ህጉ በሚጠይቀው አግባብ ፈቃድ ሳያወጣ ወይም የጸና ፈቃድ ሳይኖረው ከቴልኮሚኒኬሽን እውቅናና ፈቃድ ወጭ ሶፍትዌሮችን በመገልግል በኢንተርኔት ስልኮች ማስደወል ላያስከትለው ስለሚችለው ኃላፊነት የቴልኮሚኒኬሽን አዋጅ ቁጥር 49/1989 ለማሻሻል የወጣው አዋጅ ቁጥር 281/1994 አንቀጽ 13
No summary available.
ቀን 24/05/2008 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ተኽላት ይመሰል .እንደሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- ወ/ሮ አመለወርቅ ጌታነህ ቀረቡ ተጠሪ፡- የፍድራል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዐ/ህግ የቀረበ የለም መዝገቡ መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የወንጀል ክስ የሚመለከት ሲሆን የተጀመረው በፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው። የአሁኑ ተጠሪ የአሁኗ አመልካች ጨምሮ በ17 ተከሳሾች ላይ ክስ ማቅረቡን መዝገቡ ያስረዳል። የአሁኑ ተጠሪ በስር ፍ/ቤት 9ኛ ተከሳሽ በነበሩት የአሁኗ አመልካች ያቀረበው ክስ ባጭሩ፡- በንፋስ ስልክ ከተማ ቀበል 12/13 የቤት ቁጥር የማይታወቅ ንግድ ቤት ውስጥ ስልክ የማስደወል ፈቃድ ሳይኖራት ከቴል ኮሚንኬሽን ሲስተም በመደበቅ ስልክ ማስደወል የሚያስችል ራስ አዲስ ፒሲቶከር እና ራስ ዳሽን የተባሉ ሶፍትዌሮችና የካርድ ቁጥሮች (Accounts numbers) ከ3ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች በመግዛት እንዱሁም ለጊዜው ማን እንዳስመጣው የማይታወቅ ኔት 2ፎን ዲያለር የተባለ ሶፍትዌር በመጠቀም 3ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች ከ1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ጋር በስውር በመመሳጠር ባዘጋጁት ህገወጥ ተግባር በመታገዝ ወደ ወጭ አገር ስልክ በማስደወል እ.ኤ.አ ከ01/11/2004 እስከ 06/10/2010 ለ5 አመታት ከ339 ቀናት 779,040 ደቂቃዎች ወደ ተለያየ አገራት ከኢትዮጵያ ቴልኮሚኒኬሽን ሲስተም መደበቅ የሚያስችል ቴክኖሎጄ በመጠቀም በህገወጥ መንገድ በማስደወል ብር 7,70,400 (ሰባት ሚላዮን ሰባት መቶ ዘጠና ሺህ አራት መቶ ብር) በመንግስት ጥቅም ላይ ጉዳት እንዲዲረስ በማደርገና በህገወጥ መንገድ 0.00 (ሶስት ሚላዮን ዘጠና አምስት ሺህ ሁለት መቶ ብር) ተጠቃሚ በመሆኗ እንዲሁም በሽያጭ የተዘጋጁ ግምታቸው USD 17500 የሚያወጡ የካርድ ቁጥሮች በህገ ወጥ ሱቋ ውስጥ በመገኘታቸው የኢፍድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32(1) (ሀ)፤ 33፣ 411(1) ሐ የተመለከተው በመተላለፍ በህዝብና በመንግስት ጥቅም ላይ ጉዳት አድርሳለች የሚል ነው።
አመልካች በተጠሪ የቀረበባት ክስ ክዳ በመከራከሯ የስር ፍርድ ቤት የዐቃቤ ህግ ማስረጃ ካደመጠ በኃላ እንድትከላከል ብይን ሰጥቷል። የአሁኗ አመልካች የበኩሐን የመከላከያ ማስረጃ በማስቀረብ አስምታለች። ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙ ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኃላ የአሁኗ አመልካች እና ልሎች ተከሳሾች በክሱ በተገለጸው አግባብ ከቴልኮሚኒኬሽን እውቅናና ፈቃድ ውጭ ሶፍትዌሮችን በመገልግል በኢንተርኔት ስልኮች በማስደወል ከፍተኛ ገንዘብ መሰብሰባቸውንና መጠኑ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ የቴልኮሙኒኬሽንን መስርያቤት ማስጣታቸውን ተረጋግጦባቸው አልተከላከሉም። በክሱ ላይ የተገለጹት 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች መከላከላቸው የተረጋገጠ ስለሆነ ጉዳዩ የሙስና ወንጀል መሆኑ ይቀራል ይህ በመሆኑም በ1ኛ ክስ የቀረበባቸው ዘጠኝ ተከሳሾች (3ኛ፣ 5ኛ፣ 6ኛ፣ 7ኛ፣ 9ኛ፣ 11ኛ፣ 12ኛ እና 13ኛ ተከሳሾች) በህገወጥ መንገድ ስልክ በማስደወል ስልክ ለማስደወል ሶፍትዌሮች ማስደወያ ካርድ ቁጥሮችን በማከፋፈል ለአገኙት ህገወጥ ጥቅምና ለአሳጡት ጥቅም ተጠያቂና ጥፋተኛ የሚሆኑት በሙስና ወንጀል መሆኑ ቀርቶ ተከሳሾች ላጠየቁ የሚገባቸው በኢትዮጵያ ቴልኮሚኒኬሽን አዋጅ ቁጥር 49/1989 ለማሻሻል የወጣው አዋጅ ቁጥር 281/1994 አንቀጽ 23 ንኡስ አንቀጽ 11(4) ድንጋጌ ኢንተርኔት በመጠቀም የድምጽ መልእክትን ማስተላለፍ ወይም የማስተላለፍ አገልግሎት መስጠት ድንጋጌ ተላልፎ መገኘት በመሆኑ የተከሰሱበትን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32(1) (ሀ)፣ 33፣ 411(1) (ሐ) እና (2) ድንጋጌዎች በወ/መ/ስ/ስ/ቁ. 113(2) በመለወጥ ከላይ በተጠቀሰው የአዋጅ ቁጥር 281/1994 አንቀጽ 2 ንዑስ አንቀጽ 13 ድንጋጌ ጥፋተኛ ናቸው በማለት በአብላጫ ድምጽ ፍርድ ሰጥቷል።
የስር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙ ክርክር የመረመረ ሲሆን ወንጀሉ በከፍተኛ ደረጃ መድቦ ቅጣቱ ፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባወጣው መመሪያ ቁጥር 2/2006 መሰረት በማስላት ወስኗል።
ድንጋጌው ከ3 እስከ ከ5 አመት የሚያስቀጣ በመሆኑ ለከባድ ወንጀል የቕጣት መነሻና መድረሻ ከ4 ዓመት አስከ 4 ዓመት ከ6 ወር የሚያስቀጣ በመሆኑ በእርከን 18 የሚውድቅ ነው። በአሁኗ አመልካች የቀረበው አንድ የቅጣት ማቅለያ ተቀብሎ በእርከን 17 ስር በ3 አመት እንዲትቀጣ፤
የገንዘብ መቀጮ በተመለከተ ከኢፍድሪ የኢንፎርመሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በ11/04/2003 ዓ/ም በተጻፈ ደብዳቤ መሰረት በአሁኗ አመልካች ተሰበሰበ የተባለው የገንዘብ መጠን 3,895,200 (ሶስት ሚላዮን ስምንት መቶ ዘጠና አምስት ሺ ሁለት መቶ) ያለፈቃድ በሰሩበት ጊዜ ውስጥ አግኝተውታል ተብሎ የቀረበባቸውንና በመከላከያቸው ያላስተባበሉት ገንዘብ እጥፍ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ያደረጉ ሲል ፍርድ ሰጥቷል።
የአሁኗ አመልካች የስር ፍርድ ቤት የሰጠው የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በመቃወም ለፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት አላገኘም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበገውም የስር ፍ/ቤቶች በሰጡት ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል በማለት ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- የወንጀል ድርጊቱ እንዳልፈጸሙ፤ በማስደወል አገኙት የተበለው ገንዘብም ሆነ በመንግስት ላይ ደረሰ የተባለው ጉዳት አልተረጋገጠም፤ የተወሰነው የእስራት ቅጣት ይሁን የገንዘብም መቀጮ የግህ መሰረት የለውም በማለት መከራከራቸውን ያሳያል። የአሁኑ ተጠሪ በበኩሉ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ የተፈጸመው የወንጀል ድርጊት ያገናዘበ ስለመሆኑ ላጸና ይገባል በማለት መልስ አቅርበዋል።
የመልስ መልስም ቀርባዋል።
ከስር የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆነ እኛም ግራ ቀኘ በጽሁፍ ያደርጉት ክርክር ፤ ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ውሳኔ አግባብነት ካለው ድንጋጌ ጋር በማገናዘብ እንዲሁም ጉዳዩን ለሰበር ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር እንዲሚከተለው መርምረናል። ጉዳዩን ለሰበር ሲቀርብ የተያዘው ጭብጥ በስር ፍ/ቤት የተሰጠው የጥፋተኝነትና የእስራት ቅጣት በአግባቡ ሆኖ በወንጀል ስራ ምክንያት አመልካች አግኝታለች የተባለው የገንዘብ መጠን የተወሰነበት ስርዓት በህጉ አግባብ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ነው።
ጉዳዩ እንደመረመረነውም አመልካች ፈቃድ ሳያወጡ ወይም የፀና ፈቃድ ሳይኖራቸው ስልክ በማስደወላቸው ጥፋተኛ ተብሐል። የስር ፍርድ ቤት ባደረገው ማጣራት የአሁኗ አመልካች ምንም ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸው ስልክ በማስደወል 0.00 እንደሰበሰቡ ቴልኮሚንኬሽን ደግሞ 0.00 ማጣቱን ከኢፍድሪ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ማስረጃ መቅረቡን በውሳኔው አስፍሯል። አመልካች የወንጀል ድርጉቱን አልፈጸምኩም፣ ስልክ በማስደወል ገንዘብ አላገኘሁም በማለት የተከራከሩ ቢሆንም የስር ፍ/ቤት በውሳኔው እንደገለጸው የቀረበው ማስረጃ የሚያስተባብል ነገር አለማቅረባቸውን ነው። የስር ፍርድ ቤት ፍሬ ነገር በማጣራት እና ማስረጃ በመመዘን ረገድ የሚደርስበት ድምዳሜ ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት እንዳለ የሚቀበለው እንጂ በድጋሚ የሚያጣራበት ስርዓት የልለ ስለመሆኑ ከኢፍድሪ ህገመንግስት አንቀጽ 80(3) (ሀ) እና አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 10 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ነው። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት በፍሬ ነገር ደረጃ ያረጋገጠው የአሁኗ አመልካች (የስር 9ኛ ተከሳሽ የነበሩ) ያለ ፈቃድ ስልክ በማስደወል ሶስት ሚላዮን ስምንት መቶ ዘጠና አምስት ሺ ሁለት መቶ ብር ጥቅም እንዳገኙ ነው። ይህ የፍሬ ነገር ድምዳሜ ይዘን የአዋጅ ቁ
No topics extracted.