No summary available.
ቀን 05/09/2006 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- አቶ ገ/መድህን ኃ/ማሪያም - ቀረቡ(በV.c) ተጠሪ፡- የትግራይ ክልል ዐ/ህግ - የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
አመልካች በዚህ መዝገብ አቤቱታ ያቀረቡት ጉዳዩ በልሉበት እንዲታይ የተደረገው መጥሪያው በመደበኛ መኖሪያ አድራሻቸው እንዲደርሳቸው ሳይደረግ በመሆኑ ክርክሩ በልሉበት ታይቶ የቴልኮምኒኬሽንና የኤልክትሪክ ኃይል አውታሮችን ደህንነት ለመጠበቅ በወጣው አዋጅ ቁጥር 464/1997 በአንቀጽ 4 ስር በ29/05/2005 ዓ/ም የተሰጠባቸው የጥፋተኝነት እና የአስር ዓመት ጽኑ እስራት የቅጣት ውሳኔ ተነስቶ ጉዳዩ እንደገና ባሉበት እንዲታይ ያቀረቡትን ማመልከቻ እና ተጠሪው የሰጠውን መልስ ከመረመረ በኋላ የአመልካችን ጥያቄ ባለመቀበል የትግራይ ብ/ክ/መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ.50320 በ19/11/2005 ዓ/ም. በወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ.202 (2) መሰረት የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ላታረም ይገባዋል በማለት ነው።
የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ በዚህ ጉዳይ አመልካች ፍ/ቤት እንድቀርብ ባስመዘገብኩት አድራሻ የተላከ መጥሪያ የልለ ከመሆኑም በተጨማሪ ለዋሴም በተመሳሳይ የደረሰ ነገር የለም በማለት በልሉበት የተሰጠው ፍርድ እንዲነሳላቸው ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ የመደረጉን አግባብነት ተጠሪ ባለበት ላማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዳዩ ለሰበር ክርክር እንዲቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል። የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት መሆኑ አለመሆኑ ለክርክሩ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር መርምረናል።
በዚህ መሰረት የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ጉዳዩን ያየው በፍ/ከ/ፍ/ቤት ስልጣኑ ሲሆን ጉዳዩ ተከሳሹ በልለበት እንዲታይ ትዕዛዝ የሰጠውም በተደጋጋሚ በፓላስ ተፈልገው አልተገኙም፣ በጋዜጣም ተጠርተው አልቀረቡም በማለት ነው። ተከሳሽ በበኩላቸው በልሉበት ታይቶ የተሰጠው ውሳኔ ላነሳልኝ ይገባል በማለት የሚከራከሩት መጥሪያው በምርመራ ጊዜ ቃልን ስሰጥ በገለጽኩት እና በዚሁ መሰረት ተጠሪው በክስ ማመልከቻው ላይ በገለፀው መደበኛ መኖሪያ አድራሻዬ አልደረሰኝም፣ ተከሳሽን ማግኘት አልቻልኩም በማለት ለፍ/ቤቱ የገለፀው ከመደበኛ መኖሪያ ቦታዬ ውጪ የሚገኝ የልላ ወረዳ ፓላስ ነው በማለት መሆኑን ተገንዘበናል። በመሰረቱ አንድ ከሳሽ በልለበት የተሰጠበት ውሳኔ እንዲነሳለት የሚያቀርበውን ማመልከቻ ለመቀበል ከሚቻልባቸው ምክንያቶች አንዱ መጥሪያ ለተከሳሹ ያልደረሰው የመሆኑ ጉዳይ ስለመሆኑ በወ/መ/ሕ/ስ/ስ/ቁ.
199/ሀ/ ስር የተመለከተ ሲሆን በተያዘው ጉዳይ ለአመልካች መጥሪያው የተላከው የአመልካቹ መደበኛ መኖሪያ አድራሻ በሆነው ውቅሮ ወረዳ ፓላስ በኩል ሳይሆን ወንጀሉ ተፈፀመ በተባለበት ወረዳ በሚገኘው እና ምርመራውን አጣርቷል በተባለው አጽቢ ወንበርታ ወረዳ ፓላስ በኩል ስለመሆኑ በክርክሩ ተረጋግጧል።
የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ተከሳሹን በጋዜጣ ላያስጠራ የቻለው እና ቀጥሎም ጉዳዩን አመልካች በልለበት እንዲታይ ትዕዛዝ የሰጠው የአጽቢ ወንበርታ ወረዳ ፓላስ ቁጥር 1008/8/34 በ07/09/2004 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ ተከሳሹ ከአካባቢያችን ውጪ ስለሆነ እና ዋሱም ተነግሮት ላቀርበው አልችልም ስላለ ልናቀርበው አንችልም ሲል በሰጠው ምላሽ ሳቢያ ስለመሆኑ አመልካች ከስር ጀምሮ እየተከራከሩ ሲሆን መጥሪያው በአመልካቹ የተመዘገበ የመኖሪያ አድራሻ ተልኮ የነበረ ስለመሆኑ ወይም አመልካቹ ከዚሁ አድራሻቸው ተፈልገው ላገኙ ያልቻሉ ስለመሆኑ የመዝገቡ ግልባጭ የማያመለክት ከመሆኑም በላይ የአጽቢ ወንበርታ ወረዳ ፓላስ በቁጥር 1008/8/34 በ07/09/2004 ዓ.ም የተሰጠውን ምላሽ አስመልክቶ አመልካች በሰበር አቤቱታቸው ላቀረቡት ክርክር ተጠሪው ያቀረበው ግልፅ ማስተባበያ አለመኖሩን ተገንዝበናል። በመሰረቱ ባስመዘገቡት አድራሻ መጥሪያው ለአመልካቹ የተላከ መሆኑ ወይም አመልካቹ በዚህ አድራሻቸው ተፈልገው ያልተገኙ መሆኑ ሳይረጋገጥ ወደ ጋዜጣ ጥሪ አማራጭ የሚኬድበት አግባብ ስለማይኖር የጥሪ ማስታወቂያው በጋዜጣ መነገሩ ብቻውን መጥሪያው ለአመልካች በአግባቡ እንዲደርስ ተደርጓል ለማለት የሚያስችል አይደለም። ዋሱ ተከሳሹን ላቀርበው አልችልም ብለዋል መባሉም ኃላፊነት ላያስከትል የሚችለው በዋሱ ላይ እንጂ በተከሳሹ ላይ አይደለም።
በመሰረቱ በወንጀል ጉዳይ የተከሰሱ ሰዎች የቀረበባቸውን ማንኛውንም ማስረጃ የመመልከት፣ የቀረቡባቸውን ምስክሮች የመጠየቅ፣ ለመከላከል የሚያስችላቸው ማስረጃ የማቅረብ ወይም የማስቀረብ እንዲሁም ምስክሮቻቸው ቀርበው እንዲሰሙላቸው የመጠየቅ መብት እንዳላቸው በኢ.ፍ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት በአንቀጽ 20(4) ተደንግጎ የሚገኝ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ይህንን ሕገ መንግስታዊ መብት ተግባራዊ ማድረግ የሚችሉት ደግሞ ክስ የቀረበባቸው መሆኑን በወ/መ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 123 በተመለከተው መሰረት በሚላክ መጥሪያ እንዲያውቁት ሲደረግ ነው።
ሲጠቃለል ጉዳዩ አመልካች በልሉበት ታይቶ የጥፋተኝነት እና የአስር ዓመት ጽኑ እስራት የቅጣት ውሳኔ የተሰጠባቸው መጥሪያው ባስመዘገቡት የመኖሪያ አድራሻ እንዲደርሳቸው ሳይደረግ ሆኖ እያለ እና ይህም በልሉበት የተሰጠባቸውን ውሳኔ ለማንሳት በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 199(ሀ) ድንጋጌ መሰረት በቂ ምክንያት ሆኖ እያለ ውሳኔው ተነስቶ ጉዳዩ ባሉበት እንደገና እንዲታይ አመልካች ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
በልሉበት ታይቶ የተሰጠባቸው የጥፋተኝነት እና የአስር ዓመት ጽኑ እስራት የቅጣት ውሳኔ ተነስቶ ጉዳዩ ባሉበት እንደገና እንዲታይ አመልካች ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት በመ/ በ19/11/2005 ዓ/ም የሰጠው ትዕዛዝ ተሽሯል።
አመልካች በልሉበት ታይቶ የጥፋተኝነት እና የአስር ዓመት ጽኑ እስራት የቅጣት ውሳኔ የተሰጠባቸው መጥሪያው ባስመዘገቡት የመኖሪያ አድራሻ እንዲደርሳቸው ሳይደረግ ወይም በዚሁ አድራሻቸው ተፈልገው ላገኙ አለመቻላቸው ሳይረጋገጥ በመሆኑ እና ይህም በልሉበት የተሰጠባቸውን ውሳኔ ለማንሳት በወ/መ/ሕ/ስ/ስ/ቁ. 199(ሀ) ድንጋጌ መሰረት በቂ ምክንያት በመሆኑ ውሳኔው ተነስቶ ጉዳዩ ባሉበት እንደገና እንዲታይ አመልካች ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ያለው ነው በማለት ወስነናል።
የትግራይ ብ/ክ/መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት በወ/መ/ሕ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 202(1) በተደነገገው መሰረት ቀድሞ ጉዳዩን ያዩት ዳኞች በማይሰየሙበት ችሎት አመልካች ባሉበት ጉዳዩን እንደገና በማየት በስነ ስርዓት ሕጉ በተመለከተው መሰረት የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ሰምቶ ተገቢውን ውሳኔ ላሰጥበት ይገባል በማለት ወስነናል።
በዚሁ መሰረት መፈፀም ያስችለው ዘንድ የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ለክልሉ ጠ/ፍ/ቤት እንዲሁም በሚገኙበት የመቀል ከተማ ማረሚያ ተቋም በኩል ለአመልካቹ ይላክ።
ውሳኔው የተሰጠው በአብላጫ ድምጽ ነው።
እኛ ስማችን በተራ ቁጥር 3 እና 4 የተጠቀሰው ዳኞች በአብላጫ ድምጽ በተሰጠው ፍርድ ሰላልተስማማን የልዩነት ሀሳባችን እንደሚከተለው አቅርበናል።
በመሰረቱ ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነውን የኤልክትሪክ ኃይል ሰርቆት ወንጀል ያጣራው የአፅቢ ወረዳ ፖላስ ሳይሆን የትግራይ ብ/ክ/መ/ፖላስ ኮሚሽን ስለመሆኑ የክልል ጠ/ፍርድ ቤት በሰጠው ትዕዛዝ ላይ በግልጽ ተመልክቷል።እንዲሁም የክልሉ ጠ/ፍርድ ቤት አመልካችን የክልሉ ፖላስ ኮሚሽን እንዲያቀርበው በተደጋጋሚ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ፖላስ ከአድራሻው ፈልጎ ማጣቱን እና ማቅረብ አለመቻሉን ገልጾ ምላሽ የሰጠው የክልሉ ፖላስ ኮሚሽን እንጂ የወረዳው ፖላስ ጽ/ቤት አለመሆኑን የክልሉ ጠ/ፍርድ ቤት የሰጠውና ለዚህ የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው የትዕዛዙ ግልባጭ በግልጽ ያሳያል።ከዚህም መገንዘብ የሚቻለው የክልሉ ጠ/ፍርድ ቤት ለሰጠው ትዕዛዝ መነሻ ያደረገው አመልካች በሰበር አቤቱታው እንደገለጸው በወረዳ ፖላስ የተሰጠውን ምላሽ ሳይሆን ከክልሉ ፖላስ ኮሚሽን የተሰጠውን ምላሽ መሆኑን ነው።የክልሉ ፖላስ ኮሚሽን ደግሞ አመልካችን ከአድራሻው ፈልጎ ማጣቱንና በዚህም ምክንያት ማቅረብ አለመቻሉን አረጋግጦ እስከገለጸ ድረስ ለአመልካች መጥሪያው በአድራሻው እንዲደርሰው ተገቢው ጥረት አልተደረገም ለማለት የሚቻል አይሆንም ።
በአድራሻው ተፈልጎ ማግኘት ካልተቻለ ደግሞ የሚኖረው አማራጭ የመጥሪያ አደራረስ ሥርዓት በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 162(1) ሥር እንደተመለከተው የጥሪ ማስታወቂያ በጋዜጣ እንዲወጣ ማድረግ ሲሆን በጋዜጣም ጥሪ ተደርጎለት አመልካች ላቀርብ አልቻለም።እንዲሁም ዋሱም ተጠይቆ አመልካች በአድራሻው እንደልለ እና ማቅረብ እንደማይችል ገልጿል። እነዚህም ጠቅላላ ሁኔታዎች አንድ ላይ ሲታዩም አመልካች በራሱ ምክንያት ፍርድ ቤት ቀርቦ ለመከራከር አለመፈለጉን መደምደም ከሚቻል በስተቀር ከመጥሪያ አደራረስ ሥርዓት አንጻር የተፈጸመ ጉድለት የለም። በአጠቃላይ መጥሪያው በአድራሻ እንዲደርሰው ተገቢው ጥረት ተደርጎ ከታጣ በኋላ በጋዜጣም ጥሪ ተደርጎለት ባለመቅረቡ የተነሳ ጉዳዩ አመልካች በልለበት እንዲታይ በማድረግ የተሰጠው ውሳኔ መጥሪያው በአድራሻው እንዲደርሰው አልተደረገም በሚል ምክንያት እንዲነሳ ማድረግ በክልሉ ጠ/ፍርድ ቤት የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮች መሰረት ያላደረገ በመሆኑ አብላጫው ድምጽ መጥሪያው በአግባብ ለአመልካች እንዳልደረሰው ቆጥሮ በልለበት የተሰጠው ውሳኔ እንዲነሳ መወሰኑ ተገቢ ሆኖ ባለማግኘታችን በሀሳብ ተለይተናል።
No topics extracted.