No summary available.
የሰ/መ/ ሐምል 30 ቀን 2006 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽላት ይመሰል አመልካች፡- መምህር ግዛቸው ጥሪት - ቀረቡ ተጠሪ፡- ወሎ ዩንቨርስቲ አያና ስማቸው - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የቀረበው አመልካች ወሎ ዩንቨርሲቲ ቦርድ የሰጠው የዲሲፕላን ውሳኔ በይግባኝ ታይቶ እንዲታረም ያቀረብኩትን የይግባኝ ቅሬታ በፍደራል የመንግስት ሰራተኞች አስተዳዳር ፍርድ ቤት እና በፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ውድቅ መደረጉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዳዩ ወሎ ዩንቨርሲቲ ቦርድ የሰጠውን የዲስፕላን ውሳኔ፣ የፍደራል የመንግስት ሰራተኞች አስተዳደር ፍርድ ቤት በይግባኝ የሚታይና የሚታረም መሆኑን ወይም አለመሆኑን የሚመለከት ነው።
የክርክሩ መነሻ አመልካች ያለአግባብ የተማሪዎቹን ውጤት ቀይሯል ወይም ውጤት ሞልቷል በሚል መንገድ የቀረበውን የዲሲፕላን ክስ፣ በዩኒቨርሲቲው የዲሲፕላን ኮሚቴ ተጣርቶ ከቀረበለት በኋላ የዩኒቨርሲቲው ቦርድ አመልካች ከሥራ እንድሰናበት የሰጠው ውሳኔ ነው። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፍደራል የመንግስት ሰራተኞች አስተዳደር ፍርድ ቤት አቅርቧል። የፍደራል የመንግስት ሰራተኞች አስተዳደር ፍርድ ቤት የዩኒቨርሲቲው ቦርድ የሰጠው ውሳኔ የመጨረሻና ይግባኝ ላቀርብበት የማይችል ነው፣ ጉዳዩን በይግባኝ አይቶ የመወሰን ሥልጣን የለኝም በማለት በድምጽ ብልጫ ውሳኔ ሰጥቷል። አመልካች የፍደራል የመንግስት ሰራተኞች አስተዳደር ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቅርቧል። የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አመልካች ያቀረበውን ይግባኝ በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል።
አመልካች የፍደራል የመንግስት ሰራተኞች አስተዳደር ፍርድ ቤትና የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የዩኒቨርሲቲው ቦርድ የሰጠው ውሳኔ የመጨረሻና ይግባኝ ላቀርብበት የማይችል ነው በማለት የሰጡት የሕግ ትርጉምና ውሳኔ የፍደራል ከፍተኛ ትምህርት ማቋቋሚያ አዋጅና አዋጁን ለማስፈጸም የወጣውን ደንብ ድንጋጌዎች ያገናዘበ አይደለም። ውሳኔው አመልካች በሕገ መንግስት የተረጋገጠለትን ፍትህ የማግኘት መብት የሚያጣብብ ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ የሚል ይዘት ያለው የሰበር አቤቱታ አቅርቧል። ተጠሪ በበኩሉ የፍደራል የመንግስት ሰራተኞች አስተዳደር ፍርድ ቤትና የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የዩኒቨርሲቲው ቦርድ የሰጠው ውሳኔ የመጨረሻና ይግባኝ ላቀርብበት የማይችል ነው በማለት የሰጡት የሕግ ትርጉምና ውሳኔ መንግስት ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ነጻነት ለማረጋገጥ በአዋጅ የሰጣቸውን ሥልጣን ያገናዘበና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያልተፈጸመበት ነው። የዩኒቨርሲቲው ቦርድ የሰጠው ውሳኔ የመጨረሻና ይግባኝ የማይቀርብበት በመሆኑ፣ አመልካች የዩኒቨርሲቲው ቦርድ የሰጠው ውሳኔ የመጨረሻና ይግባኝ የማይቀርብበት በመሆኑ አመልካች የዩኒቨርስቲው ቦርድ ውሳኔ ከሰጠበት ቀን ጀምሮ በዘጠና ቀናት ውስጥ የሰበር አቤቱታውን ለፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ማቅረብ ሲገባው ጉዳዩን በይግባኝ ለማየት ሥልጣን ለልላቸው አካላት ማቅረቡ የህግ መሰረት የለውም ተብሎ ውድቅ መደረጉ ተገቢ ነው የሚል ይዘት ያለው ክርክር አቅርቧል። አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና ግራ ቀኙ በዚህ ሰበር ችሎት ያቀረቡት የጽሑፍ ክርክር ይዘት ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የፍደራል የመንግስት ሰራተኞች አስተዳደር ፍርድ ቤት እና የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የዩኒቨርሲቲው ቦርድ የሰጠው ውሳኔ የመጨረሻና ይግባኝ ላቀርብበት የማይችል ነው በማለት የሰጡት የሕግ ትርጉምና ውሳኔ የሕግ መሰረት ያለው ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዳዩን መርምረናል።
የፍደራል የመንግስት ሰራተኞች አስተዳደር ፍርድ ቤት እና የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ለዚህ ሰበር ችሎት አከራካሪ ጭብጥ ሆኖ የቀረበውን የዩኒቨርሲቲው ቦርድ የሰጠው ውሳኔ የመጨረሻና ይግባኝ ላቀርብበት የማይችል ነው የሚለውን የሕግ ትርጉምና ውሳኔ የሰጡት የከፍተኛ ተቋማት አዋጅ ቁጥር 650/2001 አንቀጽ 44 ንዑስ አንቀጽ 1ኀየዩኒቨርሲቲው ቦርድ በመንግስታዊ ተቋሙ ውሳኔ ላይ ቅሬታ ሲቀርብ መመርመርና የመጨረሻ ውሳኔ የመሥጠት ስልጣን ያለው መሆኑን በግልጽ ደንግጓል በማለት ነው።
ይህም የከፍተኛ ተቋማት አዋጅ ቁጥር 650/2001 አንቀጽ 44 ንዑስ አንቀጽ 1ኀ ድንጋጌ መሰረታዊ ባህሪው ከልካይና የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ሰራተኞች እንደማንኛውም መንግስት ሰራተኛ ፣ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የበላይ አመመራር አካል የሆነው የዩኒቨርስቲው ቦርድ፣ የሚሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለፍደራል የመንግስት ሰራተኞች አስተዳደር ፍርድ ቤትና ደረጃውን ጠብቀው ለፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ማቅረብ የማይችሉ መሆኑን የሚደነግግ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ለድንጋጌው ትርጉም መስጠት የሚጠይቅ ሆኖ አግኝተነዋል። የአዋጅ ቁጥር 650/2001 አንቀጽ 44 ንዑስ አንቀጽ 1ኀ መሰረታዊ ባህሪና ዓላማ እንደዚሁም ድንጋጌው በአካዳሚክ ሰራተኞች የይግባኝ መብት ላይ የሚኖረውን ሕጋዊ ውጤት ለመረዳት የድንጋጌውን የተናጠል የቃል በቃል ንባብ ማየት ብቻዉን በቂ አይደለም።
የአዋጁን አንቀጽ 44 ንዑስ አንቀጽ 1ኀ ድንጋጌ መሰረታዊ ባህሪና ዓላማ እንደዚሁም፣ ድንጋጌው በአካዳሚክ ሰራተኞች የይግባኝ መብት ላይ የሚኖረው ሕጋዊ ውጤት ለመገንዘብ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ዓላማዎች፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላያከብራቸውና ላመሩባቸው የሚገቡ ቋሚና መሰረታዊ እሴቶች፣ በአዋጁ የተረጋገጠውን የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አካዳሚክ ነጻነት ይዘትና የአካዳሚክ ሰራተኞች ስላላቸው መብትና ግድታ እንዲሁም የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አደረጃጀትና የዩኒቨርሲቲው ቦርድና ሰኔት በአዋጁ የተሰጣቸውን ጥቅልና ዝርዝር ስልጣንና ኃላፊነትና ግድታ አግባብነት ያላቸውን የፍደራል የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 515/1999 ድንጋጌዎች ጋር በጣምራ መታየትና መተርጎም ይኖርበታል።
የመንግስት ሆነ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ሰራተኞች፣ አስተዳደርና ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞችና የቴክኒክ ሰራተኞች ላኖራቸው እንደሚችል ከአዋጅ ቁጥር 650/2001 አንቀጽ 2፣ ንዑስ አንቀጽ 3፣ንዑስ አንቀጽ 13 ፣ ንዑስ አንቀጽ 15 ድንጋጌዎች ለመረዳት ይቻላል። አዋጅ ቁጥር 650/2001 አንቀጽ 4 የከፍተኛ ተቋማት ዓላማዎችን ይዘረዝራል። የከፍተኛ ትምህርት ዓላማዎች አንደኛው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማዊ ነጻነት ከተጠያቂነት ጋር ማረጋገጥ እንደሆነና በከፍተኛ ትምህርት ተቋም እንቅስቃሴ ፍትሕን፣ ፍትሐዊነትና የህግ የበላይነትን ማራመድና መጠበቅ እንደሆነ በአዋጁ አንቀጽ 4 ንዑስ አንቀጽ 5 እና ንዑስ አንቀጽ 6 ተደንግጓል። ከዚህ በተጨማሪ ማናቸውም ከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ እውነትን የመሻትና እውነትን የመግለጽ ነጻነት፣ አሳታፊና የሕግ የበላይነት፣ፍትህንና ፍትሐዊነትንና ልሎች በአዋጁ አንቀጽ 6 የተደነገጉ እሴቶች በቋሚነት የመያዝና ቋሚ እሴቶቹን ተግባራዊ የማድረግ ግድታ እንዳለበት በአዋጁ አንቀጽ 6 ንዑስ አንቀጽ 1፣ ንዑስ አንቀጽ 5፣ እና ንዑስ አንቀጽ 6፣ ንዑስ አንቀጽ 11 እና በአዋጁ አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 ተደንግጓል።
ሕግ አውጭው የከፍተኛ ትምህርት ዓላማዎችና ቋሚ እሴቶች በአዋጅ ቁጥር 650/2001 የደነገገው ያለ ምክንያት አይደለም። ሕግ አውጭው የግልም ሆነ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚፈጽሟቸው ትምህርትና ምርምር ተግባራትና ተቋማቱ ከአካዳሚክ ሰራተኞች፣ ከአስተዳደርና ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች፣ከቴክኒክ ሰራተኞች እና ከተማሪዎች ጋር የሚኖራቸው ግንኙነትና የሚከተሉት አስተዳደር ጥበብ ከላይ የተገለጹትን የከፍተኛ ትምህርት ዓላማዎችና ቋሚ እሴቶች በሚያረጋግጥ መንገድ መሆን እንዳለበትና ተቋማቱ የሚሰጧቸው ውሳኔዎችም ከላይ ከተገለጹት ዓላማዎችና እሴቶች አንጻር ላመዘኑና ላመረመር የሚገባው መሆኑን ግልጽ ለማድረግ በማሰብ ከላይ የተገለጹት ድንጋጌዎች በማካተት አዋጁን ያወጀ መሆኑን ለመገንዘብ ይቻላል። ከዚህ አንጻር የዩኒቨርሲቲው በላይ አመራር የሆነው ቦርድ በዲስፕላን ጉዳይ የሚሰጠው ውሳኔ በይግባኝ የዳኝነት ሥልጣን በተሰጣቸው አካላት የሚታይበትንና ስህተትም ካለው የሚታረምበት እድል በሚያጣብብ ሁኔታ የአዋጁን አንቀጽ 44 ንዑስ አንቀጽ 1ኀ ድንጋጌ መተርጎም ዩኒቨርሲቲው የከፍተኛ ትምህርት ዓላማዎችና በቋሚነት ላይዛቸው፣ ላተገብራቸው የሚገባውን ቋሚ እሴቶች ለማስፈጸምና ለማጎልበት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ያለ መሆኑ መመዘን ይገባዋል።
ከላይ የተገለጹትና ሕግ አውጭው በተቋማቱ ውስጥ ፍትህን የማስፈን፣ ፍትሐዊነትና የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ዓላማና ቋሚ እሴት እንዲኖር የመድረግ መሰረታዊ ግብን ለማሳካት ከደነገጋቸው ድንጋጌዎች በተጨማሪ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ነጻነታቸው የተረጋገጠላቸው መሆኑን የአዋጅ ቁጥር 650/2001 አንቀጽ 17 ንዑስ አንቀጽ 1 በጥቅሉ አገላለጽ ይደነግጋል። የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአዋጁ የተረጋገጠላቸው አካዳሚክ ነጻነት አመላካች በሆነ መንገድ የሚዘረዝረው አንቀጽ 17 ንዑስ አንቀጽ 2 የተቋማቱ የአካዳሚክ ነጻነት የአካዳሚክ ሰራተኞችና ልሎች ሰራተኞች የመቅጠርና በሥራ አፈጻጸም ውጤታቸው መሰረት መድቦ የማሰራትንና የሰው ኃይሉን በአዋጅ ቁጥር 650/2001 እና በልሎች ተፈጻሚነት ባላቸው ሕጎች መሰረት የሰው ኃይሉን የማስተዳደርንና ልሎች ነጥቦችን የሚያካትት መሆኑን ከአንቀጽ17 ንዑስ አንቀጽ 2ለ እና ሐ ድንጋጌዎች ይዘት ለመረዳት ይቻላል።
እዚህ ላይ በትኩረት መታየት ያለበት ሕግ አውጭው የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ነጻነት በሚደነግገው ድንጋጌ ሥር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በአዋጁና በልሎች ተፈጻሚነት ባላቸው ሕጎች መሰረት የሰው ኃይሉን የማስተዳደር ነጻነት ያላቸው መሆኑን በአንቀጽ 17 ንዑስ አንቀጽ 2 (ሐ) የደነገገበት ምክንያት ነው። ሕግ አውጭው ይህንን ድንጋጌ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ነጻነት በሚያውጀው የአዋጁ ክፍልና ድንጋጌ ሥር ያካተተው ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በአዋጅ ቁጥር 650/2001 የተረጋገጠላቸው አካዳሚክ ነጻነት በውስጡ ተነጻጻሪ ግድታንም የያዘ በተለይም ተቋማቱ አዋጁንና አዋጅ ለማስፈጸም የወጣውን የፍደራል የዩንቨርሲቲዎች ደንብ ቁጥር 210/2003 እና በአዋጅ ቁጥር 515/199 እንደ አግባብነቱ ልሎች አግባብነትና ተፈፃሚነት ያላቸውን የፍደራል ሕጉች መሰረት በማድረግ የሰው ሀይላቸውን የማስተዳደር ኃላፊነት ያለባቸው መሆኑን የሚያካትት እና ይህንን ለተቋማቱ የተሰጠው አካዳሚክ ነጻነት ይህንን ተቋማቱን መሰረታዊ ግድታ የማያስቀር ወይም የማይቀንስላቸው መሆኑን በግልጽ ለማስቀመጥ እንደሆነ ለመገንዘብ ይቻላል።
አከራካሪውን ጭብጥ ለመወሰን መታየት ያለበት ልላው ነጥብ በአዋጅ ቁጥር 650/2001 የአካዳሚክ ሰራተኞች የተረጋገጠላቸውን መብትና የተጣለባቸው አንጻራዊ ግድታ ነው።
በመንግስት ከፍተኛ ተቋማት ተቀጥረው የሚሰሩ የአካዳሚክ ሰራተኞች ያላቸውን መብት በአመላካች ሁኔታ የሚዘረዝረው የአዋጅ ቁጥር 650/2001፣ አንቀጽ 31 ንዑስ አንቀጽ 1(ሰ) የአካዳሚክ ሰራተኞች ግልጽና ፍትሐዊ አስተዳደር የማግኘት መብት ያላቸው መሆኑን የሚደነግግ ሲሆን በዲሲኘላን ጉዳይ የመስማት እድል የማግኘትና ተገቢ ያልሆነ ውሳኔ እንዲነሳላችው የመጠየቅና ፍትህ የማግኘት መብት ያላቸው መሆኑን የአዋጁ አንቀጽ 31 ንዑስ አንቀጽ 1(ተ) በግልጽ ይደነግጋል ይህ ያአካዳሚ ሰራተኞች በአዋጅ ቁጥር 31 ንዑስ አንቀጽ 1(ተ) የተረጋገጠላቸው ተገቢ ያልሆነ ውሳኔ እንዲነሳላቸው የሚጠይቅ እና ፍትሕ የማግኘት መብት እስከምን ድረስ ነው የሚለው ነጥብ ከሕገ መንግስቱ መሰረታዊ መርሆና ድንጋጌዋች አንፃር መታየት እና መተርጐም እንዳለበት ግንዛቤ ላያዝበት የሚገባ ነው።
ከላይ ከተገለጹት በተጨማሪ የዩኒቨርሲቲ ቦርድ በዩኒቨርሲቲው ድርጅታዊ መዋቅር ውስጥ ከፍተኛውና የመጨረሻ አስተዳደራዊ ውሳኔ የሚሰጥ አካል መሆኑን ከአዋጅ አንቀጽ 43 ድንጋጌዎችና ከአንቀጽ 44 ድንጋጌዎች ይዘት ለመረዳት ይቻላል። በተለይም ቦርዱ የተቋሙ የላይ አመራር መሆኑ በአንቀጽ 44 ንዑስ አንቀጽ 1 በግልጽ የሚደነግግ ሲሆን ቦርዱም ቀዳሚ ኃላፊነት አዋጁ መከበሩንና መልካም አስተዳደር መሰፈኑን የማረጋገጥ እንደሆነ በአንቀጽ 44 ንዑስ አንቀት 1(ሀ) በግልጽ ተደንግጓል። የዩኒቨርሲቲው ቦርድ በተቋሙ ውስጥ አዋጁ መከበሩንና መልካም አስተዳደር መስፈኑን ለማረጋገጥ የተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች የዩኒቨርሲቲው አመራር አማካሪ አካላት፣ የአካዳሚክ ሰራተኞች፣ የቴክኒክ ሰራተኞች፣ የአስተዳደርና ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች እና ተማሪዎች የከፍተኛ ክፍል ተቋማት አዋጅ የሚያከብሩና የሚተገብሩ መሆኑን መከታተልና መምራት ይጠበቅበታል። ቦርዱ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ መልካም አስተዳደርን ለማስፈንና ለማረጋገጥ በዩኒቨርሲቲው ተፈጽመዋል የሚባሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በበላይነት በማየት የመልካም አስተዳደር ችግር አለበት የሚባለው አስተዳደራዊ ውሳኔ በማየት የማረም ሥልጣን ላኖረው ይገባል። ቦርዱ የሚሰጠው ውሳኔም በተቋሙ በልላ አካል ላሻሻል ወይም ላለወጥ የማይችል የመጨረሻ አስተዳደራዊ ውሳኔ ላሆን ይገባል። የከፍተኛ ተቋማት አዋጅ ቁጥር 650/2001 አንቀጽ 44 ንዑስ አንቀጽ 1(ኀ) ድንጋጌ በመሰረታዊ ባህሪውና ይዘቱ ከላይ የገለጽነውንና ቦርዱ በተቋሙ ውስጥ አዋጁን ለማስከበርና ተግባራዊ እንዲሆን ለማድረግ፣ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ውስጥ መልካም አስተዳደርን ለማስፈንና ለማረጋገጥ የሚያስችለውን በዩኒቨርሲቲው መዋቅራዊ እርከን፣ የቦርዱን የመጨረሻ አስተዳደራዊ ውሳኔ ሰጭነት የሚደነግግ ድንጋጌ ነው።
የአዋጅ ቁጥር 650/2001 አንቀጽ 44 ንዑስ አንቀጽ 1(ኀ) ድንጋጌ ቃል በቃል ሲነበብ የዩኒቨርሲቲው ቦርድ በመንግስታዊ ተቋሙ ውሳኔ ላይ ቅሬታ ሲቀርብ መመርመርና የመጨረሻ ውሳኔ የመስጠት የሚል ይዘት ያለው ሲሆን ይህ በተለየ ሁኔታ አካዳሚክ ሰራተኞች የተሰጠ የዲሲኘላን ውሳኔ ብቻ የሚመለከት አይደለም። የድንጋጌው አወቃቀር ጠቅላላና ሰፊ ነው። ድንጋጌው ማናቸውም የአካዳሚክ ሰራተኞች፣ የአስተዳደርና ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች፣ የቴክኒክ ሰራተኞች፣ ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲው ጋር የአቅርቦት ወይም ልላ የውል ግንኙነት ያላቸው ሶስተኛ ወገኖች በዩኒቨርሲቲው የሥራ ኃላፊ ወይም ልላ አካል ደርሶብናል የሚሉትን የመልካም አስተዳደር በደል፣ በየደረጃው ባሉ የተቋሙ ኃላፊዎች ካልተፈታና ወይም ውሳኔያቸው ቅሬታ ወይም አቤቱታ የቀረበበት ከሆነ፣ ጉዳዩን አይቶ የመጨረሻ አስተዳደራዊ ውሳኔ የሚሰጠው ቦርዱ እንደሆነ የሚደነግግ ድንጋጌ ነው።
ከዚህ አንጻር ሲታይ ቦርዱ ከፍደራል የመንግስት አዋጅ ቁጥር 515/199 አንቀጽ 2 ንዑስ 3 በሚሰጠው ትርጓሜ የዩኒቨርሲቲው የመጨረሻ አስተዳደራዊ ውሳኔ ሰጭ አካል መሆኑን ለመገንዘብ ይቻላል። የዩኒቨርሲቲው ቦርዱ የሰጠው ውሳኔ የመጨረሻና ይግባኝ ላቀርብበት የማይችል ነዉ የሚለው የሕግ ትርጉምና ውሳኔ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማዊ ነጻነት ከተጠያቂነት ጋር ማረጋገጥና የከፍተኛ ትምህርት ተቋም እንቅስቃሴ ፍትሕን፣ ፍትሐዊነትና የህግ የበላይነትን የማራመድና የመጠበቅ ዓላማዎች በማሳካት አንጻር ሲመዘን ተገቢነት የልለው በመሆኑና የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላያዳብሩት የሚገባውን እውነትን የመሻትና እውነትን የመግለጽ ነጻነት፣ አሳታፊና የሕግ የበላይነት፣ የፍትህንና ፍትሐዊነትን እሴቶች ለማረጋገጥ በጎ አስተዋጽኦ የማያበረክትና አዋጅ የደነገጋቸውን ቋሚና መሰረታዊ እሴቶች ግብና አላማ ጋር የማይሄድና አተረጓጎም መሆኑን ለመገንዘብ ይቻላል።
ከላይ ከተገለጸው በተጨማሪ የአዋጅ ቁጥር 650/2001 አንቀጽ 44 ንዑስ አንቀጽ 1(ኀ) ድንጋጌ የአካዳሚክ ሰራተኞችን የይግባኝ መብት ከልካይና ገዳቢ እንደሆነ የተሰጠው ትርጉም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በአዋጅ ቁጥር 650/2001 የተረጋገጠላቸው አካዳሚክ ነጻነት በውስጡ ተነጻጻሪ ግድታንም የያዘ፣ በተለይም ተቋማቱ አዋጁንና አዋጅ ለማስፈጸም የወጣውን የፍደራል ዩኒቨርሲቲዎች ደንብ ቁጥር 210/2003 እና በአዋጅ ቁጥር 515/199 አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎችና ልሎች ተፈጻሚነት ያላቸውን የፍደራል ሕጎች መሰረት በማድረግ የሰው ኃይላቸውን የማስተዳደር ኃላፊነት ያለባቸው መሆኑንና ተቋማቱ ይህን ኃላፊነታቸውን ካልተወጡ በሕግ አግባብ ላጠየቁ የሚችሉበትን ሁኔታ የሚያካትት መሆኑን ያላገናዘበ ነው። በልላ አነጋገር በአዋጁ ለተቋማቱ የተሰጠው የአካዳሚክ ነጻነት ተቋማቱን አዋጁንና ልሎች ሕጎችን መሰረት በማድረግ የሰው ኃይላቸውን እንዲያስተዳድሩ የተጣለባቸውን መሰረታዊ ግድታ የማያስቀር ወይም የማይቀንስላቸው መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባ ሆኖ አግኝተነዋል።
እንደሁም የአዋጅ ቁጥር 650/2001 አንቀጽ 44 ንዑስ አንቀጽ 1(ኀ) ድንጋጌ የአካዳሚክ ሰራተኞችን የይግባኝ መብት ከልካይና ገዳቢ እንደሆነ የተሰጠው ትርጉም በአዋጅ ቁጥር 650/2001 አንቀጽ 31 ንዑስ አንቀጽ 1(ሰ) የአካዳሚክ ሰራተኞች ግልጽና ፍትሐዊ አስተዳደር የማግኘት መብት ያላቸው መሆኑንና በዲስኘላን ጉዳይ የመስማት እድል የማግኘትና ተገቢ ያልሆነ ውሳኔ እንዲነሳላቸው የመጠየቅና ፍትህ የማግኘት መብት ያላቸዉ መሆኑ በግልጽ የሚደነግግ መሆኑን ያገናዘበ አይደለም። በመሰረቱ በአዋጁ አንቀጽ 31 ንዑስ አንቀጽ 1(ተ) የተገለጸው ፍትህ የማግኘት መብት፣ የአንድ ሰው ፍትህ የማግኘት መብት በፍርድ ላያልቁ የሚችሉ ጉዳዮችን ለፍርድ ቤት ወይም ለልላ የዳኝነት ሥልጣን በሕግ ለተሰጠው አካል አቅርቦ የማስወሰን መብትን የሚያካትት መሆኑን በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 37 ከተደነገገው ጋር በሚጣጣም ሁኔታ መተርጎምና ተግባራዊ መሆን ይኖርበታል።
የአዋጅ ቁጥር 650/2001 አንቀጽ 44 ንዑስ አንቀጽ 1(ኀ) ድንጋጌ ቃል በቃል ሲነበብ የዩኒቨርሲቲው ቦርድ በመንግስታዊ ተቋሙ ውሳኔ ላይ ቅሬታ ሲቀርብ መመርመርና የመጨረሻ ውሳኔ የመስጠት የሚልና አግባብነት የተዋቀረ ድንጋጌ ነው ጥቅል የአካዳሚክ ስራተኞችን ጉዳይ ብቻ የማይመለከት ልሎች ሰራተኞችና ሰዎች በዩኒቨርሲቲው የሥራ ኃላፊ ወይም አካል ደርሶብናል የሚሉትን የመልካም አስተዳደር በደል በየደረጃው ባሉ የተቋሙ ኃላፊዎች ካልተፈታና ቅሬታ ወይም አቤቱታ የቀረበበት ከሆነ ጉዳዩን አይቶ የመጨረሻ አስተዳደራዊ ውሳኔ የሚሰጠው ቦርዱ እንደሆነ የሚደነግግ ድንጋጌ መሆኑን ሣይመረምር የተሰጠ ትርጉምና ውሳኔ ነው።
ከላይ በዝርዝር በገለጽናቸው ምክንያቶች የዩኒቨርሲቲው ቦርዱ የሰጠው ውሳኔ የፍደራል የመንግስት ሰራተኞች አስተዳደር ፍርድ ቤት እና የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ይግባኝ ላቀርብበት የማይችል ሆኖ አላገኘነውም። የፍደራል የመንግስት ሰራተኞች አስተዳደር ፍርድ ቤት ይኸ ሰበር ችሎት በመዝገብ በአካዳሚክ ሰራተኛ ላይ የተሰጠ የዲሲኘላን የቅጣት ውሳኔ በዩኒቨርሲቲው ኘሬዝዳንት ከጸደቀ በኋላ፣ አዋጅ ቁጥር 650/2001 አንቀጽ 44 ንዑስ አንቀጽ 1(ኀ) መሰረት በቦርድ ቀርቦ የመጨረሻ አስተዳደራዊ ውሳኔ ሳይሰጥበት በይግባኝም ሆነ በሰበር ቀርቦ ላታይ እንደማይገባው በመግለጽ የሰጠውን የሕግ ትርጉም በተዛባ ሁኔታ በመረዳት የሰበር ችሎት ቦርዱ የሰጠው ውሳኔ የመጨረሻና ይግባኝ እንደማይባልበት፣ የአዋጅ ቁጥር 650/2001 አንቀጽ 44 ንዑስ አንቀጽ 1(ኀ) ትርጉም እንደሰጠ አድርጎ በውሳኔው ማስፈሩ የተሳሳተና ላታረም የሚገባው ሆኖ አግኝተነዋል።
የፍደራል የመንግስት ሰራተኞች አስተዳደር ፍርድ ቤት እና የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የዩኒቨርሲቲው ቦርድ የሰጠው ውሳኔ በይግባኝ ሲመለከቱ በአዋጅ ቁጥር 650/2001 አንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ያወጣውን አካዳሚክ ሰራተኞች መተዳደሪያ ደንብ ተግባራዊነት በሚያረጋግጥ መንገድ መሆን እንደሚገባው ግንዛቤ ላያዝበተ የሚገባው ነው።ከላይ በዝርዝር በገለጽናቸው ምክንያቶች የዩኒቨርስቲው ቦርድ የሰጠው ውሳኔ የመጨረሻና ይግባኝ ላቀርብበት የማይችል ነው በማለት የፍደራል የመንግስት ሰራተኞች አስተዳደር ፍርድ ቤት እና የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የሰጡት የህግ ትርጉምና ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት ወስነናል።
የፍደራል የመንግስት ሰራተኞች አስተዳደር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ እና በፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የሰጠው ትዕዛዝ ተሸሯል።
የፍደራል የመንግስት ሰራተኞች አስተዳደር ፍርድ ቤት ጉዳዩ በይግባኝ አይቶ የመወሰን ሥልጣን አለው በማለት ወስነናል።
የፍደራል የመንግስት ሰራተኞች አስተዳደር ፍርድ ቤት፣የአዋጅ ቁጥር 650/2001፣የፍደራል የዩኒቨርሲቲዎች ደንብ ቁጥር 210/2003፣ በአዋጅ ቁጥር 650/2001 አንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ያወጣውን የአካዳሚክ ሰራተኞች መተዳደሪያ ደንብ እና የአዋጅ ቁጥር 515/1999 እንደ አግባብነቱ መሰረት በማድረግ በግራ ቀኙ መካከል ያለውን ክርክር ሰምቶ ውሳኔ እንዲሰጥበት ጉዳዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 341 (1) መሰረት መልስን ልከንለታል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻሉ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.