የኮንዶሚኒየም ቤት የደረሰው ሰው ልላ የኮንዶሚኒየም ቤት ከደረሰው ሰው ጋር እጣው ከደረሰው አምስት ዓመት ባይሞላውም በልውውጥ(በስምምነት ላቀያየሩ የሚችሉ ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 19/97 አንቀፅ 14(2)
No summary available.
ቀን ጥቅምት 4/2008ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ አመነው ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ አመልካች፡- ወ/ሮ መኪያ አብደላ -ጠበቃ ቶማስ ወ/ሰንበት ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ጣሰው ሸምሱ -ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዳይ የኮንዶሚኒየም ቤት ልውውጥ ውል መሰረት ያደረገ ክርክር ነው።
በስር ፍ/ቤት ከሳሽ የአሁኑ ተጠሪ ሲሆን ክሱም ከአመልካች ጋር ባደረግነው የኮንዶሚኒየም ቤት ልውውጥ ውል መሰረት ቤቱን ታስረክበኝ የሚል ሲሆን አመልካች ክሱ ከደረሳቸው በኋላ ውሉ በተንኮልና በማሳሳት የተደረገ ነው በሚል እንዲፈርስ እንዲወሰን የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ አቅርበዋል። ጉዳዩን በመጀመሪያ ያከራከረው የፍድራል የመ/ደረጃ ፍ/ቤት በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የተደረገው የኮንዶሚኒየም ቤት ልውውጥ ውል የሚፈርስበት ምክንያት የለም አመልካች በዚህ የልውውጥ ውል መነሻም ተጨማሪ ብር 9000 (ዘጠኝ ሺ) መቀበላቸው ስለተረጋገጠ በውሉ መሰረት ይፈጸም በማለት ወሰነ።
አመልካች ለፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው የነበረ ቢሆንም ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን አከራክሮ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ አጽንቷል።
ለዚህ ሰበር ችሎት አቤቱታ የቀረበው በዚሁ ላይ ሲሆን የሰበር ችሎቱም ኮንኮሚኒየም ቤት የደረሰው ሰው እስከ አምስት አመት ድረስ ቤቱን ለልላ ሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ ይችላል ወይ?
የሚለውን ጭብጥ ከአዋጅ ቁጥር 19/1997 አንቀጽ 14(2) አንጻር ለመመርመር ተጠሪ መልስ እንዲሰጡ አዝዟል።
ተጠሪም በግራቀኙ መካከል የተደረገው የቤት ልውውጥ ውል ያልተሻረ እና ጸንቶ ያለ ስለሆነ ላፈጸም ይገባል በማለት ተከራክሯል።
የጉዳዩ አመጣጥና የግራቀኙ ክርክር ባጭሩ ከላይ የተገለጸ ሲሆን እኛም ጉዳዩ ለሰበር ችሎት ያስቀርባል ሲባል የተያዘውን ጭብጥ መሰረት በማድረግ አግባብነት ካለው ሕግ ጋር በማገናዘብ መርምረናል።
ከመዝገቡ መገንዘብ እንደተቻለው መጋቢት 14ቀን 2001ዓ.ም በግራ ቀኙ መካከል በተደረገው የኮንዶሚኒየም ቤት ቅይይር ውል በአመልካች ስም በጀሞ 1ሳይት ብሎክ ቁጥር 1 የሕንጻ ቁጥር 93 የወለል ቁጥር 1 የቤት ቁጥር JG - B 93/9 የሆነው ቤት በተጠሪ ስም ያለው ጀሞ 1ሳይት ቁጥር - 163 ወለል ቁጥር 1 የቤት ቁጥር JC - B – 163/11 በሆነ ኮንዶሚኒየም ቤት በመለዋወጥ መስማማታቸውን ይገልጻል። የቤቶቹ ይዘት በተመለከተ በተጠሪ ስም ያለው ስቱዲዮ ሲሆን በአመልካች ስም ባለ አንድ መኝታ በመሆኑ ይህንኑ በገንዘብ ለማስተካከል ተስማምተው ብር 9000 (ዘጠኝ ሺህ) ተጠሪ ለአመልካች ለመጨመር መስማማታቸውም ተገልጿል።በክርክሩ ሂደትም አመልካች ብር 9000 መቀበላቸው ተረጋጧል።
እንግዲህ ይህ የኮንኮሚኒየም ቤት ልውውጥ በአዋጅ ቁጥር 19/97 አንቀጽ 14/2/ መሰረት የተከለከለ ነው ወይ? የሚለው ጭብጥ ምላሽ ማግኘት ያለበት ጉዳይ ነው።
የአዋጁ አንቀጽ 14(2) ገዢው ጠቅላላው ዋጋውን ከፍሎ ቢያጠናቅቅም ቤቱን ለሶስተኛ ወገን በሽያጭ ወይም በስጦታ ማስተላለፍ የሚችለው ቤቱን ከገዛ 5(አምስት) አመት ሲሞላው ብቻ ይሆናል በማለት ደንግጓል።
ድንጋጌው በግልጽ ቃል የጠቀሰው ቤቱን በሽያጭ ወይም በስጦታ ማስተላለፍ የከለከለ መሆኑን ሲሆን አመልካች በማንኛውም መልክ ማስተላፍን ይከለክላል በሚል ህሳቤ ይከራከራሉ። የተያዘው ጉዳይ የኮንዶሚኒየም ቤት ልውውጥ እንጂ በሽያጭ ወይም በስጦታማስተላለፍ የተመለከተ ባለመሆኑ ሕግ አውጭው ይህንንም ለመከልከል ፈልጎ ቢሆን ኖሮ "በማናቸውም አኳኋን" ማስተላለፍ አይቻልም የሚል አጠቃላይ የሆነ ቋንቋ መጠቀም ይችል እንደነበር መገንዘብ አያዳግትም።
በመሰረቱ እዚህ መነሳት ያለበት መሰረታዊ ጥያቄ በአንድ በኩል አንድ ዜጋ ባፈራው ንብረት የመጠቀም ሙሉ መብት ያለው መሆኑ በልላ በኩል ደግሞ በተያዘው የኮንዶሚንየም ቤት አጠቃቀም መብት ላይ በጊዜ ገደብ በተወሰነ ሁኔታ ገደብ ማድረጉን አስፈላጊነትና አላማ በማመዛዘን የሕጉን አላማ በሚያሳካ መልኩ ማስተግበር መቻሉን ማረጋገጥ ነው።
ስለሆነም በእጣ የደረሰው ሰው ቤቱን በሽያጭም ሆነ በስጦታ ለሶስተኛ ወገን እስከአምስት አመት ጊዜ ድረስ ማስተላለፍ አይችልም ተብሎ በሕገ መብቱ ሲገደብ ታሳቢ የተደረገው ጥቅም የራሱ የመብቱ ተጠቃሚ የሆነው ባለእጣ መሆኑን ግልጽ ነው። ይኸውም የአዋጅ መግቢያ እንደሚያመላክተው በከተማ ውስጥ ያለውን አነስተኛ የመጠለያ ችግር መቅረፍ እና በሂደትም ነዋሪው የቤት ባለቤት እንዲሆን ማስቻል ነው።
ከዚህ አኳያ የኮንዶሚኒየም ቤት እጣ የደረሰው የከተማው ነዋሪ በተለያዩ ጊዜያዊ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ችግሮች ተገፋፍቶ ቤቱን በሽያጭ ወይም በስጦታ የሚያስተላልፍ ከሆነ ነዋሪው የቤት ባለቤት እንዲሆን በሕጉ ታስቦ የተሰራው ስራ መክኖ ይቀራል የሚል ህሳቤ በመያዝ ምናልባት ችግሮች እንኳን ቢኖሩበት ወይም ልላ ማህበራዊ ምክንያቶች ቢያስገድዱት በ5አመት ቆይታ ጊዜ ስለጥቅምና ጉዳት የማሰላሰያ ጊዜ አግኝቶ አመዛዝኖ ከውሳኔ ይደርሳል ተብሎ ተገምቶ ነው ማለት ይቻላል።
ስለሆነም ወደተያዘው ጉዳይ ስንመለስ አመልካችና ተጠሪ ያደረጉት ውል የኮንዶሚኒየም ቤት ልውውጥ እስከሆነ ድረስ አንዳቸውም ያለቤት ቀርቷል የሚያሰኝ ባለመሆኑ የህጉን ሃሳብና አላማ ይጥሳል ወይም ሕገ-ወጥ ውል ነው ለማለት አልተቻለም።
ይህ ፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መ/ አዋጅ ቁጥር 19/97 አንቀጽ 14(2) ጠቅሶ ውሉ ሕገወጥ ነው በማለት የሰጠው ፍርድ ለተያዘውም ክርክር ተፈጻሚነት ላኖረው ይገባል በማለት በአመልካች በኩል የቀረበውን ክርክር መሰረት አድርገን በመ/ የተሰጠውን ፍርድ ይዘት ስንመረምር ተጠቃሹ መዝገብ ላይ የቀረበው ክርክር የኮንዶሚኒየም ቤት በሽያጭ ለማስተላለፍ የተደረገ ውል የሚመለከት ሆኖ አግኝተናል። ስለሆነም በዚህ መዝገብ ከተያዘው ኮንዶሚኒየም ቤት በልውውጥ ማስተላለፍ ጋር ተመሳሳይ ባለመሆኑ አግባብነት የለውም ብለናል።
ሲጠቃለል አመልካች የኮንዶሚኒየም ቤት ልውውጥ አዋጅ ቁጥር 19/97 አንቀጽ 14(2) ድንጋጌ የተላለፈ ሕገ-ወጥ ውል ነው በማለት ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት አላገኘም። ስለሆነም በስር ፍ/ቤት በዚህ ረገድ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት አልተቻለም።
በልላ በኩል አመልካች በስር ፍ/ቤት ለቀረበባቸው መልስ ሲሰጡ ልውውጥ ከተደረገ በኋላ የቤቱን ማጠናቀቂያ ስራዎች ለመስራት ብር 12,000 (አስራ ሁለት ሺህ) ወጪ ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል። ለዚህም ማስረጃ አለኝ ሲሉ ዘርዝረዋል። ይሁን እንጂ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ሲያቀርቡ ተጠሪ ይህንን ገንዘብ እንዲተካላቸው በተለዋዋጭ (በአማራጭ) ዳኝነት የጠየቁ ስለመሆኑ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ይዘት አያመለክትም።
ስለሆነም ውሉ የጸና ነው የሚለው የስር ፍ/ቤት ውሳኔ በዚህ ሰበር ችሎት የሚሻርበት ህጋዊ ምክንያት ባለመገኘቱ አመልካች ከውሉ በኋላ አወጣሁ ያሉት ብር 12,000 አስመልክቶ ወደፊት የሚጠይቁት ዳኝነት ካለ ይህ ፍርድ አያግዳቸውም ብለናል።
የፍድራል መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ በ22/5/2005 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ እና የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በ4/02/2007ዓ.ም የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ጸንቷል።
የዚህን ፍርድ ቤት ወጪና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ
በዚህ መዝገብ ታህሳስ 15 ቀን 2007ዓ.ም የተሰጠው የእግድ ትእዛዝ ተነስቷል። ይጻፍ።
የስር ፍ/ቤት መዝገብ በመጣበት ሁኔታ ይመለስ። መዝገቡ ተዘግቷል ወደመዝገብ ቤት ይመለስ።
መ/ይ ys¼m¼q$¼98348 ¬HúS 18 qN 2008 ›¼M Ä®CÝxL¥ý wl@ ›l! m/mD t<l!T YmsL XNÄšý xÄn qn› qEȬ xmLμÓCÝ.1ኛ አቶ ዘሪሁን የኔነህ ቀረቡ 2ኛ የአቶ የኔነህ ጨርቆሴ ህጋዊ ወረሾች
በስር ፍርድ ቤት ተከሳሾች የነበሩ የአሁኑ ተጠሪ ጨምሮ መልስ አቅርቦዋል። 1ኛ ተከሳሽ የነበረቸው የሚትከሰስበት ምክንያት እንደልላ፤ ውሉ በ2ኛ ተከሳሽ ፍላጎትና ውሳኔ ተቋርጠዋል፤
በጨረታው አሸናፊ የሆነውን 2ኛ ተጫራች የነበረው ተተክቶ ከ2ኛ ተከሳሽ ጋር የውል ግድታ ገብቶ ሥራን ቀጥሐል። 2ኛ ተከሳሽ የሚጠይቀው ዕዳ የለውም መያዣው ላለቀቅ ይገባል የሚል ይዘት ያለው መልስ ያቀረበች ሲሆን፤ 2ኛ ተከሳሽ (የአሁኑ ተጠሪ) ደግሞ ከአመልካች ጋር የውል ግንኝነት የልለው በመሆኑ ተጣምሮ መከሰስ እንዳልነበረበት ክሱን ንብረቱን በያዘው አካል ላይ ብቻ መቅረብ ያለበት ስለመሆኑ በፍሬ ጉዳዩም የምግብ አቅርቦት ውሉ የተቋረጠው በ1ኛ ተከሳሽ ግድታ ያለመወጣት ምክንያት በመሆኑ ተጠሪ ለተጨማሪ ኪሳራ ተደርጓል። መያዣው ላመሰስ አይገባም የሚል ክርክር አቅርቦዋል 3ኛ ተከሳሽ የነበረው የዳሽን ባንክ 1ኛ ተከሳሽ የውል ግድታቸው ባለመወጣታቸውን በገባው ውል መሰረት የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና ብር 658,568.00 ለሐዋሳ ዩኒቨርሰቲ ገቢ አደርገዋል። መያዣው ላለቅ አይችልም። ክሱ ውድቅ ላደረግ ይገበል የሚል ይዘት ያለው መልስ አቅርበዋል።
የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኃላ በመጀመሪያ ደረጃ የቀረቡ መቃወሚያዎች ውድቅ አድርጓል። በፍሬ ጉዳዩም 2ኛ ተከሳሽ (ተጠሪ) 1ኛ ተከሳሽ በውሉ መሰረት ግድታዋን አልተወጣችም በሚል ያፈረሰው በመሆኑ ተዋዋይ ወገኖች ወደ ነበሩበት ሁኔታ መመለስ የሚገበቸው ነው። ይህ ከሆነ ደግሞ ውሉን ለመፈጸም የተሰራው ሁሉ ቀሪ ሆኖ ውጤት ስለማይኖረው በፍ/ሕ/ቁ. 1815 መሰረት አመልከቾች የገቡት ዋስትና ቀሪ ይሆናል። 2ኛ ተከሳሽ (ተጠሪ) ውሉን እስከ ፈረሰ ድረስ ከ1ኛ ተከሳሽ አለኝ የሚለው ቀሪ ሂሣብ ከለው በህግ ከመጠየቅ ውጭ ለዋስትና ግድታ የተገባው ንብረት ለ3ኛ ተከሳሽ ላከለከል አይገበም። የምግብ አቅርቦት ውሉ ሲቋረጥ መያዣው ይቋረጣል። 3ኛ ተከሳሽ ገንዘቡን መክፈል አልነበረበትም። 3ኛ ተከሳሽ ለመልካም አፈፃፀም የከፈለው ገንዘብ የማስመለስ መብቱ ተጠብቆ ከአመልካቾች የተያዙ መኖሪያ ቤቶችና መኪና የባለቤትናት ማረጋገጫ ሰነዶች ጭምር ይመለስ በማለት ወስኗል።
የአሁኑ ተጠሪ እና በስር ፍርድ ቤት 3ኛ ተከሳሽ የነበረው ዳሽን ባንክ እንደቅደም ተከተላቸው በፍ/ብ/ይ/መ/ቁ. 63309 ለፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ይግባኝ ቅሬታ አቅርበው ተቀባይነት አላገኘም። የአሁኑ ተጠሪ እና በስር ፍርድ ቤት 3ኛ ተከሳሽ የነበረው ዳሽን ባንክ በስር ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረቡት ቅሬታ ተቀበይነት በማግኘቱ ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን በማከራከር የሃዋሳ ዩኒቨርሰቲ በራሱ አነሰሽነት ውሉን ለማቋረጥ የሚችል ስለመሆኑ በሕግ መብት ያለው ቢሆንም እንደ ውሉ ያልፈጸመው ወገን ማን ነው? የሚለውን ክርክር ባስነሳ ጊዜ እና እንደውሉ ባለመፈፀሙ ምክንያት የደረሰው የጉዳት ኪሣራ ምን ያህል ነው? የሚለው ሁሉ የመረጋገጥ ግድታ ስላለበት በዚህ ጭብጥ መሰረት 1ኛ ተከሳሽ ባለችበት የግራ ቀኙ ክርክር እና ማስረጃ ተሰምቶ ላወሰን እንደሚገባ፤ በዚህ ክርክር ውጤት መሰረት በማድረግ የዳሽን ባንክ ለዩኒቨርሲቲው የከፈለው የክፍያ መጠን አግባብ መሆኑና አለመሆኑን ታይቶ አሰፈላጊው ዳኝነት እንዲሰጥበት በጭብጥ የተያዙ ነጥቦች በክርክር እና በማስረጃ መሰረት ተለይቶ ከመታወቁ በፊት በመያዣ የተያዙ ንብረቶች ላለቀቁ አይገበም በማለት ጉዳዩን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343 (1) መሰረት ተጠርቶ እንዲወሰን ለሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት መልሶታል።
የሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የኮ/መ/ቁ. 67820 በማንቀሰቀስ ጉዳዩ በድጋሚ የተመለከተው ሲሆን 1ኛ ተከሳሽ ባለመቅረቧ ክርክሩ በልለችበት እንዲቀጥል አደርጓል፡፤ ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙ ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኃላ 1ኛ ተከሳሽ ከተጠሪ ጋሪ በፈፀመችው የምግብ አቅርቦት ውል ከ11/2/2000 እስከ 11/12/2000 ዓ/ም ለ10 ወር ጊዜ ለማቅረብ የተስማማች ቢሆንም 2 ወር አቅርቦት ከፈጸመች በኃላ በማቋረጧ ተጠሪ ውሉን በ14/04/2000 ዓ/ም በተፃፈ ደብዳቤ ማቋረጡን፤ ለውሉ ማቋረጥ ምክንያትም በጥራትና በጊዜ መቅረብ ባለመቻሉ ስለመሆኑ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ያሰያል። 1ኛ ተከሳሽ ቀርባ አልተከራከረችም በመሆኑም 1ኛ ተከሳሽ ለውሉ መቋረጥ ኃላፊነት ያለበት መሆኑን ማረጋገጥ ተችሎአል። ሁለተኛ ጭብጥ በተመለከተ የጉዳት ከሳ ከደረሰው ጉዳት አንፃር መታየት ያለበት ስለመሆኑ ተጠሪ የገባው ሁለተኛ ውል በመጀመሪያ ውል ከተቀመጠው ዋጋ በልዩነት 1,347,403.02 ተጨማሪ ወጭ የሚጠይቀው መሆኑ መከራከሩን፣ አቅርቦት በመጠን ሲያንስ ሂሳቡ ሲቀነስ እንደነበር ውሉ ከመቋረጡ በፊት የደረሰው ኪሳር ዝርዝር አለመያዙን ውሉ በመቋረጡ ምክንያት የደረሰ ጉዳት ሲመዘንም ከ14/4/2000 እስከ 17/4/2000 ዓ/ም በለው ጊዜ የደረሰ ኪሳራ መሆኑን እንደሚያሳይ ለ8 ሺህ ተማሪዎች ለዳቦ ግዥ ለ3 ቀናት ያወጣው የኪሳራ ልክ 96,000 ብር መሆኑ እንዳረጋገጠ፤ 3ኛ ጭብጥ በተመለከተ 2ኛ ተከሳሽ የደረሰበት የጉደት መጠን አስልቶ ክስ ከሚያቀርብ በቀር አጠቃላይ ለውሉ አፈፃፀም የተያዘው መብት እንደልለው፤ 3ኛ ተከሳሽ (ዳሽን ባንክ) የሚፈጸመው ክፍያም ውል ባለመፈፀሙ የደረሰ ጉዳት ታሳቢ የሚያደረግ እንጂ ጉዳት ቢደርስም በይደርስም ለመክፈል ይገደዳል ማለት አለመሆኑን፤ በዚሁም በሁለተኛ ጭብጥ በተረጋገጠው መሰረት 3ኛ ተከሳሽ ለ2ኛ ተከሳሽ ላከፈል የሚገባው ብር 658,568 ሳይሆን ብር 96,000 መሆኑን፤
አራተኛው ጭብጥ መያዣው ከላይ በተመለከተው የካሣ ልክ ያረፈበት በመሆኑ ይህ ክፍያ ሳይፈፀም መያዣ ላለቀቅ የሚችልበት አግባብ የለም በማለት ወስኗል።
የአሁኑ ተጠሪ በስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙ ክርክር ከመረመረ በኃላ በመጀመሪያ እና ሁለተኛ አቅረቢ የዋጋ ልዩነት መኖሩን አልተከደም። በስር 1ኛ ተከሳሽ የነበሩ አቅረቢ ለ8 ወራት ቢያቀርቡ ችግሩ አይከሰትም ነበር። 2ኛ ተጫራች የነበረው ልላ ውድድር ሳይደረግ የአቅረቦት ውል እንዲቀጥል የተፈቀደው የ8,000 ተማሪዎች የምግብ አቅርቦት ማሟላት ፋታ የማይሰጥ ነው። የፍድራል መንግስት የግዥ አዋጅ መመሪያ ይዘት መረዳት የሚችለው በአቅራቢ ችግር ምክንያት ውሉ በመቋረጡ ላከሰት የሚችለው ተጨማሪ ውጭ /ጉዳት/ መሸፈን የሚገበው አቅረቢ መሆኑንና ለዚህም ለውሉ መልከም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና የተያዘው ገንዘብ ለደረሰው ጉዳት መተኪያ ላውል የሚችል መሆኑን ነው። ተጠሪ በውሉ መቋረጥ ምክንያት ደረሰብኝ የሚለው ጉዳት ብር 1,453,429.20 ነው። ይሁን እንጂ ክርክሩ ሲጀመረም ይሁን አሁን በይግባኝ ደረጃ ይህ ገንዘብ ላከፈልኝ ይገበል የሚል ግልጽ ጥያቄ አላቀረበም፤ በግልጽ የጠየቀው ለመልከም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና የተያዘው ብር 658,568.00 ላከፈለኝ ይገባል በማለት ስለሆነ በይግባኝ ባይ (ተጠሪ) ለደረሰው ጉዳት ላከፈል የሚገበው ብር 96,000 ሳይሆን ለውሉ መልካም አፈፃፀም የተያዘ ጠቅላላ ገንዘብ ብር 658,568 ነው። አመልከቾች ይህንን ገንዘብ ለሥር 3ኛ ተከሳሽ (ዳሸን ባንክ) ሲተኩ የዋስትና መያዝው ይለቀቅላቸው በማለት ወስኗል።
የአሁኑ አመልከቾች በስር ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የሰጠው ውሳኔ በመቃወም ጉዳዩን በሰበር ታይቶ እንዲመረመር እና እንዲለወጥ የሚጠይቅ የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል።
አቤቱታው ተመርምሮ በዚህ ችሎት እንዲታይ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦ ግራ ቀኙ በጽሑፍ ክርክር አደርጓል። የአመልካቾች ቅሬታ መሰረታዊ ይዘትም ውሉ የተቋረጠው በዩኒቨርሰቲው ድብቅ ምክንያት ነው። አቅርቦቱ የተቋረጠው ለ3 ቀን ብቻ በመሆኑ የጉዳት ከሳ ልክ መታየት ያለበት ከዚህ አንፃር መሆኑን እርግጠኛ ጉዳት መድረሱ ሳይረጋገጥ የጉዳት ከሳው ለመልከም አፈፃፀም ዋስትና የተያዘው በሙሉ እንዲከፈል መውሰኑ በአግባቡ አይደለም። የግዥ አዋጅና መመሪያ አፈፃፀም በአግባቡ አልታየም። ጉዳዩ ሰበር በመለሰው መሰረት አልተጣራም የሚል ነው። ተጠሪ በበኩሉ የአቅርቦት ውሉ የተቋረጠው በስር 1ኛ ተከሳሽ በነበረችው ምክንያት መሆኑን መረጋገጡን በመጀመሪያ እና ሁለተኛ አቅራቢ የዋጋ ልዩነት መኖሩን በተጠሪ ተቋም ላይ ጉዳት ማድረስን ተረጋግጦ የተሰጠ ውሳኔ በመሆኑ ላጸና ይገባል በማለት ተከራክራዋል።
የመልስ መልስም ቀርበዋል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችሎትም ግራ ቀኙ በጽሑፍ ያደረጉት ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ውሳኔ አግባብነት ከለው ድንጋጌ ጋር በማገናዘብ እንዲሁም ጉዳዩ ለሰበር ችሎት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመርነውም አመልካቾች እና ተጠሪ እያከራከራ ያለው መሰረታዊ ነጥብ ለመልካም አፈጻጸም የተሰጠ ዋስትና ሙሉ በሙሉ ገቢ ላሆን የሚችልበት የህግ አግባብ መኖር ያለመኖሩን ነው። የአሁኑ አመልካቾች በተጠሪ ላይ የደረሰው ጉዳት የሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዳጣራው የምግብ አቅረቦቱ ለ3 ቀን ብቻ ተቋረጦ የነበረ መሆኑን እየታወቀ የ8 ወር አቅርቦት መሰረት ተደርጎ የጉዳት ከሳው ላሰላ አይገባም በሚል ምክንያት ነው። ተጠሪ በበኩሉ የመጀመሪያ አቅርቢ በውሉ በሰረት ባለ መፈፀምዋ ውሉን እንደተቋረጠ 2ኛ አቅረቢ ሲመረጥ ያቀረበው ዋጋ ከመጀመሪያው የአቅርቦት ዋጋ በግልጽ ጭማሪ ያለው በመሆኑ የሥር ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይህንን በማጣራት ለመልከም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና የተያዘው ገንዘብ ገቢ እንዲሆን መወሰኑ በአግባቡ ነው የሚል ክርክር ማቅረቡን ተመልክተናል።
በስር ፍርድ ቤቶች በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠው 1ኛ ተከሳሽ የነበረችው ወ/ት ንሰሐ ወርቅነህ በገባችው ውል መሰረት የምግብ አቅርቦቱ በመጠን በጊዜ እና በጥራት ባለማከናወንዋ ተጠሪ ማስጠንቀቅያ በመስጠት ውሉን አቋርጦታል። በስር 1ኛ ተከሳሽ የነበረችው ለውሉ መቋረጥ መነሻ አለመሆናን ያቀረበችው ክርክር ይሁን ማስተባበያ የለም ። በስር 3ኛ ተከሳሽ የነበረው ዳሽን ባንክ የመልከም ስራ አፈፃፀም ዋስትና ላሰጥ የተቻለው ምናልባት በስር 1ኛ ተከሳሽ የነበረችው በውሉ ይዘትና መንፈስ አቅርቦቱን ከለከናወነች ተጠሪ ለሚደርስባት ጉዳት ለማከከሻ እንዲሆን ነው።
በስር ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሳሽ የነበረችው ለሁለት ወር ያህል ስታቀርብ በነበረችበት ጊዜ የነበረው ዋጋ እና ውሉ ከፈረሰ /ከተቋረጠ/ በኃላ በ2ኛ አቅራቢ የተጠየቀው ዋጋ ለወንዶ ገነት ዳን ኮልጅ የ0.28 ሳንቲም ለልሎች ከምፓሶች ደግሞ 0.39 ሳንቲም የዋጋ ልዩነት እንዳለው በስር ፍ/ቤት የተረጋገጠ ፍሬ ጉዳይ ነው። የዋጋ ልዩነቱ በ8 ወራት ሂሣብ ስልቱ ሲሰራ በድምሩ ብር 1,453,429.20 ስለመሆኑ ግልጽ ነው። ከዚህ መረዳት የሚቻለው መጀመሪያ ከነበረው የአቅርቦት ውል 2ኛ አቅራቢ ዋጋ በመጨመሩ በተጠሪ ላይ ተጨማሪ ገንዘብ ወጭ ለማድረግ የሚገደድ ስለመሆኑ የሚካድ አይደለም። አመልካቾች አቅርቦቱ የተቋረጠው ለ3 ቀን ብቻ ነው የሚል ክርክር ያቀረቡ ቢሆንም በተጠሪ ላይ የደረሰው ጉዳት ለ8 ወራት የሚዘልቅ ስለመሆኑ በስር ፍ/ቤት ከተደረገው ክርክር መረዳት ተችሐል። ምክንያቱም የአሁኑ ተጠሪ ከ2ኛ አቅራቢ ጋር ያደረገው ውል ከአንድ ሚላዮን ብር በላይ ተጨማሪ ወጭ የጠየቀው በመሆኑ በስር 1ኛ ተከሳሽ የነበረችው በውሉ መሰረት በጊዜ መጠን እና ጥራት የምግብ አቅረቦቱ ቢቀጥል ልላ 2ኛ አቅራቢ በላሰፈለገ ነበር። በመሆኑም በተጠሪ ላይ ጉዳት አልደረሰም የሚለውን ክርክር በስር ፍ/ቤት በፍሬ ነገር ደረጃ ከተረጋገጠው አንጻር የህግ መሰረት ያለው ክርክር ሁኖ አላገኘነውም።
በመሰረቱ ለመልካም ስራ አፈፃፀም የሚሰጥ ዋስትና ዓይነተኛ ዓለማው በተሰራው ነገር ጉዳት የደረሰበት ተዋዋይ ወገን በገንዘብ ረገድ ለመካስ ነው። ከስር ፍ/ቤት የክርክር ሂደት መገንዘብ እንደተቻለው በስር ፍ/ቤት 1ኛ ተከሳሽ የነበረችው አቅራቢ በውሉ መሰረት ማቅረብ ባለመቻሐ ውሉ ፈርሷል። ተጠሪ ከልላ ተዋዋይ የአቅርቦት ውል የፈፀመ መሆኑ ባይካድም በመጀመሪያ እና ሁለተኛ አቅርቦት ላይ በዋጋ ረገድ ከፍተኛ ልዩነት መኖሩን ግልጽ ነው። በአሁኑ ተጠሪ እና በስር ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሳሽ የነበረችው ግለሰብ ተፈፀሞ የነበረው የምግብ አቅርቦት ውሉ ለ10 ወራት የሚቆይ እንደነበር፤ ይሁንና በ1ኛ ተከሳሽ ውል አለመፈፀም ምክንያት በ2ኛ ወር ተቋርጧል። በአሁኑ ተጠሪ 1ኛ ተከሳሽ የነበራችው እንደውሉ ባለመፈፀምዋ ከ2ኛ ተዋዋይ የአቅርቦት ውል ለማድረግ የተገደደ በመሆኑ ተጨማሪ ወጭ የጠየቀው ስለመሆኑ አላከራከረም።
እንዲህ ከሆነ ደግሞ ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት 3ኛ ተከሳሽ ከነበረው ዳሽን ባንክ የውል ማሰከበሪያ ገንዘብ ገቢ እንዲሆንለት መጠየቁ ውሉን መሰረት ያደረገ በደረሰው ጉዳት ልክ ሳይሆን በተሰጠው የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና ገንዘብ ብር 658,568,00 የተገደደ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል።
ከዚህ አንፃር የስር ጠቅለይ ፍርድ ቤት በከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠውን ውሳኔ በማሻሻል መልካም የስራ አፈፃፀም ዋስትና ላይ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ማለትም ብር 658,568.00 ገቢ እንዲሆን መወሰኑ ውሉን በህጉ አግባብ ተፈፃሚ አደረጓአል ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የህግ ስህተት መፈጸሙን አያሳይም። በእነዚህ ሁሉ ምክንያት የስር ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ደረሰ በተባለው ጉዳት ላከፈል ይገባል በማለት የወሰነው 96,000 ብር በማሻሻል ለመልከም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና የተያዘው ብር 658,568.00 ገቢ እንዲሆን መወሰኑ በህጉ አግባብ ሆኖ በመገኘቱ የሚታረም የህግ ስህተት የለውም። በመሆኑም ተከታዩን ወስነናል።
የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ በ30/03/2006 ዓ/ም የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 67820 በ 09/07/2005 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ በማሻሻል የሰጠው ውሳኔ ጸንቷል።
በተጠሪ ላይ ለደረሰ ጉዳት ላከፈል የሚገባው ብር 96,000 ሳይሆን ለውሉ መልከም ስራ አፈፃፀም የተያዘው ጠቅላላ ገንዘብ ብር 658,568 /ስድስት መቶ ሃምሳ ስምንት ሺህ አምስት መቶ ስልሳ ስምንት/ ተብሎ መወሰኑ በአግባብ ነው ብለናል።
አመልካቾች ይህንን ገንዘብ በስር 3ኛ ተከሳሽ ለነበረው ደሽን ባንክ ሲተኩ የዋስትና መያዣው ይለቀቅለቸው ብለናል።
በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት ለተደረገው ክርክር በጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸው ይቻሉ ብለናል።
መዝገቡ ተዘጋ ወደ መ/ቤት የመለስ።