣ተከሳሽ እና መቃወሚያ አቅራቢዎቹ እኩል ላካፈሉ ይገባል በማለት የተሰጠው የውሳኔ ክፍል የሚነቀፍበትን ሕጋዊ ምክንያት አላገኘንም።
ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ በከፊል መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቶአል።
2ኛ አመልካች ተከራካሪ ወገን ባልነበሩበት በ09/11/2006 ዓ.ም. በተሰጠው ውሳኔ ላይ ይግባኝ እና አቤቱታ የማቅረብ መብት የላቸውም በማለት ወስነናል።
በኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ዞን በደብረ ላባኖስ ወረዳ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ09/11/2006 ዓ.ም. ተሰጥቶ በኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ28/12/2006 ዓ.ም. በፍርድ እና በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በመዝገብ በ09/04/2007 ዓ.ም. በትዕዛዝ የጸናው ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሻሽሐል።
የእንስሳቱን ግምት ብር 7,000 (ሰባት ሺህ) ከሳሾች፣ተከሳሽ እና መቃወሚያ አቅራቢዎቹ እኩል ላካፈሉ ይገባል በማለት የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ፀንቷል።
ክርክር ያስነሳውን የእርሻ ይዞታ ከሳሾች፣ተከሳሽ እና መቃወሚያ አቅራቢዎቹ እኩል ላካፈሉ ይገባል በማለት የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ተሽሯል።
የአሁኖቹ 5ኛ እና 6ኛ ተጠሪዎች የመኖሪያ አድራሻ እንደ 1ኛ አመልካች አባባል በአዲስ አበባ ከተማ ነው ወይስ እንደ 5ኛ እና 6ኛ ተጠሪዎች አባባል ክርክር የተነሳበት የእርሻ መሬት በሚገኝበት ወረዳ እና ቀበል ነው? 5ኛ እና 6ኛ ተጠሪዎች ከደመወዝ በሚገኝ የሚተዳደሩ ናቸው ወይስ አይደሉም? የሚሉትን እና ተያያዥ ነጥቦችን በግራ ቀኙ ማስረጃ፣እንደሁም ጉዳዩ ከሚመለከተው አካል ሁሉ በፍርድ ቤት በትዕዛዝ በሚቀርብ የማጣሪያ ማስረጃ እንዲጣራ ካደረገ በኃላ 5ኛ እና 6ኛ ተጠሪዎች በክልሉ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/1999 አንቀጽ 9 (2) እና በደንብ ቁጥር 151/2005 አንቀጽ 10 (1) ድንጋጌዎች አነጋገር መሰረት ክርክር የተነሳበትን የእርሻ ይዞታ ውርስ የመካፈል መብት ያላቸው መሆን አለመሆኑን በተመለከተ ተገቢውን ውሳኔ ይሰጥበት ዘንድ ጉዳዩ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 343 (1) መሰረት ለደብረ ላባኖስ ወረዳ ፍርድ ቤት እንዲመለስ ወስነናል።
የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ተገቢውን መፈጸም ያስችለው ዘንድ ለደብረ ላባኖስ ወረዳ ፍርድ ቤት፣እንዲያውቁት ደግሞ ለሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና ለኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይላክ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ።
ውሳኔ ያገኘ ሰለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.