አቃቤ ህግ በዋስትና መለቀቅ ውሳኔ ላይ ይግባኝ ለመጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ ፍርድ ቤት የዋስትና መብትን የሚከለከልበቻው ምክንያቶች ከተለየዩ ሁኔታዎች በመመልከት ላመዝናቸው የሚገባቸው ስለመሆኑ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር67፣75 XIV
No summary available.
ቀን 22/02/2008 ዓ/ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ ሙስጠፋ መሐመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ስርጋጋ አብረሃ መሰለ አመልካች፡- አቶ ሀሰን አብዳል ጠበቃ ገበዮህ ይርደው ቀርበዋል ተጠሪ፡- የፍድራል ማዕከል ዐቃቤ ህግ የቀረ የለም መዝገቡ ተመርምሮ ተከተዩ ፍርድ ተሰትቷል
በዚህ ጉዳይ አመልካች የፀና ንግድ ፈቃድ ሳይኖረው የንግድ ስራ ሰርቷል በሚል በአዋጅ ቁጥር 686/2002 አንቀጽ 2(3) 31(1) እና 60(1) የተመለከተውን የወንጀል ድርጊት ፈፅሟል በሚል የወንጀል ክስ የቀረበበት ሲሆን ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ እየተመለከተ የነበረው ፍርድ ቤትም የአመልካቾችን ዋስትና መብት በብር 50,000 ወይም ለዚሁ ብቁ የሆነ ዋስትና ከቀረበ በኃላ ከእስር እንዲለቀቅ በሚል የዋስትና መብቱን ጠብቆለታል። ተጠሪ ቅሬታ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት በማቅረቡ ግራ ቀኙን አስቀርቦ በዋስትና ጉዳይ ላይ እነዲከረከሩ ከዳረገ በኃላ የስር ፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ በመሻር የአመልካችን ዋስትና መብት ጥያቄ ከወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 67(ሀ) አንፃር በመካልከል አመልካች ማረሚያ ቤት ሆኖ ጉዳዩን ይከታተል ስል ወስነዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስላወጥ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም በዋስትና መፍቀድ ላይ ዐቃቤ ህግ ይግባኝ ለማለት ስልጣን አለው የሚል አንቀጽ በወ/መ/ስ/ስ/ህጉ ላይም ሳይኖር ፍርድ ቤቱ ይህንኑ ተቀብሎ አከራክሮ ዋስትናውን መሻሩ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለሆነ ላታረም ይገባል፤ ዐቃቤ ህግ አመልካች በዋስትና ቢወጣ የዋስትና ግድታውን አክብሮ አይመጣም ለማለት የቀረበው ምክንያት አድራሻ የለውም ቢፈረድበት ብዙ ዓመት ስለሚቀጣ የሚል ሲሆን አድራሻ የለውም የሚለው አመልካች አድራሻ እንዳለው የተረጋገጠና ላረጋገጥ የሚችል በመሆኑ የዋስትና መብት የሚያስከለክል ሁኔታ ስለልላ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለለበት በመሆኑ ነው ተብሎ ተሽሮ የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ፀንቶ አመልካች በዋስ ሆኖ ጉዳዩን እንዲከታተል የሚል ትዕዛዝ እንደሰጠው የመለከተው። አቤቱታው ተመርምሮ በዚህ ችሎት እንዲታይ የተደረገ ሲሆን ተጠሪም ቀርቦ መልሱን በፅሑፍ ሰጥቶአል።
ይህ ችሎትም አመልካችና አቃቤ ህግ ያቀረቡትን የፅሑፍ ክርክር አቤቱታው ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ ተመልክቶታል። ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሲቀረብ እንዲታይ የተደረገው ጭብጥ ተጠሪ በአመልካች በዋስትና መለቀቅ ላይ ይግባኝ ማቅረብ የሚችል መሆኑ ያለመሆኑን ይህ ቢታለፍ ከሆነም ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ የስር ፍርድ ቤት ትዕዛዝን መሻሩ ከወ/መ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 67(ሀ) እና አዋጅ ቁጥር 686 (2002 አንቀጽ 60(1) ድንጋጌ አንፃር በአግባቡ ነው? ወይስ አይደለም የሚለውን የሚመለከት ነው። በዚህም መሰረት ጉዳዩን እንደሚከተለው ተመልክተናል።
አቃቤ ህግ በዋስትና መለቀቅ ውሳኔ ላይ አቃቤ ህግ ይግባኝ ለመጠየቅ የሚችል መሆን ያለመሆኑን በተመለከተ፡- በመሰረቱ በወ/መ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 75 ርዕሱ ሲታይ በዋስትና ወረቀት እንዲለቀቅ ያልተፈቀዳ ሲሆን ለይግባኝ ፍርድ ቤት ማመልካቻ ስለማቅረብ በሚል የተቀመጠ ሆኖ ዝርዝር ይዘቱ በዋስትና ወረቀት እንዲለቀቅ ያልተፈቀደለት ተካሳሽ ለይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ማመልካቸውን ማቅረብ የሚችል መሆኑንና የጊዜ ገደቡን የሚያስቀምጥ መሆኑ ግልጽ ነው።
ድንጋጌው አቃቤ ህግ የዋስትና መብት ሲፈቀድ ይግባኝ ማቅረብ የማይችል መሆኑን አይደነግግም። የድንጋጌው ይዘትና መንፈስ በስነ ስርዓት ህጉ ስለ ይግባኝ አቅራረብ ከተመለከቱት ድንጋጌዎችና ከወንጀል ሕጉ መሰረታዊ አላማ ሲታይ የዋስትና መብት ጠይቆ ላከለከል የሚችለው ተከሳሽ በመሆኑ ተከሳሹ በህጉ ላኖረው የሚችለውን የመብት ማስከበሪያ መንጋድ ለመጠቆም ተብሎ የተቀመጠ ከመሆኑ ውጭ ህጉ በማይፈቅደው አግባብ የዋስትና መብት የተከበረለት ተካሳሽ ሁሉ ዋስትና መብቱ ተከብሮለት በዋስትና ወረቀት ሲለቀቅ የወንጀል ሕጉን የሚያስፈፅመው አቃቤ ህግ በጉዳዩ ላይ ይግባኝ ለማለት አይችልም በሚል ላተረጎም የማይገባው መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው። በመሆኑም ድንጋጌው የአቀቤ ሕግን ይግባኝ የማቅረብ መብት የማይከለክል በመሆኑ በዚህ ረግድ ይግባኝ ሰሚው ችሎት የፈፀመው መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት አለ ለማለት አልተቻለም።
አመልካች ወደ ፊት ቀጠሮ አክብረው ላቀርቡ አይችሉም ተብሎ ግምት መወሰዱን በተመለከተ፡የስር ፍርድ ቤትም ሆነ ይግባኝ ሰሚው ችሎት በአመልካች ላይ የተጠቀሰው ድንጋጌ በረሱ ዋስትና የሚከለክል አለመሆኑን የተቀባሉት ጉዳይ ነው። ይግባኝ ሰሚው ለዋስትና መከለካል ምክንያት ያደረገው በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ ቁጥር 67(ሀ) ሲሆን ፍረድ ቤቱ ይህንኑ ድንጋጌ ተግባራዊ ሲያደርግ ግምትን መነሻ ለማድረግ የሚችለው ሕጋዊ ስልጣን ያለው መሆኑን ነው። የዋስትና መብት መሰረታዊ የሆነ ህግ መንግስታዊ መብት ቢሆንም ፍፁም መብት ሳይሆን በሕጉ አግባብ ላከለከል የሚችል ነው። ፍርድ ቤት አግባብነት የለውን ልዩ ህግ መሰረት አድርጎ ጉዳዩን ላመዝነውና ተገቢውን ውሳኔ ላሰጥበት የሚገባው ጉዳዩ መሆኑ ግልጽ ነው።
የስር ፍርድ ቤት የአመልካቾች የዋስትና ጥያቄ ያልተቀበለው በወ/መ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 67(ሀ) መሰረት ነው። ይህ ድንጋጌ በዋስትና ወረቀት የመልቀቅ ማመልካቻ ለመቀበል የማይቻልባቸውን ሁኔታዎችን አስቀምጧል። ፍርድ ቤቱ ዋስትናውን ለመከለከል ግምቱን መነሻ የሚያደርግባቸው ሁኔታዎች በተጠቀሰው ድንጋጌ በግልፅ አልተመለከቱም እንዲህ ከሆነ አንድ ተካሳሽ የዋስትና መብት ቢከባርለት ግድታውን የሚፈፅም፣ የማይመስል ነው ተብሎ ግምት የሚወስዳው በቂና እና ህጋዊ ላባሉ በሚችሉ ምክንያቶች ላሆኑ ይግባል ተብሎ የሚታመን ሲሆን ምክንያቶቹ በቂና ህጋዊ ናቸው የሚለው ጉዳዩ ከተለያዩ ከባባዊ ሁኔታዎችና ከጉዳዩ ልዩ ባህሪይ አንፃር እየተየ በፍርድ ቤቱ ግንዘቤ ላወስድባቸው የሚችላቸው ነጥቦች ናቸው ተብሎ የሚታሰብ እንጂ ቁርጥ ያለ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ የሚችልባቸው ሁኔታዎች አሉ ለማለት የማይችልበት ጉዳይ ነው።
ስለሆነም የወ/መ/ስ/ስ/ሕ/ቁጥር 67 በጠቅላላው ሲታይ ፍርድ ቤት የወስትና መብትን የሚከለከልበቻው ሁኔታዎች የሚያሰይ ሲሆን ምክንያቶችን ፍርድ ቤቱ ከተለየዩ ሁኔታዎች በመመልከት ላመዝናቸው የሚገባቸው ሲሆን የድንጋጌው ቅርፅ ይዘትና መንፋስ ሲታይ በሁኔታዎቹ ግምት የመውሰድ የለመውሰድ ጉዳይ የስር ፍርድ ቤት ስልጣን (Discretion) መሆኑን ያሰያል በዚህ ረገድ ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በ
በቀረበው ጉዳይ በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2(1) መሰረት በየትኛውም እርከን የሚገኝ ፍርድ ቤት የሚያስገድድ የሕግ ትርጉም ሰጥቶአል።
ወደ ተያዘው ጉዳይ ስንመለስም ይግባኝ ሰሚ ችሎት የአመልካችን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ያደረገው ቢወጣ የዋስትናውን ግድታ አክብሮ ይገኛል ለማለት የሚችል አይደለም በሚል ምክንያት ነው።
ይህ ግምት መሰረቱ በአመልካች ቋዋሚ አድራሻ አለመኖር ሳይሆን ትኩረት የተሰጠው በአመልካች ላይ የተመሰረተው ክስ ላያስከትል ከሚችለው የእስራት ቅጣት ከፍተኛነትና ከወንጀሉ ልዩ ባህሪይ መሆኑ መገመቱን ፍርድ ቤቱ በውሳኔው ላይ ገልፀዋል።
ፍርድ ቤቱ በእነዚህ ምክንያቶች ላይ በመመስረት ዋስትናውን ከልክለዋል። እነዚህን ምክንያቶች ለግምቱ መነሻ እንዲያደርግ ደግሞ ከላይ እንደተገለፀው በህጉ የተከለከለ ካለመሆኑንም በላይ ግምት የመውሰድ ጉዳይ በህጉ ለፍርድ ቤቱ ስልጣን የተሰጠው ነው። ግምቱ በቂ ነው ወይም አይደለም የሚለው ክርክር ደግሞ የጠቅላላ ሁኔታዎች ምዘና ጉዳይ ነው። ይህ ሰበር ችሎት ደግሞ በኢፍ/ዲ/ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3) ሀ እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 መሰረት የተሰጠው ስልጣን መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የለበትን ማንኛውንም የመጨረሻ ውሳኔ ማረም እንጂ የማስረጃና የልሎች ክባቢያዊ ነገሮችን ምዘና ጉዳይ ተገቢ መሆን ያለመሆኑን አይደለም። ይግባኝ ሰሚ ችሎት ግን ፍሬ ነገሩን የማጠረትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ስላለው ይህ ችሎት የክርክር አጠቃላይ በህሪይ መሰረት በማድረግ የሚዘው ድምዳሜ በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ነው ላባል የሚቸልበት አግባብ የለም። ስለሆነም ይጋባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በኢ/ፍ/ዲ/ሪ/ ህገ መንግስት አንቀጽ 19(6) እና የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 67(ሀ) መሰረት የሰጠው መሳኔ ሕጉ የተሰጠውን ስልጣን መሰረት ያደረገ እና በሕጉ አተረጋጓም አተገባበር ረገድ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አልተገኘም። የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።