No summary available.
ሚያዚያ 2 ቀን 2006 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር - ነ/ፈጅ ግርማ ሞገስ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ደስታ ጁላ ቤካሎ - ጠበቃ አንዱዓለም በእውቀቱ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ ያላግባብ ለውጭ አገር ጉዞ የተከፈለ የመጓጓዣ ወጪና አበል ይመለስልኝ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች ባሁኑ ተጠሪ ላይ በፍድራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረተው ክስ መነሻ ነው።የአመልካች የክስ ይዘትም፡-ተጠሪ በአመልካች መስሪያ ቤት የአንድ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ኃላፊ በመሆናቸው ለስራቸው ጠቃሚ የስራ ልምድ ገብይተው እንዲመለሱ አመልካች ከፍተኛ ወጪ አውጥቶ ወደ አውስትራላያ አገር ልኳቸው የተላኩበትን ትምህርት አጠናቅቀው ሃላፊነታቸውን መወጣት ሲገባቸው ከተላኩበት አገር ሳይመለሱ መቅረታቸውን ገልፆ ለአበል፣ለስልጠናና ለአውሮፕላን መጓጓዣ የተከፈላቸውን ብር 180,574.94 (አንድ መቶ ሰማንያ ሺህ አምስት መቶ ሰባ አራት ብር ከዘጠና አራት ሳንቲም) ከእነ ወለዱ እንዲመልሱ ይወሰንለት ዘንድ ዳኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው።የአሁኑ ተጠሪ በጠበቃቸው አማካኝነት ለክሱ በሰጡት መልስ ወደ ውጪ አገር የተላኩት ለስራ ጉብኝት እንጂ ለትምህርት አለመሆኑ ጠቅሰው ለክሱ መሰረት የሆነውን ገንዘብ ለመመለስ ከሕግም ሆነ ከውል የመነጨ ግድታ የለብኝም ሲሉ ተከራክረዋል።
የስር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ጉዳዩን መርምሮ አመልካች ተጠሪ ገንዘቡን እንዲመልሱ እየጠየቀ ያለው ያላግባብ ስለመበልጸግ የተጠቀሱትን ድንጌዎችን መሰረት በማድረግ ስለመሆኑ በቃል ክርክር ጊዜ ግልጽ ያደረገ ቢሆንም ተጠሪ ያላግባብ ተገልግሐል በማለት አመልካች ከመግለጽ ውጪ ያገኘው ጥቅም ስለመኖሩ አላስረዳም በሚል ምክንያት የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2162 ድንጋጌን በዋቢነት ጠቅሶ የአመልካችን ክስ በከፊል ውድቅ አድርጎታል።እንዲሁም የተጠሪ ጠበቃ ተጠሪ በአገር ውስጥ እያለ ለአበል ወስደው ያላወራረዱት ብር 832.00 (ስምንት መቶ ሰላሳ ሁለት ብር) መኖሩን ያመኑ በመሆኑ ይህንኑ ገንዘብ ከሕጋዊ ወለድ ጋር ለአመልካች ላመልሱ ይገባል በማለት ወስኗል።አመልካች በዚህ ውሳኔ በከፊል ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበ ቢሆንም ተቀባይነት ያላገኘ ሲሆን የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- ተጠሪ በአመልካች መስሪያ ቤት ውስጥ የፍድራል የተቀናጀ የከተማ መሬት መረጃ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከፍተኛ ኃላፊ ሆነው ሲሰሩ ለስራው ጠቃሚ የሆነ ትምህርታዊ እውቀት ገብይተው እንደሚመለሱ ወደ አውስትራላያ አገር ሲላኩ ለአበል ለስልጠናና ለአውሮፕላን መጓጓዣ አመልካች ብር 180,574.94 ከፍሎላቸው ከሄዱና ስልጠናውን ከወሰዱ በኋላ ወደ አገራቸው ተመልሰው በቀሰሙት ሙያ ለአገራቸው አገልግሎት መስጠትና ኃላፊነታቸውን መወጣት ሲገባቸው በዚያው ሳይመለሱ መቅረታቸው ተረጋግጦ እያለ ጥቅም ስለማግኘታቸው አልተረጋገጠም ተብሎ ክሱ ውድቅ መደረጉ ያላግባብ ነው የሚል ነው።አቤቱታው ተመርምሮ በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት እንዲታይ በመደረጉ ለተጠሪ ጥሪ ተደረጎላቸው ቀርበው ግራ ቀኙ በፅሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዳዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።እንደመረመረውም የዚህን ችሎት ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ነጥብ አመልካች ተጠሪው ለመንግስት ስራ እንዲረዳቸው ከውጪ አገር ልምድ ቀስመው እንዲመጡ ወጪ አውጥቶ ከላካቸው በኋላ ወደ አገራቸው ሳይመለሱ መቅረታቸው በተረጋገጠበት ሁኔታ ተጠሪ ያገኙት ጥቅም ስለመኖሩ አልተረጋገጠም ተብሎ የአመልካች የዳኝነት ጥያቄ ውድቅ መደረጉ ተገቢ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሁኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች በተጠሪ ላይ ክስ የመሰረተው ተጠሪ ለመንግስት የስራ ጉዳይ ወደ ውጪ አገር ሂደው በዚያው ስለቀሩ ለጉዞና ለስልጠና የወጣ ወጪ ላመለስልኝ ይገባል በሚል ሲሆን ተጠሪ በአመልካች የስራ ምክንያትና ወጪ ወደ ውጪ አገር መሄዳቸውን ሳይክዱለክሱ ኃላፊነት የለብኝም በማለት የሚከራከሩት የተገኘ ጥቅም የለም፣ወደ ውጪ አገር የሄዱበትን ስራ ሰርተው ተገቢውን ሪፖርት አጠናቅረው ለአመልካች መስሪያ ቤት አስረክበዋል በሚሉ ምክንያቶች መሆኑን ነው።
No topics extracted.
በመሰረቱአንድ ሰው የልላውን ሰው የሥራ ድካም ወይም በልላው ሰው ሀብት በመገልገል በቂ ባልሆነ ምክንያት ጥቅም ያገኘ እንደሆነ አላግባብ ባገኘው ጥቅም መጠን ለባለሀብቱ ወይም በጉልበቱ የደከመው ሰው የመመለስና የመካስ ግድታ ያለበት መሆኑ በፍታብሕር ህግ ቁጥር 2162 በመሰረታዊ መርህነት ተደንግጓል።የዚህ ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ ሲታይ የሚከፈለው የካሳ መጠን የሚወሰነው ተከሳሹ ያገኘው ጥቅምና ከሳሹ የደረሰበት ኪሳራ ተመዛዝነው በመታየት ስለመሆኑ ያስገነዝባል። በመሆኑም ለከሳሹ የሚወሰንለት ካሳ ተከሳሹ ካገኘው ጥቅምም ሆነ ከሳሹ ከደረሰበት ኪሳራ ላበልጥ እንደማይገባ ሕጉ ያሳያል።ሕጉ ተከሳሹ የሚያገኘው ጥቅም በንብረት ላይ የተቋቋመ ግዙፍ መብት ወይም ከአንድ ሰው ላይ የሚጠየቅ መብት ላሆን እንደሚችል፣እንዲሁም ተከሳሹ የነበረበት እዳ ተሰርዞለት ወይም ግድታው ቀርቶለት ወይም ኪሳራ ሳይደርስበት ቀርቶ ላሆን እንደሚችል ያስረዳል።ስለሆነም በተከሳሹ በኩል የተገኘው ጥቅም መኖር ብቻ ሳይሆን የተገኘው ጥቅም የሕላና እርካታን የሚያስገኝና በገንዘብ ላተመን የሚችል መሆን አለበት።
ወደ ተያዘው ጉዳይ ስንመለስም ተጠሪ በአመልካች መስሪያ ቤት በነበራቸው ኃላፊነት አበልና የአውሮፕላን ትራንስፖርት የስልጠና ወጪ ተከፍሎላቸው ወደ ውጪ አገር መሄዳቸውና በስራ ምክንያት ሂደው ሳይመለሱ መቅረታቸው ግራ ቀኙን ያላከራከሩ ፍሬ ነገሮች ሲሆኑ ተጠሪ የአመልካችን ክስ ተቀባይነት የለውም በማለት የሚከራከሩትና የስር ፍርድ ቤት የአመልካችን ክስ ውድቅ ያደረገው ተጠሪ ጥቅም ማግኘታቸው አልተረጋገጠም በሚል ነው።ይሁን እንጂ ወደ ውጪ አገር ለመሄድ ለትራንስፖትም ሆነ ለተለየዩ ጉዳዮች የገንዘብ ወጪ የሚያስፈልግ መሆኑ ግልጽ ሲሆን ተጠሪ ወደ ውጪ አገር ሲሄዱ አመልካች ገንዘብ ማውጣቱ ተረጋግጧል።ከዚህ መገንዘብ የሚቻለው ተጠሪ በአመልካች መስሪያ ቤት ሰራተኛ ባይሆኑና ለስራ ምክንያት ወደ ውጪ አገር የማይሄዱ ቢሆኑ ኑሮ ለአውሮፕላን ትራንስፖርትና ተያያዥ ወጪዎችን መሸፈን የሚገባቸው ተጠሪ ራሳቸው መሆኑን ነው።እንዲህ ከሆነ ተጠሪ ጥቅም አላገኙም ለማለት የሚቻልበት አግባብ የለም።ምክንያቱም በአመልካች መስሪያ ቤት በነበራቸው የስራ ግንኙነት ወደ ውጪ የተላኩት አስፈላጊውን ልምድ ቀስመው አመልካችን ያገለግላሉ በሚል ሀሳብ ሲሆን ይኼው የአመልካች ሃሳብ ተጠሪ ከሄዱበት ባለመመለሳቸው ውጤት ሳይገኝ መቅረቱን የክርክሩ ሂደትና ይዘት ያሳያልና።አመልካች ኪሳራ የደረሰበት፣ተጠሪ ደግሞ በአመልካች መስሪያ ቤት የተመቻቸላቸውን አጋጣሚ በመጠቀም በአመልካች ወጪ ወደ ውጪ አገር ሄደው የቀሩ በመሆኑ ለአውሮፕላን ትራንስፖርትና ለስልጠና በተከፈለው ገንዘብ መጠን ጥቅም አላገኙም ላባል የሚችልበት የሕግ ምክንያት የለም።ስለሆነም የበታች ፍርድ ቤቶች ተጠሪ ከአመልካች ጋር የነበራቸውን የስራ ግንኙነት፣ወደ ውጪ ላሄዱ የቻሉበትን ምክንያትና አንድ ሰው ወደ ውጪ ሲሄድ ደግም የግድ ወጪ የሚያስፈልገው መሆኑንና ተጠሪ በራሳቸው ወደ ውጪ ቢሄዱ ኑሮ የራሳቸውን ገንዘብ ላከፍሉ ይችሉ የነበረ መሆኑን፣አመልካች ተጠሪ ከተላኩበት ተመልሰው ላያገለግሉ ይችላሉ በሚል ሙሉ እምነት ወጪውን አውጥቶ ልኳቸው ተጠሪ ያለመመለሳቸውተጠሪ በአመልካች መስሪያ ቤት ገንዘብ በመገልገል ጥቅም ማግኘታቸውን የሚያረጋግጥ እና ይህም ጥቅም በገንዘብ ላተመን የሚችል ሁኖ እያለ አመልካች ተጠሪ ጥቅም ማግኘቱን አላስረዳም በማለት የሰጡት ውሳኔ የክርክሩን ይዘትና ባህርይ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2162 ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ ጋር ያላገናዘበ ሁኖ ተገኝቷል።ከላይ በዝርዝር በገለፅናቸው ምክንያቶች የበታች ፍርድ ቤቶች በጉዳዩ ላይ የሰጡት ውሣኔ የክርክሩን ይዘት፣ የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 2162 እና የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 2164 /1/ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ መሰረት ያላደረገ ስለሆነ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የአውሮፕላንና የስልጠና ወጪን አስመልክቶ በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ሚያዚያ 08 ቀን 2005 ዓ/ም ተሰጥቶ በፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ሐምል 23 ቀን 2005 ዓ/ም የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
ተጠሪ ለአመልካች ብር 179,742.94 (አንድ መቶ ሰባ ዘጠኝ ሺህ ሰባት መቶ አርባ ሁለት ብር ከዘጠና አራት ሳንቲም) ከዛሬ ሚያዚያ 20 ቀን 2006 ዓ/ም ጀምሮ ተከፍሎ እስከሚጠናቀቅ ጊዜ ድረስ ከሚታሰብ ሕጋዊ ወለድ 9%(ዘጠኝ ከመቶ) ላከፍሉ ይገባል በማለት ወስነናል።
ለአበል ወሰዱ በተባለው ብር 832.00 የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ጸንቷል።
በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻሉ።