በወንጀል ጉዳይ ተከሳሽ በልለበት ጠበቃ ብቻውን ላቀርብ አይችልም የሚለው ጉዳይ ተፈፃሚ የሚሆነው ለተፈጥሮ ሰዎች እንጂ የህግ ሰውነት ላላቸው ሰዎች ስላለመሆኑ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.127
No summary available.
የሰ/መ/ቁ/120762 የካቲት 25 ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ተኽላት ይመሰል እንዳሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- የፍደራል ዐቃቤ ሕግ - ሮዛ በላቸው ቀረቡ ተጠሪ፡-
ይህ የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የቻለው አመልካቾች ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ታህሳስ 28 ቀን 2007 ዓ.ም በሰጠው ትእዛዝ ላይ የቀረበውን ይግባኝ የፍደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ጥቅምት 1 ቀን 2008 ዓ.ም ይግባኝ የሚባልበት አይደለም በማለት መዝገቡን በመዝጋቱ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለቱ ነው።
ጉዳዩ የሕግ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት የወንጀል ክስ በቀረበበት ጊዜ በጠበቃ የመወከል ላይ የተሰጠ ትእዛዝ ይግባኝ ላቀርብበት የሚገባ መሆን አለመሆኑን የሚመለከት ነው። በስር ፍ/ቤት ከሳሽ አመልካች ሲሆን ተከሳሾች እነአሽረፋ አወል አብዩ /17 ሰዎች/ ሲሆን ተጠሪዎች 12ኛ እና 13ኛ ተከሳሾች ነበሩ። አመልካች በተከሳሾች ላይ 6 የተለያዩ ክሶችን ያቀረበ ሲሆን በተጠሪዎች ላይ ያቀረበው ክስ 3ኛ ክስ የወ/ህ/ቁ 32/1/ /ለ/፣ 34/1/ እና የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 96 የተመለከተውን በመተላለፍ የንግድ ትርፍ ግብር ባለመክፈል፣ 4ኛ ክስ የወ/ህ/ቁ 32/1/ /ለ/፣ 34/1/ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 49 በመተላለፍ ግብይት ባካሄዱባቸው ሥራዎች ተጨማሪ እሴት ታክስ አሳውቆ ባለመክፈል፣ 5ኛ ክስ የወ/ህ ቁጥር 32/1/ /ለ/34/1/ እና የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 37/1/ /ሀ/፣/ለ/ እና 3/ለ/ በመተላለፍ ለባለሥልጣኑ መስሪያ ቤት መካተት የሚገባውን ነጥብ በማስቀረትና ሀሰተኛ ወይም አሳሳች ማስረጃ በማቅረብ 6ኛ ክስ የወ/ህ/ቁ 32/1/ /ሀ/ /ለ/፣ 34/1/ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 50/1/1ሀ/ /ለ/ እና /3/ በመተላለፍ ለግብር ሰብሳቢ ባለሥለጣን መሥሪያ ቤት መካተት የሚገባውን ነጥብ በማስቀረት እና ሀሰተኛ ወይም አሳሳች ማስረጃ በማቅረብ የሚሉ ሲሆኑ 12ኛ ተከሳሽ የነበረው 1ኛ ተጠሪ በፍ/ቤቱ ጥሪ መሰረት 13ኛ ተከሳሽ የነበረው 2ኛ ተጠሪ በጋዜጣ ጥሪ መሰረት ጠበቃው ቀርበው የክሱ ማመልከቻ የደረሳቸው ሲሆን ፍርድ ቤቱ በጋዜጣ ተጠርተው ባልቀረቡት ላይ በልሉበት ክርክሩ እንዲቀጥል አዞ በክሱ ላይ የተጠሪዎች ጠበቃን መቃወሚያ መቀበል ሲጀምር አመልካች የተጠሪዎች ሥ/አስኪያጅ እና ባለቤት የሆኑት በክሱ በተራ ቁጥር 14፣15 እና 16 የተጠቀሱት ከህግ ተሰውረዋል። ስለዚህ እነዚህን የወከሉ ጠበቃ ለድርድቶቹም መከራከር አይችሉም። ድርጅቶቹ የሚከሰሱት ሥ/አስኪያጅ ወይም ሰራተኞች በፈፀሙት ድርጊት ነው። ሥ/አስኪያጅ በልለበት እንዲታይ ከታዘዘ የድርጅቶቹም ጉዳይ በልሉበት መታየት አለበት በማለት ያቀረበው ከአቤቱታ በመመርመር አመልካች ያቀረበው ክስ የድርጅቶቹ ከሥራ አስኪያጆች የተለያየ ነው። በጠበቃ የመወከል መብት ደግሞ ለሁሉም እኩል የሚያገለግል መብት ነው። አንድ ድርጅት በወንጀል ህግ ድንጋጌ ተከሳሽ ለመሆን የሚያበቃ ሁኔታ አለ ተብሎ ክስ ከቀረበ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 20/5/ መሰረት በጠበቃ የመወከል መብት አለው ይህንን የሚጻረር አሰራርም ሆነ ልላ ህግ ተፈጻሚነትየልለው መሆኑን ይደነግጋል ስለዚህ የአሁን ተጠሪዎች በጠበቃ መወከል ይችላሉ አለ።
አመልካች ይህንን ትእዛዝ በመቃወም ያቀረቡትን ይግባኝ የተመለከተው የፍደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም በሰጠው ውሳኔ ዳኝነተት የሚታየው በህጉ በተመለከተው መሰረት ነው። በወ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ 184 እና 185 በግል ይግባኝ የሚባልባቸውን ምክንያቶች በዝርዝር የተቀመጠ በመሆኑ አሁን ይግባኝ የተባለበት ጉዳይ ወደፊት በክርክር መጨረሻ ውሳኔ ሲሰጥ ተጠቃልሎ ይግባኝ ላባልበት የሚችል እንጂ አሁን በዚህ ደረጃ ይግባኝ የሚባልበት አይደለም በማለት ዘግቶታል። የአመልካች 8 ገጽ የሰበር አቤቱታ መሰረት ያደረገውም በዚሁ ውሳኔ ሲሆን ይዘቱም የወ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ 184 ይግባኝ የማይባልባቸውን ትእዛዞች የሚዘረዝረው ሆኖ በስር ፍ/ቤት ይህንኑ በመጥቀስ ውድቅ ማድረጉ መሰታዊ ስህተት ነው። የወ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ 185 የጥፋተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ ላይ የሚቀርብ እንጂ ከዚህ ውጭ በሆኑ ጉዳዮች ይግባኝ ማለት ይቻላል አይልም። ከቁጥር 184 ጋር ተጣጥሞ ላተረጐም የሚገባና ከሰበር መ/ ከተሰጠው ትርጉም ጋር የሚጋጭ ነው።
የወ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ 127/1/ በወንጀል ጉዳይ ተከሳሽ በልለበት ጠበቃ ብቻውን ላቀርብ እንደማይችል የሚያሳይ ነው። የተከሳሽ በጠበቃ የመወከል መብት የተቀመጠው ተከሳሹ በቀረበ ጊዜ ተፈጻሚነት ያለው እንጂ ለመቅረብ ፈቃደኛ ባልሆነ ጊዜ አይደለም። የወ/ህ/ አንቀጽ 34/1/ እንደተመለከተው ድርጅት በወንጀል የሚጠየቀው የድርጅቱ ኃላፊ ወይም ሰራተኛ በሰራው ወንጀል በመሆኑና ለጠበቃው ውክልና የሰጠው 15ኛ ተከሳሽ የሆነው የ12ኛ እና 13ኛ ተከሳሽ ድርጅቶች ባለቤትና ሥራ መሪ ከቀረበባቸው ክስ ተሰውረው በልሉበት እየታየ በጠበቃ ተወክለው መከራከር የህግ መሰረት የለውም፣ በወንጀል ጉዳይ ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶት ከድርጅቱ ባለቤት ወይም ሥራ አስኪያጆችና ሰራተኞች ተነጥለው የሚታይ አይደለም። ተጠሪዎች በ15ኛ ተከሳሽ በተሰጠ ውክልና እንዲከራከሩ መፍቀድ በልሉበት እንዲታይ ብይን የተሰጣቸውን ተከሳሾች በጠበቃ እንዲከራከሩ የመፍቀድ ውጤት አለው። ስለዚህ በወንጀል ፍትህ ሥርዓቱ ላይም ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድር በመሆኑ እንዲሻርልኝ የሚል ነው።
ፍርድ ቤቱም የስር የፍደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ ከወ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 184 እና 185 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ጋር አገናዝቦ ለመመርመር ለሰበር ችሎት ያስቀርባል በመባሉ ተጠሪዎች በሰጡት መልስ የስር ፍ/ቤት ተጠሪዎች በጠበቃ መወከል አይችሉም በማለት አመልካች ያቀረበው ተቃውሞ የመሰረታዊ ህግም ሆነ የስነ-ሥርዓት ህግ መሰረት የልለው በመሆኑ ፍ/ቤቱ በወ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ 184 ውጭ በመሆኑ ላያልፈው ይገባ ነበር፣ በጠበቃ የመወከል መብት ሕገ-መንግስታዊ ሆኖ በአንቀጽ 20/5/ የተደነገገ ሲሆን አመልካችም በውጤት ደረጃ በወንጀል ፍትህ ሥርህቱ የሚያስገኘው አሉታዊ ተጽዕኖ አንጻር አክብሮ ላቀበለው የሚገባ ነው፣ ሰበር መ/ የሰጠው ውሳኔ በወ/ህ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 185 /2/ የይግባኝ መብቱ የተገደበውን አመልካችን የሚመለከት አይደለም። ከአመልካችና ከተጠሪ ክርክር ጋር ግንኙነት የልለው በመሆኑ ለጉዳዩ አግባብነት የለውም፣ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች በመልስ ሰጪዎችላይ የወንጀል ዳኝነት ሥልጣን የላቸውም፣ የወ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 127/1/ እና 197 ተፈጻሚ የሚሆነው ለተፈጥሮ ሰዎች እንጂ የህግ የሰውነት ባላቸው ሰዎች አይደለም፣ አንድ ሰው በግሉ የተከሰሰበት ጉዳይ በሥ/አስኪያጅነት ከሚመራው የህግ ሰውነት ካለው ድርጅት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፣ ውክልና ለመስጠት መብት ያለው የተፈጥሮ ሰው ስለድርጅቱ በመሆን ጠበቃ መወከል የተፈቀደ ተግባር ነው። ተጠሪዎች ከ14፣15 እና 16ኛ ተከሳሾች ጋር ፈፀሙ ያለው ተግባር ምንም ግንኙነት የለውም ተጣምረው ወይም በግብረ አበርነት የቀረበባቸው ክስ የለም፣ የወ/ህ/ቁ 34/1/ ተፈጻሚ የሚሆነው በኢትዮጵያ ለተመዘገቡ ድርጅቶች ሲሆን ተጠሪዎች ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ያልተመዘገቡ ዓለምዓቀፋ የንግድ ድርጅቶች ናቸው ስለዚህ በተጠሪዎች ላይ ተፈጻሚነት የለውም፣ የድርጅት የወንጀል ኃላፊነት የሥ/አስኪያጅ የወንጀል ኃላፊነት አያስከትልም 15ኛ ተከሳሽ የተከሰሰው በራሱ በግሉ ሲሆን ከተጠሪዎች ጋር ክስ አልቀረበበትም፣ ልሎች በአመልካች ተነስተዋል ባሉት ነጥብም በዝርዝር መልስ ሰጥተዋል። አመልካችም የመልስ መልስ አቅርበዋል።
የክርክሩ አጠቃላይ ሂደት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የተነሱትን ክርክሮች ያስቀርባል ከተባለበት ጭብጥ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል።
አመልካች በእነ አሽረፍ አወል /17 ሰዎች/ ላይ በፍደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረበው የወንጀል ክስ የአሁን ተጠሪዎች 12ኛ እና 13ኛ ተከሳሾች በመሆን በጠበቃቸው አማካኝነት በችሎት የተገኙ ቢሆንም አመልካች ተከሳሾች ያልቀረቡና ሥራ አስኪያጆችም በልሉበት ክርክሩ እንዲሰማ ትእዛዝ ተሰጥቶ ባለበት እነዚህ ተከሳሾች በጠበቃ ተወክለው መከራከር አይችሉም በማለት የቀረበውን ተቃውሞ ፍርድ ቤቱ ውድቅ በማድረግ ትእዛዝ የሰጠ ሲሆን በዚሀ ትእዛዝ ላይ የቀረበውን ይግባኝ ሰሚው የፍደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወደፊት በክርክሩ መጨረሻ ውሳኔ ሲሰጥበት ይግባኝ ላባልበት የሚችል እንጂ በዚህ ደረጃ ይግባኝ የሚቀርብበት አይደለም በማለት በወ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 184 እና 185 መሰረት መዝገቡን ዘግቷል። ስለሆነም በዚህ ሰበር ችሎት በቅድሚያ መታየት ያለበት ተጠሪዎች በጠበቃ ላወከሉ ይገባል ወይስ አይገባም የሚለው ጭብጥ እና አመልካችና ተጠሪ በሰፊው ያደረጋቸውን ክርክሮች ሳይሆን ተጠሪዎች በጠበቃ ላወከሉ ይገባል በማለት የፍደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰጠው ትእዛዝ ላይ ይግባኝ ላቀርብ አይገባም በማለት የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይ/ሰሚ ችሎት በሰጠው ውሳኔ ላይ መሰታዊ ስህተት መኖር አለመኖሩን ነው።
የፍደራሉ ጠቅላይ ፍድ ቤት ለውሳኔው መሰረት ያደረገው የወ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 184 የትእዛዝ ይግባኝ ስላለመኖሩ እና የወ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 185 የጥፋተኝነት ውሳኔ በተሰጠበት ወይም በቅጣቱ ይግባኝ ስለማለት የሚደነግገውን ነው።
ይግባኝን በተመለከተ መሰረቱ የኢ.ፍ.ድ.ሪ ሕገ-መንግስት ሲሆን የተከሰሱ ሰዎችን መብት በሚደነግገው አንቀጽ 20/6/ ላይ ክርክሩ በሚታይበት ፍርድ ቤት ትእዛዝ ወይም ፍርድ በተሰጠባቸው ጉዳዮች ላይ ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ይግባኝ የማቅረብ መብት ያላቸው መሆኑን ይደነግጋል። ስለዚህ አንድ የበታች ፍርድ ቤት በሰጠው ትእዛዝ ወይም በፍርዱ ቅር የተሰኘና ፍትህ ተዛባብኝ የሚል ተከራካሪ ወገን ቅሬታውን ለበላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ ፍርዱ እንዲመረመር እና ተፈፀመ ያለው ሥህተት እንዲታረምለት ይግባኝ የማለት መብት ተሰጥቶታል።
የሥነ-ሥርዓት ህጐች ዋናው ዓላማ ፍትሐዊ ኢኰኖሚያዊና አፋጣኝ በሆነ መንገድ ክርክሮች እንዲያልቁ ማስቻል በመሆኑ ፍርድ ቤቶች የሥነ-ሥርዓት ህጉን አስመልክቶ ክርክሮች ሲቀርቡ ከተከራካሪ ወገኖች መብት አልፎም የሕዝብን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅና የተፋጠነ ፍትህ ለመስጠት በሚያስችል መልኩ መተርጐም ይኖርባቸዋል። ከዚህም አንጻር በወንጀል ክስ ጉ ዳይ ይግባኝ የሚባልባቸውን የፍርድ ቤት ውሳኔዎች የወ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 181 ስለ ይግባኝ መሰረቱ ላዘረዘር የሥረ-ነገር ክርክሩን የሚያቋርጡ መሆናቸውን የሚያመለክት ሲሆን ይኸውም የጥፋተኝነት ውሳኔ፣ የቅጣት ውሳኔ፣ ለጊዜው የመለቀቅ /Discharge/ እና በነፃ የመለቀቅ ውሳኔ /aquittal/ መሆናቸውን ያመለክታል። ነገር ግን የሥረ-ነገር ክርክር የሚያቋርጡ እንደቀጠሮ መስጠት አለመስጠት እንደማስረጃ መቀበል አለመቀበል የመሳሰሉት የብይን /ትእዛዝ/ ሁኔታዎች ወዲያውኑ ይግባኝ የማይባልባቸው ናቸው ሆኖም ግን በእነዚህ ብይን/ትእዛዞች ላይ ወዲያውኑ ይግባኝ ለማለት ባይቻልም ፍርድ ቤቱ ነገሩን ሰምቶ የመጨረሻ ውሳኔ በሚሰጥበት ጊዜ ፍርዱን በመቃወም ይግባኝ ሲቀርብ እነዚህን በክርክሩ ሂደት የተሰጡ እትዛዞች የቅሬታው ምክንያት ላሆኑ እንደሚችሉ የወ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 184 መደንገጉ የተፋጠነ ፍትህ የማይግኝት ህገ-መንግስትዊ መብት ያለውን ተከራካሪ ተጠቃለው መታየት በሚችሉ ሁኔታዎች ምክንያት ክርክሩ እንዳይዘገይ የማድረግ ዓላማ ያለው መሆኑን የማያስገነዝብ ነው።
በዚህ በያዝነው ጉዳይም የስር ፍርድ ቤት ይግባኝ ላባልበት የሚገባ አይደለም ያለው በወ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 181 እንደተመለከተው የሥረ-ነገር ክርክሩን የማያቋርጥ እና ፍርድ ቤቱ ነገሩን ሰምቶ የመጨረሻ ውሳኔ በሚሰጥበት ወቅት የቅሬታ ምክንያት ሆነ ተጠቃሎ ይግባኝ ላባልበት የሚችል መሆኑን መሰረት በማድረግ ነው። አመልካች የሰበር መ/ የተሰጠን አስገዳጅ የህግ ትርጉም መሰረት በማድረግ ያቀረቡት መከራከሪያም ቢሆን ጉዳዩ የክስ ማሻሻልን የሚመለከት ሆኖ የተሰጠው ትእዛዝ በቀጣይ የወንጀል ክርክር ሂደት ጋር የሚያስተሳስረው ነገር ባለመኖሩ ድጋሚ ክርክር የሚቀርብበት ዕድል የልለ በመሆኑ ትእዛዙ የመጨረሻ በመሆኑ ከዋናው ክርክር ጋር ተጠቃልሉ ይግባኝ ላባልበት የማይችል መሆኑን መሰረት በማድረግ የተሰጠ በመሆኑ ጠበቃ በመወከል ላይ በተሰጠው ትእዛዝ ጋር ተመሳሳይነት የላቸውም።
በአጠቃላይ የፍደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተጠሪ በጠበቃ መወከልን አስመልክቶ በተሰጠው ትእዛዝ ላይ ይግባኝ ላቀርብበት የሚገባ አይደለም በማለት የሰጠው ውሳኔ ከወ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 181, 184 እና 185 አንጻር መሰረታዊ ሥህተት የተፈፀመበት ሆኖ አልተገኘም። ስለሆነም ተከታዩ ተወስኗል።