No summary available.
ሰኔ 17 ቀን 2006 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ አልማው ወል ረታ ቶሎሳ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- 1.አቶ አዳሙ ዘለቀ 2.አቶ ሽባባው ወሂሶ የቀረበ የለም 3.አቶ ኃይሉ ሸበት ተጠሪ፡- የአማራ ክልል አቃቤ ሕግ የቀረበ የለም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ የአንድ ወንጀል ጉዳይ በስነ ስርዓት ሕጉ መሰረት ተከሳሹ በልለበት እንዲታይ ተደርጎ የጥፋተኛነትና የቅጣት ውሳኔ የተወሰነበት ሰው ውሳኔውን እንዲነሳለት ለመጠየቅ የሚችልበትን የጊዜ ገደብ አተገባበርን የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በአዊ ብሕረሰብ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው።አመልካቾች በዚህ ፍርድ ቤት በዞኑ አቃቤ ሕግ የተከሰሱት ታደሰ ግዛት ከተባለ ግለሰብ ጋር ሁነው ገበየሁ ጋው የተባለ ሰው በግፍ ገድለዋል ተብሎ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1) (ሀ) እና 539(1/ሀ) ተጠቅሶባቸው ነው።የአሁኑ አመልካቾች በበኩር ጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ላቀርቡ አልቻሉም ተብሎ ጉዳዩ በልሉበት የታየ ሲሆን የስር 4ኛ ተከሳሽ የነበረው ታደሰ ግዛት ግን ቀርቦ ተከራክሯል።ፍርድ ቤቱም በአቶ ታደሰ ግዛት የቀረበውን ክስ በተመለከተ የአቃቤ ሕግ ምስክሮች ከሰማ በኋላ ጉዳዩን መርምሮ የምስክሮች ቃልና ተከሳሹ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 27(2) መሰረት ለፖላስ የሰጠው ቃል የማይጣጣም፣ እርስ በእራሱ የሚጋጭ ሁኖ ተገኝቷል በሚል ምክንያት ተከሳሹን በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 141 መሰረት በነጻ ያሰናበተው ሲሆን የአሁኑ አመልካቾችን በተመለከተ ግን በአቃቤ ሕግ ምስክሮች የሰው ግድያ ወንጀል የፈፀሙ መሆኑ ተረጋግጦባቸዋል በማለት ለወንጀሉ ኃላፊ ያደረጋቸው ሲሆን አድራጎቱንም በአቃቤ ሕግ የክስ ማመልከቻ በተጠቀሰው ድንጋጌ ስር ሳይሆን ተራ በሆነ የሰው ግድያ ወንጀል የሚሸፈን ነው በማለት በክስ ማመልከቻው ላይ የተጠቀሰውን ድንጋጌ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 113(2) መሰረት ወደ የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 32(1/ሀ) እና 540 ድንጋጌ ለውጦ አመልካቾችን እያንዳንዳቸውን በ18 (አስራ ስምንት) አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ጥቅምት 08 ቀን 2004 ዓ/ም በዋለው ችሎት ወስኗል።ከዚህ በኋላ የአሁኑ አመልካቾች ከመጋቢት 29 ቀን 2004 ዓ/ም ጀምሮ ፍርዱን መፈፀም መጀመራቸውንና በዋናው ጉዳይ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በ01/08/2004 ዓ/ም ይግባኝ ጠይቀው እንደሚገኙ ገልጸውና ቀድሞ መፈፀም ያለበት ስርዓት በልሉበት የተሰጠው ውሳኔ እንዲነሳላቸው ፍርዱን ለሰጠው ፍርድ ቤት ማቅረብ መሆኑን መገንዘባቸውን ጠቅሰው በልሉበት የተሰጠው ውሳኔ ውድቅ ሁኖ ክርክሩ ባሉበት እንደገና እንዲሰማ ትእዛዝ እንዲሰጥላቸው ግንቦት 20 ቀን 2004 ዓ/ም በተጻፈ ማመልከቻ ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በአሁኑ አመልካቾች ጥያቄ ላይ የዞኑ አቃቤ ሕግ አስተያየት እንዲሰጥበት ከአደረገ በኋላ ጉዳዩን መርምሮ አመልካቾች ጉዳዩ በልሉበት ታይቶ የተወሰነ መሆኑን ያወቁት ከመጋቢት 29 ቀን 2004 ዓ/ም ጀምሮ መሆኑን፣አንድ የወንጀል ጉዳይ በልለበት ታይቶ እንዲወሰንበት የተደረገ ሰው ደግሞ ውሳኔው ውድቅ እንዲሆን ጥያቄ ማቅረብ ያለበት ውሳኔው መሰጠቱን ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ በሚቆጠር በሰላሳ ቀናት ውስጥ መሆኑን በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 198 ስር የተደነገገ መሆኑን እንዲሁም አመልካቾች ይግባኙን ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስርዓቱን ባለማወቅ አቅርበናል የሚሉት ምክንያትም ሕጋዊ ያለመሆኑን በምክንያትነት ይዞ የአመልካቾችን ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል።በዚህ ትዕዛዝ የአሁኑ አመልካቾች ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታቸውን ለክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት አቅርበው ከተጠሪ ጋር እንዲከራከሩ ከተደረገ በኋላ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በጉዳዩ ላይ ሰኔ 08 ቀን 2004 ዓ/ም የሰጠው ትዕዛዝ ጸንቷል።የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- የክልሉ ፍርድ ቤቶች የሰላሳ ቀናት ጊዜ ለመቁጠር መነሻ ያደረጉት ሁኔታ የአመልካቾችን በዋናው ጉዳይ ላይ ይግባኝ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው ቆይተው በስነ ስርዓት ተገቢውን ለመፈጸም ጥያቄውን ማቅረባቸውንና የመከራከር መብት መከበር ያለበት መሆኑን በአግባቡ ሳይገነዘቡ ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በዚህ ችሎት እንዲታይ በመደረጉ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦ ግራ ቀኙ በፅሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዳዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የአመልካቾች ጥያቄ በሰላሳ ቀናት ያልቀረበ ነው ተብሎ ውድቅ መደረጉ በአግባቡ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን ነጥብ የችሎቱን ምላሽ የሚያስፈልገው ሁኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካቾች በልሉበት እንዲታይ ተደርጎ የተወሰነባቸው የጥፋተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ መኖሩን ያወቁት መጋቢት 29 ቀን 2004 ዓ/ም መሆኑን፣ሚያዚያ 01 ቀን 2004 ዓ/ም ደግሞ በዋናው ጉዳይ ላይ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ይግባኝ ማቅረባቸውን፣ በዚህ ሂደት ውስጥ ከቆዩ በኋላ በዋናው ጉዳይ ላይ ያቀረቡት ይግባኝ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ ጥቅምት 30 ቀን 2005 ዓ/ም የህግም ሆነ የፍሬ ነገር ስህተት ያልተገኘበት ነው ተብሎ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 195(1) ከመጽናቱ በፊት ግንቦት 20 ቀን 2004 ዓ/ም በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በልሉበት ታይቶ የተሰጠው ውሳኔ ውድቅ እንዲሆንላቸው አቤቱታቸውን ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡ መሆኑን ነው።
በመሰረቱ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ከአንቀጽ 197 እስከ አንቀጽ 202 የተደነገገው ሥርዓት ጉዳዩን ተከሣሹ በልለበት (default) በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 160 እስከ አንቀጽ 163 በተደነገገው መሰረት አይቶ የተሰጠውን የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሣኔ ውድቅ ለማስደረግ የሚያገለግሉ ድንጋጌዎችን ያካተቱ ሲሆኑ ድንጋጌዎች ጥያቄ መቅረብ ያለበት እና የጊዜ ገደብ፣ የጥያቄ አቅራቢ ማመልከቻ ምክንያት መግለጽ ያለበት መሆኑን፣ በጊዜ ገደቡ ውስጥ የቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት የማያገኝበትንና የሚያገኝበትን አግባብና በዚህ አግባብ በፍርድ ቤቱ የሚሰጡ ትዕዛዛት ያላቸውን ሕጋዊ ውጤቶቻቸውን በተመለከተ የሚያሳዩ ናቸው።
ወደተያዘው ጉዳይ ስንመለስም የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካቾችን ጥያቄ ውድቅ ያደረገው በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 198 በተደነገገው መሰረት በሰላሳ ቀናት ውስጥ አመልካቾች በልሉበት የተፈረደውን ፍርድ ውድቅ ለማስደረግ ፍርዱን ለሰጠው ፍርድ ቤት ማመልከቻቸውን አላቀረቡም፣ ፍርዱን ያወቁት ከመጋቢት 29 ቀን 2004 ዓ/ም ጀምሮ ሁኖ እያለ ጥያቄውን ግንቦት 20 ቀን 2004 ዓ/ም ማቅረባቸው ስነ ሥርዓታዊ አይደለም በማለት ነው።ይህ መሆኑን አመልካቾችም የሚክዱት የፍሬ ጉዳይ ክርክር አይደለም።አመልካቾች የሚከራከሩት በዋናው ጉዳይ ላይ ይግባኝ ካሉ በኃላ ትክክለኛውን ስነ ስርዓት መከተል ያለባቸው መሆኑን በመገንዘብ ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥያቄያቸውን ማቅረባቸውን በመግለጽ ነው። በእርግጥ ትክክለኛውን የህግ ስነ ስርዓት አለማወቅ ለአቤቱታው አቀራረብ በሕጉ የተደረገውን የጊዜ ገደብ ለመተው የሚያስችል ምክንያት ባይሆንም በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 198 ስር የተመለከተው የጊዜ ገደብ ማቋረጫ ሕጋዊ ምክንያት በስነ ስርዓት ሕጉ በግልጽ ያለመመልከቱ ግን ይኼው ምክንያት መኖር ያለመኖሩን ከመከራከር አጠቃላይ መብትና ከወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 160 እና ተከታይ ድንጋጌዎች መሰረታዊ አላማ አንጻር ፍርድ ቤቱ ከማየት የሚከለክል ሕጋዊ ምክንያት የልለ ሁኖ ተገኝቷል።
የመከራከር መብት በኢ.ፍ.ዲ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 20 ድንጋጌ እና በልሎች የአገሪቱ የሕግ አካል በሆኑ አለም አቀፍ ስምምነቶች ጥበቃ ያገኘ መሰረታዊ መብት መሆኑ ይታወቃል።የአለም አቀፍ የሲቪልና ፖለቲካ መብቶች ቃል ኪዳን ስምምነት አንቀጽ 14 በጠቅላላውና ንዑስ አንቀጽ 3/መ/ በልዩ ሁኔታ በአቀራረቡም ሆነ በይዘቱ የወንጀል ክስ ተከሣሽ ባለበት መታየት ያለበት መሆኑን የሚደነግግና በወንጀል የተከሰሰ ሰው ላከበርለት የሚችል ሰፊ መብት ያለው መሆኑን በዝርዝር ይደነግጋል። ይህ መብት ላከበር የማይችለው በሕጉ የተዘረጋው ስርዓት መሰረት ተደርጐ ሲሆን ከእነዚህ በህግ ከተዘረጉ ስርዓቶች አንዱ የወንጀል ክስ ተከሣሹ በልለበት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ከአንቀጽ 160 እስከ አንቀጽ 163 በተመለከተው አግባብ እንዲታይ የተዘረጋው ስርዓት ነው። የእነዚህ ድንጋጌዎች መሰረታዊ አላማ ወንጀል የፈፀሙ ሰዎች ከፍትህ ሸሽተው ተገቢውን ፍርድ ሳያገኙ እንዳይቀሩ ለማድረግ ነው ተብሎ የሚታሰብ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ድንጋጌዎቹን ተፈፃሚ የሚያደርገው ተገቢውን የመጥሪያ አደራረስ ስርዓት ተከትሎ መሆኑንም ያስገነዝባሉ። በእነዚህ ድንጋጌዎች አግባብ የመጀመሪያው የወንጀል ክሱ በልለበት የታየ ተከሣሽ በልለበት የተሰጠው ፍርድ ውድቅ እንዲሆንለት ያቀረበው ማመልከቻ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ከአንቀጽ 197 እስከ አንቀጽ 201 በተደነገገው ሥርዓት እንዲታይ መደረጉም የተከሳሽን የመከራከር መብት ከመጠበቅ አንጻር የጎላ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል። ይህ ስርዓት ሕጋዊ ምክንያት ያለውና ጥሪውን ለመስማት ያልቻለ ሰው ባለመቅረቡ ብቻ የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ ተሰጥቶ እንዳይቀር ታስቦ የተቀመጠ ስርዓት ነው ተብሎ ይታሰባል። ስለሆነም በዚህ አግባብ የሚቀርብ ጥያቄ ከመከራከር ህገ መንግስታዊ መብትና ከዝርዝር ሕጉ ድንጋጌዎች መሰረታዊ አላማ፣ ይዘትና መንፈስ ጋር ተዛምዶ መታየት ያለበት ጉዳይ ሁኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 198 ስር የተቀመጠው የሰላሳ ቀናት የጊዜ ገደብ ድንጋጌ መተርጎም ያለበት የመከራከር መብትን በማያሣጣ ወይም በማያጣብብ መንገድ መሆን አለበት።
ከዚህ አንጻር ጉዳዩን ስንመለከተው አመልካቾች በዋናው ጉዳይ ላይ ለይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበው ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ጉዳዩን ተቀብሎ በማየት ላይ እንዳለ ውጤቱን ሳይጠብቁ የመከራከር መብታቸው እንዲጠበቅላቸው ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥያቄ ያቀረቡበት ሁኔታ ጥያቄያቸውን በሰላሳ ቀን የጊዜ ገደብ ውስጥ አላቀረቡም ለማለት የሚያስችል ሁኖ አልተገኘም። እንደዚህ አይነት ጥረት የነበረው ሰው በሰላሳ ቀናት የጊዜ ገደብ ውስጥ ጥያቄውን አላቀረበም ተብሎ አቤቱታውን ውድቅ ማድረግ የመከራከር መብትን በአግባቡ ለማስከበር የሚያስችል ነው ተብሎ የማይታሰብ በመሆኑ ተቀባይነት ላሰጠው የሚገባው አይደለም። ሲጠቃለልም የበታች ፍርድ ቤቶች የአመልካቾች ሕግን አለማወቅ ጥያቄያቸውን ለመቀበል የሚያስችል አይደለም፣ ጊዜው መቆጠር ያለበት ፍርዱ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ ነው በማለት ያሰፈሩት ምክንያት ሕጋዊ ቢሆንም በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 198 ስር የተመለከተው የሰላሳ ቀናት የጊዜ ገደብ ላቋረጥ የሚችልበትን ምክንያት ግን አመልካቾች ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ይግባኝ አቅርበው ቆይተው ውጤቱን ሳይጠብቁ ትክክለኛውን ስነ ስርዓት ከመከተላቸውና ይህም ከመከራከር መብት ጋር አንፃር ሲታይ የሰላሳ ቀናት ጊዜውን ቀሪ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በሕገ መንግስቱ የተከበረው የመከራከር መብት ከወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 198 ድንጋጌ ይዘትና መሰረታዊ አላማ ጋር አጣጥሞ በመተርጎም ረገድ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የፈፀሙ ሁኖ አግኝተናል።በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በአዊ ብሕረሰብ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ሰኔ 08 ቀን 2004 ዓ/ም ተሰጥቶ በአማራ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ መስከረም 28 ቀን 2006 ዓ/ም በሰጠው ፍርድ የጸናው ትዕዛዝ ተሽሯል።
አመልካቾች ያቀረቡት አቤቱታ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 198 መሰረት በሰላሳ ቀናት ይታገዳል መባሉ ተገቢ አይደለም ብለናል።
የአዊ ብሕረሰብ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካቾች ግንቦት 20 ቀን 2004 ዓ/ም ያቀረቡትን አቤቱታ የሰላሳ ቀናት የጊዜ ገደብ የማያግደው ነው ተብሎ መወሰኑን ተገንዝቦ ጥያቄያቸውን ከወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 199 እና ተከታይ ድንጋጌዎች በመመርመር አመልካቾች በልሉበት የተሰጠውን ፍርድ ውድቅ ለማድረግ የሚያስችል ምክንያት አለው ወይስ የለውም የሚለውን ነጥብ በመመርመር ተገቢውን ዳኝነት ላሰጥበት ይገባል በማለት ጉዳዩን መልሰን ልከንለታል።ይጻፍ።፡
No topics extracted.