No summary available.
ሐምል 17 ቀን 2006 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽላት ይመሰል አመልካች፡- አቶ ኢብራሂም መሐመድ ኑር - ጠበቃ አሸናፊ ወጂ ቀረቡ።
ተጠሪዎች፡-
ወ/ሮ ጀሚላ መሐመድ ኑር
አቶ ሰይድ መሐመድ ኑር
ወ/ሮ ነጃት መሐመድ ኑር የቀረበ የለም።
ወ/ሮ ሐያት መሐመድ ኑር መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
በዚህ መዝገብ አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት የአሁኖቹ ተጠሪዎች የሟች አባታችን የአቶ መሐመድ ኑር ኢብራሂም ውርስ ይጣራልን ሲሉ ባቀረቡት አቤቱታ መነሻ ውርሱ ተጣርቶ ውጤቱ እንዲቀርብ ከተደረገ በኃላ በውርስ አጣሪው የቀረበውን ሪፖርት አሻሽሎ በማጽናት የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠው እና በፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጸናው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ላታረም ይገባል በማለት ነው።
የጉዳዩን አመጣጥ በተመለከተ ተጠሪዎቹ የሟች አባታችን የአቶ መሐመድ ኑር ኢብራሂም ውርስ ይጣራልን ሲሉ በወ/ሮ ባህሯ አብዱ፣በአሁኑ አመልካች እና በአቶ ጀማል መሐመድ ኑር ላይ በ18/08/2002 ዓ.ም. የተጻፈ አቤቱታ ማቅረባቸውን፣1ኛ እና 3ኛተጠሪ የነበሩት ወገኖች ውርሱ ቢጣራ ተቃውሞ እንደልላቸው የገለጹ ሲሆን 2ኛ ተጠሪ የነበሩት የአሁኑ አመልካች በበኩላቸው የሟች አቶ መሐመድ ኑር ኢብራሂም ውርስ ጉዳይ አስቀድሞ በሸሪዓ ፍ/ቤት በውሳኔ ያለቀ በመሆኑ በድጋሚ የውርስ ይጣራልን አቤቱታ ላቀርብበት አይችልም የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በማስቀደም በፍሬ ጉዳዩ ረገድም መልስ ሰጥተው መከራከራቸውን፣ፍ/ቤቱም በ12/02/2003 ዓ.ም. በሰጠው ውሳኔ አመልካች ያቀረቡትን የመጀመሪያ ደረጃ የመቃወሚያ ነጥብ ውድቅ አድርጎ በማለፍ ውርሱ ተጣርቶ ውጤቱ ይቀርብ ዘንድ አጣሪ እንዲመደብ ማድረጉን፣የማጣራቱ ሂደት መጀመሩን ተከትሎ አመልካች የውርስ ይጣራልን አቤቱታው በይርጋ የሚታገድ ነው የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ለአጣሪው ማቅረባቸውን፣አጣሪውም የዚህ ዓይነቱ መቃወሚያ መቅረብ የሚገባው ለፍርድ ቤቱ እንጂ ለአጣሪው አለመሆኑን በመግለጽ የማጣራቱን ሂደት አጠናቆ የወራሾችን ማንነት እና የውርሱን ሀብት በመለየት በ10/06/2003 ዓ.ም. የተጻፈ ሪፖርት ማቅረቡን፣ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን አስተያየት ከተቀበለ በኃላ ሪፖርቱን አሻሽሎ ማጽደቁን፣አመልካች በአጣሪው ሪፖርት ላይ ካቀረቡት አስተያየት መካከል የውርስ ይጣራልን አቤቱታው በይርጋ የሚታገድ ነው የሚል ነጥብ የሚገኝበት መሆኑን፣ይሁን እንጂ ፍርድ ቤቱ አመልካች ይህንን የመቃወሚያ ነጥብ ማቅረብ ይገባቸው የነበረው ለውርስ ይጣራልን አቤቱታው የመከላከያ መልስ በሰጡበት ጊዜ እንጂ ውርሱ ተጣርቶ ውጤቱ ከቀረበ በኋላ አይደለም በማለት የይርጋ መቃወሚያውን ሳይቀበለው መቅረቱን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።
አመልካች አቤቱታቸውን ለዚህ ችሎት ያቀረቡት የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የውርስ አጣሪው ሪፖርት ተሻሽሎ የጸደቀበትን የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ በማጽናቱ ሲሆን የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ በዚህ ጉዳይ አመልካች በሸሪዓ ፍርድ ቤቶች የታየው ክርክር በመደበኛ ፍርድ ቤቶች ላታይ አይገባውም በማለት ያቀረቡት መቃወሚያ እና የይርጋ መቃወሚያ በስር ፍርድ ቤቶች ውድቅ የመደረጉን አግባብነት ተጠሪዎቹ ባሉበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዳዩ ለሰበር ክርክር እንዲቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም ለክርክሩ በተያዘው ጭብጥ መሰረት በጉዳዩ እልባት ማግኘት የሚገባቸው ነጥቦች፡-
የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ የሰጡት አስቀድሞ በፍርድ ባለቀ ጉዳይ ነው በማለት አመልካች ያቀረቡት ክርክር ሕጋዊ ተቀባይነት ያለው ነው ወይስ አይደለም?
የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ የሰጡት በይርጋ በታገደ ጉዳይ ነው በማለት አመልካች ያቀረቡት ክርክር ሕጋዊ ተቀባይነት ያለው ነው ወይስ አይደለም?
የሚሉ መሆናቸውን በመገንዘብ አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለክርክሩ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር መርምረናል።
በዚህም መሰረት የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ በሕግ ስልጣን የተሰጠው ማንኛውም ፍርድ ቤት ክርክሩን ተቀብሎ የመጨረሻ የፍርድ ውሳኔ ከሰጠ በኃላ ቀድሞ በፍርድ የተወሰነው ክርክር ስረ ነገርና የተያዘው ጭብጥ አንድ ዓይነት ከሆነ በክርክሩ ላይ የነበሩት ወይም ከተከራካሪዎቹ መብት ያገኙ ሶስተኛ ወገኖች በዚያው ነገር ሁለተኛ ክስ ወይም ማናቸውንም ዓይነት ልላ ክርክር ለማቅረብ እንደማይችሉ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 5(1) ስር የተደነገገ ሲሆን የዚህ ዓይነቱ መቃወሚያ በተከሳሽ ወገን ላቀርቡ ከሚችሉ የመቃወሚያ ነጥቦች ውስጥ የሚካተት ስለመሆኑ፣ፍርድ ቤቱ ማስረጃ ተቀብሎ ከመመርመሩ ወይም ምስክሮችን ከመስማቱ አስቀድሞ በመጀመሪያ ደረጃ ለቀረበለት መቃወሚያ ውሳኔ መስጠት ያለበት ስለመሆኑ፣እንዲሁም ጉዳዩ አስቀድሞ በፍርድ ያለቀ መሆኑ በተረጋገጠ ጊዜ ፍርድ ቤቱ መዝገቡን ዘግቶ ባለጉዳዮችን ማሰናበት የሚገባው ስለመሆኑ እንደቅደም ተከተሉ በዚሁ ሕግ በቁጥር 244(2)(ለ)፣244(1) እና 245(2) ላይ ተመልክቷል።
በተያዘው ጉዳይ ተጠሪዎቹ የሟች አባታችን የአቶ መሐመድ ኑር ኢብራሂም ውርስ ይጣራልን በማለት በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ላቀረቡት አቤቱታ አመልካች በሰጡት የመከላከያ መልስ የሟች አቶ መሐመድ ኑር ኢብራሂም ውርስ ጉዳይ አስቀድሞ በክልል 14 መስተዳድር በ2ኛ ናዓባ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 1952/88 ታይቶ በ25/11/1988 ዓ.ም.
እልባት ያገኘ በመሆኑ በድጋሚ የክርክር ምክንያት ላሆን የሚችልበት የሕግ አግባብ የለም ሲሉ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርበው የነበረ ሲሆን ፍርድ ቤቱም በዚህ የመቃወሚያ ነጥብ ላይ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ እንደተባለው የሸሪዓ ፍርድ ቤት በሟች አቶ መሐመድ ኑር ኢብራሂም ውርስ ጉዳይ ውሳኔ መስጠቱን ተቀብሎ ነገር ግን የሸሪዓ ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን የሰጠው በኢትዮጵያ ፍድራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብላክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 34(5) እና የፍድራል ሸሪዓ ፍርድ ቤቶችን አቋም ለማጠናከር በወጣው አዋጅ ቁጥር 188/1992 አንቀጽ 4(2) እና 5(1) መሰረት የአሁኖቹ ተጠሪዎች በሸሪዓ ፍርድ ቤት ቀርበው ለመዳኘት ፈቃደኞች መሆናቸውን ካረጋገጡ በኋላ ስለመሆኑ የውሳኔው ይዘት እንደማያረጋግጥ ገልጾ የአሁኑ አመልካች ያቀረቡትን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በ12/02/2003 ዓ.ም. በነበረው ችሎት ውድቅ በማድረግ ውርሱ እንዲጣራ መወሰኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።
ጉዳዩ አስቀድሞ በፍርድ አልቋል በማለት ያቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ በመደረጉ ቅር በመሰኘት አመልካች ያቀረቡትን ይግባኝ የተመለከተው የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ በመዝገብ በ27/03/2004 ዓ.ም.በዋለው ችሎት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን ማጽናቱን እና ይህንኑ ውሳኔ ለማስለወጥ አመልካች ለፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ያቀረቡት አቤቱታም በመዝገብ በ24/08/2004 ዓ.ም. በአጣሪ ችሎት ተቀባይነት ማጣቱን ከመዝገቡ ተገንዝበናል።አመልካች ጉዳዩ አስቀድሞ በፍርድ አልቋል በማለት ያቀረቡት መቃወሚያ የሰበር አጣሪ ችሎትን ጨምሮ በየደረጃው ባሉት ፍርድ ቤቶች አስቀድሞ ተቀባይነት ያጣ መሆኑ ከተረጋገጠ ደግሞ የመቃወሚያ ነጥቡ ውድቅ የተደረገው በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ነጥብ ክርክሩ አሁን ባለበት ደረጃ ላታይ የሚችልበት ስነ ስርዓታዊ አግባብ የለም።በመሆኑም ጉዳዩ አስቀድሞ በፍርድ አልቋል በማለት አመልካች በዚህ ችሎት ያቀረቡት ክርክር ሕጋዊ ተቀባይነት ላሰጠው የሚገባ ሆኖ አልተገኘም።
ሁለተኛውን ነጥብ በተመለከተ የይርጋ መቃወሚያ በመከራከሪያነት ለማቅረብ ለተከሳሽ ወገን ከተሰጡት መብቶች ውስጥ የሚካተት ሲሆን የዚህ ዓይነቱ መቃወሚያ መቅረብ የሚገባውም ተከሳሽ ወገን ለቀረበበት ክስ የመከላከያ መልሱን በሚያቀርብበት ጊዜ በመከላከያ መልሱ ውስጥ በማካተት ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 234(1)(ሐ) እና 244(2)(ሰ) ድንጋጌዎች ተመልክቷል።በዚህ ሁኔታ መቅረብ ከሚገባቸው መቃወሚያዎች ውስጥ ሳይቀርቡ የቀሩት ትክክለኛውን ፍርድ ለመስጠት የሚያሰናክሉ እስካልሆነ ድረስ ባለጉዳዩ ራሱ ሆነ ብሎ ለማቅረብ ባለመፈለግ እንደተዋቸው የሚቆጠሩ ስለመሆኑም በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 244(3) ድንጋጌ በግልጽ ሰፍሮ ይገኛል።
በተያዘው ጉዳይ የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአመልካችን የይርጋ መቃወሚያ ሳይቀበል የቀረው እና ይግባኝ ሰሚው ፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በዚህ ረገድ አመልካች ያቀረቡትን ቅሬታ ውድቅ ያደረገው ውርሱ እንዲጣራ ለቀረበባቸው ክስ መልስ በሰጡበት ጊዜ የይርጋ መቃወሚያ ሳያቀርቡ ቀርተው መቃወሚያውን በውርስ አጣሪው ዘንድ እና ቀጥሎም ውርሱ ተጣርቶ ውጤቱ ከቀረበ በኋላ በውርስ አጣሪው ሪፖርት ላይ አስተያየት እንዲያቀርቡ በተጠየቁበት ጊዜ ቀደም ሲል ያላነሱትን የይርጋ መቃወሚያ ማንሳታቸው ስነ ስርዓታዊ አለመሆኑን በመግለጽ እንደሆነ ተገንዝበናል።የይርጋ መቃወሚያውን ለክሱ በሰጡት የመከላከያ መልስ አካተው ያላቀረቡ ስለመሆኑ ደግሞ አመልካች በሰበር አቤቱታቸውም ላይ ገልጸዋል።
በመሆኑም አመልካች ለክሱ በሰጡት የመከላከያ መልስ የይርጋ መቃወሚያ እንዳላቀረቡ የተረጋገጠ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች አመልካች ከጊዜ በኋላ ያቀረቡትን የይርጋ መቃወሚያ አለመቀበላቸው ላነቀፍ የሚችልበት ሕጋዊ ምክንያት አልተገኘም።
ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ ስላልተገኘ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
ተሰጥቶ በፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ26/03/2005 ዓ.ም.
በውሳኔ የጸናው ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
ቁጥሩ 1952/88 የሆነው የሸሪዓ ፍርድ ቤት መዝገብ ተመላሽ ይደረግ።
የውሳኔው ቅጂ ለስር ፍርድ ቤቶች ይላክ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.