በክርክሩ ተካፋይ ያልሆነውን ወገን የሚጎዳ ውሳኔ የተላለፈው ጉዳዩን በተዋረድ ባየው የሰበር ችሎት በሚሆንበት ጊዜ ይህ በክርክሩ ተካፋይ ያልሆነው ወገን አለኝ የሚለውን መብት ለማስከበር ይችል ዘንድ መብቴን ተጋፍቷል በሚለው ሰው ላይ በስሙ ቀጥታ ክስ በመመስረት መብቱን ከማስከበር ውጪ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.358 መሰረት ተቃውሞውን ለሰበር ችሎቱ ላያቀርብ የሚችል አቶ ሳምሶን ካሳዬ እና ወ/ሮ መሰረት ግርማ (አራት ሰዎች)
No summary available.
ታህሳስ 18 ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ተኽላት ይመስል እንዳሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- አቶ ሳምሶን ካሳዬ - የቀረበ የለም ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ የውርስ ንብረት ይለቀቅልኝ ጋር ተያይዞ የተሰጠው ውሳኔ ላይ የቀረበውን የፍርድ መቃወሚያ አቤቱታ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች በአደአ ወረዳ ፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ ነው። አመልካች በዚህ ፍርድ ቤት ያቀረቡት አቤቱታ በ17/04/2006 ዓ/ም የተፃፈ ሁኖ 1ኛ ተጠሪ ተከሳሽ፣ የአሁኑ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተራ ያሉት ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረው በመ/ በ16/10/2002 ዓ/ም የተሰጠው ውሳኔ ከእናቴ ከወ/ሮ ፀሐይ ገብሬ በውርስ ላተላለፍልኝ በሚገባ ንብረት ላይ የተሰጠና መብቴን የነካ ነው በሚል ምክንያት ውሳኔ ተነስቶ የክርክሩ ተካፋይ ልሆን ይገባል የሚል ሲሆን የአሁኑ ሥር ፍርድ ቤትም ለፍርዱ መሰረት የሆነው ንብረት ላይ የተሰጠው ውሳኔ የተፈጸመ ነው በሚል ድምዳሜ የአመልካች የፍርድ መቃወሚያ አቤቱታ በመዝገቡ ላስተናገድ እንደማይችል፣ ሆኖም አመልካች መብታቸውን ቀጥታ ክስ አቅርበው ማስጠበቅ የሚችሉ መሆኑን ጠቅሶ የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ አድርጎባቸዋል። ከዚህም በኋላ የአሁኑ አመልካች ይግባኛቸው ለምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ ጉዳዩን መርምሮ የአሁኑ ከተራ ቁጥር 2 እስከ 4 ያሉት ተጠሪዎች በአሁኗ 1ኛ ተጠሪ ላይ የውርስ ንብረት ይለቀቅልን ክስ አቅርበው የወረዳው ፍርድ ቤት ክርክር ያስነሳው ይዞታና ንብረት ለከሳሾች እንዲለቀቅላቸው መወሰኑን፣ ይህ ውሳኔ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፀንቶ የነበረ ቢሆንም የአሁኗ 1ኛ ተጠሪ የሰበር አቤቱታቸውን ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎትም በመ/ በ03/03/2005 ዓ/ም በዋለው ችሎት የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ የበታች ፍርድ ቤቶች በጉዳዩ ላይ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በሚል ምክንያት ሙሉ በሙሉ በመሻር ክርክር የተነሳበት ይዞታና ንብረት የ1ኛ ተጠሪ ነው በማለት የወሰነ መሆኑን፣ ይህ ውሳኔ በመሰጠቱ ምክንያትም 1ኛ ተጠሪ የተወሰደባቸው ንብረት እንዲመለስላቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 349(1) ድንጋጌ መሰረት አቤቱታ አቅርበው ፍርድ ቤቱም ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተጠሪዎች ባሉት ተጠሪዎች የ1ኛ ተጠሪ ቤት ፈርሶ ስለነበር በአሁኗ 2ኛ ተጠሪ ስም ያለው ቤት ተሽጦ ለ1ኛ ተጠሪ ግምቱ እንዲከፈል ጨረታ እንዲወጣ አድርጎ በሂደት እንደሚገኝ፣ የወረዳው ፍርድ ቤት በዚህ አግባብ አፈጻጸሙን እየመራ ያለው የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ የሰጠውን ውሳኔ መነሻ አድርጎ ስለመሆኑና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 መሰረት የፍርድ መቃወሚያ ላቀርብ የሚገባው ደግሞ ፍርዱን ለሰጠው ፍርድ ቤት መሆኑን ጠቅሶ የአሁኑ አመልካች የፍርድ መቃወሚያ አቤቱታ አቀራረብ ስርዓት ስርዓቱን የተከተለ አይደለም በሚል ድምዳሜ የሥር ፍርድ የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ ማድረጉን ተገቢ ነው በማለት ወስኖአል። ከዚህም በኋላ አመልካች የሰበር አቤቱታቸውን ለክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- የወረዳው ፍርድ ቤት እያስፈጸመ ያለው የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ የሰጠውን ውሳኔ ሁኖ እያለና በክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎትም ሆነ በበታች ፍርድ ቤቶች ክርክሩ መኖሩን አመልካች ባላወቁበት ሁኔታ እንዲሁም የ1ኛ ተጠሪ አፈጻጸም ሂደት ላይ ስለመኖሩ ክርክሩ እያሳየ ፍርዱ ተፈጽሟል ተብሎ የፍርድ መቃወሚያው በወረዳው ፍርድ ቤት ውድቅ መደረጉም ሆነ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠው ውሳኔ በወረዳ ፍርድ ቤት የፍርድ መቃወሚያ ላቀርብበት የሚችል አይደለም በማለት መወሰኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 ድንጋጌ አላማ ውጪ የሆነ እና የአመልካችን የውርስ መብት የጎዳ ነው በማለት መከራከራቸውን የሚሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በዚህ ችሎት እንዲታይ የተደረገ ሲሆን ተጠሪዎች ቀርበውም ግራ ቀኙ በፅሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጎአል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችሎት የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዳዩ ለሰበር ችሎት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች እና የአሁኑ ተጠሪ ከተራ ቁጥር 2 እስከ 4 የተጠቀሱት ተጠሪዎች የወ/ሮ ጸሐይ ገብሬ ወራሽ መሆናቸውን፣ የአሁኑ አመልካች ከተራ ቁጥር 2 እስከ 4 የተጠቀሱት ተጠሪዎች ከወ/ሮ ጸሐይ ገብሬ በውርስ የሚተላለፍልን ቤትና ይዞታ በ1ኛ ተጠሪ ከሕግ ውጪ ተይዞ ይገኛል በሚል በተጠሪዋ ላይ ክስ መስርተው በወረዳው ፍርድ ቤት ንብረቱ እንዲለቀቅላቸው ተወስኖላቸው በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ፀንቶ የነበረ ቢሆንም በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ግን የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ተሽሮ አከራካሪው ቤትና ይዞታ የ1ኛ ተጠሪ ነው ተብሎ መወሰኑን፣ በዚህ ሂደት ግን የስር ከሳሾች በ1ኛ ተጠሪ ቤት ላይ ጉዳት አድርሰው/አፍርሰው/ ስለነበር ተጠሪዋ የፈረሰው ቤታቸው ግምቱ እንዲከፍላቸው አፈጻጸሙን በወረዳው ፍርድ ቤት ቀጥለው ባሉበት ሁኔታ የአሁኑ አመልካች በዋናው ጉዳይ የተሰጠው ፍርድ የውርስ መብቴን የነካ ነው በሚል የፍርድ መቃወሚያ ያቀረቡና ተቀባይነት ያጡ መሆኑን ነው።
የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በግልፅ የሚያሳየው አመልካች የፍርድ መቃወሚያ ያቀረቡበት ውሳኔ በክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ የተሰጠና ፍርዱ ከተፈፀመ በኃላ የቀረበ መሆኑን ነው። አመልካች መቃወሚያው የቀረበበት ፍርድ አልተፈፀመም፤ በሂደት ላይ ያለ ነው የሚሉት 1ኛ ተጠሪ ቤታቸው በልሎች ተጠሪዎች የፈረሰባቸው በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 349(1) መሰረት የቤቱን ግምት ላከፍሉኝ ይገባል በማለት ያቀረቡትን አቤቱታ መነሻ አድርጎ የስር ፍርድ ቤት ይህንኑ አቤቱታ ለማስፈፀም በ28/04/2006 ዓ/ም የሰጠውን ትዕዛዝ መሰረት በማድረግ ስለመሆኑ ከወረዳው ፍርድ ቤት መዝገብ ግልባጭ ተመልክተናል።
በእግርጥ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 358 መሰረት የሚቀርበው አቤቱታ የሚስተናገደው ለመቃወሚያው መነሻ የሆነውን ውሳኔ ለሰጠው ፍ/ቤት ነው። አቤቱታው የሚጣራው ወይም የሚስተናገደው ማንኛውም ክስ በሚስተናገድበት ሥርዓት በመሆኑ እና ይህም ማስረጃ መስማትንና ማስረጃውን መዝኖ ውሳኔ መስጠትን የሚጠይቅ ነው። ስለሆነም
No topics extracted.