ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ተከስቷል ላባል የሚችለው በባለእዳው በምንም መልኩ በቅድሚያ ላያስበው ወይም ላገምተው የሚያስችል ክስተት ሲፈጠር ስለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ. 1792 በየብስ የእቃ ማጓዝ ስራን ለመደንገግ ተሻሽሎ የወጣው አዋጅ ቁ. 547/1999
No summary available.
የካቲት 24 ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ተኽላት ይመሰል እንዳሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- የሺ ትራንስፖርት /የሺ ትራንስፖርት የጭነት ማመላለሺያ ባለንብረቶች ማህበር/ ደምሴ ገበየሁ ተጠሪ፡- አቶ እስክንድር ዘርፉ - ዳዊት አባተ መዝገቡ የተቀጠረው መርምሮ ፍርድ ለመስጠት ነው። በመሆኑም ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የቻለው አመልካች የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 13/02/07 ዓ.ም የሰጠውን ፍርድ የፍደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 09/07/0227 ዓ.ም በማጽናቱ መሰረታዊ ስህተት የተፈፀመበት መሆኑን በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለታቸው ነው።
ጉዳዩ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ጉዳት መድረስን የሚመለከት ነው። ክርክሩ የጀመረው በፍደራል የመጀመሪያ ደረጀ ፍ/ቤት ሲሆን ከሳሽ የነበረው የአሁን ተጠሪ ሲሆን አመልካች 2ኛ ተከሳሽ እንዲሁም የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት ትራንዚት ሎጀስቲክ አገልግሎት 1ኛ ተከሳሽ ሲሆኑ ጣልቃ ገብ የነበሩት ደግሞ ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ እና አዋሽ ኢንሹራንስ አ.ማ ነበሩ።
ተጠሪ በተከሳሾች ላይ አቅርቦት የነበረው ክስ ቶዮታ ያሪስ 998 ሲሲ. የሻንሲ ቁጥር VNKKG96320A001372 የ2005 ምርት ዋጋ ብር 3000 ዩሮ የሆነ ከቤልጂየም ኢንትዊፕ ወደብ ኢትዮጵያ ሞጆ ደረቅ ወደብ ለሟጓጓዝ እና ለማስረከብ በሰነድ ቁጥር LAU538 ከ1ኛ ተከሳሽ ጋር ውል የገባ ቢሆንም 1ኛ ተከሳሽ ከተጠሪ ጋር የማጓጓዣ ውል የልለው ንብረትነቱ የ2ኛ ተከሳሽ /የአሁን አመልካች/ የሆነ የሰልዳ ቁጥር 3-51671 ኢት/3-17327 ኢት ተሳቢ በሆነ ተሽከርካሪ ከጅቡቲ ወደ ሞጆ ደረቅ ወደብ ሲጓጓዝ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ሙሉ ለሙሉ ወድማል ስለዚህ በመኪናው የጉዞ ሰነድ ላይ የተቀነሰውን .50 /3000ዩሮ/፣ ለጭነት /1272.76 ዩ.ኤስ.ዲ/ እና ብር 3862.08፤ ለኢንሹራንስ ብር 235.60 እንዲሁም የተቀረጠ ጥቅም በድምሩ .24 እንዲከፍሉኝ የሚል ነው። 1ኛ ተከሳሽ የነበረው የኢትዮጵያ ባህር ትራንዚት ሎጀስቲክ አገልግሎት በሰጠው መልስ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን መኪና ከቤልጂየም ኢንትዋፕ ጅቡቲ ወደብ ለማድረስ በተሰማማው መሰረት ያደረሰ እና ከተጠሪ ጋር በነበረው ውል አጓጓዡ ሁሉንም ወይም ከፊሉን የሟጓጓዙ ሥራ በውለታ ለልላ ማስተላለፍ የምንችል መሆኑ ስለተገለፀ ለ2ተኛ ተከሳሽ የአሁን አመልካች ያስተላለፈ መሆኑን አመልካች ተረክቦ በሟጓጓዝ ላይ እያለ በደረሰ ቃጠሎ መኪናዋ ሙሉ ለሙሉ መውደሟን መኪናው የተጓዘው በመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ውል በመሆኑ በአዋጅ 348/44 መሰረት ኃላፊነት ያለበት አመልካች ነው ስለዚህ ክስ ላያቀርብብን የሚያስችል መብት የለውም ኃላፊ ነው ከተባልንም ልንጠየቅ የሚገባው በዕቃው ክብደት ልክ በኤስ.ዲ.አር ወይም በጥቅል ሲሆን ይህም ነው የሚሆነው እንዲሁም ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ እና አዋሽ ኢንሹራንስ አ.ማ የመድን ሽፋን የሰጡ በመሆኑ ወደ ክርክሩ ይግቡልኝ ብሐል። አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስም ከከሳሽ ጋር ውል የገባው 1ኛ ተከሳሽ በመሆኑ ኃላፊነት የለብንም በከሳሽ መኪና ላይ ጉዳት አልደረሰም፣ መኪናው ጉዳት የደረሰበት በአመልካች መኪና ሳይሆን በደረሰ ቃጠሎ ምክንያት ነው ይህ ደግሞ ከአቅም በላይ የደረሰ ጉዳት ነው። የመኪናው ዋጋ የመድን ውል ሲገባ የተገለፀው .88 እያለ ተጠሪ ያቀረበው ያለአግባብ ነው። በማጓጓዝ የከፈለው ምንዛሬ መሰራት ያለበት መኪናውን ለመጫን በተከፈለ ቀን ነው ተጠሪ አጣሁ ያለውን ጥቅም በተመለከተም የቀረበ ማስረጃ የለም አለ ቢባልም መተካት ያለበት መድን ሰጪው ነው ብሐል። ፍርድ ቤቱም ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ እና አዋሽ ኢንሹራንስ አ.ማ ወደ ክርክሩ እንዲገቡ አዞ መልሳቸውን በዝርዝር አቅርበዋል። ጉዳት ደረሰበት ለተባለው መኪናም የመድን ሽፋን ያልሰጡ መሆናቸውን የገለጹ መሆኑን መዝግቧል። እንዲሁም የአሁን አመልካች በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 256 መረት እንዲቀርብ ጠይቆ መኪናው የተቃጠለበትን ሁኔታ የሚገልይ የፍደራል ፖላስ የምርመራ ዘርፍ የፎረንሲክ ምርመራ ውጤት ለቃጠሎው መፈጠር ምክንያት የሆነው የተሽከርካሪው ተሳቢ የፊት የግራ ጐማዎች የውስጥ ጐማ በመፈንዳቱ ምክንያት ቸርኬው ከመሬት ጋር በመጋጨቱ የተፈጠረ እሳት ከተቀጣጣይ ነገሮች ጋር መያያዙ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ቀርቧል።
ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ በአዋጅ 547/99 አንቀጽ 36 አጋዥ የማጓጓዝን ሥራ በአንድ ውል የሚገዛ ሆኖ በተለያዩ አጓጓዦች በመቀባበል የሚፈጽሙ ከሆነ የመጀመሪያው አጓጓዥ በገባው የመጓጓዣ ውል መሰረት 2ኛ አጓጓዥና ተከታዮች የመጓጓዥያ ሰነዱንና ውሉ የሚያስከትለውን ግድታ በመቀበላቸው የተነሳ የማጓጓዥያ ውሉ ተዋዋይ ወገን ተደርገው በመቆጠሩ እያንዳንዱ አጓጓዥ በተናጠል ስለአጠቃላዩ የማጓጓዝ ስራ ኃላፊነት የሚኖርበት መሆኑ የተደነገገ በመሆኑ ተጠሪ ከ1ኛ ተከሳሽ ጋር የነበረው የማጓጓዥያ ውል ስምምነት መሰረት ከጅቡቲ ወደብ ሞጆ ደረቅ ወደብ ድረስ የማጓጓዝ ሥራ ለአመልካች መስጠቱን በግራ ቀኙ ወይም ውልም ሆነ በህጉ ተቀባይነት ያለው በመሆኑ 1ኛ ተከሳሽ መኪናውን ለአመልካች ካስረከበ በኋላ የተፈጠረ አደጋ በመሆኑ የመጨረሻ ኃላፊነት የሚወድቀው በ2ኛ ተከሳሽ ነው። አመልካች የማጓጓዝ ሥራውን በሚረከብ ጊዚ እንደውሉ አካል የሚቆጠር እና ለሚደርሰው ጉዳት ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ ከተረከበ በኋላ ለተፈጠረው አደጋ አመልካች ኃላፊ ነው በማለት የኋላፊነት መጠን በተመለከተ በአዋጅ ቁጥር 547/99 አንቀጽ 27/3/ እና 29 መሰረት መኪናው የተገዛበት .5፣ የመኪናውን ማስጫኛ እና የኢንሹራንስ ክፍያ በውላቸው አንቀጽ 5/2/ መሰረት ለጭነት ለኢንሹራንስ ብር 235.60 በድምሩ .10 እንዲሁም መኪናው የተገዛበትን ዋጋ ክስ ከቀረበበት 12/04/2005 ዓ.ም ጀምሮ 9% ወለድ ጋር አመልካች ለተጠሪ እንዲከፍል 1ኛ ተከሳሽ እና ጣልቃ ገቦች ከክሱ በነፃ ተሰናብተዋል በማለት ወስኗል።
አመልካች በዚህ ፍርድ ቅር በመሰኘት ያቀረቡትን የይግባኝ አቤቱታ የፍደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባለመቀበል በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 337 መሰረት ሰርዞታል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታም የቀረበው ይህንኑ በመቃወም መሰረታዊ ስህተት ተፈጽሟል በማለት ሲሆን ይዘቱም በክሱ ላይ የተገለፀሙ መኪና ጉዳት የደረሰው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 547/1999 አንቀጽ 10 እና 22 መሰረት ኃላፊነት የለብንም ጉዳት የደረሰበት መኪና ሙሉ በሙሉ ከነወለዱ የምንከፍል ከሆነ ጉዳት የደረሰበትን መኪና /ሰልባጁን/ እንዲመለስልን ላወሰን ይገባ ነበር የሚል ነው። ፍርድ ቤቱም የአመልካችን አቤቱታ መርምሮ እሳቱ የተፈጠረው የመኪናው የውስጥ ጐማ /ከመነዳሪ/ ፈንድቶ ቸርኬው ከመሬቱ ጋር በመጋጨቱ ምክንያት መሆኑ በባለሙያ ከመረጋገጡ አንጻር ክስተቱ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ሥር የሚሸፈን መሆን አለመሆን እና ጉዳት የደረሰበትን መኪና ሙሉ ዋጋ አከፋፈል የመኪናውን ቅሪት አካል /ሰልባጅ/ ተመላሽ እንዲሆን በቃል ክርክር ወቅት ጠይቀው መታለፋን ለመመርመር ያስቀርባል በማለቱ ተጠሪ ለሰጠው መልስ አደጋው የደረሰው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ስለመሆኑ በስር ፍርድ ቤት ያቀረበው ማስረጃ የለም ከፍ/ህ/ቁ 1793 ከተዘረዘረው ምክንያት ውስጥም የሚካተት አይደለም። የደረሰው ጉዳት ለጉዞ ከመሰማራት በፊትም ሆነ በጉዞ ላይ እያለ ተገቢውን ጥንቃቄ ባለማድረግ የደረሰ ጉዳት ነው። በተለይም የእሳት መከላከያና ማጥፊያ ቁሳቁስ በአጓዥ ተሽከርካሪ ውስጥ አለመኖር ወዲያውኑ እንዲጠፋ አላደረገም። ጐማው ሲፈነዳም በጥንቃቄ አቁሞ መቀየር ሲገባው መሄዱ ቸልተኝነቱን የሚያሳይ ነው። በልላ በኩል የተሽከርካሪ አካልን በተመለከተ በስር ፍርድ ቤት አልተነሳም ዳኝነትም አልተከፈለበት፣ አመልካች ይህንን ቅሪትም አላስረከበኝም ስለዚህ የስር ፍ/ቤት ይጽናልኝ ብሐል። አመልካችም የመልስ መልስ አቅርቧል።
የክርክሩ አጠቃላይ ሂደት ከለይ የተመለከተው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ፍርድ እና ያስቀርባል ከተባለው ነጥብ አንፃር አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረነዋል።
የክርክሩ አጠቃላይ ሂደትም የሚያስገነዝበው ተጠሪ አንድ ቶዮታ ያሪስ 998 ሲሲ የሻንሲ ቁጥር VNKKG96320a001372 የ2005 ምርት የሆነች መኪና ከቤልጅየም ኢንትዊፕ ወደብ እስከ ኢትዮጵያ ሞጆ ደረቅ ወደብ ድረስ ለማጓጓዝና ለመረከብ በስር ፍ/ቤት 1ኛ ተከሳሽ ከነበረው ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት ትራንዚት ሎጅስቲክ አገልግሎት ጋር ውል ገብተዋል። ይህ 1ኛ ተከሳሽ በውላቸው ላይ ሁሉንም ወይም ከፊሉን የማጓጓዝ ሥራ በውል ለልላ ማስተላለፍ የሚችል መሆኑን በተስማሙት መሰረት ከጅቡቲ ወደብ እስከ ኢትዮጵያ ሞጆ ደረቅ ወደብ እንዲያጓጉዝ ለአሁን አመልካች ጅቡቲ ወደብ አስረክቧል። አመልካች በዚሁ መሰረት ሲያጓጉዝ የአጓዥ ተሽከርካሪ ተሳቢ የፊት የግራ ጐማዎች የውስጥ ጐማ በመፈንዳቱ ምክንያት ቸርኬው ከመሬት ጋር በመጋጨቱ በተፈጠረ እሳት መኪናው መቃጠሉ ሲሆን ይህም በስር ፍርድ ቤት የተረጋገጡ ናቸው። አመልካች አጥብቀው እየተከራከሩ ያሉት በመኪናው ላይ የደረሰው ጉዳት ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 547/1999 አንቀጽ 10 እና 22 ኃላፊነት የለብኝም የሚል ነው። በየብስ የዕቃ ማጋዝ ስራን ለመደንገግ ተሻሽሎ በወጣው በአዋጅ ቁጥር 547/1999 ዓ.ም ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ “በማለት ምን ማለት እንደሆነ የተመለከተ ነገር ስለልለ ትርጉሙን ለማወቅ ወደ ጠቅላላ ህጉ በተለይም ደግሞ ስለውሎች በጠቅላላ ስለሚመለከቱ ድንጋጌዎች መምራት የግድ ይሆናል። በዚህም መሰረት በፍ/ህ/ቁ 1792 ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ አለ ለማለት የሚቻለው መቼ እንደሆነ የተመለከተ ሲሆን ይህም ከአቅም በላይ የሆነ ላመልሱት የማይቻል ኃይል ደርሷል የሚባለው ባለዕዳው ባላሰበው ነገር ድንገት ደራሽ ሆኖበት ግድታውን እንዳይፈጽም ፍፁም መሰናክል በሆነበት አይነት የሚያግደው ነገር ባጋጠመው ጊዜ እንደሆነ ተመልክቷል። በዚሁ አንቀጽ ንዑስ ቁጥር 2 ደግሞ በአእምሮ ግምት ባለዕዳው ቀደም ብሎ ላያስብበት የሚችል መሆኑ የታወቀ አንድ ድንገተኛ ደራሽ ነገር ወይም ለውሉ አፈጻጸም ከባድ የሆነ ወጪ በባለዕዳው የሚደርስ ቢሆን ከአቅም በላይ የሆነ ኃይል ነው ተብሎ እንደማይገመት ተልክቷል።
ስለሆነም በእነዚህ የህጉ ድንጋጌዎች መሰረት ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ተከስቷል ላባል የሚችለው በባለዕዳው በምንም መልኩ በቅድሚያ ላያስበው ወይም ላገምተው የሚያስችል ክስተት ሲፈጠር ነው። ነገር ግን ባለዕዳው ሁኔታው ላፈጠር ወይም ላከሰት እንደሚችል ቀድሞ ላገምት ወይም ላያስብና ጥንቃቄ ላያደርግበት የሚችል ከሆነ ሁኔታው ድንገት ደራሽ ቢሆንም እንኳን ከአቅም በላይ የሆነ ነገር ተብሎ እንደማይገመት መገንዘብ ይቻላል። በተያዘው ጉዳይም የሥር ፍርድ ቤቱ አመልካችን ኃላፊ ያደረገው የክሱ ምክንያት የሆነው መኪና በእሳት ቃጠሎ ምክንያት ላወድም የቻለው የመኪናው የውስጥ ጐማ /ከመነዳሪ/ በመፈንዳቱ እና ቸርኬው ከመሬቱ ጋር ሲጋጭ ለተፈጠረ እሳት ምክንያት መሆኑን ነው። አመልካች ይህ አጓዡ ላገምተውና ላያስቀረው የማይችል በመሆኑ ሁኔታው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት የተፈጠረ ነው የሚል ነው። ይሁንና የተሽከርካሪው አጓዥ የሆነው አመልካች ተሽከርካሪውን በዚህ አይነት ሥራ በሚያሰማራበት ወቅት ምንም አይነት ቴክኒካዊ ችግሮች እንዳያጋጥሙ ተሽከርካሪው የሚጓዘውን ርቀት የአየር ሁኔታ ልሎች በሚያረጋግጥበት ጊዜ ጐማውን ማየት እና ደረጃውን መገመት የሚቻለው ሲሆን በጉዞ ላይም ችግሩ በድንገት ደርሷል ቢባል እንኳን ላቆጣጠረው የሚችል እና ከአቅም በላይ የሆነ ነገር ነው ተብሎ ላገመት የሚችል መሆኑ የፖላስ ቴክኒካል ማስረጃን የስር ፍርድ ቤት የመዘነበት አግባብ ያስረዳሉ። ስለሆነም የስር ፍርድ ቤት አደጋው የደረሰው የአቅም በላይ በሆነ ምክንያት አይደለም የማለት የደረሰበት ድምዳሜ መሰረታዊ ስህተት ያለበት አይደለም።
በልላ በኩል አመልካች ጉዳት የደረሰበትን መኪና ሙሉ ለሙሉ ከነወለዱ የምከፍል ከሆነ ጉዳት የደረሰበትን መኪና /ሰልባጁን/ እንዲመልስልኝ ላወሰን ይገባ ነበር በማለት ያቀረቡትን አቤቱታ አመልካች ይህንን አስመልክቶ በስር ፍርድ ቤት አንስተው የተከራከሩበት ሁኔታ እንደልለ ተጠሪ የገለፀ ሲሆን የስር ፍርድ ቤት መዝገብም እንደሚያስገነዝበው አመልካች በስር ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሳሽ ከነበረው የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት ትራንዚት ሎጀስቲከ የተጠሪ ንብረት የሆነውንና ለዚህ ክርክር ምክንያት የሆነውን ቶዮታ ያሪስ መኪና ጅቡቲ ወደብ መረከባቸውንና ወደ ኢትዮጵያ ሞጆ ደረቅ ወደብ ሲያጓጉዙ በእሳት ሙሉ ለሙሉ መውደሙን የሚገልጽ ነው። ይህ ደግሞ ጉዳት ደረሰበት የተባለው መኪና በእሳት መውደሙን አላያም በአመልካች እጅ መሆኑን የሚያመለክት ከመሆኑም ባሻገር በስር ፍ/ቤትም አልተነሳም። አመልካች በስር ፍርድ ቤት በህጉ በተቀመጡት ሁኔታዎች መሰረት ላያነሳቸው የሚገቡ እና ያላነሳቸውን መከራከሪያዎች በራሱ ምክንያት ሳያቀርብ እና ተጠሪም ባልተከሪከረበትና ባልተነሳ ሁኔታ በይግባኝ ወይም በዚህ ሰበር ችሎት የቀረበው ከፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 329/1/ እና 182/2 ድንጋጌዎች ዓላማ ጋር የማይጣጣም ነው።
ስለሆነም በዚህ ረገድ ያቀረቡት አቤቱታ ከላይ በተገለጹት ምክንያቶች ተቀባይነት ያላቸው አይደሉም።
በአጠቃላይ የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ፍርድ እና ትእዛዝ መሰረታዊ ሥህተት የተፈፀመበት ሆኖ አልተገኘም። ስለሆነም የሚከተለው ተወስኗል።
የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 13/02/07 የሰጠው ፍርድ እና የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 04/07/2007 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348/1 መሰረት ፀንቷል።
አመልካች ጉዳት የደረሰበትን መኪና ለተጠሪ ስለማስረከባቸው እና የመኪናውን ቅሪት /ሰልባጅ/ አስመልክቶ ክስ ለማቅረብ ይህ ውሳኔ አያግዳቸውም።
ግራ ቀኙ በዚህ ችሎት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ይቻቻሉ።
ት እ ዛ ዝ ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠ ትእዛዝ የስር ፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ የተጀመረው አፈጻጸም እንዲታገድ የተሰጠው የእግድ ትእዛዝ ተነስቷል። ይጻፍ፡
No topics extracted.