በወንጀለኛ ህግ ቁጥር 627(2) መሰረት በክብረ ንህፅና ላይ የሚደረግ ድፍረት የተበዳይ ክብረ ንፅህና በጥቃቱ መገርሰስ ወይም አለመገርሰስ እንደ መስፈርት ላቆጠር የሚገባው መኳንንት ግርማ እና የኦሮሚያ ፍትህ ቢሮ
No summary available.
ቀን ጥቅምት 4/2008 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ አመነው ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብራሃ መለሰ አመልካች፡- መኳንንት ማሞ - አልቀረቡም ተጠሪዎች፡- የኦሮሚያ ፍትህ ቢሮ - አልቀረቡም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች የኢ.ፍ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 627(1) ተላልፎ እድሜዋ 8 ዓመት የሆናት የግል ተበዳይ ሕፃን ያብስራ አብይ ላይ የግብረሥጋ ግንኙነት ፈፅሟል ተብሎ የቀረበበት ክስ የሥር ፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ እና የ16 ዓመት ጽኑ እስራት ቅጣት ወስኖበት በየደረጃው ያሉት ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ስለፀኑበት ውሳኔው መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት ስለሆነ ይታረምልኝ ሲል አመልካች ስለጠየቀ ነው።
የአመልካች የቅሬታ ነጥብ የግል ተበዳይ ክብረ ንፅህና ያልተገረሰሰ ስለሆነ በሙከራ ደረጃ የቀረ ስለሆነ የጥፋተኝነት ውሳኔም ሆነ ቅጣቱ እንዲሻሻል የሚል ነው።
ይህንኑ ጉዳይ ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ያስቀርባል ተብሎ ዐቃቤ ሕግ መልስ ሰጥቷል ።
ዐቃቤ ሕግም የአመልካች ድርጊት በዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ተበዳይን ጨምሮ የተረጋገጠ መሆኑን ጠቅሶ በሥር ፍርድ ቤት የተላለፈው የጥፋተኝነትም ሆነ የቅጣት ውሳኔ በአግባቡ ነው ተብሎ አንዲፀና ተከራክሯል ።በእኛ መኩል ጉዳዩን ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መርምረናል አመልካች የሚከራከረው የሕፃኗ ክብረ ንፅህና አለመገርሰሱ በህክምና ማስረጃ ተረጋግጧል በሚል ምክንያት ድርጊቱ በሙከራ ቀርቷል በማለት ነው።ከመዝገቡ መገንዘብ የተቻለው አመልካች የተከሰሰበትን የወንጀል ተግባር (ድርጊት) ስለመፈፀሙ በዐቃቤ ሕግ ማስረጃ የተረጋገጠ ስለመሆኑ ፍሬ ነገር የመመርመርና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን የተሰጣቸው የሥር ፍርድ ቤቶች ያረጋጡት ጉዳይ ነው ። የድርጊቱ አፈፃፀም ሲታይ አመልካች የወንድ ብልቱን በሕፃኗ የሴት ብልት ውስጥ ማስገባቱ በግል ተበዳይ የተመሰከረ ሲሆን በዚህም ምክንያት ማህፀኗ ላይ የመቅላት ምልክት የታዬ ስለመሆኑ በህክምና ማስረጃ የተረጋገጠ ሲሆን ክብረንፅህና አለመገርሰሱ ድርጊቱን በሙከራ የቀረ ነው የሚያሰኝ ባለመሆኑ የአመልካች ክርክር ተቀባይነት የለውም ። የወንጀል ሕጉ አንቀፅ 627(1) ድንጋጌም ክብረ ንፅህና መኖር አለመኖር ወይም መገርሰስ አለመገርሰስ እንደ መስፈርት ያስቀመጠው ጉዳይ ባለመሆኑ ክርክሩ የሕግ መሰረት የለውም ብለናል።
በቅጣት ረገድ አመልካች ጥፋተኛ የተባለበት አንቀጽ 627(1) ከአሥራ አምስት ዓመት እስከ ሃያ አምስት ዓመት (15-25) በሚደርስ ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ ሲሆን የሥር ፍርድ ቤት በፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወጣውን የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 መሰረት በማድረግ በሕግ ተቀባይነት ያለው እና በማስረጃ የተደገፈ የቅጣት ማቅለያ ተቀብሎ የድንጋጌው መነሻ የሆነ ቅጣት አሥራ ስድስት ዓመት (16) ጽኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት ነው የሚያስኝ የሕግ ምክንያት አልተገኘም ።
በመሆኑም ተከታዩ ተወስኗል።
የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መ/ በ 20/01/07 የሰጠው ትዕዛዝ ፣የኦሮሚያ ጠ/ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ በ 22/11/06 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ እና የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በ 08/09/06 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 195/2-.ለ-.2/ መሰረት ፀንቷል።
መዝገቡ ተዘግቷል። ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ይፃፍ።
No topics extracted.