ጋብቻ በሁኔታ ፈርሷል ላባልባቸው ስለሚችሉባቸው ሁኔታዎች ጋብቻ በሁኔታ ፈርሷል ተብሎ ከሚታሰብበት ጊዜ አንስቶ በአስር ዓመት ጊዜ ውስጥ የንብረት ክፍፍል ጥያቄ ካልቀረበ ወ/ሮ አልማዝ ለሼ እና አቶ በቀለ በላቸው VI የሚታገድ ስለመሆኑ
No summary available.
የካቲት 15 ቀን 2008 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ተኽላት ይመሰል እንዳሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- ወ/ሮ አልማዝ ለሼ- ጠበቃ ኤርሚያስ ደስታ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- አቶ በቀለ በላቸው- ወኪል ትርፍነሽ በቀለ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ ጋብቻ ፈርሷል ላባል የሚችልበትን አግባብ የሚመለከት ነው።ጉዳዩ የተጀመረው በአማራ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት የደብረብርሃን ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን ክሱን ያቀረቡት የአሁኑ አመልካች ናቸው። የክሱ ይዘትም፡- ከአሁኑ ተጠሪ ጋር በአገር ባህል የጋብቻ አፈጻጸም ስርዓት ጋብቻ ፈጽመው ለአርባ አመታት ያህል አብረው መኖራቸውን፣ ይሁን እንጂ ከመስከረም 2006 ዓ/ም ጀምሮ ላስማሙ ባለመቻላቸው በመካከላቸው ሰላም እንደልለ ገልፅው ጋብቻው ፈርሶ የጋራ ንብረት እንዲካፈሉ ይወሰን ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ ተጠሪ ለክሱ በሰጡት መልስም ከአመልካች ጋር ባልና ሚስት የነበሩ መሆኑን ሳይክዱ አመልካች ከአስራ ዘጠኝ አመታት በፊት ቤቱን ጥለው መሄዳቸውንና ተለያይተው የሚኖሩ መሆኑን ጠቅሰው ክሱ በይርጋ ላታገድ ይገባል በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያስቀደሙ ሲሆን በፍሬ ነገር ረገድ ደግሞ ከአመልካች ጋር ያፈሩት የጋራ ንብረት የልለ መሆኑን ዘርዝረው ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲሉ ተከራክረዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለት የሥር ፍ/ቤትም ጉዳዩን መርምሮ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የነበረው ጋብቻ ከአስር አመታት በፊት ፈርሷል የሚል ድምዳሜ ደርሶ የአመልካች ክሱ በይርጋ የታገደ ነው በማለት ውድቅ አድርጎታል። በዚህ ብይን የአሁኗ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለሰሜን ሸዋ አስተዳደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም።
ከዚህም በኋላ አመልካች የሰበር አቤቱታቸውን ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አቅርበውም በጉዳዩ ላይ በተሰጠው ብይን መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለም ተብሎ መዝገቡ ተዘግቶባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ሲሆን ይህ ችሎት የቀረበውን አቤቱታ መርምሮ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን በጽሑፍ አከራክሯል።እንዲሁም የወረዳው ፍርድ ቤት ዋና መዝገብ እንዲመጣ አድርጓል።
በአጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ምላሽ ማግኘት የሚገባው የጉዳዩ ጭብጥ በተጠሪና በአመልካች መካከል ጋብቻ በሁኔታ ፈርሷል ተብሎ በበታች ፍርድ ቤቶች መወሰኑ ተገቢነት አለውን? የሚለውነው።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የወረዳው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ምስክሮች ሰምቶ በአመልካችናበተጠሪ መካከልየነበረውጋብቻ በሁኔታ ፈርሷል በማለት በአመልካች በኩል የቀረበውን ክርክር አልተቀበለውም። ፍርድ ቤቱ ወደዚህ ድምዳሜ የደረሰው በአመልካችና በተጠሪ መካከል የነበረው የጋብቻ ግንኙነታቸው ከ1987 ዓ/ም ጀምሮ ተቋርጦ ግራ ቀኙ ለየብቻ መኖር መጀመራቸው ተረጋግጧል በሚል አቢይ ምክንያት ነው። ይህ የወረዳው ፍርድ ቤት የፍሬ ነገር ማጣራትና የማስረጃ ምዘና ድምዳሜ በዚህ ረገድ ተመሳሳይ የሆነ ስልጣን ባለው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት አግኝቷል። አመልካች በዚህ ችሎት አጥብቀው የሚከራከሩት ግራ ቀኙ ልላ ትዳር መስርተው የራሳቸውን ሕይወት የማይኖሩ መሆኑን፣ አልፎ አልፎ በጤና ምክንያት አመልካች ለፀበል ወደ ልላ ቦታ ከመሄዳቸው ውጪ አመልካችና ተጠሪ ያልተለያዩና እስከ መስከረም 2006 ዓ/ም ድረስ አንድ ላይ የሚኖሩ መሆኑን ዘርዝረው ለጉዳዩ አግባብነት የልለው አስገዳጅ ውሳኔ ተጠቅሶ መወሰኑ ያላግባብ ነው በሚል ነው። እኛም ጉዳዩን ይህ ሰበር ችሎት በመ/ቁ. 14290 እና በልሎች በርካታ መዛግብት ከሰጣቸው አስገዳጅ ውሳኔዎች ጋር አገናዝበን ተመልክተናል።
በመሰረቱ የወረዳው ፍርድ ቤት ለውሳኔው መሰረት ያደረገውና ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ ልሎች ከላይ በተጠቀሱት መዛግብት በሰጣቸው አስገዳጅ ውሳኔዎች በባልና ሚስት መካከል ያለ ጋብቻ በፍ/ቤት በተሰጠ የፍቺ ውሳኔ ፈርሷል ባይባልም የተጋቢዎች ተለያይቶ ለረጅም ጊዜ መኖር፣ በዚህም ጊዜ ልላ ትዳር መሥርቶ መገኘት የቀድሞው ጋብቻ በሕጋዊ መንገድ ተቋርጧል ላያስብል ይችላል በማለት በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2(1) መሰረት በየትኛውም እርከን የሚገኝ ፍርድ ቤትን የሚያስገድድ የሕግ ትርጉም የሰጠበት ጉዳይ ነው። ከዚህም ውሳኔ ይዘትና መንፈስ መረዳት የሚቻለው የጋብቻ መፍረስ በተጋቢዎች የረዥም ጊዜ መለያየት ላከናወን የሚችል መሆኑና ፍርድ ቤቱም በዚህ አግባብ የፈረሰውን ጋብቻ እንደገና እንዲፈርስ ውሳኔ የሚሰጥበት አግባብ የልለ መሆኑን ነው። በሰ/መ/ የተሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ደግሞ በቤተሰብ ሕጉ አግባብ የመተጋገዝና የመተባበር ግድታቸውን ሲወጡና የነበሩና ያልተለያዩ መሆኑ ከተረጋገጠ ጋብቻ በሁኔታ ፈርሷል ለማለት የማይቻል መሆኑን በመዝገቡ ከተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች በመነሳት የተወሰነ ነው።
ወደ ተያዘው ጉዳይ ስንመለስም አመልካችና ተጠሪ በሕጉ አግባብ ጋብቻ መሰርተው ልጆችን ከወለዱ በኋላ በ1987 ዓ/ም ጀምሮ በአካል ተለያይተው ለአስራ ዘጠኝ አመታት ያህል ሳይገናኙ የኖሩ መሆኑን ከግራ ቀኙ ምስክሮች ቃል የተረጋገጠ መሆኑን የበታች ፍርድ ቤቶች ደምድመዋል። ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት ያስቀረበው የወረዳው ፍርድ ቤት ዋና መዝገብም የግራ ቀኙ ምስክሮች የመሰከሩት የፍሬ ነገር ነጥብ በይዘቱ የበታች ፍርድ ቤቶች ከደመደሙት ጋር ተመሳሳይነት ያለው መሆኑን ተገንዝቦአል። በመሆኑም አመልካች ከተጠሪ ጋር እስከ መስከረም 2006 ዓ/ም ድረስ አልተለያየንም በማለት የሚያቀርቡት ቅሬታ በስር ፍርደ ቤት ዋና መዝገብ ውስጥ በምስክሮች ከተነገረው የምስክርነት ቃል ይዘትና ፍሬ ነገሩን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያላቸው ፍርድ ቤቶች ከደረሱበት ድምዳሜ ውጪ በመሆኑ ተቀባይነት የሚሰጠው ሁኖ አልተገኘም። በዚህ ረገድ አመልካች ያቀረቡት ቅሬታ ለዚህ ችሎት በኢ.ፍ.ዲ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3(ሀ)) እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 ድንጋጌዎች አግባብ የተሰጠውን ስልጣንም ያላገናዘበ ሁኖ አግኝተናል።
በመሰረቱ ጋብቻ በተጋቢዎች መካከል የመተጋገዝ፣ የመከባበርና መደጋገፍ እንዲሁም አብሮ የመኖር ግድታን የሚጥል መሆኑን ከክልሉ የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 60 እና 61 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዳይ ነው። ከዚሁ አኳያ በተጠሪና በአመልካች መካከል የነበረው ጋብቻ ይህ ሰበር ችሎት አስቀድሞ በተመሳሳይ ጉዳይ ከሰጠው ውሳኔ አንጻር ተቋርጧል? ወይንስ አልተቋረጠም? የሚለውን ለመወሰን ከፍ ብሎ በአመልካችና በተጠሪ መካከል በጋብቻ ውስጥ በግራ ቀኙ የሚጠበቁ ግድታዎች ባግባቡ ሲተገበሩ ያልነበሩና እነዚህን ግድታዎችን ለመወጣት ደግሞ በአመልካች በኩል ያጋጠመው ሁኔታ በሕጉ የተጣሉባቸውን ግድታቸውን ለመወጣት የማያስችል የነበረ መሆኑ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ አመልካች ከተጠሪ ጋር አልተለያየንም፣ በጤና ችግር ምክንያት አልፎ አልፎ ለፀበል ልላ ቦታ እሄድ ነበር በማለት የሚያቀርቡት ክርክር በክርክሩ ሂደት በማስረጃ የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮችን መሰረት አድርጎ ያልቀረበ ሁኖ አግንተነዋል። ከዚህም በተጨማሪ በተያዘው መዝገብና ይህ ሰበር ችሎት አስገዳጅ የሕግ ትርጉም የሰጠባቸው መዛግብት የያዟቸው መሰረታዊ ፍሬ ነገሮች ከዚህ መዝገብ ከተረጋገጡት እውነታዎች ሙሉ በሙሉ የተመሳሳይነት ያላቸው ሁኖ እያለ አመልካችም ሆነ ተጠሪ ልላ ትዳር መስርተው ሕይወታቸውን በመምራት ላይ አይገኙም በማለት በሰ/መ/ የተሰጠውን አስገዳጅ የሕግ ትርጉም በመተውና ግንኙነቱ ያልተቋረጠ ተጋቢዎችን መሰረት ተደርጎ በመ/ የተሰጠውን ውሳኔ መሰረት በማድረግ አመልካች መከራከራቸው ከአዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀጽ 2 (1) አተገባበር ጋር የሚጋጭ ሁኖ አግኝተናል። ስለሆነም የአመልካችና የተጠሪ ግንኙነት ከ1987 ዓ/ም ጀምሮ በሁኔታ የፈረሰ በመሆኑ እና ለጉዳዩ አግባብነት በላቸው ከላይ በተጠቀሱት መዛግብት በተሰጠው ትርጉም መሰረት የጋራ ንብረት ጥያቄም በአስር አመት ያልቀረበ በመሆኑ የተጠሪ ክስ በይርጋ የታገደ ነው ተብሎ ብይን መሰጠቱ የሚነቀፍበትን የሕግ ምክንያት አላገኘንም። ሲጠቃለልም በጉዳዪ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ሁኖ ስላላገኘነው ተከታዩን ወስነናል።
የደብረብርሃን ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በመ/1/06 በ22/08/2006 ተሰጥቶ በሰሜን ሸዋ መስተዳደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/8 በ30/08/2006 ዓ/ም፣ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 030- 5041 ግንቦት 19 ቀን 2006 ዓ/ም የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ጸንቷል።
በአመልካችና በተጠሪ መካከል በአገር ባህል የጋብቻ አፈፃጸም ስርዓት ተመስርቶ የነበረው ጋብቻ ለረዥም ጊዜ ተለያይቶ በመኖር ምክንያት ፈርሷል በማለት ወስነናል።
በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።
ከደብረብርሃን ከተማ ወረዳ ፍርደ ቤት የመጣ መዝገብ 1/06 በመጣበት አኳሀን ይመለስ ብለናል።