No summary available.
ሰኔ 04 ቀን 2006 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ አዳነ ንጉሤ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ዘይነብ ጀማል አልቀረቡም ተጠሪዎች፡- 1.የቦል ክፍለ ከተማ የዲዛይንና ግንባታ አስተዳደር ጽ/ቤት አልቀረበም 2. አብዱልወሃብ መሐመድ አልቀረበም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ በአሁኗ የሰበር አመልካች ከሳሽነት የተጀመረው በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁኖቹ ተጠሪዎች ደግሞ እንደቅደም ተከተላቸው 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ነበሩ። ከሳሽ ነሐሴ 12 ቀን 2004 ዓ/ም ያቀረቡት ክስ፡በብሕራዊ ሎተሪ አዳራሽ መጋቢት 19 ቀን 1993 ዓ/ም በወጣው 10ኛ ዙር የመኖሪያ ቤት የላዝ ዕጣ በቦል ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር ክልል ውስጥ የመለያ ቁጥሩ BKB-17-B56 የሆነ 160 ካሬ ሜትር ቦታ ደርሶኝ ጥቅምት 17 ቀን 1995 ዓ/ም ለ99 ዓመት የሚቆይ የላዝ ውል ፈጽሜ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የተሰጠኝ ሲሆን በቦታው ብር 90,000.00 የሚያወጣ ግንባታ በማከናወን የፕላን ስምምነት እንዲሰጠኝ ለ1ኛ ተከሳሽ ሳመለክት የ1ኛ ተከሳሽ ባለሙያ የሆኑት 2ኛ ተከሳሽ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታዬን እና ልሎች ሰነዶቼን (ዶክመንቶቼን) ከተቀበሉኝ በኋላ የከለከሉኝ በመሆኑ ተከሳሾቹ የፈጠሩት ሁከት ተወግዶ የተቀበሉትን የቦታውን ካርታ እና ሰነዶቹን እንዲመልሱ፣የግንባታ ማከናወኛ ፈቃድም 1ኛ ተከሳሽ እንዲሰጠኝ ይወሰንልኝ የሚል ነው።
የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም፡-ከሳሽ ያቀረቡትን ክስ ከመረመረ በኋላ በሰጠው ትዕዛዝ የከሳሽ ጥያቄ ይዞታን የሚመለከት ሳይሆን በ2ኛ ተከሳሽ የተወሰዱባቸው ሰነዶች እንዲመለሱላቸው እንዲወሰን የሚል በመሆኑ ጥያቄያቸው በአስተዳደሩ በኩል ደረጃውን ጠብቆ መፍትሕ የሚያገኝ እንጂ በሁከት ይወገድልኝ ቀርቦ በፍርድ ቤት እልባት የሚያገኝ ባለመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ተቀብሎ አከራክሮ ለመወሰን ሥልጣን የለውም ሲል የክሱን መዝገብ ዘግቷል።
ከሳሽም በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ቅር በመሰኘት ለፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ይግባኙን በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/337 መሰረት በመዝጋት በማሰናበቱ የሰበር አቤቱታቸውን ለዚህ ችሎት አቅርበዋል።
አመልካች በሰበር አቤቱታቸውም በዋናነት የጠቀሱት የቅሬታ ነጥብ፡- 1ኛ ተጠሪ የፕላን ስምምነት እንዲሰጠኝ በሚል ባቀረብኩት አቤቱታ መነሻ በእጄ የሚገኙትን የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እና ልሎች ሰነዶችን 2ኛ ተጠሪ ነጥቀውኝ ለመመለስ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው አመልካችም በመሥሪያ ቤት ውስጥ በጉልበት ከ2ኛ ተጠሪ ለመቀበል ስለማልችል ያለኝ አማራጭ በፍርድ ቤት ክስ አቅርቦ ማስወሰን ሆኖ ሳለ የሥር ፍርድ ቤቶች የሁከት ተግባር በመሬት ይዞታ ብቻ እንደሚፈጸም በመቁጠር ተጠሪዎቹ የፈጸሙት ሰነዶችን የመንጠቅ ተግባር በሁከት እንደማይጠቃለል በመቁጠር ሥልጣን የለንም ሲሉ ክሴን ውድቅ ያደረጉት ያለአግባብ ነው የሚል ነው።
2ኛ ተጠሪ መጥሪያ ደርሷቸው መልስ ባለመስጠታቸው መልስ የመስጠት መብታቸው የታለፈ ሲሆን 1ኛ ተጠሪ ለሰበር አቤቱታው በሰጠው መልስ፡ አመልካች ክስ ያቀረቡት የባለይዞታነት መብት በልላቸው ጉዳይ ላይ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም፣በልላ በኩል የባለይዞታነት መብት ለማረጋገጥ የሚቻለው ለዚሁ ሲባል ከሚመለከተው መንግስት አካል በህጋዊ መንገድ የተሰጠ ይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት በማቅረብ ሲሆን ከዚህ ውጪ የሚቀርቡ ሰነዶችን በተመለከተ ግን በመመርመር መፍትሕ ላሰጥ የሚችለው የአስተዳደሩ መስሪያ ቤት እንጂ ፍርድ ቤት ባለመሆኑ እና ጉዳዩ በፍርድ ቤት ይታያል ቢባል የአስተዳደር መስሪያ ቤቱ ካርታ እንዲሰጥ የሚያስገድድ ውሳኔ ስለሚሆን የሥር ፍርድ ቤቶች ሥልጣን የለንም ሲሉ የአመልካችን ክስ ውድቅ ያደረጉት የሚነቀፍበት ምክንያት የለውም ብሐል።
1ኛ ተጠሪ ለሰጠው መልስ አመልካችም የበኩላቸውን የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል።
የጉዳዩ አመጣጥ ከዚህ በላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም፡- አመልካች ያቀረቡት ጉዳይ በፍርድ ቤት ቀርቦ ላወሰን የሚችል ነው ? ወይስ አይደለም?
ጉዳዩ በፍርድ ቤት ቀርቦ ላወሰን የሚችል ነው ቢባል የሥር የፍድራል ፍርድ ቤቶች ጉዳዩን ተቀብለው ለመወሰን የሥረ ነገር ሥልጣን አላቸው ? ወይስ የላቸውም ?
የሚሉትን ጭብጦች ይዘን ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ፡- በኢ/ፍ/ዲ/ሪ/ህገ መንግስት አንቀጽ 37(1) ማንኛውም ሰው (የተፈጥሮም ሆነ በህግ የሰውነት መብት ያለው ድርጅት) በፍርድ ቤት ላወሰን የሚገባውን ጉዳይ (justiciable matter) ለፍርድ ቤት ወይም ለልላ በህግ የዳኝነት ስልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት ያለው ስለመሆኑ ከመደንገጉም በተጨማሪ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/ 4 በቀጥታ ወይም በግልጽ ካልታገዱ በስተቀር የፍትሃብሕር ጉዳዮች ለመደበኛው ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ስለመሆናቸው ተመልክቷል። ሆኖም በቀጥታ ወይም በግልጽ በወጡ ወይም በሚወጡ ህጎች ከመደበኛ ፍርድ ቤቶች ውጪ በህግ የዳኝነት ሥልጣን የተሰጣቸው አካላት ተለይቶ የተሰጣቸውን ፍትሃብሕር ጉዳዮች ተቀብለው የመወሰን ሥልጣን ይኖራቸዋል።
በእነዚህ ድንጋጌዎች መሰረትም አንድ ጉዳይ በፍርድ ቤት ወይም በልላ በህግ የዳኝነት ስልጣን የተሰጠው አካል ተቀብሎ አከራክሮ ውሳኔ ወይም ፍርድ ላሰጥ የሚችለው ዳኝነት የተጠየቀበት ጉዳይ በፍርድ ቤት ላወሰን የሚችል ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው። ወደተያዘው ጉዳይ ስንመለስ አመልካች በክሳቸው የፕላን ስምምነት እንዲሰጣቸው በሚል በእጃቸው የነበረውን የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እና የተለያዩ ሰነዶችን (ዶክመንቶችን) ከጻፉት አቤቱታ ጋር በማያያዝ የ1ኛ ተጠሪ ሰራተኛ ለሆኑት 2ኛ ተጠሪ መስጠታቸውን 2ኛ ተጠሪም ካርታውን እና ልሎች ሰነዶችን ከተቀበሉ በኋላ ለመመለስ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን በመጥቀስ እንዲመለስላቸው ዳኝነት መጠየቃቸውን ከክሱ መገንዘብ የተቻለ ሲሆን ተጠሪዎችም ይዞታ ማረጋገጫ ካርታውን እና ልሎች ሰነዶችን ከአመልካቿ የተቀበሉ መሆን አለመሆናቸውን፤ከተቀበሉ ደግሞ ለመመለስ እንቢተኛ የሆኑበት ህጋዊ ምክንያት ካላቸው ማስረዳት የሚጠበቅባቸው ሲሆን ይህ ደግሞ ውሳኔ ላያገኝ የሚችለው ለመደበኛ ፍርድ ቤት ክስ ቀርቦ እንጂ ፍርድ ቤቶቹ በሰጡት ትዕዛዝ እንዳሰፈሩት በአስተዳደር መስሪያ ቤቱ አይደለም። በመሆኑም የሥር ፍርድ ቤቶች ጉዳዩ ከይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እና ከሰነዶች ጋር የተያያዘ በመሆኑ ብቻ ተጠሪዎቹ ካርታውን እና ሰነዶቹን ወስደው ከሆነ የወሰዱበት አግባብ ህጋዊ መሆን አለመሆኑ በፍርድ ቤት ላጣራ የሚችል ጉዳይ ሆኖ ባለበት ጉዳዩ በፍርድ ላወሰን የሚችል አይደለም ሲሉ መደበኛ ፍርድ ቤት የሥረ ነገር ሥልጣን እንደልለው በመቁጠር በሰጡት ትዕዛዝ ላይ ያሰፈሩት መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት ነው።
ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ፡- አመልካች በክሳቸው የመሬት ይዞታውን ያገኙት በወጣው የላዝ ጨረታ በመሳተፍ ዕጣው ደርሷቸው መሆኑን፤ በዚሁ የመሬት ይዞታ ላይ የላዝ ውል መግባታቸውን የገለጹ ሲሆን ይህ ችሎትም በሰበር መ/ቁ/ 77175 ሐምል 19 ቀን 2004 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ፍርድ የላዝ ውሎች አስተዳደራዊ ውሎች ተብለው እንደሚወሰዱና በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 41(1)(መ) የከተማው አስተዳደር አስፈጻሚ አካላት ወይም የከተማው አስተዳደር በባለቤትነት ሥር ያሉ ተቋማት የሚገቧቸውን አስተዳደራዊ ውሎች በተመለከተ የሚነሱ ጉዳዮችን የማየት የሥረ ነገር ሥልጣን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች ስለመሆኑ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል። በመሆኑም ጉዳዩን በየደረጃው ያዩት የሥር የፍድራል ፍርድ ቤቶች አመልካች ክስ ያቀረቡበት ጉዳይ በህጉ ለመዳኘት ከተሰጣቸው የሥረ ነገር የዳኝነት ሥልጣን ውጪ ሆኖ ሳለ የሥረ ነገር የዳኝነት ሥልጣን የልላቸው መሆኑን በመግለጽ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/9(1)፣ 231(1)(ለ) መሰረት የክስ አቤቱታው ተቀባይነት የለውም በሚል መመለስ ሲገባቸው ተቀብለው መመርመራቸው ከዚህ በላይ ከተጠቀሱት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ድንጋጌዎች እና ይህ ችሎት በሰበር መዝገብ ከሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም አንጻር ሲታይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ቢሆንም በውጤት ደረጃ ግን ፍርድ ቤቶቹ የአመልካችን የክስ አቤቱታ ውድቅ ማድረጋቸው ተገቢ በመሆኑ ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/ 198320 በቀን 28/09/2005 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠውን ትዕዛዝ እና የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/140656 በቀን 10/03/2006 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠውን ትዕዛዝ ምክንያቱን ሳንቀበል በውጤት ደረጃ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/ 348(1) መሰረት አጽንተናል።
አመልካች ያቀረቡት ጉዳይ በፍርድ ቤት ቀርቦ ላወሰን የሚችል ነው ብለናል።
የሥር የፍድራል ፍርድ ቤቶች አመልካች ያቀረቡትን ክስ ተቀብለው የመረመሩት የሥረ ነገር የዳኝነት ሥልጣን በልላቸው ጉዳይ በመሆኑ ተገቢነት የልለው ቢሆንም የክስ አቤቱታውን ውድቅ ማድረጋቸው በውጤት ደረጃ ሲታይ የሚነቀፍበት ምክንያት ያለው ሆኖ አልተገኘም።
ይህ ውሳኔ መብቱን የሚጠይቅ ወገን ሥልጣን ላለው ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤት ላያቀርብ የሚችለውን ክስ የሚያግድ አይሆንም ብለናል።
የዚህን ፍርድ ቤት ወጪና ኪሳራ የግራ ቀኙ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻሉ።
No topics extracted.