No summary available.
ግንቦት 18 ቀን 2006 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሣ ሙሰጠፋ አህመድ አመልካች፡- የኢትዮጱያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሰልጣን ዐ/ሕግ ምህረት ቁምላቸው ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
ቅ ጣ ት ተጠሪዎች በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 91(1) ሥር የተመለከተውን ድንጋጌ የተላለፉ ጥፋተኞች ናቸው ተብሎ የተወሰነ ሲሆን ጥፋተኝነቱ የተረጋገጠበት ሰው ደግሞ ተገቢውን ቅጣት ላያገኝ ይገባል።
ተጠሪዎች ጥፋተኛ የተባሉበት ድንጋጌ የሚያስቀጣው ወንጀሉ የተፈፀመባቸው እቃዎችና መሳሪያዎች እና የወንጀሉ ፍሬ መወረሱ እንደተጠበቀ ሆኖ በእቃዎቹ ላይ ላከፈል ከሚገባው ቀረጥና ታክስ ጋር በሚመጣጠን የገንዘብ መቀጫና ከሰባት እስከ አስራአምስት አመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ነው።ድንጋጌው በፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በወጣው የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ መሰረት የወንጀል ደረጃ እርከን ያልወጣለት በመሆኑ በመመሪያው መሰረት በድንጋጌው የመነሻ ቅጣት ሰባት አመት እና በጣሪያው፤በአስራ አምስት አመት መካከል ያለውን ልዩነት በአራት በማካፈል የምናገኘው የመጀመሪያውና ቀላል ተብሎ የሚታወቅ ደረጃ ቅጣት ፍቅድ ስልጣን ከሰባት አመት እስከ ዘጠኝ አመት ሲሆን መካከለኛው ደግሞ ከዘጠኝ አመት እስከ አስራ አንድ አመት ነው።ከባድ ተብሎ የሚለየው ደግሞ ከአስራ አንድ አመት እስከ አስራ ሶስት አመት ነው። በስልቱ መሰረት የመጨረሻው ደግሞ ከአስራ ሶስት አመት እስከ አስራ አምስት አመት ይሆናል።
ዓቃቤ ሕግ ደረጃው መካከለኛ ተብሎ እንዲመደብ ያመለከተ ሲሆን ለዚሁ ምክንያት ያደረገውም የወንጀል ሕጉን አንቀፅ 84(1(ሐ)) ድንጋጌ ነው።ይሁን እንጂ የወንጀሉ አፈጻጸም ዘድ፤ጊዜ ቦታና የአፈጻጸሙ አኳኋን ሲሆን በዚህ ድንጋጌ በተመለከተው ይዘትና መንፈስ ነው ለማለት የሚቻል ያለመሆኑን ከድርጊቱ አጠቃላይ አፈፃጸም የተረዳን በመሆኑ የዓቃቤ ህጉን አስተያየት አልተቀበልነውም።በመሆኑም ተጠሪዎች ስልጣን ከልለው አካል ደረሰኝ በመያዝና ተገቢውን ቀረጥና ታክስ ያህል ሳይከፍሉ እቃውን ወደ ውጪ አገር በማውጣት ላይ ሳሉ መያዛቸው የወንጀሉን ደረጃ ዝቅተኛ ላያደርገው የሚገባው ሁኖ አግኝተናል።በዝቅተኛ የወንጀል ደረጃ ስር የፍርድ ቤቱ ፍቅድ ስልጣን ከሰባት አመት እስከ ዘጠኝ አመት ሲሆን ይህ ፍቅድ ስልጣን ደግሞ በቅጣት አወሳሰን መመሪያው በእርከን 23 ስር የሚወድቅ ነው።ከዚሁ ውስጥ መነሻ ቅጣቱ ሰባት አመት ላሆን እንደሚገባው ይዘናል። በዓቃቤ ሕግ በኩል በተጠሪዎች ላይ የቀረበ የቅጣት ማክበጃ ምክንያት የልለ ሲሆን ተጠሪዎች ሪከርድ ያልቀረበባቸው በመሆኑ ከዚህ ወንጀል በፊት መልካም ባህርይ የነበራቸው መሆኑን ችሎቱ ተገንዝቧል፡፤ክርክሩ በተነሳበት ጊዜ ስራ ላይ በነበረው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ አንቀጽ 16(7) ደግሞ መነሻ ቅጣታቸው ሰባት አመት በላይ ለሆኑት ወንጀሎች አንድ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት የሚያስቀንሰው ሶስት እርከን መሆኑ ተመልክቷል። በመሆኑም በአንድ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት ከእርከን 23 ወደ እርከን 20 አውርደናል። በዚሁ እርከን ውስጥ የፍርድ ቤቱ ፍቅድ ስልጣን ደግሞ ከአራት አመት ከአምስት ወር እስከ አምስት አመት ከአራት ወር ነው። ተጠሪዎች ስራቸው የተለያዩ ሲሆን በወንጀሉ የነበራቸው ሚናም ተመሳሳይ ነው ተብሎ አይገመትም። በመሆኑም 1ኛ ተጠሪ የእቃው ባለቤትና ቀረጥና ታክስ አከፋፈል ላይም ከልሎቹ ተጠሪዎች የላቀ ኃላፊነት ያለበት ሲሆን 3ኛ ተጠሪ ደግሞ የመኪናው ረዳት በመሆኑ ከልሎቹ ያነሰ ተሳትፎ እንደሚኖረው ይታመናል። ቅጣት ደግሞ መወሰን ያለበት የአጥፊዎችን የተሳትፎ ደረጃም ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ስለመሆኑ ከወንጀል ሕጉ አንቀጽ 41 ድንጋጌ ይዘት የምንረዳው ጉዳይ ነው። ከዚህ አንፃር ስንመለከተው በተጠሪዎች ላይ የሚጣለው ቅጣት በአንደኛ ተጠሪ ጋርዊች ዋንግ አምስት አመት ጽኑ እስራት፣ በሁለተኛ ተጠሪ፣ ሽመልስ አየለ አራት አመት ከሰባት ወር፣ በሶስተኛ ተጠሪ፣ ሰሎሞን ተሾመ አራት አመት ከአምስት ወር ፅኑ እስራት ሆኖ አግኝተናል። የገንዘብ መቀጮውን በተመለከተም እያንዳንዳቸው ብር 250,759.16 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ ዘጠኝ ብር ከአስራ ስድስት ሳንቲም) እንዲከፍሉ፣ ለክሱ መሰረት የሆነው አርባ ስምንት በርሜል ነዳጅና አንድ መቶ ኩንታል ሲሚንቶ ደግሞ ለመንግስት ውርስ እንዲሆን ብለናል።
ተጠሪዎችን የፍድራል ፖላስ ከክፍሉ ፖላስ ጋር በመተባበር ካሉበት በመያዝ ለጋምቤላ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር እንዲያስረክብ፣ ማረሚያ ቤቱም ተጠሪዎቹን ፖላስ ይዞ ሲቀርብ በመረከብ በዚህ ችሎቱ በተወሰነው የቅጣት ውሳኔ መሰረትና በጉዳዩ ላይ የታሰሩት ጊዜ ካለ በማሰብ ተከታትሎ እንዲያስፈፅም ብለናል። ይጻፍ።
የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔውን እንዲያውቁት የውሳኔው ግልባጭ ይድረሳቸው ብለናል።
No topics extracted.