No summary available.
ሐምል 29 ቀን 2006 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሀመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽላት ይመሰል አመልካች፡- ማም ኢንዱስትሪ ኃላ/የተ/የግል/ማህበር አልቀረቡም ተጠሪዎች፡-
ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዳዩ በኮንቴነር ዲፖዚት ዋስትና የተያዘ ገንዘብ ይለቀቅልኝ ወይም ይከፈለኝ በሚል መንገድ የቀረበ ጥያቄን የሚመለከት ነው።
በስር ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ አንደኛ ተጠሪ /አንደኛ ተከሳሽ/ ሁለተኛ ተጠሪ /ሁለተኛ ተከሳሽ/ በመሆን ተከራክረዋል።
ሰነዶችን በአንደኛ ተከሳሽ አቅርቦ ገንዘብ እንዲመለስ በማድረጉ በከሳሽ ላይ ለደረሰው ኪሳራ ኃላፊነት አለበት። ስለዚህ ገንዘቡን በአንድነትና በነጠላ እንዲከፍሉ ውሳኔ ቢሰጥልኝ በማለት ክስ አቅርቧል።
የስር ፍርድ ቤትም ይህንን የአንደኛ ተከሳሽ የመጀመሪያ የክስ መቃወሚያ በመቀበል ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን የለኝም በማለት በብይን መዝገቡን ዘግቷል። አመልካች በዚህ ብይን ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቧል። ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የአመልካችን ይግባኝ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 339 መሰረት ሰርዞታል።
አመልካች የመልስ መልስ ባለማቅረቡ፤ የመልስ መልስ የማቅረብ መብቱ ታልፏል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የስር ፍርድ ቤት አመልካች በተጠሪዎች ላይ ያቀረበውን ክስ በዳኝነት አይቶ የመወሰን ሥልጣን የለኝም በማለት የሰጠው ብይን የህግ መሰረት ያለው ነው ወይስ አይደለም የሚለው ጭብጥ በመያዝ ጉዳዩን መርምረናል።
ጉዳዩን እንደመረመርነው አመልካች አንደኛ ተጠሪ ክስ ያቀረበበት ገንዘብ የመመለስ ኃላፊነት አለበት የሚለው አንደኛ ተጠሪ የአዋጅ ቁጥር 622/2001 ከሚደነግገው ውጭ ከኮንቴነር ዋስትና ያስያዝኩትን ገንዘብ አይመለስልህም ያለኝ በመሆኑ ገንዘቡን እንዲመልስ ይወሰንልኝ በማለት ነው። ይህም አመልካች አንደኛ ተጠሪ ዋስትና ያስያዝኩትን ገንዘብ የመመለስ ህጋዊ ግድታ አለበት የሚልና የአንደኛው ተጠሪ ኃላፊነት የሚመነጨው ከሕግ መሆኑን አመልካች በግልፅ ጠቅሶ የተከራከረ መሆኑን ያሳያል።
አመልካች በሁለተኛው ተጠሪ ዙሪያ የቀረበው ጥያቄ፤ ሁለተኛው ተጠሪ አስፈላጊ የግምሩክ ስርዓት እንዲፈጽምና የትራንዚት ሥራ እንዲሰራ ውክልና ተሰጥቶታል።
በሁለተኛ ተጠሪ ለአመልካች ለመስጠት በተዋዋለው የትራንዚት አገልግሎት መሰረት አስፈላጊ ሰነዶችን በአንደኛ ተጠሪ በማቅረብ ገንዘቡን በወቅቱ መጠየቅና ማስመለስ ሲገባው ይህንን ግድታውን ባለመፈጸም ገንዘቡን አንደኛ ተጠሪ ገቢ አድርጎታል። ስለዚህ የደረሰብኝን ኪሳራ የመተካት ኃላፊነት አለበት በማለት የሁለተኛው ተጠሪ ኃላፊነት ምንጩ በሁለተኛ ተጠሪ በአመልካች መካከል ያለው የትራንዚት አገልግሎት ውል መሆኑን በመግለፅ ክስ ያቀረበ መሆኑን ተረድተናል።
አንደኛ ተጠሪ አመልካች ዕቃ ላስገባባቸው ኮንቴነሮች በመያዝ እስከ ሚይዙ የነበረውን ገንዘብ መኖሩን የማይክድ አመልካች ተገቢውን የጉምሩክ ስርዓት በመፈፀም ኮንቴነሮቹን የመለሰ መሆኑን ገልፆ በወቅቱ ገንዘብ እንዲመለስለት ጥያቄ አላቀረበም። ስለዚህ ገንዘቡ ለመንግስት ገቢ ሆኗል። አመልካች ቢያንስ አስተዳደራዊ ውሳኔ ስህተት ነው የሚል ከሆነ በመጀመሪያ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያቋቋማቸው አቤቱታና ቅሬታ ሰሚ አካላት ማቅረብ አለበት በመሆኑ ይህ ስርዓት ሳይጠናቀቅ በፍርድ ቤት አይታይም በማለት መቃወሚያ አቅርቧል።
የአንደኛ ተጠሪን መቃወሚያ ስንመረምረው ጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ጋር በሚሰጡ አስተዳደራዊ ውሳኔዎች ቅር የተሰኘ ሰው ባለስልጣኑ አቤቱታ አጋር ቡድን ውሳኔው በተሰጠ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ ማቅረብ እንደሚገባም ከአዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀፅ 89 ንዑስ አንቀፅ 2 እና ንዑስ አንቀፅ 3(ሐ) ድንጋጌ ለመረዳት ይቻላል። በአዋጅ አንቀፅ 2 ንዑስ አንቀፅ 17 መሰረት የጉምሩክ ሥርዓት የሚለው ቃልና ወደ አገር የሚገባ፤ ወደ ውጭ አገር የሚላክ ወይም ተላላፊ ዕቃ ከጉምሩክ ወደብ ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ ከጉምሩክ ቁጥጥርም እስከሚወጣ ድረስ የሚከናወን ማናቸውንም የጉምሩክ አፈፃፀም ሂደት የሚጨምር ስለመሆኑ ተደንግጓል። ከዚህ አንፃር ሲታይ አመልካች ዕቃ አስቦ ያስገባቸውና ወደ ውጭ የሚመልስ ስለመሆኑ የዋስትና ገንዘብ ያስያዘባቸው ኮንቴነሮች ከጉምሩክ ቁጥጥር ስር የሚወጡበትን የሚሄዱበትን አመልካች መያዣውን የሚጠይቅበትን ሂደት የሚያካትት መሆኑን ለመገንዘብ ይቻላል።
አመልካች የመያዣያ ገንዘቡን ለማስመለስ አስፈላጊውን ሥርዓት አሟልቶ ለባለስልጣኑ መስሪያ ቤት መጠየቂያና ባለስልጣኑ ለሚወሰነው ውሳኔ ቅር ከተሰኘ በአስራ አምስት ቀናት ውሰጥ ለባለስልጣኑ አቤቱታ አጣሪ ቡድን ቅሬታውን ማቅረብ እንዳለበት የአቤቱታ አጣሪ ቡድን የሚያቀርበውን የውሳኔ ሀሳብ ተከትሎ ዳይሬክተሩ በሚሰጠው ውሳኔ ቅር በተሰኘ በሰላሳ ቀናት ውስጥ ለግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ማቅረብ እንደሚገባውና አመልካች በሰላሳ ቀናት ውስጥ የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ካላቀረበ የዳይሬክተሩ ውሳኔ የመጨረሻ እንደሚሆን በአዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀፅ 89 ንዑስ አንቀፅ 2 ንዑስ አንቀጽ 3(ሐ) ንዑስ አንቀፅ 5 እና ንዑስ አንቀፅ 6 ድንጋጌዎችና ከባለስልጣን በቦንድ ወይም በዋስትና ስለተያዘ ገንዘብ አመላላሽ የወጣውን መመሪያ ቁጥር 37/2002 አንቀፅ 9 ድንጋጌዎች ይዘት ለመረዳት ይቻላል። ከዚህ አንፃር ሲታይም አመልካች በዋስትና ያስያዝኩት ገንዘብ ይመለስልኝ በማለት የስር ፍርድ ቤት ቀጥታ ክስ ያቀረበው በአዋጅ ቁጥር 622/2001 እና አዋጁን ለማስፈፀም በወጣው መመሪያ ቁጥር 37/2002 አንቀፅ መሰረት ሥልጣን ላላቸው አካላት ቅሬታውን ሳያቀርብና ሳይወሰን በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት አመልካች በአንደኛው ተጠሪ ላይ ያቀረበውን የክስ በዳኝነትን አይቶ የመወሰን ሥልጣን የለኝም በማለት የሰጠውን ብይን ከላይ የጠቀስናቸውን የሕግ ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገና የህግ ስህተት ያልተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የስር ፍርድ ቤት አመልካች በአንደኛ ተጠሪ ላይ የቀረበውን ክስ ለማየት የዳኝነት ሥልጣን የልለው መሆኑ፤ የስር ፍርድ ቤት አመልካች በሁለተኛው ተጠሪ ላይ የቀረበውን ክስ በዳኝነት አይቶ በመወሰን የሚገድበው አይደለም። አመልካች በሁለተኛው ተጠሪ ላይ ያቀረበው ክስ ሁለተኛው ተጠሪ የአመልካች ትራንዚተር ሆኖ ውክልና ወስዶ እያለ ተገቢውን የጉምሩክ ስርዓት ፈፅሞ በመያዣ የተሰጠውን ገንዘብ ባለማስመለሱ የደረሰብኝን ኪሳራ እንዲተካ ይወሰንልኝ የሚል ነው። ይህ አመልካች በሁለተኛ ተጠሪ ላይ ያቀረበው ክስ በባህሪው አመልካች በአንደኛ ተጠሪ ላይ ባቀረበው ክስ ተነጥሎ ላታይና ላወሰን የሚችል ዳኝነት የተጠየቀበት የገንዘብ መጠንም በስር ፍርድ ቤት የዳኝነት የስረ ነገረ ስልጣን ስር የሚወድቅ ነው። ከዚህ አንፃር ሲታይ (ሀ) በአመልካች በሁለተኛው ተጠሪ መካከል የተደረገ የትራንዚት አገልግሎት ውል አለ ወይስ የለም (ለ) በሁለቱ መካከል የተደረገ የትራንዚት አገልግሎት ውል አለ ከተባለ ሁለተኛ ተጠሪ አመልካች ለኮንቴነሮች ያሰያዘው የዋስትና ገንዘብ እንዲመለስ የመጠየቅ ኃላፊነት አለበት ወይስ የለበትም? ሁለተኛ ተጠሪ በዋስትና የተያዘውን ገንዘብ የመጠየቅ ኃላፊነት አለበት ቢባል፤ ሁለተኛ ተጠሪ ይህንን ኃላፊነቱን በአግባቡ ተወጥቷል ወይስ አልተወጣም?
የሚሉትንና ልሎች አከራካሪ ጭብጦች በመጨረሻም ሁለተኛ ተጠሪ ገንዘቡን ለአመልካች የመተካት ኃላፊነት አለበት ወይስ የለበትም የሚሉትን ጭብጦች በመያዝ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ በመስማት መወሰን ሲገባው የስር ፍርድ ቤት አመልካች በአንደኛው ተጠሪ ላይ ያቀረበው ክስና አመልካች በሁለተኛ ተጠሪ ላይ ያቀረበው ክስ የተለያዩ መሆናቸውን ሳያገናዝብ፤ ጉዳዩን የማየት ስልጣን የለኝም በማለት የሰጠው ብይን የአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀፅ 14 ድንጋጌዎች የሚጥስና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት ተወስኗል።
የፍድራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የመዝገብ ሰኔ 19 ቀን 2005 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔና የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ህዳር 12 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ ተሻሽሐል።
የፍድራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አመልካች በአንደኛ ተጠሪ ላይ ያቀረበውን ክስ በዳኝነት አይቶ የመወሰን ሥልጣን የለኝም በማለት የሰጠው የውሳኔ ክፍል ፀንቷል።
የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች በሁለተኛ ተጠሪ ላይ ያቀረበውን ክስ በዳኝነት አይቶ የመወሰን ሥልጣን የለኝም በማለት የሰጠው የውሳኔ ክፍል ተሽሯል።
የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች በሁለተኛ ተጠሪ ላይ ያቀረበውን ክስ በዳኝነት አይቶ የመወሰን ሥልጣን ያለው በመሆኑ፤ የአመልካችንና የሁለተኛ ተጠሪን ክርክርና ማስረጃ በመስማት ውሳኔ እንዲሰጥበት ጉዳዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 341(1) መሰረት መልሰን ልከንለታል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ግራቀኙ ለየራሳቸው ይቻሉ መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.