No summary available.
ሐምል 29 ቀን 2006ዓ.ም.
ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽላት ይመሰል አመልካች፡- ዶ/ር ሕላና ፍቅሬ ጠበቃ ሶፊያ ክፍል ቀረቡ ተጠሪ፡- የፍድራል ፖላስ ሆስፒታል ነገረ ፈጅ ረ/ኢንስፒክተር ወተቱ ተገኘ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ የስራ መልቀቂያ ይሰጠኝ ጥያቄን የሚመለከት ሆኖ ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች ለፍድራሉ ሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የአስተዳደር ፍርድ ቤት ባቀረቡት የይግባኝ አቤቱታ መነሻ ነው።
የአመልካች የይግባኝ አቤቱታቸው ይዘትም ባጭሩ፡- ከጥር 03 ቀን 2005 ዓ/ም ጀምሮ በስራ ላይ ባለመሆናቸው በገዛ ፈቃዳቸው ስራ ስለለቀቁ የሥራ መልቀቂያ እንዲሰጣቸው የአሁኑን ተጠሪን ጠይቀው የተከለከሉ መሆኑን ገልጸው የስራ መልቀቂያ እንዲሰጣቸውና ከለቀቁበት ቀን ጀምሮ ለደረሰባቸው ኪሳራ ተሰልቶ እንዲከፈላቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ ተጠሪ ለይግባኙ በሰጠው መልስም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያስቀደመ ሲሆን ይዘቱም፡- አመልካች በተጠሪ መስሪያ ቤት ከሚያዚያ 01 ቀን 2002 ዓ/ም ጀምሮ በኮንስታብል ማእረግ በመለዩ ለባሽነት ቅጥር የፈፀሙ በመሆኑ የሚተዳደሩት በመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ደንብ ሳይሆን በኢትዮጵያ ፍድራል ፖላስ ኮሚሽን መተዳደሪያ ደንብ ቁጥር 268/2005 ስለሆነ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን የማየት ስልጣን የለውም የሚል ነው።የአስተዳደር ፍርድ ቤቱም በዚህ መልክ የቀረበውን የተጠሪን መቃወሚያ መነሻ በማድረግና ከአዋጅ ቁጥር 720/2004 እና ደንብ ቁጥር 268/2005 ድንጋጌዎች ጋር አገናዝቦ በመመርመር አመልካች በተጠሪ መስሪያ ቤተ ተቀጥረው ለመስራት ማመልከታቸውን፣መብቶቻቸውና ጥቅሞቻቸው በፍድራል ፖላስ አባላት መተዳደሪያ ደንብ ቁጥር268/2005 መሰረት ሲጠበቁላቸው የነበረ መሆኑ መረጋገጡን፣የመንግሰት ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 714/2003 መሰረት ለጡረታ ፈንድ መዋጮ ይዋጣላቸው የነበረው 20% መሆኑ መረጋገጡን፣አመልካች ሲቀጠሩ በሞሉት ፎርም ላይ በኮንስታብል ማዕረግ ለመስራት መፈረማቸውና በሕይወት ታሪክ ፎርሙም የፍድራል የመንግስት ሰራተኞች ከሚሞሉበት ፎርም የተለየና በፍድራል የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 515/1999 አንቀጽ 2(1) ስር ስለመንግስት ሰራተኛ የተመለከተውን ትርጉም የማያሟሉ መሆኑን መረዳቱን ገልፆ የአመልካች ጥያቄ በአዋጅ ቁጥር 515/1999 መሰረት የሚታይ ሳይሆን በፍድራል ፖላስ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የሚታይ ነው በማለት በድምፅ ብልጫ ውድቅ አድርጎታል።በዚህ ውሳኔ የአሁኗ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቅርበው ችሎቱ ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ ጉዳዩን መርምሮ የአስተዳደር ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ የሰጠውን ውሳኔ በድምፅ ብልጫ ሙሉ በሙሉ አፅንቶታል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም አመልካች የሰበር አቤቱታቸውን በማቅረባቸው ነው።የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡-አመልካች አንድ ሰው የፍድራል ፖላስ አባል ለመሆን መሟላት ያለባቸው መስፈረቶች በሕጉ በግልጽ በተቀመጡበት ሁኔታ አመልካች ለደመወዝ አከፋፈል ሲባል እንዲሞሉ በተደረገው ፎርም ላይ ኮንስታብል ተብሎ በመገለፁና ለፖላስ የሚሰጡ ጥቅማ ጥቅሞችን ሲቀበሉ ስለቆዩ ብቻ የፍድራል ፖላስ አባል ናቸው ተብሎ ጉዳዩ በፍድራል ፖላስ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት እንዲታይ ተብሎ መወሰኑ የአዋጅ ቁጥር 720/2004 አንቀጽ 2(1) እና ደንብ ቁጥር 268/2005 አንቀጽ 5(1)፣6(1)፣7(1) ድንጋጌዎች ስር የተመለከተውን አግባብ የጣሰና መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው የሚል ነው።አቤቱታው ተመርምሮም የአመልካች ጉዳይ በፍድራል ፖላስ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የሚታይ ነው ተብሎ መወሰኑ ተገቢ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዳዩ ለዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት እንዲቀርብ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ ቀርቦ በሰጠው መልስ አመልካች የፖላስ አባላቱ የሚያገኙትን ማዕረግና ጥቅማ ጥቅም እያገኙ ሲሰሩ የቆዩ መሆኑ የተረጋገጠ መሆኑን ጠቅሶና አመልካች የፖላስ መሰረታዊ ስልጠና ያልወሰዱት ለጊዜው መሆኑን ጠቅሶ አመልካች የፖላስ አባል አይደሉም ተብሎ ላወሰዱበት የሚችልበት የሕግ አግባብ የለም ሲል የተከራከረ ሲሆን አመልካችም በመልስ መልሳቸውን ላይ የሰበር አቤቱታቸው አጠናክረው ተከራክረዋል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዳዩን ለሰበር ችሎቱ ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች በተጠሪ ተቋም ሲቀጥረው የኮንስታብል ማዕረግ የተሰጣቸው መሆኑ፣ ሲቀጠሩ የሞሐቸው ቅጾች ፖላሳዊ ባህርይ ያላቸው መሆኑን፣ለፖላስ አባላት የሚሰጡ ጥቅማ ጥቅሞች እና የጡረታ መዋጮ ለአመልካች ሲከፈልላቸው የነበረ መሆኑ በአስተዳደር ፍርድ ቤት የተረጋገጡ ከመሆናቸውም በላይ በግራ ቀኙ ያልተካዱ መሆኑን፣አመልካች እነዚህ ፍሬ ነገሮች መኖራቸውን ሳይክዱ አጥብቀው የሚከራከሩት እነዚህ የተጠቀሱት ተግባሮች ላፈፀሙ የቻሉት በጁኒየር ጄኔራል ሚዲካል ፕራክቲሽነር የስራ መደብ በተጠሪ መስሪያ ቤት ሲቀጠሩ የደመወዝ ቅጥራቸው ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የደመወዝ ስኬል ጋር አቻ እንዲሆን ታስቦና የአመልካችን ጥቅም ለመጠበቅ ታስቦ እንጂ ፖላስ በመሆናቸው የተጠበቁላቸው ጥቅሞች ያለመሆናቸውን ጠቅሰው መሆኑን፣ተጠሪ በበኩሉ ይህንኑ የአመልካችን ክርክር የሚያስተባብል ማስረጃ ያለው ስለመሆኑ በግልጽ ሳይገልጽ አመልካች ወደውና ፈቅደው ፖላስ ሁነው ስራቸውን መጀመራቸውንና የፖላስ አባላቱ የሚያገኟቸውን ጥቅማ ጥቅሞችን ሲያገኙ የቆዩ በመሆኑ ፖላስ ተብለው ላወሰዱ ይገባል በማለት የሚከራከር መሆኑን ነው።
በዚህጉዳይበዋነኛነትየተያዘውጭብጥአንድ ሰው የፍድራል ፖላስ አባል ነው ተብሎ ጉዳዩ በዚህ ረገድ በተዘጋው የሕግ ስርዓት የሚታየው ምን ምን ሕጋዊ ሁኔታዎች ሲሟሉ ነው? የሚለው ነው።ይህንኑ ጥያቄ ለመመለስ ይቻል ዘንድም ለጉዳዩ ቀጥተኛ ተፈፃሚነት ያላቸውን አዋጅ ቁጥር 720/2004 እና ደንብ ቁጥር 268/2005 ድንጋጌዎችን መመልከት ተገቢነት ይኖረዋል።
አዋጅ ቁጥር 720/2004 አንቀጽ 2(1) “የፖላስ አባል” ማለት መሰረታዊ የሆነ የፖላስ ሙያ ስልጠና ተሰጥቶት በኢትዮጵያ ፍድራል ፖላስ ኮሚሽን ተቀጥሮ የሚሰራ የፍድራል ፖላስ አባል ነው በሚል ትርጉም የሰጠ ሲሆን በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 27(1) እና በአዋጅ ቁጥር 691/2003 አንቀጽ 5 ድንጋጌዎች መሰረት አዋጁን ለማስፈፀም ደንብ ቁጥር 268/2005 ወጥቶ ስራ ላይ ውሐል።ይህ ደንብ የፍድራል ፖላስ አባላት መተዳደሪያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 268/2005 ተብሎ የሚጠቀስ ሲሆን ደንቡ የተፈፃሚነት ወሰኑን በአንቀጽ 3 ስር በግልፅ አሰቀምጧል።በዚህም መሰረት ደንቡ ኮንስታብል እስከ ኮሚሽነር ማዕረግ ባላቸው የፍድራል ፖላስ አባት ላይ ተፈጻሚ እንደሚሆን በተጠቃሹ ድንጋጌ ንዑስ ቁጥር አንድ ያስቀምጣል።እንዲሁም የደንቡ አንቀጽ 4 ድንጋጌ ስለፖላስ ምልመላ፣ስልጠናና ምደባ የሚደነግግ ሲሆን የደንቡ አንቀጽ 5 ድንጋጌ በተለይ ሲታይም ማንኛውም ምልምል ፖላስ በፖላስ አባልነት ከመቀጠሩ በፊት መሰረታዊ የፖላስ ትምህርትና ስልጠና መውሰድና የሚሰጠውን ፈተና ማለፍ አለበት በሚል በንዑስ ቁጥር አንድ ስር ሃይለ ቃል በያዘ አቀራረፅተቀምጦ ይገኛል።በደንቡ አንቀጽ 6(1) ደግሞ ማንኛውም ምልምል ፖላስ መሰረታዊ የፖላስ ትምህርትና ስልጠና እንዳጠናቀቀ ስራ ከመጀመሩ በፊት ቃለመሐላ መፈፀም እንዳለበት እና ላፈፀም የሚገባውን የቃለ መሓላ ይዘት አስፍሯል።እንዲሁም የደንቡ አንቀጽ 7 ድንጋጌ ሲታይም የቅጥር ውል የሚደረግበትን አግባብ ይደነግጋል።በዚህ ድንጋጌ ንዑስ ቁጥር አንድ መሰረት ምልምል ፖላስ የፖላስ አባል የሚሆነው መሰረታዊ የፖላስ ትምህርትና ስልጠና አጠናቅቆ ቃለ መሃላ ፈፅሞ የቅጥር ውል ከፈረመ በኋላ መሆኑን አስገዳጅነት ባለው መልኩ የሚያስቀመጥ ሲሆን የተጠቃሹ አንቀጽ ንዑስ ቁጥር ሁለት ድንጋጌም ውሉ ከተፈረመበት በኋላ ስለሚኖረው የአገልግሎት ዘመን ለይቶ የሚደነግግ ነው።ደንቡ በትርጓሜ ክፍሉ አንቀጽ 2(2) በአዋጁ አንቀጽ 2 የተሰጡ ትርጓሜዎች ለደንቡም ተፈፃሚ ይሆናል ሲል ያስቀመጠ ሲሆን በዚህ ደንብ አዋጅ ማለት ደግሞ የኢትዮጵያ ፍድራል ፖላስ ኮሚሽን ማቋቋሚ አዋጅ ቁጥር 720/2004 ስለመሆኑ በአንቀጽ 2(1) በግልፅ ያሳያል።በዚህ አግባብ ሲታይ ደግሞ ፖላስ ማለት በአዋጁ አንቀጽ 2(1) የተሰጠውን ትርጉም የሚይዝ ሁኖ በደንቡ አንቀጽ 4፣5፣6 እና 7 ድንጋጌዎች መሰረት በሕጉ የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቶ የተቀጠረ ላሆን እንደሚገባው ከድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንረዳው ጉዳይ ይሆናል።በመሆኑም በሕጉ የተቀመጡት ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉ አንድ ሰው የፖላስ ቅጥር ፎርም የሚል ስያሜ የያዘ ሰነድ ስለሞላ ወይም በቅጥር ፎርሙ በሕጉ አግባብ የሚገኙት ማዕረጎች ተሰጥተውት የጥቅማ ጥቅሙ ተጋሪ መሆን እንደ ሕጉ አነጋገርና ይዘት ፖላስ ነው ብሎ ትርጉም ለመስጠት የሚያስችሉ ሁኔታዎች ስለመሆናቸው ጉዳዩን በተለይ እንዲገዙ የወጡ ሕጎች አያሳዩም።
አዋጅ ቁጥር 720/2003 የወጣበት መሰረታዊ አላማ የፍድራል ፖላስ የኢትዮጵያ ፍድራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብላክ ሕገመንግሥትንና ሕገመንግሥቱን መሰረት አድርገው የሚወጡ ህጎችን የማስከበር ተልዕኮውን በብቃት በመወጣት የዲሞክራሲ ሥርዓትን ለመገንባት፣ ሰላምን ለማስፈንና ልማትን ለማፋጠን በሚደረገው አገራዊ እንቅስቃሴ የበኩሉን ድርሻ ለማበርከት እንዲችል በተሻለ ሁኔታ እንዲደራጅ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ የፍድራል ፖላስ ተቋም ማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ገለልተኛ የሆነ፣ ሕብረተሰቡን በእኩልነት የሚያገለግል፣ በፖላሳዊ ሥነ-ምግባሩ የታነፀና ብቃትና ጥራት ያለው አገልግሎት ላሰጥ የሚችል ተቋም መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት ስለመሆኑ አዋጁ በመግቢያው ላይ የሚገልፅ ሲሆን ይህንኑ አዋጅ በአግባቡ ለማስፈፀም ይቻል ዘንድ ደግሞ ደንቡ ወጥቷል።በመሆኑም አዋጁ የራሱን አላማ እንዲያሳካ በአዋጁ የተቀመጡትና አዋጁን መሰረት አድርጎ በወጣው ደንብ ስር ያሉት ድንጋጌዎች በአግባቡ ላከበሩና ላተገበሩ ይገባል።ከዚህ ውጪ ከአዋጁ የወጡ አሰራሮችና ልማዶች በአዋጁና በደንቡ ጥበቃ የሚያገኙበት አግባብእንዲኖር ማድረግ ጉዳዩን ለመግዛት ታስቦ ስልጣን ባለው አካል የወጣውን ሕግ ትርጉም የሚያሳጣ ሁኔታ እንዲፈጠር የሚያደርግ በመሆኑ ተቀባይነት ያለው አይደለም።
ወደተያዘው ጉዳይ ስንመለስም አመልካች መሰረታዊ የፖላስ ትምህርትና ስልጠና ያልወሰዱ፣በደንቡ መሰረትም ቃለ መሃላ ያልፈፀሙ ቅጥሩን የሞሉትም ምልምል ፖላስ ላወሰደው የሚገባውን መሰረታዊ የፖላስ ትምህርትና ስልጠና አጠናቅቀው ሳይሆን ምንም ስልጠና ሳይወስዱ መሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ በሚገባ የተረጋገጡ ነጥቦች ናቸው። የፍድራል ፖላስ የፖላስ አባላቱን የሚመለምለው የሚያሰለጥነው የሚቀጥረውና የሚያስተዳድረው በሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚወጣው ደንብ ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 720/2004 አንቀጽ 14 በግልፅ የተቀመጠ ሲሆን ደንቡን ለማውጣት በሕጉ ስልጣን የተሰጠው አካል ደግሞ ደንብ ቁጥር 268/2005 አውጥቶ ከህዳር 10 ቀን 2005 ዓ/ም ጀምሮ ተፈፃሚ ሁኗል።በደንቡ አንቀጽ 96(2) ድንጋጌ ስር ደግሞ ከደንቡ ጋር የሚቃረኑ ደንቦች፣መመሪያዎች ወይም የአሰራር ልማዶች በደንቡ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት እንደማይኖራቸው አስገዳጅነት ባለው መልኩ አስቀምጧል።በመሆኑም በአዋጁና በደንቡ ከተመለከቱት ሕጋዊ ስርዓቶች ውጪ የሚፈጸሙ የፖላስ ቅጥሮች አንድን ሰው የፖላስ አባል ነው ብሎ ለመደምደም የሚያስችሉ አይሆኑም።
እንዲሁም ከጊዜ ቅደም ተከል አንፃር ይታይ ቢባል እንኳን አዋጅ ቁጥር 720/2004 ተፈፃሚ የሆነው ከሕዳር 18 ቀን 2004 ዓ/ም ጀምሮ ነው።አመልካች የቅጥር ፎርሙን የሞሉበት ጊዜ ሚያዚያ 01 ቀን 2002 ዓ/ም መነሻ ተደርጎ በጊዜው ተፈፃሚነት የነበራቸው ሕጎች አዋጅ ቁጥር 313/1995 እና ደንብ ቁጥር 86/1995 ድንጋጌዎች ሲታይም የፖላስ ትምህርትና ስልጠና ያልወሰደ ሰው የፖላስ አባል ነው የሚለውን ትርጓሜ ላያገኝ የሚችልበትን አግባብ የሚያሳዩ ድንጋጌዎችን ይዘው አይገኙም።ስለሆነም ተጠሪ ለአመልካች የፖላስ ማእረግ ሰጥቶ ቅጥሩ ላይም ማእረጉ ተጠቅሶ ፎርሙ መሞላቱም ሆነ አመልካች የአንድ ፖላስ ጥቅማ ጥቅሞችን ሲያገኙ መቆየታቸው በአዋጁ ጥብቅ አነጋገር ስንነሳ በማናቸውም መመዘኛ አመልካች የፖላስ አባል ናቸው ወደሚለው ድምዳሜ ለመውሰድ የሚያስችሉ አይደሉም።ተጠሪ አመልካች የፖላስ ትምህርትና ስልጠና ያልወሰዱ መሆናቸውን አምኖ ወደፊት የሚወስዱበት ሁኔታ መኖሩን ጠቅሶ ያቀረበው ክርክርም የአዋጁንና የደንቡን ድንጋጌዎችን ይዘትና መንፈስ ያላገናዘበ በመሆኑ ተቀባይነት የሚያገኝበትን የሕግ አግባብ አላገኘንም።
ሲጠቃለልም አመልካች የፖላስ አባል ናቸው ተብሎ የሚደመደምበት አንዳችም የሕግ ምክንያትን በልለበት ሁኔታ ማዕረጉ ተሰጥተው የፖላስ አባል ጥቅማ ጥቅም ተጠቃሚ ነበሩ በሚሉ ምክንያቶች ብቻ ጉዳያቸው በፖላስ መተዳደሪያ ደንብ እንጂ በአዋጅ ቁጥር 515/1999 በተዘረጋው ስርዓት የሚታይ አይደለም ተብሎ በአስተዳደር ፍርድ ቤቱ መወሰኑም ሆነ ይኼው ውሳኔ በፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በድምጽ ብልጫ መጽናቱ ከላይ የተመለከቱትን የሕግ ማዕቀፎችን ጥብቅ ስርዓት ያላገናዘበና መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
በኢ.ፍ.ዲ.ሪ የሲቭል ሰርቪስ ሚኒስቴር የአስተዳደር ፍርድቤት በይ/መ/ቁጥር 162/2006 ጳጉሜ 04 ቀን 2005 ተስጥቶ በፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ ጥር 26 ቀን 2006 ዓ/ም የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረትተሽሯል።
አመልካች በአዋጅ ቁጥር 720/2004 አንቀጽ 2(1)፣14(1) እና በደንብ ቁጥር 268/2005 አንቀጽ 4፣5፣6 እና 7 ድንጋጌዎች መሰረት የፍድራል ፖላስ አባል ናቸው ተብሎ የሚወሰዱ አይደለም ብለናል።
አመልካች በተጠሪ መስሪያ ቤት የነበራቸው ቅጥር ከፖላስ አባልነት ውጪ የነበረ በመሆኑ ጉዳዩ መታየት ያለበት በአዋጅ ቁጥር 515/1999 በተዘረጋው አግባብ ነው በማለት በግራ ቀኙ መካከል ያለውን ጉዳይ የኢ.ፍ.ዲ.ሪ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የአስተዳደር ፍርድ ቤት በይ/መ/ቁጥር 162/2006 ክርክሩን ቀጥሎና በአግባቡ አጣርቶ ተገቢውን ዳኝነት እንዲሰጥበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 341(1) መሰረት መልሰን ልከንለታል።ይጻፍ።
በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።
No topics extracted.