No summary available.
ግንቦት 18/2006 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ አደነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- አቶ ሸኩር ጀማል - ጠበቃ አቶ ሳሙኤል ደመቀ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሪት ኤደን ነጋሽ ጠበቃ አቶ ተስፋዬ ወረደ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዳዩ በስርቆት ወንጀል ለተወሰደ ንብረት ግምት የቀረበን የአንድነት ኃላፊነት የሚመለከት ነው። በሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
የክርክሩ መነሻ ተጠሪ ያቀረባቸው ክስ ነው። ተጠሪ አመልካችና ቢኒያም ታደስ ግምቱ ብር 65,000 (ስልሳ አምስት ሺ ብር) የሚሆን ንብረት ሰርቀው የወሰዱ መሆኑ በፍድራል የመጀመረያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ነሐሴ 7 ቀን 2005 ዓ/ም በወንጀል ጥፋተኛ መሆናቸውን አርጋግጦ ውሳኔ ስጥቷል። አመልካች ለሱቅ የምከፍለው ኪራይና ዕቃዎች በመስረቃቸው የደረስብኝ ኪሳራ ብር 20,000 (ሃያ ሺ በር) ጨምርው እንዲከፍሉ ይወስንልኝ በማለት ክስ ያቀረበች ሲሆን በቢኒያም ታደስ ላይ ያቀረበችው ክስ እንዲቋረጥ አመልክታ ክሱ ተቋርጧል። አመልካች ንብረቶች ባለሀብት ከሳሽ መሆኗና የንብረቶቹ ግምት በማስረጃ አልተረጋገጠም በማለት ተከርክሯል። የስር ፍርድ ቤት አመልካች በስርቆት ወንጀል ለተወሰዱት የተጠሪ ንብረቶችና በዚህ ምክንያት ለደረሰው ኪሳራ አመልካች የአንድነትና የነጠላ ኃላፊነት አለበት በማለት ብር 85,000 (ሰማኒያ አምስት ሺ ብር) እንዲከፍል ውሳኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርቧል። ይግባኝ ሰሚው ችሎት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ አፅንቶታል።
አመልካች መሰከረም 30 ቀን 2006 ዓ/ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ተሰረቁ የተባሉት ንብረቶች የተገዙበት ደረሰኝ አልቀረበም። በክርክሩ የግድታ ተካፋይ መሆን የሚገባው ወገን ተጠሪ ክሱ እንዲቋረጥ ጠይቃ እንዲቋረጥ አድርጋለች። ስለዚህ ተጠሪ የዕቃውን ዋጋና የደረሰባትን ኪሳራ ሳታስረዳና በክስ የጠየቀችውን ገንዘብ በሙሉ አመልካች የመክፍል ኃላፊነት አለበት መባሉ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ታረምልኝ በማለት አመልክታለች። ተጠሪ ከአመልካች ጋር የወንጀል ተካፋይ የነበረው ሰው አድራሻ አፈላልጌ ላገኘው አልቻልኩም። ዕቃው ተጭኖ የተወሰደው ከአመልካች ቤት መሆኑ ተረጋግጧል። አመልካች በስርቆት ለተወስደው ንብረት ግምት የአንድነትና በነጣላ ኃላፊነት ያለበት ስለሆነ ውሳኔው ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥታለች። አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በስበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም አመልካች ተጠሪ ክስ ያቀርበችበትን ገንዘብ የመክፈል ኃላፊነት አለበት ተብሎ የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዳዩን መርምረናል።
ጉዳዩን እንደመርመርነው አመልካችና የፍትብሕር ክስ በከሳሽ ጠያቂነት የተቋረጠበት ቢኒያም ታደሰ በወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1)ሀ እና አንቀጽ 665 የተመለከተውን በመተላለፍ፣ ግምታቸው ብር 65,000 (ስልሳ አምስት ሺ ብር) የሚሆኑ ንብረቶች ሰርቀው የወሰዱ መሆናቸውን በማረጋገጥ፣ የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ነሐሴ 7 ቀን 2005 ዓ/ም የጥፋተኝነት ውሳኔ የሰጠ መሆኑን ከስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ተገንዝብናል። ይህ ከሆነ አመልካች የንብረቶቹ ዋጋ ብር 65,000 (ስልሳ አምስት ሺ ብር) መሆኑ አልተረጋገጠም በማለት የሚያቀርበው ክርክር የፍትብሕር ህግ ቁጥር 2035 እና የፍትብሕር ህግ ቁጥር 2091 ድንጋጌን መሰረት ያላደረገ በመሆኑ አልተቀበልነውም።
አመልካችና የወንጀል ስራ ተካፋይ የነበረው ቢኒያም የስርቁት ተጠሪ የንግድ ስራ የምታከናውንባቸውን ዕቃዎች እንደሆነ ተረጋግጧል። ተጠሪ ዕቃዎቹ በመሰረቃቸውና የንግድ ስራውን በአግባቡ ለማከናወን ባለመቻሐ ብር 20,000 (ሃያ ሺ ብር) ኪሳራ የደረሰባት መሆኗን ገልጻለች። ተጠሪ ይህንን ያህል ኪሳራ የደርሰባት ስለመሆኑ የማሰረዳት ግድታ እንዳለበት በፍትብሕር ህግ ቁጥር 2141 የማስረዳት ግድታ ያለባት ቢሆንም፣ ይህንን ለማስረዳት በስር ፍርድ ቤት ያቀረበችው ማስረጃ ስለመኖሩ በውሳኔው አልገለፀም። የስር ፍርድ ቤት አመልካች ለተጠሪ ብር 20,000 (ሃያ ሺ በር) የጉዳት ካሳ እንዲከፍል የወሰነው አመልካች ክሱን በግልጽ ክዶ መልስ አልሰጠም በሚል ምክንያት መሆኑን ከስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ተገንዝበናል። ሆኖም የካሳን ልክ በተመለከተ፣ ከሳሽ የጠየቀውን የካሳ ገንዘብ ተካሳሽ በግልጽ አለመካዱ የካሳውን መጠን በሙሉ ወይም በከፊል እንዳመነ እንደማያስቆጥረው በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.83 ተደንግጓል።
ከዚህ አንጻር ስናየው ተጠሪ በፍትብሕር ህግ ቁጥር 2141 መሰረት በማስረጃ ያላረጋገጠችውን የጉዳት ካሳ ብር 20,000 (ሃያ ሺ ብር) አመልካች ክዶ አልተከራከርም በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ.83 ድንጋጌ ይዘት ያላገናዘበና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ተሻሽሐል።
የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች የተሰረቁትን የተጠሪ ንብረቶች ዋጋ ብር 65,000 (ስልሳ አምስት ሺ ብር) የመክፈል ኃላፊነት አለበት በማለት የሰጠው ውሳኔ ክፍል ፀንቷል።
የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ተጠሪ የጠየቀችውን ብር 20,000 (ሃያ ሺ ብር) ካሳ ይክፈል በማለት የሰጡት የውሳኔ ክፍል የፍትብሕር ህግ ቁጥር 2141 እና የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.83 ድንጋጌዎች የሚጥስ በመሆኑ ተሸሯል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ ለያራሳቸው ይቻሉ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.