No summary available.
ሐምል 1 ቀን 2006 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፉ አህመድ አመልካቾች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ የፍርድ አፈፃፀም ክርክርን የሚመለከት ሆኖ አፈፃፀሙን ሲመራ የነበረው ፍ/ቤትም የምስራቅ ጎጃም አስተዳደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው። በስር ፍ/ቤት አመልካቾች የአፈፃፀምከሳሾች ደግሞ የአፈፃፀም ተከሳሽ ነበር።
ለፍርድ አፈፃፀሙ ክርክር መነሻ የሆነው ፍርድ የተሰጠው በፍድራሉ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ.መ. የካቲት 27 ቀን 2004 ዓ/ም በዋለው ችሎት ሲሆን ይዘቱም ባጭሩ፡የወቅቱ የቤቱ ግንባታ ዋጋ በወራሾች መካከል የእኩልነት መብትን ስለሚያረጋግጥ የሚያከራክረው የውርስ ንብረት ወይም ቤት ለክፍፍል በሚቀርብበት ወቅት በሚኖረው የገበያ ዋጋ መሰረት ግምቱ ሲቀርብ አመልካቾች (የአሁኑ አመልካቾች)የግምቱን ግማሽ ድርሻ እንዲያገኙ የሚል ነው።ይህ ውሳኔው በአሁኑ አመልካቾች አማካኝነት በምስራቅ ጎጃም አስተዳደር ዞን ከ/ፍ/ቤት ለአፈፃፀም ቀርቦ ፍ/ቤቱም በበኩሉ የአሁን ተጠሪን አስቀርቦ አስተያያቱን ከጠየቀ በኃላ በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ መሰረት ለማስፈፀም ይችል ዘንድ ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት የወቅቱ የገበያ ዋጋ ግምት ምን ያክል እንደሆነ ግምቱ በደብረ ማርቆስ ከተማ አገልግሎት ፅ/ቤት በኩል በባለሙያ ተገምቶ ውጤቱ እንዲቀርብ በሰጠው ትዕዛዝ መነሻነት በብር 39,119.09 ተገምቶ መቅረቡን የስር ፍ/ቤት ትዕዛዝ ግልባጭ የሚያስረዳ ሲሆን ፍ/ቤቱም በበኩሉ የቤቱ ጨረታ መነሻ ግምት ብር 39,119.09 መሆኑ ታውቋል በማለት ለአፈጻጸሙ መነሻ በሆነው ውሳኔ መሰረት የቤቱን የገበያ ዋጋ ግምት ለማወቅ ይቻል ዘንድ የፍ/ቤቱ ተወካይ በተገኙበት ቤቱ ለጨረታ ቀርቦ የጨረታ አሽናፊ የሆነው ዋጋ ታውቆ ለፍ/ቤቱ እንዲገለፅ የሚል ይዘት ያለው ትዕዛዝ ሰጥቶ ውጤቱን ለመጠባበቅም ቀጠሮ ለሐምል 2 ቀን 2004 ዓ/ም ይዟል።
የአሁኑ ተጠሪም በዚህ ትዕዛዝ ቅር ተሰኝቶ የይግባኝ አቤቱታውን ለክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቅርቦ ችሎቱም በበኩሉ ቅሬታውን መርምሮ በሰጠው ትዕዛዝ ፡- በስር ፍ/ቤት የተሰጠው ትዕዛዝ ጊዜያዊ አገልግሎት ያለው እንጂ የጨረታው የመጨረሻ ውጤቱ የታወቀ ስላልሆነ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 320(3) መሰረት የይግባኝ አቤቱታ ላቀረብበት የሚችል አይደለም በማለት ቅሬታውን ሰርዞታል።ሆኖም ግን ቀጥሎ በአሁኑ ተጠሪ አመልካችነት ጉዳዩን የተመለከተው የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በበኩሉ ግራ ቀኙን አስቀርቦ ከሰማ በኋላ ጉዳዩን መርምሮ የአከራካሪው ቤት የወቅቱ የገበያ ዋጋ ግምት በፍ/ቤቱ ትዕዛዝ መሰረት በደ/ማርቆስ ኢንዲስትሪ ልማት ከተማ አገልግሎት ፅ/ቤት ብር 39,119.09 መሆኑ ተገምቶ ውጤቱ ቀርቦ እያለ የስር ፍ/ቤት ቤቱ በጨረታ ተሽጦ ክፍፍሉ እንዲፈፀም በማሰብ የጨረታ ማስታወቂያ እንዲወጣ ትዕዛዝ መስጠቱ ለአፈፃፀም መነሻ የሆነውን ውሳኔ (በፍድራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የተሰጠውን)ሙሉ ይዘት ያገናዘበ አይደለም የሚል ምክንያት ጠቅሶ የስር ፍ/ቤቱን ትዕዛዝ በፍ/ብ/ህ/ስ/ስ/ቁ 348(2) መሰረት በመሻር የአሁኑ ተጠሪ ተገምቶ በቀረበወ “የቤቱ ገበያ ዋጋ ግምት ብር 39,119.09” መሰረት ግማሹን ብር 19,559.55 ለአሁኑ አመልካቾች ይክፈል ሲል ወስኗል።
አሁን በአመልካቾች የቀረበው የሰበር አቤቱታም ይሄንኑ በክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የተሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ሲሆን ይዘቱም ባጭሩ፡- የቤቱ ገበያ ዋጋ ግምት የሚታወቀው ቤቱ ለጨረታ ቀርቦ በሚሰጠው ከፍተኛ ዋጋ መሰረት በማድረግ መሆኑ የሚታወቅ ነው። የስር ፍ/ቤትም የጨረታ ማስታወቂያውን ያወጣው በዚሁ መሰረት የቤቱን የገበያ ዋጋ ግምት ለማወቅ እንዲቻል እንጂ ቤቱ ተሽጦ ከተጠሪ እጅ እንዲወጣ በማሰብ አይደለም። ስለሆነም የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የስር ፍ/ቤትን ትዕዛዝ ሽሮ የውርስ ንብረት ድርሻችንን በባለሙያ ግምት መሰረት ግማሹን ገንዘብ እንድንቀበል በማለት የሰጠው ውሳኔ ለአፈፃፀም መነሻ የሆነው ውሳኔ ይዘት በትክክል ያላገናዘበ ከመሆኑም በላይ መብታችንም በእጅጉ የጐዳ በመሆኑ ውሳኔው ተሸሮ ቤቱ ለጨረታ ቀርቦ 3ኛ ወገን በሚያቀርበው የገበያ ዋጋ መሰረት ግማሹ እንዲከፈለን የሚያደርግ ውሳኔ ይሰጠን የሚል ነው።
አቤቱታውም በሰበር አጣሪ ችሎት ተመርምሮ ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት ከዚህ ቀደም በሰ/መ/ ለክርክሩ መነሻ የሆነው የውርስ ሀብት በወራሾች መካከል በእኩል ክፍፍሉ እንዲፈፀም በሚያስችል መልኩ የወቅቱ የገበያ ዋጋ ግማሽ ድርሻ አመልካቾች እንዲያገኙ በማለት ከሰጠው ውሳኔ አንፃር የክልሉ ሰበር ችሎት ያሳለፈውን ውሳኜ ተገቢነተ ለማጣራት ሲባል አቤቱታው ለዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት እንዲቀርብ ተደርጐ ተጠሪም ቀርቦ የበኩሉን መልስ በፅሁፍ ሰጥቷል።ይዘቱም ባጭሩ፡- የክልሉ ሰበር ችሎት አመልቾች ድርሻቸውን እንዲያገኙ የወሰነው የወቅቱን የገበያ ዋጋ ግምት መሰረት ባደረገ መልኩ ስለሆነ ውሳኔው የሚነቀፍ አይደለም በማለት ተከራክሯል።አመልካቾችም የመልስ መልሳቸውን ሰጥተውበታል ።
No topics extracted.
የጉዳይ አመጣጥና ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም በበኩላችን የአንድ ንብረት የገበያ ዋጋ ግምቱ ምን ያህል እንደሆነ የሚወሰነው ወይም የሚታወቀው በምን አግባብ ነው?የሚለውን በጭብጥነት ይዘን ጉዳዩን በሚከተለው መልኩ መርምረናል።
በመሰረቱ ተጠሪ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን የውርስ ሀብት ወይም ቤት ግምት ግማሹን ድርሻ ለአመልካቾች ከፍሎ ቤቱን በቀዳሚነት ለራሱ እንዲያስቀር ተብሎ አስቀድሞ የተወሰነ በመሆኑ አመልካቾች በዚህ ረገድ ያቀረቡት ቅሬታ የለም።እንዲሁም ግምቱን በተመለከተም የውርስ ሀብቱን በወራሾች (በግራ ቀኙ )መካከል በእኩል ለማከፉፈል በሚያስችለው መልኩ በወቅቱ ገበያ የዋጋ መሰረት ግምቱ ሲቀርብ አመልካቾች የግምቱን ግማሽ ድርሻ እንዲያገኙ ተብሎም ከዚህ ቀደም በሰ/መ/ በሆነው ላይ በግራ ቀኙ መካከል የስረ ነገር ክርክርን አስመልክቶ በቀረበው ጉዳይ ላይ በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት ተወስኗል።ሆኖም ግን ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት ከዚህ ቀደም በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ሲሰጥ የውርስ ሀብቱ የገበያ ዋጋ በምን አግባብ ላቆረጥ ወይም ተወስኖ ላታወቅ እንደሚችል በግልፅ አለማመላከቱን ከውሳኔው ይዘት ለመገንዘብ ተችሐል።ይሁን እንጂ ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በዚህ በተጠቀሰው ውሳኔ ይሄንን ጉዳይ በግልፅ ባያመለክትም በልሎች በርካታ መዝገቦች ላይ ግን በተለይም በሰበር መ/ ላይ የአንድ ንብረት ወይም ቤት የወቅቱ የገበያ ዋጋ ላቆረጥ የሚችለው ከተቻለ በስምምነት ይህ ካልተቻለ ደግሞ ቤቱ ለጨረታ ቀርቦ በሚያወጣው ከፍተኛ ዋጋ መሰረት መሆኑን በአዋጅ ቁ 454/97 አንቀጽ 2(1) ድንጋጌ መሰረት አስገዳጅ የህግ ትርጉም ተሰጥቶበታል።ይህ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔም ለዚህ ለተያዘው ጉዳይም አግባብነት ያለው ሆኖ ስላገኘን አመልካቾች የውርስ ሀብቱን ግማሽ ድርሻቸውን የወቅቱን የገበያ ዋጋ ግምት ተቆርጦ ወይም ታውቆ ላከፈላቸው የሚገባው በዚህ መሰረት ሆኑ አግኝተነዋል።ስለሆነም የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎትም ጉዳዩን ከዚህ አንፃር ተመልክቶ ውሳኔ መሰጠት ሲገባ በደ/ማርቆስ ከተማ አገልግሎት ፅ/ቤት ባለሙያ ተገምቶ የቀረበውን የቤቱን ግምት የገበያ ዋጋ ግምት እንደሆነ አድርጐ በመውሰድ እና አመልካቾች በዚህ መሰረት ግማሽ ድርሻቸውን ብር 19,559.55 እንዲያገኙ በማለት የሰጠው ውሳኔ ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን አስገዳጅ የሰበር ውሳኔዎችን ይዘት ያላገናዘበ በመሆኑ ውሳኔው መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል።በመሆኑም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
1.የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ/ 25073 በ5/02/06 ዓ/ም የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ተሸሯል።
2.የምስራቅ ጉጃም አስተዳደር ዞን ከፍ/ፍ/ቤት