ተተኪ ወራሽ ለመሆን ላሟሉ ስለሚገባቸው ሁኔታዎች የፍ/ሕ/ቁ. 842(3) ውል VIII
No summary available.
የሰ/መ/ቁ/ 110040 የካቲት 3 ቀን 2008 ዓ/ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ አመልካች፡-
ይህ ጉዳይ ውርስ ጥያቄ የመመልከት ነው። አመልካቾች ለአ.አ.ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባቀረቡት የአያታቸው ወ/ሮ ደብረወርቅ ሀ/ሚካኤል ወራሽነት ይረጋገጥልን በማለት አቅርበዋ። የአባታቸው ሻለቃ አክሎግ አድማሱ ወራሽነት ያረጋገጡ ሲሆን የወላጅ አባታቸው እናት ወራሽነት ለማረጋጥ የቀረበ አቤቱታ ነው።ወላጅ አባታቸው በ1981 ዓ/ም ከዚህ አለም በሞት የተለዩ ሲሆን አያታቸው ወ/ሮ ደብረወርቅ ሀብተ ሚካኤል የሞቱት ደግሞ በ1978 ዓ/ም ነው። በመጀመሪያ የተመለከተው ፍርድ ቤቱም አያታቹህ ከአባታቹሁ ቀድመው የሞቱ ስለሆነ ተተኪ ወራሽ ልትሆኑ አትችልም በማለት ብይን ሰጥተዋል። በዚህ ብይን ባለመስማማት አቤቱታቸውን ለአ.አ.ከተማ ይግባኝ ሰሚና ለሰበር ሰሚ ችሎት ቢያቀርብም ተቀባይነት ሳያገኝ በትእዛዝ ሰርዞውታል። የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ የበታች ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካቾች ተወካይ የካቲት 10 ቀን 2007 ዓ/ም በፃፉት የሰበር አቤቱታ በበታች ፍ/ቤቶች ብይን ተእዛዝ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል የሚሉባቸውን ምክንያቶችን ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ ወላጅ አባታችን እናቱ ከሞቱ ጀምሮ እስከ ሞተበት ጊዜ ድረስ በህመም ላይ እንደነበረ ለስር ፍርድ ቤቶች አስረድተን እያለን የአያታችን ወራሽነት አታረጋግጡም መባሉ ከፍተኛ የህግ ስህተት ያለበት ነው። ወላጅ አባታችን ለ3 አመት የአልጋ ቁራኛ ሆኖ የእናቱ ወራሽነት ሳያረጋግጥ ቢቀርም አመልካቾች ተተኪ ወራሾች የአያታችን ወራሽነት የሚከለክለን አንዳችም ህግ የልለ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ብይንና ትእዛዝ በመሻር የአያታችን ወራሽነት እንዲረጋገጥላቸው አቤቱታቸውን አቅርበዋል።
የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ተተኪ ወራሾች ላሆኑ አይችሉም በማለት የተሰጠ ብይን ከፍ/ብ/ህ/ቁ/ 830፣831/3/844 እና 839 አንፃር ለመመርመር በሰበር ችሎቱ ላታይ ይገባዋል በመባሉ ላቀርብ የቻለው። የጉዳዩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ እንደተገለጸው ሲሆን ይህ ችሎትም የሰበር አቤቱታ ካቀረበበት ብይን እና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
የአመልካቾ ጥያቄ ወላጅ አባታቸው ተከተው የአያታቸው ወራሽነት እንዲረጋጥላቸው ነው።
የስር ፍርድ ቤቶች ደግሞ ተተኪ ወራሾች ልትሆኑ አትችሉም በማለት ብይን ተሰጥተዋል።
የፍ/ብ/ህ/ቁ/ 842/3/ ስር እንደተመለከተው የሟች የመጀመሪያ ደረጃ ወራሾች ሲሆኑ ልጆች ቀድመው ከሞቱና ወደታች የሚቆጠር ተወላጅ ትተው ከሆነ ተወላጆቹ ወላጃቻውን ተተክተው ሟችን እንደሚወርሱ ያመላክታል። የተተኪ ወራሽነት የተፈፃሚነት ወሰን ወደ ታች የሚቆጥሩ ተወላጆች እንደሆነ መረዳት ይቻላል። ወላጅ አባታቸው የእናታቸው የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ ናቸው። አመልካቾችም የወላጅ አባታቸው የመጀመሪያ ደረጃ ወራሾች እንደሆኑ ህጉ ከመገንዘብ ይቻላል። ተተኪ ወራሽ ለመሆን ከፍ/ብ/ህ/ቁ/ 842/3/ አንፃር ሲታይ የአመልካቾ ጥያቄ የሚያሟላ አይደለም። ምክንያቱም ወላጅ አባታቸው የእናታቸው የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ በመሆን የወረሱ ስለሆነ የምትክ ጉዳይ ላነሳ አይችልም። በልላ አነጋገር አመልካቾች አባታቸው ተክተው አያታቸውን መውረስ የሚችሉት አባታቸው ከአያታቸው በፊት የሞቱ እንደሆነ ብቻ ነው።
ስሆነም የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ብይንና ትእዛዝ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አልተገኘም። በልላ በኩል አመልካቾች የሟች አባታቸውን ወራሽነት ስለማረጋገጣቸው ከክርክሩ ስለተረዳን አባታቸው የወረሱትን ንብረት ለመጠየቅ ይህ ውሳኔ አያግዳቸውም ብለናል።
በዚሁ መሰረትም የሚከተለው ውሳኔ ሰጥተናል።
የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪየ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ/ 1118/07 ጥር 6 ቀን 2007 ዓ/ም የሰጠው ብይን፤ የአ/አ፤ የአ/አ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በመ/ቁ/23073 ጥር 21 ቀን 2007 ዓ/ም እና የአ/አ ከተማ ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ/ 23140 የካቲት 2 ቀን 2007 ዓ/ም የሰጡት ትእዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ/ 348/1/መሰረት በአብላጫ ድምጽ ጸንቷል።
በዚህ ፍ/ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻሉ።
መዝገብ ተዘግተዋል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.