No summary available.
ሐምል 4 ቀን 2006 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማዉ ወል አላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- ሚ/ር አደም ሐሚድ - ጠበቃ አቶ ኪዳነማርያም ሃጐስ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ ሐናእ አብዱልቃድር - ጠበቃ ደበበ መንግስቱ ቀረቡ።
መዝገቡንመርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ታህሳስ 4 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዳዩ ከህፃን ልጅ ማሣደጊያ የሚቆረጥ ገንዘብ መጠን የሚመለከት ክርክር ነውጉዳዩ በመጀመሪያ የታየው በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በሥር ፍርድቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
የክርክሩ መነሻ ተጠሪ ያቀረበችው ክስ ነው። ተጠሪ /ከሳሽ/ ከተከሳሽ /አመልካች/ጋር የነበራት ጋብቻ በፍቺ የፈረሰ መሆኑን ገልፃ ከሳሽና ተከሳሽ በጋብቻ ስንኖር ህፃን ሁዳ አደም የተባለች ልጅ ወልደናል። ህፃኗ አንድ ዓመት ከአስር ወሯ ነው። ስለዚህ ለህፃኗ ማሳደጊያ የሚሆን በወር ብር 94,927 /ዘጠና አራት ሺ ዘጠኝ መቶ ሃያ ሰባት ብር /ተከሳሽ እንዲከፍል ውሳኔ ይሰጥልኝ በማለት ክስ አቅርባለች። አመልካች በተከሳሽነት ቀርበው ከሳሽ የጠየቀችውን ገንዘብ ተከሳሽ በየወሩ ለህፃኗ ማሳደጊያ ለመክፈል አልችልም የሚል ክርክር አቅርበዋል። ከሳሽ ተከሳሽ ከፍተኛ ገቢ ያላቸው መሆኑን በመግለጽ ስለተከራከሩ የሥር ፍርድ ቤት የተከሳሹን ገቢ ለማረጋገጥ የተለያዩ መረጃዎችን ከሚመለከታቸው የመንግሰት አካላት ጠይቋል። ከዚህ በተጨማሪ ከሳሽ /ተጠሪ ህፃኗን ለማሳደግ የሚያስፈልጋት የትምህርትና ልሎች ወጪዎች በሰንጠረዥ መልክ አዘጋጅታ ያቀረበችውን የወጭ ዝርዝር ተመልክቶ ተከሳሽ ለሕፃኗ ማሳደጊያ በወር ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር / እንዲከፍል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት አመልካች ይግባኝ ለፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዋል። ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ይግባኝ ባይ /አመልካች / ለህፃኗ ማሳደጊያ በወር 12,000 /አስራ ሁለት ሺ ብር / እንዲከፍል ውሳኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት መጋቢት 3 ቀን 2006 ዓ.ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታ አቅርቧል። አመልካች በኢትዮጵያ የኑሮ ደረጃ አንድ ህፃን ለማሳደግ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወሰነውን ከሚፈለገው መጠን በላይ ነው። የአመልካች ትክከለኛ ገቢ አልተረጋገጠም የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ብር 12,000/ አስራ ሁለት ሺህ ብር/ እንዲከፍል የወሰነው ውሳኔውን ከሰጠበት ታህሳስ 4 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ ነው። ይህም ማለት ከሐምል 19 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ አመልካች ለህፃን ማሳደግያ ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር / እንዲከፍል የሰጠውን ውሳኔ ሳያሻሽለው አልፎታል። ስለዚህ በሰበር ታይቶ ላታረም ይገባዋል በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ በሰበር አቤቱታው ሚያዚያ 20 ቀን 2006 ዓ.ም ፅፎ ያቀረባቸው መልስ የህፃን ማሳደጊያ ገንዘብ የጠየቅሁት ለህፃኗ የትምህርት ቤት የትራንስፓርት የአልባሣት የቀለብና ልሎች ወጪዎችን በመዘርዘር ነው። አመልካች በኢትዮጵያ ውስጥ በሚላዮኖች የሚቆጠር ገቢ በዓመት ያገኘ መሆኑ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በላከው መረጃ ተረጋግጧል። አመልካች ከኢትዮጵያ ውጭ ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኙ የተለያዩ የንግድ ድርጅቶች እና የአክሲዮን ድርሻ ያለው ነው። አመልካች ከልላ የወለዳቸውን ልጆቹን ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ እየከፈለ እያሳደገ ነው። ስለዚህ የአመልካች ውሳኔ ተገቢነት የለውም በማለት ተከራክራለች። አመልካች ግንቦት 7 ቀን 2006 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው የፅሑፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለህፃን ማሳደጊያ አመልካች እንዲከፍል ውሳኔ የሰጠው በሕግ የተመለከቱትን ሁኔታዎች መሰረት በማድረግ ነው ወይስ አይደለም ?
የሚውን ጭብጥ በመያዝ ጉዳዩን መርምረናል።
ጉዳዩን እንደመረመርነው አመልካች ከተጠሪ ጋር በጋብቻ ተሣስሮ በነበረበት ወቅት ለወለዳት ህፃን ሁዳ አደም ለማሣደግ የሚያስፈልገውን ወጪ የመጋራትና የመሸፈን ግድታ ያለበት መሆኑ አላከራከረም አመልካችንና ተጠሪ የሚያከራክረው አመልካች ለህፃኗ አስተዳደግ ላከፍለው የሚገባው የገንዘብ መጠን ነው። ለህፃን ልጅ ማሳደጊያ ቀለብ የመስጠት ግድታ ያለበት ወላጅ፣ የሚከፍለው የገንዘብ መጠን የሚወስነው እንደባለ ጉዳዩ ሁኔታና እንደ አካባቢው ልምድ የሚስማማውን በመከተል በቀለብ ተቀባዩ ምግብ፣ መኖሪያ፣ ልብስ፣ ጤናውን የሚጠብቅበትና እንደ ሁኔታው ለትምህርት አስፈላጊ የሆኑትን ወጭዎች የሚሸፍን መሆን እንደሚገባው በተሻሻለው የፍድራል የቤተሰብ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 197 አንቀጽ 2 ይደነግጋል። ከዚህ አንፃር ሲታይ አመልካች በኢትዮጵያ ውስጥ በተቋቋመውና የአክሲዮን ባለድርሻ ከሆኑበት የንግድ ድርጅት በሚላዮን የሚቆጠር ገቢ በዓመት የሚያገኙ መሆኑን ፍሬ ጉዳይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ባላቸው ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል።
ይህም በመሆኑ ህፃኗን ለማሳደግ የሚያስፈልግ፣ የምግብ፣ የመኖሪያ፣ የጤና አጠባበቅና የትምህርት ወጭ ሲታሰብ፣ አንድ ከፍተኛ ገቢ የሚያገኝ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ቤተሰብ፣ ህፃን ልጁን በጥሩ ሁኔታ ለመመገብ፤ በጥሩ መኖሪያ አካባቢ ለማኖርና ጤናው ለመጠበቅ እንዲሁም ጥሩ ትምህርት እንዲያገኝ ለማድረግ የሚያስፈልገውን ወጭ መሰረት በማድረግ ላወሰን ይገባዋል። ይህም ማለት አመልካች ለህፃኗ ማሳደጊያ የሚከፍለው ገንዘብ ገቢያቸው ስለማይፈቅድላቸው በህፃን አስተዳዳር አስፈላጊ የሆኑ የምግብ አይነቶች ንጥረ ነገሮች በተሟላ ሁኔታ ሣያቀርቡ፣ ህፃን ልጆቻቸው በየወቅቱ የጤና ክትትልና ምርመራ ሣያደርጉ ምቹና ፅዳት በጐደለው የመኖሪያ ቤት ውስጥ ህፃን ልጃቸው ለማኖርና ለማሣደግ ሁኔታው ያስገደዳቸዉን ወላጆች ለህፃን ልጆቻቸው የሚያወጡትን ዝቅተኛ ገንዘብ መሰረት በማድረግ ላወሰን አይገባውም ከዚህ አንፃር ሲታይ አመልካች ህፃኗን ለማሣደግ ከብር 2000 በላይ አስፈላጊ አይደለም በማለት ያቀረበውን ክርክር አልተቀበልነውም።
የአመልካች ከፍተኛ ገቢ ያለው መሆኑ ፍሬ ጉዳይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ባላቸው ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል። አመልካች ገቢውን በተመለከተ በዚህ ሰበር ችሎት ያቀረበው ክርክር በሕገ መንግስቱን አንቀጽ 80 ንዑስ አንቀጽ 3(ሀ) እና የአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 20 ለዚህ ችሎት የተሰጠውን ሥልጣን ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባ ባለመሆኑ አልተቀበልነውም። በልላ በኩል የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወሰነውን የቀለብ ገንዘብ ህፃኗን መዋለ ህፃናት ለማስገባትና ለማማላለስ ህፃኗን ለጤና ምቹ የሆነ መኖሪያ ቤት ውሰጥ ለማኖር ሕፃኗ የተሟላ ምግብ ፣ አልባሳትና መጫወቻ እንዲኖራት ለማድረግ ከሚያስፈልገው መጠን በላይ ስለመሆኑ አመልካች የማስረዳት ግድታውን አልተወጣም። አመልካች በኢትዮጵያ ሁኔታ አንድ ህፃን ለማሳደግ ከብር 2000 በላይ አስፈላጊ እንደልሆነ በጥቅል አገላለፅ ተከራክሯል። ይህም አመልካቹ የህፃኗ አስተዳደግ ስስታዊ ሣይሆን ዝቅተኛ ገቢ ስላላቸው የልጆቻቸውን መሰረታዊ ፍላጉት የማያሟሉና የልጆችቻውን ፍላጐት ገድበው የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ቤተሰቦች ልጆቻቸውን በሚያሳድጉበት መንገድ እንዲሆንለት የሚያከራከር መሆኑን የሚያሳይ ነው። ይህ የአመልካች መከራከሪያ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 197 እና አንቀጽ 202 ድንጋጌዎችን መሰረት ያላደረገ በመሆኑ አልተበቀልውም። በዚህ ምክንያት የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለአመልካች ለህፃኗ አስተዳደግ እንዲከፍል የወሰነው የቀለብ ገንዘብ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የልለበት ነው በማለት ወስነናል።
የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻሉ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.