ከመንግስት ገዥና አቅርቦት ጋር በተያያዘ የሚነሳ ክርክር በመጀመሪያ ስልጣኑ የማየት መብት ያለው የመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ ቅሬታ ሰሚ ቦርድ እንጂ የመደበኛ ፍ/ቤት ስላለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 649/2001 አንቀፅ 75(1) XVIII አዋጁን ለማስፈፀም የወጣው መመሪያ አንቀፅ 49(1) ኮሚሽን
No summary available.
ጥቅምት 04 ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ አመነው ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ አመልካች፡- ጄዳው አማካሪ አርክተክቶችና መሐንዲሶች ባለቤት አቶ ዳንኤል አሰፋ ጠበቃ አለሙ ገበየህ - ቀረቡ ተጠሪ፡- 1ኛ. የፍድራል ስፖርት ኮሚሽን ነገረ ፈጅ አቶ ፋሲል ተሰማ - ቀረቡ 2ኛ. የኢፍዲሪ ፍትህ ሚኒስቴር - አልቀረቡም መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን፤ መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዳይ በአስተዳደር አካል የተወሰነ ጉዳይ በመደበኛ ፍ/ቤት ቀርቦ ላታይ የሚችልበትን የአቤቱታ አቀራረብ ሥርዓትና ቅሬታውን ተቀብሎ የማየትና የመወሰን ሥልጣን ያለው በየትኛው ደረጃ የተዋቀረው ፍ/ቤት ነው? የሚለውን አስመልክቶ ግራ ቀኙ ከተከራከሩበት ጉዳይና ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ህጎች ጋር በማገናዘብ ለይቶ ለመወሰን በሚል የቀረበ ነው።
የጉዳዩም መነሻ የአሁን አመልካች በአሁን 1ኛ ተጠሪ ላይ በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በቀጥታ ያቀረበው ክስ ሲሆን የክሱም ይዘት ተከሳሹ ለብሕራዊ ስታድየም ግንባታ የሚሆን የዲዛይን ሥራ ፈልጎ ባወጣው የጨረታ ውድድር መሰረት ተወዳዳሪ አሸናፊ ሆኛለሁ በጨረታ ሰነዱ (በዝክር ተግባሩ) መሰረት ሥራው ለ2ኛው ዕጩ ተወዳዳሪ ላሰጥ የሚችለው አሸናፊው በእርሱ ምክንያት ሥራውን ለማከናወን አለመቻሉ የተረጋገጠ እንደሆነ ብቻ መሆኑ ተገልፆ እያለ ተከሳሹ በህገ-ወጥ መንገድ ጨረታ እንደገና እንዲደረግ የሚያስችል ተግባር በሚከናወን በሁለተኛ ደረጃ ለተሰየመው ተወዳዳሪ ሰጥቶ በዚሁ መሰረት እያከናወነ ስለሚገኝ ይህንኑ ተግባሩን አቁሞ በአሸናፊነቴ ቴክኒካል ፕሮፖዛል እንዲቀርብ እና የቴክኒካል ፕሮፖዛል ድርድር እንዲያደርግ ይወሰንልኝ የሚል ነው።
ተከሳሽ የነበረውም የአሁን 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ በጨረታው የአሸናፊነት ደረጃ አልደረሰም የሚልበትን ዝርዝር የክርክር ነጥብ በመጥቀስ በውድድሩ ሂደት ከሳሽ ለዲዛይን ሥራው ብቁ የሚያደርገውን መስፈርት አላሟላም፤
እንዲሁም በአዋጅ ቁጥር 649/2001 አንቀጽ 75(1) መሰረት የመንግሥት ግዥን በሚመለከት የሚቀርቡ ቅሬታዎች ሥልጣን ባለው የመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ ቅሬታ ሰሚ ቦርድ ቀርበው እንዲታዩ በማድረግ ሥልጣኑን የቦርዱ እንጂ የፍ/ቤቱ አይደለም ስለሆነም ክሱ ላዘጋ ይገባል የሚለውንም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ክርክር አቅርቧል።
ከሳሽም ጉዳዩን ለዚሁ ቦርድ አቅርቦ ማስወሰኑን ይህ ቦርድ የሚሰጠውም ውሳኔ የመጨረሻና አስገዳጅ ነው ተብሎ በአዋጅ አልተደነገገም ይልቁንም አዋጁን ተከትሎ በወጣው መመሪያ አንቀደጽ 49 (1) መሰረት በቦርዱ ውሳኔ ቅሬታ ያለው ሰው አቤቱታውን አግባብ ባለው ፍ/ቤት ማቅረብ እንደሚቻል ስለተደነገገ ፍ/ቤቱ የቀረበለት ክስ ተቀብሎ ለማየት ሥልጣን አለው በማለት ተከራክሯል።
ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤትም ለክርክሩ መነሻ የሆነው ጉዳይ በቀጥታ ተቀብሎ በማስተናገድ ሥልጣን አለው ወይስ የለውም? የሚለውን አከራካሪ ነጥብ በሚመለከት አግባብነት ያለወን የአዋጁንና የመመሪያውን ድንጋጌዎች በመጥቀስ የጉዳዩ አቀራረብ ሥርዓቱን ጠብቆ ሥልጣን ባለው ፍ/ቤት የቀረበ ነው የሚል ዳኝነት የሰጠበት ሲሆን፤
ይግባኝ ሰሚው የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በበኩሉ ጉዳዩ በይግባኝ ደረጃ የይግባኙን ጉዳዩ ለማየት ሥልጣን ላለው ፍ/ቤት ከማቅረብ በቀር የሥር ፍ/ቤት ጉዳዩን በቀጥታ ተቀብሎ ለማየትና ለመወሰን የሚያስችል የህግ የመነጨ ሥልጣን የለውም ሲል ሽሮ ወስኗል።
በሁለተኛ ደረጃ ይግባኝ ጉዳዩ የቀረበለት የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በየደረጃው የተሰጡትን ውሳኔዎች ተመልክቶ የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በይግባኝ ተመልክቶ የሰጠው ውሳኔ በአግባቡ መሆኑን አትቶ በመወሰን የአሁን አመልካችን አሰናብቷል።
የጉዳዩ አመጣጥ በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት ታይቶ ትርጉም የሚያስፈልገው ሆኖ ከተያዘው አከራካሪ ነጥብ አንፃር ባጭሩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም ጉዳዩን እንደሚከተለው ተመልክተናል።
የአሁን 1ኛ ተጠሪ ግራ ቀኙ የተከራከሩበትን ጉዳዩ በአዋጅ ቁጥር 649 /2001 አንቀጽ 75 (1) መሰረት አይቶ ለመወሰን ሥልጣን የተሰጠው ለመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ ቅሬታ ሰሚ ቦርድ እንጂ በመደበኛ ፍ/ቤት ቀርቦ ላታይ የሚችል አይደለም በሚል ያቀረበው ክርክር ይህንኑ አዋጅ ለማስፈፀም በሰጠው መመሪያ አንቀጽ 49 (1) ድንጋጌ ሥር በግልፅ እንደተመለከተው ይኸው ቅሬታ ሰሚ ቦርድ በሰጠው ውሳኔ ያለው ወገን አግባብ ላለው ፍ/ቤት አቤቱታ ማቅረብ የሚቻል በመሆኑ ጉዳዩ በማናቸውም ምክንያት ለመደበኛ ፍ/ቤት ቀርቦ ላታይ የሚችል አይደለም የሚለው ክርክሩ ህጋዊ መሰረት ያለው አይደለም።
አከራካሪ ሆኖ የተገኘው በዚሁ ቅሬታ ሰሚ ቦርድ በሰጠው ውሳኔ ላይ ቅሬታ ያለው ወገን አቤቱታውን “አግባብ ባለው ፍ/ቤት ማቅረብ ይችላሉ ተብሎ ከተደነገገው ይህ አግባብ ያለው ፍ/ቤት የትኛው ነው? የመጀመሪያ ደረጃ ክስን በጉዳዩ ዓይነት ወይም በገንዘቡ መጠን መሰረት ተቀብሎ ጉዳዩን በቀጥታ የክስ ደረጃ የሚያየው ፍ/ቤት ወይስ የቦርዱን ውሳኔ አግባብነት እንደገና ተመልክቶና ክስ በይግባኝ ዳኝነት ለመስጠት ሥልጣን ላለው ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት? የሚለው ነው።
በኢ.ፍ.ዲ.ሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 79 የዳኝነት ሥልጣን የፍርድ ቤቶች ብቻ ነው በሚል የተደነገገውን በዚሁ ህገ-መንግስት የፍ/ቤቶችን የሥልጣን ወሰን ለሚያመለክተው ከአንቀጽ 37 ጋር አጣቅሶ ማየት እንደሚቻለው ማንኛውም ጉዳይ ያለገደብ በመደበኛ ፍ/ቤት ቀርቦ ላታይ የማይችል መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው። ይልቁንም በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 37 የተቀመጠው የሥልጣን ክፍፍል ወሰን እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም ጉዳይ በፍርድ ላያልቅ የሚችል እና ጉዳዩንም አይቶ ለመወሰን ከመደበኛ ፍ/ቤት ውጭ በልላ የዳኝነት ሰጭ አካል ያልተሰጠ መሆኑ ከተረጋገጠ ይህንኑ በፍርድ ላያልቅ የሚችለውን ጉዳይ ለማየትና ለመወሰን ብቸኛ ሥልጣን ያላቸው (exclusive Jurisdiction jurisdiction ) ያላቸው ፍ/ቤቶች መሆናቸውን ለማስገንዘብ ሲባል በአንቀጽ 79 መደንገጉን መረዳት ይቻላል።
ስለሆነም መደበኛ ፍ/ቤቶች የቀረበላቸው ጉዳይ በፍርድ ላያልቅ የሚችል መሆኑን በማረጋገጥ ላይ ብቻ ላይወሰኑ በህገ- መንግስቱ አንቀጽ 37 መሰረት ይኸው ጉዳይ ከመደበኛ ፍ/ቤት ውጭ ለልላ በህግ የዳኝነት ሥልጣን ለተሰጠው አካል ቀርቦ የሚታይ መሆኑንና አለመሆኑን በቀጥታ የመመርመር ግድታ አለባቸው።
ከዚህ አንፃር አሁን የተያዘውን ጉዳይ ስንመለከት በፍሬ ነገር ደረጃ እንደተረጋገጠውና ግራ ቀኙም እንደተማመነበት ሁለቱም ወገኖች ያለያያቸው ጉዳይ በአዋጅ ቁጥር 649/2001 አንቀጽ 75(1) መሰረት ጉዳዩ ለመደበኛ ፍ/ቤት ቀርቦ ከመታየቱ በፊት በመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ ቅሬታ ሰሚ ቦርድ መቅረብ እንዳለበትና በዚሁ የቅሬታ ሰሚ ቦርድ ውሳኔ ማግኘት አለበት በዚህም መሰረት ጉዳዩ በዚሁ አካል ቀርቦ ውሳኔ የተሰጠበትን ጉዳይ ነው በዚህም አኳኃን በዚሁ የአስተዳደር አካልም (ከፊል የዳኝነት ሰጭ አካል) ታይቶ የተሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ሆኖ የሚቀር ሳይሆን በውሳኔው ላይ ቅር የተሰኘ ወገን ቅሬታውን አግባብ ላለው ፍ/ቤት አቅርቦ አቤቱታውን ማቅረብ እንደሚችል አዋጁን ለማስፈጸም በወጣው መመሪያ አንቀጽ 49(1) ተደንግጓል። ከዚህም መገንዘብ የሚቻለው በአዋጅ ቁጥር 649/2001 አንቀጽ 75(1) በህገመንግስት አንቀጽ 37 እንደተደነገገው ይህንኑ ጉዳይ በቀዳሚ ተቀብሎ ለማስተናገድ ሥልጣን ያለውን የዳኝነት አካል (ከፊል የዳኝነት አካል) ለይቶ ካስቀመጠ በኃላ እንደገና ጉዳዩን ወደ መደበኛ ፍ/ቤት ለማቅረብ የጉዳዩን አሰማምሮ አወሳሰን በሚመለከት በአስተዳደራዊ ክፍል የዳኝነት ሰጭ አካል እና በመደበኛ ፍ/ቤት መካከል ያለውን ቁርኝት በሚመለከት ይህንኑ በአዋጅ አንቀጽ 75(1) የተቀመጠውን ድንጋጌ ለማስፈፀም በሰጠው መሰረት አንቀጽ 49(1) በግልፅ ተመልክቷል። እንግዲህ በከፊል የዳኝነት ሰጭው አካልና በመደበኛው ፍ/ቤት መካከል ያለውን ቁርኝነት በተገለፀበት መመሪያ አንቀጽ 49(1) “በቦርዱ ውሳኔ ቅሬታ ያለው ሰው አግባብ ላለው ፍ/ቤት አቤቱታውን ማቅረብ ይችላል።” በሚል ከተገለፀው ቅሬታው አስቀድሞ በተሰጡ የቦርድ ውሳኔ ላይ የተመሰረተ ከመሆኑ፤ ቅሬታ የሚለውም ቀጥተኛ ትርጉም በአንድ አካል በተሰጠ ውሳኔ ላይ ያልተስማማ ወገን አለመስማማቱን የሚገልፁበት ቃል መሆኑን በዚህም ድንጋጌ የእግላዘኛ ቅጂ “Review of complaint by the coyrt” በሚል ከተገለጸው “Review” የሚለው አስቀድሞ በተወሰነ ውሳኔ ላይ ተመርኩዞ በዚሁ ውሳኔ ላይ ቅር ተሰኝቶ ከቀረበው ቅሬታ ጋር በማዛመድ ጉዳዩን እንደገና በዳኝነት ሰጭ አካል የሚታይ መሆኑን የሚያመለክት በመሆኑ በህገ - መንግስቱ አንቀጽ 37 ሆነ በአዋጅ አንቀጽ 75(1) የመደበኛ ፍ/ቤቶችን የዳኝነት ሥልጣን ወሰን ካስቀመጠ በኃላ በማስፈፀሚያው መመሪያ አንቀጽ 49(1) የተቀመጠው ከመደበኛ ፍ/ቤቶች ጋር ያለው ቁርኝት መገለጫው በይግባኝ ሥርዓቱ አማካኝነት ውሳኔውን በይግባኝ ሰሚነቱ ሥልጣን መሰረት በቦርዱ የተሰጠውን ውሳኔ አግባብነት ካለው ህግና መመሪያ አንፃር በማየት መመርመር እንዲቻል እንጂ ጉዳዩን እንደ አዲስ በመቀጠር ተከራካሪ ወገኖች በጉዳዩ ላይ ክርክር በአዲስ መልክ የሚያከናውኑበትን ሥርዓት የሚመለክት አይደለም። የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አግባብ ያለው ፍ/ቤት ጉዳዩን ከህግ አንፃር ብቻ መመልከት እንዲቻል ሆኖ አልተቀረፀም ይባል እንጂ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ የተሰጠበትና በዚህም ውሳኔ ላይ ቅሬታ ማቅረብ እንደሚቻል በመመሪያ የተፈቀደ በመሆኑ ጉዳዩን በክለሳ “Review” መልክ የሚያየው ፍ/ቤት የህግም ጥያቄ ሁሉ መመልከት የሚችል መሆኑ በውስጠ ታዋቂነት ግንዛቤ ላወሰድበት ይገባ ነበር እንጂ ጉዳዩ በቀጥታ ክስ አማካኝነት ላቀርብ ይገባል የሚለው ወደሚለው በቂ የውሳኔ መነሻ ትችትና ላያደገውም አይገባም ነበር።
በሀገራችን የህግ ሥርዓቱ በልዩ ልዩ ህጎች እንደተመለከተው በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 37 በአስተዳደርና፣ በከፊል የዳኝነት ሰጭ አካል እንጂ በመደበኛ ፍ/ቤቱ አስቀድመው ላታዩ የማይችሉን ጉዳዮች ከተመለከቱ በኃላ ፍትህ የማግኘት መብትን ይበልጥ ለማረጋገጥ ሲባል ከፍ/ቤቱ ጋር ቁርኝት ላኖራቸው እንደሚገባና ቁርኝቱም ለይግባኝ ሥርዓቱ አማካኝነት ጉዳዩ በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት አማካኝነት እንዲታዩ በማድረግ የተደነገጉ እንጂ እንደገና እንደ አዲስ ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ (of first instance ) አቅርቦ አዲስ ክርክርን በሚጋብዝ ደረጃ የተቀረፀ አይደለም።
በዚሁ ሁሉ ምክንያት በይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍ/ቤት የተሰጠው የመጨረሻ ዳኝነት መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አላገኘነውም።
የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በይግባኝ ሰሚነቱ ሥልጣን ላይ መ/ ህዳር 17/2007 ዓ.ም በአብላጫ ድምፅ በትዕዛዝ የሰጠው የመጨረሻ ዳኝነት ፀንቷል።
አመልካች በመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ ቅሬታ ሰሚ ቦርድ ውሳኔ ቅሬታ ካለው ቅሬታውን በይግባኝ አቤቱታ አቀራረብ ደንብን ሥርዓት መሰረት ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን ላለው አግባብ ላለው ፍ/ቤት ከሚያቀርብ በቀር በቀጥታ ክስ አቀራረብ ሥርዓት የጉዳዩን ዓይነትም ሆነ የገንዘብ መጠኑን መሰረት በማድረግ ጉዳዮች በቀጥታ ደረጃ በሚታዩበት ሥርዓተ መሰረት ማቅረቡ ሥነ-ሥርዓታዊ አይደለም ብለናል።
በዚህ ሰበር ደረጃ ግራቀኙ ባደረጉት ክርክር ሳቢያ ለወጣው ወጭና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻሉ። መዝገቡ ተዘግቷል። ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.