በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 188/5/ መሰረት አንድ ፍርድ በተከሳሽ ላይ ከተሰጠ ተከሳሹ ለበላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብሎ ሲቀርብ የበታች ፍርድ ቤትን ውሳኔ የበላይ ፍርድ ቤቱ ማገድ የሚችልበትን አግባብ የሚያሳይ ድንጋጌ ከመሆኑ ውጪ ከሳሽ ወገን በተከሳሽ ነፃ መለቀቅ ላይ ይግባኝ ብሎ ሲሄድ ፍርዱ እንዳይፈፀም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለመስጠት መነሻ የሚያደርገው ሀብታሙ አያልው እና የፍድራል ዐቃቤ ህግ XV
No summary available.
ቀን 24/05/2008 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ተኽላት ይመሰል እንደሻው አዳነ ቀንዓ ቂጣታ አመልካች፡- ሀብታሙ አያልው - ጠበቃ አመሃ መኮንን - ቀረቡ ተጠሪ፡- የፍድራል ዐቃቤ ህግ - ዐ/ህግ ብርሃኑ ወንድምአገኘሁ - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቶአል።
ጉዳዩ አንድ በሽብር ወንጀል የተከሰሰ ሰው ከክሱ ምንም መከላከል ሳያስፈልገው በነጻ ሲሰነበት በዚሁ ብይን አቃቤ ህግ ይግባኝ ለበላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ የስር ፍርድ ቤት የነጻ መለቀቅ ብይን እንዲታገድለት ሲያመልክት ተቀባይነት የሚያገኝበትን የህግ አግባብ የሚመለከት ነው።
ክርክሩ የጀመረው በፊድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች ከልሎች ዘጠኝ ግልሰቦች ጋር የተከሰሱበት የጸረ ሽብር አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 4 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ተላልፈው በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን ከሽብር ቡድን ጋር የተለያዩ ግንኙነቶች በመፍጥር የሽብር ቡድኑ በኢትዮጵያ ላያደርግ ያሰበውን የሽብር እንቅስቃሴ በመምራት በስሩም አባላትን በመመልመል፣ ከሽብር ድርጅቱ አባልና አመራሮች ጋር ግንኙነት በማድረግ፣ የሽብር ቡድኑን ዓላማ፣ ተግባር እና ተልእኮ ለመፈጸም በመንቀሳቀሳቸው በፈጸሙት የሽብርተኝነት ድርጊት ማቀድ፣ መዘጋጅት፣ ማሴር፣ ማነሳሳት እና ሙከራ ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ነው። አመልካቹ የወንጀል ድርጊቱን ክደው በመከራከራቸው አቃቤ ሕግ አሉኝ ያላቸው ማስረጃዎችን አቅርቦ አሰምቶአል። ከዚህም በኃላ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን መርምሮ አቃቤ ሕግ አመልካቹ የተከሰሱበትን የወንጀል ድርጊት ስለመፈፀማቸው እንደ ክሱ አላስረዳም በማለት አመልካቹን ምንም መከላከል ሳያስፈልጋቸው ከክሱ በነፃ እንዲሰናበቱና ማረሚያ ቤቱም ከእስር ወዲያውኑ እንዲፈታቸው በማለት ትዕዛዝ ሰጥቶአል። በዚህ ብይን የአሁን ተጠሪ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ያቀረበ ሲሆን ይግባኝ ሰሚ ችሎት ጉዳዩን መርምሮ የአሁኑን አመልካች እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ሳይሰጥ አመልካቹ በነፃ እንዲሰናበቱ በተሰጠው ብይን መሰረት ከእስር እንዲለቀቁ የተሰጠው ትዕዛዝ እንዲታገድ የአሁኑ ተጠሪ አመልክቶ ፍርድ ቤቱም የተጠሪን ጥያቄ መነሻ በማድረግ የአመልካችን የነፃ መለቀቅ ትዕዛዝ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 188(5) ድንጋጌ መሰረት ለጊዜው ታግዶ እንዲቆይ በማለት ትዕዛዝ ሰጥቶአል። የአሁኑ የሰበር አቤተታ የቀረበውም ይህንኑ የእግድ ትዕዛዝ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም በስር ፍርድ ቤት አመልካች በነጻ እንዲሰናበቱ የተሰጠው ትዕዛዝ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የታገደው ለጉዳዩ አግባብነት የልለው ድንጋጌ ተጠቅሶ መሆኑን የሚዘረዝር ሲሆን አቤቱታው ተመርምሮም በዚህ ችሎት እንዲታይ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ ቀርቦም ግራ ቀኙ በፅሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጓአል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ትዕዛዝ እና ከግራ ቀኙ ክርክር አንጻር እንደሚከተለው መርምሮታል። እንደመረመረውም በዚህ ችሎት እንዲታይ በሰበር አጣሪ የተያዘው ጭብጥ አመልካች በነጻ እንዲሰናበቱ በስር ፍርድ ቤት የተሰጠው ብይን በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 188(5) ተጠቅሶ መታገዱ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለው በመሆኑ ከዚሁ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለው ተመልክተናል።
በመሰረቱ ፍርድ ቤት በአንድ ጉዳይ ላይ ዳኝነት መስጠት የሚገባው በሕጉ የተዘረጋውን ስርዓት መሰረት በማድረግ ነው። በሕጉ የተዘረጋውን ስርዓት መሰረት አድርጎ ዳኝነት በመስጠት ሂደት ደግሞ ለጉዳዩ አግባብነት ያለውን ድንጋጌ መለየትና ተፈጻሚ ማድረግ የግድ ይላል። የፀረ ሽብር አዋጅ ተጠቅሶ ክስ የቀረበበት ሰው ክርክሩ የሚመራበት አግባብ በአዋጁ አንቀጽ 36 የተመለከተ ሲሆን በዚህ ድንጋጌ መሰረት የጸረ ሽብር አዋጁን መሰረት አድርገው የሚቀርቡ ክርክሮች በአዋጁ በራሱ በተጠቀሱት የስነ ስርዓት ደንቦች እንዲሁም ከአዋጁ ጋር ተቃርኖ ከልለ ደግሞ በ1996 ዓ.ም በወጣው የኢ.ፍ.ድ.ሪፐብላክ የወንጀል ሕግና በ1954ቱ የወንጀለኛ መቅጫ ስነ ሰርዓት ሕግ የሚመሩ መሆኑን ተጠቃሹ የአዋጁ ድንጋጌ ያሳያል። ከዚህ አንፃር ስንመለከተው የጸረ ሽብር አዋጅ መሰረት ክስ ቀርቦበት የአቃቤ ሕግ ማስረጃዎች ከተሰሙ በኋላ አንድ ሰው በነፃ ቢሰናበት አቃቤ ሕግ በጉዳዩ ላይ ይግባኝ ብሎ የስር ፍርድ ቤት የነፃ መለቀቅ ብይንን ማሳገድ የሚችልበት አግባብ መኖር ያለመኖሩን የአዋጅ ቁጥር 652/2001 ድንጋጌዎች አያሳዩም። በአዋጁ አንቀፅ 36 መሰረት የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 188/5/ ድንጋጌ ተፈፃሚ ላሆን ይችላል ወይ? የሚለው ጥያቄ ሲነሳም ይህ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ድንጋጌ አርዕስቱ ፍርድ እንዳይፈፀም ስለማገድ የሚል ያለው ሁኖ ዘርዝሮ ይዘቱ በተለይም የድንጋጌው ንዑስ ቁጥር አምስት ሲታይ ይግባኙ ከመሰማቱ በፊት በማንኛውም ጊዜ ወይም ይግባኙ በሚሰማበት በማንኛውም ጊዜ ፍርዱ እንዲታገድ ለይግባኝ ፍርድ ቤት ማመልከት እንደሚቻል ይደነግጋል። የዚህ ንዑስ ድንጋጌ መሰረታዊ አላማ በአንቀፁ ንዑስ አንድ ድንጋጌ ስር ያለውን ድንጋጌ ዉጤታማ ለማድረግ ነው ተብሎ የሚታሰብ ሲሆን የወንጀል ጉዳይ ከሰው ልጅ ነፃነት፣ ሕይወትና ክብር ጋር እጅጉን የተቆራኘ በመሆኑ በስር ፍርድ ቤት የተሰጠው ፍርድ ቢፈፀም በእነዚህ መብቶች ላይ ላመለስ የማይችል ጉዳት ላደርስ ስለሚችል ከወዲሁ ለመከላከል ነው ተብሎ መሆኑ ይታመናል። በመሆኑም ፍርዱ በተከሳሹ ከተሰጠ ተከሳሹ ለበላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብሎ ሲቀርብ የበታች ፍርድ ቤትን ውሳኔ የበላይ ፍርድ ቤቱ ማገድ የሚችልበትን አግባብ የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 188/5/ ድንጋጌ የሚያስገነዝብ ከመሆኑ ውጪ ከሳሽ ወገን በነፃ መለቀቅ ላይ ይግባኝ ብሎ ሲሄድ ፍርዱ እንዳይፈፀም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለመስጠት መነሻ የሚያደርገው ድንጋጌ ነው ለማለት የሚያስችል ሁኖ አልተገኘም። ሆኖም አንድ ተከሳሽ በነፃ ሲሰናበት አቃቤ ሕግ ይግባኝ ብሎ ፍርዱን ለማሳገድ የሚችልበት የሕግ መሰረት የለም ማለት ግን አይደለም። የፀረ ሙስና ጉዳዩች ላይ ተፈፃሚነት ያላቸው ሕጎችና በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 63 እና 67 ስር የተመለከቱትን ድንጋጌወችን መሰረት በማደረግ በነፃ የተለቀቀ ተከሳሽ በማረሚያ ቤት ሁኖ ጉዳዩን እንዲከታተል ማድረግ የሚቻልባቸው ሁኔታዎች መኖራቸው ግን ላስተዋል የሚገባው ጉዳይ ነው። በመሆኑም የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አመልካች በነፃ እንዲሰናበቱ የተሰጠውን የስር ፍርድ ቤትን ብይን በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 188/5/ መሰረት ያገደው ድንጋጌው ለጉዳዩ አግባብነት ሳይኖረው ሁኖ አግኝተናል።
በልላ በኩል ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ጉዳዩን የተመለከተው የፍርድ ቤቶች መደበኛ የስራ ጊዜ በተዘጋበት ተረኛ ችሎት በተመደበበት አግባብ ሲሆን ዋናውን ጉዳይ ሳይመረምር የስር ፍርድ ቤት ዋና መዝገብ እንደሚመጣ ብሎ ከአዘዘ በኃላ የስር ፍርድ ቤት ዋና መዝገብ ከመቅረቡ በፊት ስለመሆኑ ከትዕዛዙ ግልባጭ ይዘት ተገንዘበናል። የስር ፍርድ ቤት ዋና መዝገብ ቀርቦ መ/ሰጪን የሚያስቀርብ የህግና የፍሬ ነገር ነጥብ ስለመኖሩ የሚያሳይ ትዕዛዙ በተረኛው ችሎት አልተሰጠም። የስር ፍርድ ቤት ዋና መዝገብ ከቀረበ በኋላ በዋናው ጉዳይ ላይ ግራ ቀኙን ለማከራከር የሚያስችል የህግና የፍሬ ነገር ነጥብ መኖሩ ላይ ተገቢውን ትዕዛዝ ላሰጥ የሚችለው መደበናው ችሎት መሆኑን ተረኛው ችሎት በ15/12/2007 ዓ/ም ከሰጠው ትዕዛዝ በኃላ ያሉት ጊዚያትና የክርክር ሂደቶች የሚያስገነዝቡት ጉዳይ ነው። በመሆኑም ዋናውን ጉዳይ ማየት የቀጠለው መደበኛ ችሎት አመልካች ጉዳዩን በውጪ ሁነው የማይከታተሉበት ህጋዊ አግባብ መኖር ያለመኖሩ ላይ አግባብነት ያለውን ህግና ድንጋጌ በመለየት ብይን ላሰጥበት የሚገባ መሆኑን ተገንዝበናል። ስለሆነም የፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚው ችሎት በ15/12/2007 ዓ/ም የሰጠው ትዕዛዝ አግባብነት የልለውን ድንጋጌ መሰረት ያደረገ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
በፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ በ15/12/2007 ዓ/መ የተሰጠው እግድ የህግ መሰረት የለውም በማለት በድምጽ ብልጫ ሽረናል። በልላ በኩል መደበኛው ችሎት በዋናው ጉዳይ ክርክር ቀጥሎ ከሆነ አመልካች ከእስር ውጪ ሁነው ጉዳዩን መከታተል የማይችሉበት የህግ መሰረት መኖር ያለመኖሩን ተመልክቶ ተገቢውን ትዕዛዝ ላሰጥበት ይገባል በማለት ጉዳዩን መልሰንለታል።
መዝገቡ ተዘግቶአል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ብለናል።
No topics extracted.