No summary available.
ሐምል 14 ቀን 2006 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽላት ይመሰል አመልካች፡- ወ/ሪት ጦቢያው መኮንን -ጠበቃ ዘውድ ሚናስ ቀረቡ ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ ፍርድ ቤት እግድ የሰጠበት የማይንቀሳቀስ ንብረት እግዱ ተጥሶ ውል ለማዋዋል ሥልጣን ባለው አካል ፊት በተደረገ ሽያጭ ውል መብት በልላቸው ሰዎች ለሶስተኛ ወገን ንብረቱ ተላልፎ ሲገኝ ያለውን ውጤት የሚመለከት ነው።
የክርክሩ መነሻና ይዘትም የሚከተለው ነው።
የአሁኑ 1ኛ ተጠሪ ባሁኑ 2ኛ ተጠሪ ወርቅ ያልሆነውን እቃ ወርቅ ነው በማለት በተቀነባበረ የማታለል ዘድ ብር 700,000.00 (ሰባት መቶ ሺህ) ተወስዶባቸው ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ክስ መስርተው ይህንኑ ብር 2ኛ ተጠሪ እንዲከፍላቸው ተወስኖላቸው ይህንኑ ገንዘብ ለማስከፈል በኮ/መ/ በፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንደፍርዱ እንዲፈፅምላቸው የአፈጻጸም ማመልከቻ ለፍርድ ቤቱ አቅርበው አሁን ለክርክሩ መሰረት በሆነውና በአዲስ አበባ ከተማ ጉለል ክፍለ ከተማ ክልል ውስጥ በሚገኘውና ቁጥሩ 711/3 በሆነው ቤት ላይ ሐራጅ ወጥቶ አፈጻጸሙ እንዲቀጥል ባቀረቡት ማመልከቻ መሰረት ፍርድ ቤቱ እግድ ተሰጥቶበት የነበረ መሆኑን ተገንዝቦ የሐራጅ ማስታወቂያውን አውጥቶ አፈጻጸሙን በመምራት ላይ እንዳለ የአሁኗ አመልካች ቤቱን ሐምል 04 ቀን 2004 ዓ/ም በተደረገ የሽያጭ ውል ከእግድ ትዕዛዙ በፊት የገዛሁት ነው በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 418 መሰረት ሐራጁን ለማስቆም የተቃውሞ አቤቱታ አቅርበዋል።የስር ፍርድ ቤትም በዚህ መልኩ በቀረበው የአመልካች አቤቱታ ላይ ተጠሪዎች መልስ እንዲሰጡበት አድርጓል።
የአሁኑ 1ኛ ተጠሪ በሰጡት መልስም፡-የተቃውሞ ምክንያትና ለአፈጻጸሙ መሰረት የሆነው በጉለል ክፍለ ከተማ ቀበል 08/16 ክልል ውስጥ የሚገኘው ቁጥሩ 711/3 የሆነውን መኖሪያ ቤት የአሁኑ 2ኛ ተጠሪ ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ ማስተዋል መኮንን ከአቶ ፍቅረስላሴ አየለ የገዙትና ስመ ሀብቱንም ለማዞር እንቅስቃሴ ላይ የነበሩና 2ኛ ተጠሪም ቤቱ የባለቤታቸው መሆኑን በፍርድ ቤት ችሎት ፊት ገልጸው እግድ የተሰጠበትና ለሚመለከታቸው አካላትም እግዱ የተላለፈ ሁኖ እያለ የወ/ሮ ማስተዋል መኮንን እህት የሆኑት የአሁኗ አመልካች ቤቱን ገዝቻአለሁ በማለት ጥያቄ ማቅረባቸው አፈጻፀሙን ለማሰናከል ነው በሚል የአመልካችን አቤቱታ ተቃውመዋል።2ኛ ተጠሪ አከራካሪውን ቤት ከእነ አቶ ፍቅረስላሴ አየለ ባገኙት ውክልና መሰረት ለአሁኗ አመልካች በውልና ማስረጃ የሸጡ መሆናቸውን ስለማመናቸው የክርክሩ ሂደት ያሳያል።
ጉዳዩ በዚህ መልክ የቀረበለት የፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም አመልካች ቤቱን ገዛሁ የሚሉት በቤቱ ላይ በሽያጭ ምክንያት መብት ቀሪ የሆነባቸው ሰዎች ውክልና ለአሁኑ 2ኛ ተጠሪ ሰጥተው በመሆኑና ይህ ደግሞ ሕጋዊ ጥበቃ የማይደረግለትና ጥያቄው በአጠቃላይ ከቅን ልቦና ውጪ የቀረበ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ተገንዝቧል በሚል ምክንያት የሀራጅ መቃወሚያ አቤቱታውን ውድቅ አድርጎ ቤቱ ለ2ኛ ተጠሪ እዳ ማስፈጸሚያነት ላሆን ይገባል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።በዚህ ውሳኔ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበውም ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን መርምሮ የአመልካች መቃወሚያ የቤተሰቦቻቸውን ጥቅም ለመከላከል የቀረበ እንጂ ሕጋዊ ገዥ ሁነው በቤቱ ላይ ያቋቋሙትን መብት ለመከላከል የቀረበ አይደለም በሚል ምክንያት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አጽንቶታል።የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች ሐምል 22 ቀን 2005 ዓ.ም በተፃፈ አራት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚሉበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል።
ይዘቱም ባጭሩ፡-ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት አመልካች 1ኛ ተጠሪ እግዱ እንዲነሳ በመ/ በሆነው ተሰማምተው እግዱ በተነሳበት ሁኔታ እና በሕግ አግባብ የገዙት መሆኑ ተረጋግጦ እያለ በማስረጃ ባልተደገፈ ምክንያትና ከዳኝነት አካሄድ ውጪ ተቃውሞው የቤተሰብን ጥቅም ለመከላከል የቀረበ ነው ተብሎ በግምት ተቀባይነት ማጣቱ ያላግባብ ነው የሚል ነው።አቤቱታው ተመርምሮም በዚህ ችሎት እንዲታይ በመደረጉ ተጠሪዎች ቀርበው ግራ ቀኙ በፅሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዳዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።እንደመረመረውም በጉዳዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል ለማለት ይቻላል? ወይስ አይቻልም? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሁኖ ተገኝቷል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው በአከራካሪው ቤት ላይ አቶ ፍቅረስላሴ አየለ እና የአሁኑ 2ኛ ተጠሪ ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ ማስተዋል መኮንን ሐምል 11 ቀን 2000 ዓ/ም የሽያጭ ውል ማድረጋቸውና በአሁኑ 1ኛ ተጠሪ እና እነ አቶ ፍቅረስላሴ አየለ መካከል በመ/ በተሰጠው ዋና ክርክር በመ/ በነበረው የብር 840,000.00 የፍርድ አፈጻጸም ክርክር ቤቱ በሀራጅ እንዲሸጥና ለእዳው መክፈያ እንዲውል ታዝዞ ወ/ሮ ማስተዋል መኮንን ይህንኑ በመቃወም ቤቱን ከሽያጭ ለማዳን ሲባል ቀደም ሲል ከገዙበት ብር 880,000.00 (ስምንት መቶ ሰማንያ ሺህ) ብር 240,000.00(ሁለት መቶ አርባ ሺህ) በመጨመር ሰኔ 14 ቀን 2004 ዓ/ም ተጨማሪ የቤት ሽያጭ ውል ማድረጋቸው በውል ሰነዶች መረጋገጡን የስር ፍርድ ቤት መቀበሉን፣ሰኔ 22 ቀን 2004 ዓ/ም ደግሞ የአሁኑ 2ኛ ተጠሪ የፍርድ ባለእዳ በሆኑበት መዝገብ ላይ የአሁኑ 1ኛ ተጠሪ የፍርድ ባለመብት ሁነው በጠበቃቸው አማካኝነት 2ኛ ተጠሪ ያላቸውን ንብረት በቃላ መሃላ ስር ሁነው እንዲገልጹላቸው አፈፃጸሙን ለያዘው ለፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልክተው 2ኛ ተጠሪ ባለቤቱ ወ/ሮ ማስተዋል መኮንን ከአቶ ፍቅረስላሴ አየለ የገዙት በጉለል ክፍለ ከተማ ቀበል 08/16 ክልል ውስጥ የሚገኝና ቁጥሩ 711/3 የሆነ ቤት መኖሩን በመግለጻቸው ምክንያት የፍርድ ባለመብት ይኼው ቤት እንዲታገድላቸው ቃለ መሃላ አቅርበው ፍርድ ቤቱ ሐምል 04 ቀን 2004 ዓ/ም የእግድ ትዕዛዝ ማስተላለፉን፣ሐምል 18 ቀን 2004 ዓ/ም ደግሞ ቤቱ በሀራጅ ተሽጦ ለእዳ መክፈያ እንዲውል ፍርድ ቤቱ ማዘዙን፣የአሁኗ አመልካች ሐምል 04 ቀን 2004 ዓ/ም በተፈረመና በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት ቀርቦ በተመዘገበ የቤት የሽያጭ ውል የአቶ ፍቅረስላሴ አየለና የወ/ሮ ትብይን ታደሰ ወኪል ከሆኑት ከአሁኑ 2ኛ ተጠሪ ቤቱን ገዝቼአለሁ በማለት የሚከራከሩ መሆኑን ነው። እንዲሁም የአሁኑ 1ኛ ተጠሪ በእነ አቶ ፍቅረስላሴ አየለ ላይ በመ/ በሆነው በፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስፈርደው በነበሩት መዝገብ አከራካሪውን ቤት ሰኔ 17 ቀን 2003 ዓ/ም አሳግደው የነበረ ሲሆን ይህ እግድ ሰኔ 21 ቀን 2004 ዓ/ም የተነሳው የአሁኑ ተጠሪ ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ ማስተዋል ብር 600,000.00 (ስድስት መቶ ሺህ) ለእነ አቶ ፍቅረስላሴ አየለ እዳ መክፈያነት እንዲሆንና ቤቱ እንዳይሸጥ ለማስቆም በአፈጻጸም መዝገብ መክፈላቸውና ሰኔ 14 ቀን 2004 ዓ/ም መመዝገቡ መረጋገጡን የፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ሰኔ 21 ቀን 2004 ዓ/ም ከመዘገበው ላይ ዋናውን መዝገብ በመመልከት ተረድተናል።
በመሰረቱ በፍርድ ቤት የእግድ ትዕዛዝ የሚሰጠው በክርክሩ ሂደት ረቺ የሚሆነው ወገን ለፍርድ አፈጻጸም ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር እንዲያስችለው ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 154 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መንፈስና ይዘት የምንገነዘበው ጉዳይ ሲሆን የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ደግሞ ላከበር የሚገባ መሆኑ የሚያከራክር አይደለም።ፍርድ ደግሞ ላፈጸም የሚገባው በፍርድ ባለእዳውና በሕግ አግባብ እንዳይያዙ ከሚጠቀሱት ንብረቶች/መብቶች ውጪ ባሉት የፍርድ ባለእዳ ንብረቶች/መብቶች ስለመሆኑ በቁጥር 378 እና ተከታዮቹ ከተመለከቱት የፍትሐ ብሕር ስነ ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች የምንገነዘበው ጉዳይ ነው።አንድ ሰው በሕግ አግባብ ለልላ ሰው ላያስተላልፍ የሚችለው መብትም በሕግ አግባብ ገደብ ያልተደረገበትንና ያለውን መሆኑ እሙን ነው።
ወደ ተያዘው ጉዳይ ስንመለስም በቤቱ ላይ ሰኔ 17 ቀን 2003 ዓ/ም የተሰጠው እግድ ሰኔ 21 ቀን 2004 ዓ/ም በአሁኑ 1ኛ ተጠሪ ስምምነት ጭምር የተነሳ ቢሆንም እኚህ ተጠሪ ባሁኑ 2ኛ ተጠሪ ላይ ባስከፈቱት የአፈጻጸም መዝገብ ንብረት ላያፈላልጉ ሰኔ 22 ቀን 2004 ዓ/ም በጠበቃቸው አማካኝነት አፈጻጸሙን ለያዘው ፍርድ ቤት 2ኛ ተጠሪ በመሃላ ስር ሁነው ንብረቶቻቸውን እንዲያሳውቁ ጠይቀው ተጠሪው አከራካሪውን ቤት ባለቤታቸው የገዙት መሆኑን በማረጋገጣቸው ሐምል 04 ቀን 2004 ዓ/ም በቤቱ ላይ ፍርድ ቤቱ የእግድ ትዕዛዝ አስተላልፏል።አመልካች ቤቱን ከአሁኑ 2ኛ ተጠሪ ገዛሁ የሚሉት በዚሁ ቀን ሲሆን ለውልና ማስረጃ የሀምል 04 ቀን 2004 ዓ/ም እግድ ይደርሳል ተብሎ የሚታሰብበት ስለመሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ አይደለም።ይህ መሆኑ ግን አመልካች አለኝ የሚሉትን ግዥ ሕጋዊ ነው ብሎ ለመደምደም የሚያስችል አይደለም።ሽያጩ ሲከናወን የአሁኑ 2ኛ ተጠሪ ባለቤት የቤቱ ሕጋዊ ባለሃብት ሲሆኑ በዚሁ ሰፊው መብታቸው ደግሞ በሕግ ያልተገደቡ መብቶቻቸውን መጠቀም የሚችሉ እኚህ ሰው ሴት ስለመሆናቸው ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1204፣1184 እና 1185 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዳይ ነው። በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1195 ድንጋጌ መሰረት ደግሞ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሃብትነትን በማወቅ በአስተዳደር ክፍል የምስክር ወረቀት ሲሰጥ የምስክር ወረቀቱን ያገኘው ሰው የማይንቀሳቀሰው ንብረት ባለሃብት ሁኖ ላቆጠር እንደሚገባ የተመለከተ ቢሆንም ወ/ሮ ማስተዋል ቤቱን ከእነ አቶ ፍቅረስላሴ አየለ የገዙት መሆኑን በመግለጽ በፍርድ ቤት ቀርበው የቤቱ ስመ ሃብት የተመዘገበላቸው እነ አቶ ፍቅረስላሴ አየለም የወ/ሮ ማስተዋልን ሕጋዊ ገዥ መሆናቸውን ፍርድ ቤት ፊት ቀርበው የተቀበሉ በመሆኑ የቤቱ ስመ ሃብት በወ/ሮ ማስተዋል መኮንን ያለመገኘቱ በቤቱ ላይ ህጋዊ መብት የላቸውም ለማለት የሚያስችል አይደለም። በመሆኑም የቤቱ ሕጋዊ ባለሃብት ወ/ሮ ማስተዋል መኮንን ሁነው እያለ እነ አቶ ፍቅረስላሴ ለአሁኑ 2ኛ ተጠሪ ቤቱን እንዲሸጡ ውክልና መስጠታቸው በልላቸው መብት ላይ በመሆኑ በሕግ ፊት ዋጋ የሚሰጠው አይደለም።2ኛ ተጠሪ በእነ አቶ ፍቅረስላሴ አየለ ወኪልነታቸው በሕግ አግባብ ላያስተላለፉ የሚችሉት ለሰዎቹ ሕግ ጥበቃ ላያደርግላቸው የሚችለውን መብት ብቻ ነው።አንድ ሰው በሕግ ጥበቃ ያልተደረገለትን መብት ለልላ ሰው ለማስተላለፍ መብት የለውምና።በዚህ መንገድ መብቱ የተላለፈለት ሰውም በሕግ ጥበቃ ላደረግለት አይገባም።
ልላው አመልካች ሽያጩ ሕጋዊ ነው በማለት የሚያቀርቡት ክርክር ውሉ ሕግ ስልጣን በሰጠው አካል ፊት የተረጋገጠ ነው በሚል ነው።በእርግጥ ውልና ማስረጃ በዚህ ረገድ ሕጉ ስልጣን የሰጠው አካል መሆኑን ከአዋጅ ቁጥር 334/1995 የምንገነዘበው ጉዳይ ነው። በውልና ማስረጃ ጽ/ቤትም በሕግ የባለቤትነት መብት ማረጋገጫየሚሰጥባቸውን ንብረቶች ለማስተላለፍ የሚዘጋጁ ሰነዶች ከመዘጋጀታቸው በፊትም ሰነድ አረጋጋጩ ንብረቱ በመያዥነት ያልተሰጠ ወይም በፍርድ ቤት ያልታገደ መሆኑን ላያረጋገጥ እንደሚገባ አዋጅ ቁጥር 334/95 አንቀጽ 15(2) ድንጋጌ በኃይለ ቃል አስቀምጦ እናገኛለን። በመሆኑም አመልካች አከራካሪውን ቤት የገዙት በውልና ማስረጃ በተረጋገጠ ውል ቢሆንም የቤቱ ስመ ሃብት ከእነ አቶ ፍቅረስላሴ አየለ ወደ ወ/ሮ ማስተዋል መኮንን ባለመዞሩ ምክንያት በሕግ ፊት ተቀባይነት ያለውን ማስረጃ ከያዙት ግለሰብ ሽያጩን አግኝተዋል ለማለት የሚያስችል ሁኔታ የልለ መሆኑን በፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ የተሰጡ ትእዛዛት የሚያስገነዝቡን ጉዳይ ሁኖ አግኝተናል።
በአጠቃላይ ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያላቸው የፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የአከራካሪው ቤት ሕጋዊ ባለቤት የአሁኑ 2ኛ ተጠሪ ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ ማስተዋል መኮንን መሆናቸውንና እነ አቶ ፍቅረስላሴ አየለ ደግሞ በቤቱ ላይ የነበራቸውን መብት ለወ/ሮ ማስተዋል መኮንን በሽያጭ ማስተላለፋቸውን ፍርድ ቤት ቀርበው ከአረጋገጡ በኋላ ለወ/ሮ ማስተዋል መኮንን ባለቤት ለሆኑት ለአሁኑ 2ኛ ተጠሪ ቤቱን እንዲሸጡ ውክልና መስጠት የማይችሉ ስለመሆናቸው በማረጋገጥ የሰጡት ውሳኔ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አላገኘነውም።በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
No topics extracted.