No summary available.
ሚያዚያ 09 ቀን 2006 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- አቶ ጥምቀቱ ጋመነ - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- ወ/ት ታገሰች ዮሐንስ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ ከውል ውጪ ኃላፊነትን መሰረት ያደረገን የጉዳት ካሳ ይከፈለኝ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ በአሁኑ አመልካችና በአቶ ቢኒያም አሚቲ ላይ በፍድራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው።የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡ተጠሪ በገንዘብ ያዥነት ሥራ ተቀጥረው የተጣራ ብር 1717.054 በወር እየተከፈላቸው እንደሚሰሩ፣ነሐሴ 15 ቀን 2003 ዓ/ም አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሰልዳ ቁጥሩ 1-16423 አ.አ የሆነውና ንብረትነቱ የአሁኑ አመልካች የሆነ ሚኒባስ በአቶ ቢኒያም አሚቲ ይሽከረከር እንደነበርና ያለበቂ ጥንቃቄ እየተሽከረከረ ለእግረኛ ቅድሚያ መስጠት ሲገባው ይህንን ባለማድረግ በወቅቱ የዜብራ መንገድ ከቀኝ ወደ ግራ መንገዱን በማቋረጥ ላይ የነበሩትን ተጠሪን በመኪናው የፊት ለፊት አካል ገጭቶ በመጣል የግራ እጅ የላይኛው ክንድ አጥንት እንዲሰበር፣የቀኝ ትከሻ እንቅስቃሴ እንዲገደብ፣ሶስት ጥርሶች እንዲወልቁ የግራ እግር ቅልጥማቸው እንዲሰነጠቅ በማድረግ በአጠቃላይ የ30% ቋሚ የአካል ጉዳት እንዲደርስ ምክንያት መሆኑን፣ጉዳቱ ሲደርስ እድሜአቸው 28 አመት ሁኖ ወደፊት ተጨማሪ 40 አመታት ለመኖር እንደሚችሉ ገልፀው በወር እየሰሩ እስከ አርባ አመታት ላያገኙ ይችሉ የነበረውን ገንዘብ አስልተውና የሞራልና የህክምና ወጪ እንዲሁም ልሎች ተያያዥ ወጪዎችን ደምረው በጠቅላላው ብር 269,344.50(ሁለት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሺህ ሶስት መቶ አርባ አራት ብር ከሃምሳ ሳንቲም) ከወጪና ኪሳራ ጋር በአንድነትና በነጠላ እንዲከፍሐቸው ይወሰን ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጡት መከላከያ መልስም በተጠሪ ላይ የደረሰው ጉዳት ወደፊት ሰርተው ለመኖር የማይከለክላቸው እንዲሁም ደመወዛቸው ተብሎ የቀረበውም በማስረጃ ያልተረጋገጠ መሆኑን ዘርዝረው ተከራክረዋል።
ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር በመስማት ጉዳዩን መርምሮ አመልካችን ለጉዳቱ ኃላፊ በማድረግ የኃላፊነት መጠኑን ደግሞ ተጠሪ በወር ብር 1717.50 እንደሚያገኙ መረጋገጡን፣ተጠሪ የደረሰባቸው የአካል ጉዳትም 30% መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ አስገብቶ ለወደፊትም አርባ አመት ላኖሩ እንደሚችሉ ግምት ውስጥ በማስገባት ተጠሪ በወር ያገኙ የነበሩትን የተጣራ ገቢ በብር 1717.50(አንድ ሺህ ሰባት መቶ አስራ ሰባት ብር ከሃምሳ ሳንቲም) በአርባ አመት ሲሰላ ብር 247,320.00 (ሁለት መቶ አርባ ሰባት ሺህ ሶስት መቶ ሃያ ብር) እንደሚመጣ፣ከዚህም በተጨማሪ በጉዳቱ ምክንያት ለህክምና የወጣው ወጪ መጠኑ ብር 13,024.00፣የሞራል ካሳ ብር 1000.00፣የትራንስፖርት ወጪ ብር 1000.00 መሆኑን ገልፆ በድምሩ ብር 261,544.00(ሁለት መቶ ስልሳ አንድ ሺህ አምስት መቶ አርባ አራት ብር) አመልካች ለተጠሪ ላከፍሉ ይገባል በማለት ወስኗል።በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ፍርድ ቤቱ የተጠሪ የተጣራ ወርሃዊ ደመወዝ ብር 1617.50 መሆኑ መረጋገጡን በምክንያትነት ይዞ የአካል ጉዳት መጠኑን በማሻሻል ብር 232,848.00 (ሁለት መቶ ሰላሳ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ አርባ ስምንት ብር) እንዲሆን አድርጎ ልሎች ክፍያዎችን ግን ተቀብሎ የሥር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ተቀብሎ ዳኝነት ሰጥቷል።የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘቱም ባጭሩ፡-ተጠሪ በጉዳቱ ምክንያት የተቋረጠባቸው ገቢ ሳይኖር የጉዳት ካሳ ይገባቸዋል ተብሎ መወሰኑም ሆነ የጉዳት ካሳ ስልቱ እንዲሁም ካሳው በቀለብ መልክ እንዲከፈል መደረግ ሲገባው በአንድ ጊዜ እንዲከፈላቸው መወሰኑ አግባብነት የልለው መሆኑን በመዘርዘር መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው።አቤቱታቸው ተመርምሮም ይህ ችሎት እንዲመለከተው የተያዘው ጭብጥ፡-በተጠሪ ላይ ደርሷል ከተባለ የ30% የአካል ጉዳት አኳያ በስር ፍርድ ቤቶች የተወሰነው የካሳ መጠን አግባብነት ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2090 እና 2091 አንፃር ለመመርመር ሲባል ነው።በዚህም መሰረት ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው ግራ ቀኙ በፅሑፍ ተከራክረዋል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዳዩ ለሰበር ችሎት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር ብቻ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።ጉዳዩ ለሰበር ችሎት ሲቀርብ የተያዘው ጭብጥ አመልካች ለጉዳቱ ኃላፊ ተብለው መወሰኑ ላይ ሳይሆን የካሳ ስልቱን በተመለከተ ስለመሆኑ ተገንዝበናል።
ከክርክሩ ሂደት የተገነዘብነው ተጠሪ ስራቸው ገንዘብ ያዥ ሲሆኑ ከጉዳቱ በሁዋላ ለዚህ ስራ ብቁ አይደሉም ባይባልም 30% ቋሚ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከሕክምና ቦርድ መቅረቡንና በዚህ ስራ ሲያገኙ የነበረው ያልተቋረጠ ስለመሆኑ ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ባላቸው የስር ፍርድ ቤቶች የተረጋገጡ ነጥቦች መሆኑን ነው።የስር ፍርድ ቤቶች በጉዳቱ ምክንያት ወደፊት ተጠሪ የሚቀርባቸውን ገቢና ከጉዳቱ ጋር ተያይዘው የወጡትን ወጪዎች በመለየት የካሣ መጠኑንም መወሰናቸውን ከውሳኔው ይዘት ተገንዝበናል።
በመሰረቱ ካሳ የሚከፈለው ጉዳት መኖሩ ሲረጋገጥ ሲሆን የካሳ አተማመን ፣መጠንና አከፋፈልን በተመለከተ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2090፣2091፣2092፣2095 እና በልሎች ድንጋጌዎች የተቀመጠ ሲሆን ከእነዚህ ድንጋጌዎች መገንዘብ የሚቻለውም ካሳው በተቻለ መጠን ከጉዳቱ ጋር መመጣጠን ያለበት መሆኑን ነው።የበታች ፍርድ ቤቶች በሚሰጡት የካሳ መጠን ላይ ይግባኝ የልለው መሆኑ በመርህ ደረጃ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2152 ስር የተመለከተ ሲሆን ይግባኙ በልዩ ሁኔታ የሚፈቀድባቸው ሁኔታዎች ደግሞ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2153 ስር ተገልጿል።
በተያዘው ጉዳይ በአመልካች በኩል የቀረበውን ቅሬታና በሰበር ችሎቱ የሕግ ትርጉም ያስፈልገዋል ተብሎ በጭብጥነት የተያዘውን ነጥብ መሰረት ስናደርግ በካሳ አተማመኑ ላይ በሕጉ የተመለከቱት ሁኔታዎች ግንዛቤ ውስጥ ሳይገቡ በበታች ፍርድ ቤቶች በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ስለመሰጠቱ የሚያሳይ ነገር ያለ ሁኖ አልተገኘም።
ተጠሪ አካላቸው በሕገ መንግስቱም ጥበቃ የተደረገላቸው ሲሆን ካሳው ሲወሰንም ይህንኑና ጉዳቱ በአመልካች የወደፊት ኑሮ ላይ ላያስከትለው የሚችለው አጠቃላይ ችግር ግምት ውስጥ በማስገባት ላወሰን የሚችል እንጂ ተጠሪ 30%(ሰላሳ ከመቶ) ጉዳት ቢደርስባቸውም ይሰሩ የነበሩትን ስራ ላለመስራት ወይም ልላ ስራ ላለመስራት እንቅፋት አይሆንባቸውም፣እንዲያውም ስራውን በመስራት ላይ የሚገኙ በመሆኑ የተቋረጠባቸው ገቢ የለም በሚል ምክንያት ብቻ ካሳው ላቀነስ ይገባል፣ወይም ጭራሹን አይገባቸውም ላባል የሚችል አይደለም።
ከውል ውጪ ኃላፊነትን በተመለከተ የሚገዙት የፍትሐብሕር ሕጋችን ድንጋጌዎች መንፈስ የጉዳትን ጠቅላላ ባህርይና የካሣ ልክ አተማመን ሁኔታዎችን ያስገነዝቡናል። በዚህም መሰረት ጉዳት በሰው ጥቅም ላይ ችግር የሚያደርስ መሆኑን፣ ይህም ጥቅም ማቲሪያላዊ /በሰው አካል ወይም ንብረት የደረሰ/ ወይም ሞራላዊ ላሆን እንደሚችል መገንዘብ ይቻላል። የተጎዳ ሰው ደግሞ መካስ እንዳለበት ያስረዳሉ። የካሣውን አተማመን በተመለከተም መጠኑ በተበዳዩ ላይ ከደረሰው ጉዳት ጋር እኩል ሁኖ መመዘን ያለበት መሆኑን የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2091 ድንጋጌ ያሣያል።የጉዳት ካሣ ከደረሰው ጉዳት ጋር እኩል ሆኖ ሲመዘንም በተጎጂው ላይ በእርግጠኝነት መድረሱ የታወቀ /actual damage/ ወይም ወደፊት ላደርስ የሚችል ጉዳትን/future damage/ ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት የግድ የሚል መሆኑን የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2091/1/ እና 2092 ድንጋጌዎች መንፈስ ያስረዳል። በእነዚህድንጋጌዎች የጉዳት ካሣ ላተመን የሚገባ መሆኑን ሕጉ በግልጽ ከማስቀመጡም በተጨማሪ የአተማመኑ ሥርዓትም እንደጉዳቱ ዓይነትና ማስረጃ አቀራረብ ውስብስብነት ላለያይ የሚችል መሆኑን የሕጉ መንፈስ ያስገነዝባል። በዚህም መሰረት የጉዳት ካሣ መጠን አጥጋቢና በቂ ማስረጃን ወይም ርትዕን መሰረት በማድረግ ላወሰን የሚገባው መሆኑን የካሣ አከፋፈሉን ልክ በሚደነግገው የሕጉ ክፍል የተቀመጡ ድንጋጌዎች ያስገነዝባሉ በልላ በኩል የካሣ አተማመን ሥርዓት ጠቅላላ የመስራት አቅም /General utility/ ሣይሆን ልዩ ጠቀሜታ/specific utility/ መርህን ቢከተል ፍትሐዊነት ያለው አሰራር መሆኑ ይታመናል።ይህም አሰራር በተጨባጭ የደረሰው ጉዳት ምን ያህል እንደሆነማወቅአስቸጋሪ በሚሆንበት ጊዜ የካሣውን ልክ ያላግባብ ከማጋነንና ከመቀነስ የራሱ የሆነ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሎ ይታሰባል።በመሆኑም ጉዳት መድረሱ በማስረጃ ከተረጋገጠና ጉዳቱም በተጎጂው የወደፊት ሕይወት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ማሣደሩ እንደማይቀር ምክንያታዊ እርግጠኝነት ያለመሆኑ ከተረጋገጠ ካሣ መወሰን ከአጠቃላይ የሕጉ ዓላማና ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2091 እና 2092 ድንጋጌዎች መንፈስ አኳያ አግባብነት ያለው ነው። መጠኑን በተመለከተ በሕጉ ዳኞች በተሰጠው ሥልጣን ወይም በጉዳዩ ላይ በቀረበው ማስረጃ መሰረት በመተመን ለተጎጂው መፍረድ የሚቻልበት ሁኔታ በሕጉ መኖሩን ከላይ የተጠቀሱት ድንጋጌዎችና የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2101 እና 2102 ድንጋጌዎች ያስገነዝባሉ። ከዚህ ውጪ ጉዳቱ መድረሱ እየታወቀ የአሁንና የወደፊት ቁሣዊ ጉዳት /material damage/ ስለመኖሩ ተጎጂው አላስረዳም ተብሎ የመካስ መብት ማጣት ከአጠቃላይ ከውል ውጪ ኃላፊነትን ከሚገዛው ሕግ አላማ ጋር አንድ ላይ የሚሄድ አይሆንም።
ወደያዝነው ጉዳይ ስንመለስም ተጠሪ ንብረትነቱ የአመልካች በሆነው መኪና በዜብራ መንገድ ላይ በማቋረጥ ላይ በነበሩበት ጊዜ የመኪናው አሽከርካሪ ማድረግ የሚገባውን ጥንቃቄ ባለማድረጉ በፈጸመው ድርጊት ምክንያት በመኪናው ተገጭተው በተለያዩ የሰውነት ክፍሎቻቸው ጉዳት መድረሱን፣በዚህ ጉዳትም በአካላቸው ላይ 30%(ሰላሳ ከመቶ) ጉዳት መድረሱ በሚገባ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው። ጉዳቱ ወደፊት ላጠፋ የሚችል ስለመሆኑም የተገለፀ ነገር የለም።በመሆኑም ተጠሪ በአመልካች ካሳ የማይከፍሉበት ምክንያት የለም።
ልላው አመልካች አጥብቀው የሚከራከሩት የካሳ መጠኑን በተመለከተ የተጠሪ ወርሃዊ ደመወዝ በተገቢው ማስረጃ ያልተረጋገጠ ነው በሚል ነው።ይሁን እንጂ ፍሬ ነገሩን የማጣራት ስልጣን ያላቸው ፍርድ ቤቶች ተጠሪ ተቀጥረው ሲሰሩ በወር ያገኙ የነበረውን የተጣራ የደመወዝ መጠን በማስረጃ ያረጋገጡት በመሆኑ በዚህ ረገድ የቀረበውን ቅሬታ የምንቀበለው ሁኖ አልተገኘም።
ሆኖም የስር ፍርድ ቤቶች ጉዳቱ በደረሰ ጊዜ የተጠሪ እድሜ 28 አመት መሆኑን በማስረጃ አረጋግጠው ከተቀበሉ በኋላ ተጠሪ ወደፊት ላኖሩ የሚችሉት አርባ አመት መሆኑን ግን በበቂ ምክንያትና ማስረጃ አስደግፈው የተቀበሉት መሆኑን ውሳኔው አያሳይም።አንድ ሰው ወደፊት የሚኖርበትን የእድሜ መጠን በመግለጹ ብቻ ይሄው በተጎጂው የተገለፀው የእድሜ መጠን ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት አግኝቶ የጉዳት ካሳ የሚሰላበት የሕግ መሰረት የለም። በመሆኑም ወደፊት ለመኖር የሚገለፀው እድሜ በአጠቃላይ የአገሪቱን በተለይ ደግሞ የአካባቢውንና ተጨባጭ ሁኔታና በዚህ ረገድ የሚመለከተው አካል ያስቀመጠው ጥናታዊ መነሻ ካለ ይህንኑ መሰረት ማድረግ ያለበት መሆኑ ይታመናል።
በተያዘው ጉዳይ ተጠሪ ወደ ፊት በሕይወት ልኖር እችላለሁ በማለት ያቀረቡት የእድሜ መጠን በአጠቃላይ የአገሪቱን ወይም በተለይ የሚኖሩበትን አካባቢ ተጨባጭ ሁኔታ መሰረት ያደረገ ወይም የሚመለከተው አካል ይፋ ያደረገውን ጥናት መሰረት ያደረገ መሆኑን የክርክሩ ሂደት አያሳይም።በመሆኑም ተጠሪ አርባ አመት ወደፊት ላኖሩ ይችላሉ ብሎ መያዝ የሕግ መሰረት የልለው ነው።ተጠሪ በዚህ ረገድ ያቀረቡት የእድሜ መጠን ተቀባይነት ላኖረው አይገባም ከተባለ ደግሞ ምክንያታዊ የሆነ እድሜ መያዝ ተገቢነት ይኖረዋል።ተጠሪ የግል ድርጅት ተቀጣሪ ሰራተኛ እንደመሆናቸው መጠን በስራው ላይ ላቆዩ የሚችሉት ስልሳ አመት መሆኑን ከአዋጅ ቁጥር 715/2003 አንቀጽ 17(1) ድንጋጌ ተገንዝበናል።በመሆኑም ተጠሪ ከዚህ አመት በላይ በቅጥር ላይ በተመሰረተ ግንኙነት ላያገኙ የሚችሉት ገቢ ላቋረጥ ወይም ላቀንስ ይችላል ብሎ ለመውሰድ የሚያስችል ሕጋዊ ምክንያት አላገኘንም።ከዚህ አንጻር ጉዳዩን ስንመለከተው የበታች ፍርድ ቤቶች የተጠሪን የወደፊት እድሜ አርባ አመት ነው በማለት ካሳውን ከዚህ ጊዜ አንጻር በመመልከት ማስላታቸው ላገምቱት የሚገባቸውን የነገሩን አጋጣሚ ሁኔታ ያላግባብ በመያዝ ወይም ትክክለኛውን መንገድ ትተው ያላግባብ የሆነውን ያገማመት መንገድ መያዛቸውን የሚያሳይ እና በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2253(ሀ) ድንጋጌ ስር የተመለከተውን ድንጋጌ የጣሰ ሁኖ አግኝተናል።በዚህ አይነት ሁኔታ በሚወሰነው የካሳ መጠን ደግሞ ይግባኝ ማቅረብ እንዲሁም በሰበር ማሳረም የሚቻል መሆኑን ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2152 እና 2153 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዳይ ነው።እንዲሁም አመልካች ተጠሪ ወደፊት የሚኖሩበትን እድሜ አስመልክቶ በግልጽ ክርክር አላቀረቡበትም ቢባል እንኳን ጉዳዩ የጉዳት ካሳ ክፍያ ይገባኛል የሚለውን ጥያቄ የሚመለከት እንደመሆኑ መጠን በፍርድ ቤቶቹ ጉዳዩ ከመታየት ሕጉ የማይከለክል መሆኑን ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 83 ድንጋጌ ይዘት የምንረዳው ነጥብ ነው። ስለሆነም በበታች ፍርድ ቤቶች የተሰላው የካሳ መጠን በውጤት ደረጃ ሲታይ ከላይ የተመለከቱትን የካሳ አተማመን መንገዶችን ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባና ጉልሕ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት የሚያስችል ሁኖ አግኝተነዋል።
ልላው አመልካች አጥብቀው የሚከራከሩት የጉዳት ካሳ አከፋፈሉ በቀለብ መልክ በየወሩ ላሆን ሲገባ በአንድ ጊዜ እንዲከፈል መደረጉ ያላግባብ ነው በሚል ነው።ይሁን እንጂ ለጉዳዩ ቀጥተኛ ተፈፃሚነት ያለው የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2154 ድንጋጌ ሲታይ የጉዳት ካሳ አከፋፈል በአንድ ጊዜ ላሆን የሚችል መሆን ያለመሆኑን በአቀራረፁና ይዘቱ ለፍርድ ቤቱ ፈቃድ የሰጠ ከመሆኑ አንፃር የካሣው አከፋፈል በጡረታ መልክ ላሆን ይገባል የሚለው የአመልካች ቅሬታ ተቀባይነት የልለው ሁኖ አግኝተናል።ክፍያው በአንድ ጊዜ ላሆን እንደሚችልና ለፍርድ ቤቱ የተተወ ስልጣን መሆኑንም ይህ ችሎት በመ/ እና በልሎች በርካታ መዛግብት በአዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀፅ 2(1) መሰረት በየትኛውም እርከን የሚገኝ ፍርድ ቤትን የሚያስገድድ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል።
ሲጠቃለልም ከላይ በተመለከቱት ምክንያቶች በጉዳዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ በካሳ ስልት ደረጃ ሲታይ በከፊል መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ ስለአገኘነው ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፍድራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ጥር 20 ቀን 2005 ዓ/ም ተሰጥቶ በፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ሐምል 08 ቀን 2005 ዓ/ም ተሻሽሎ የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1)መሰረት ተሻሽሐል።
አመልካች ለጉዳቱ ከመኪናው አሽከርካሪ ጋር በአንድነትና በነጠላ ኃላፊ ተብሎ መወሰኑ በአግባቡ ነው ብለናል።
ለተጠሪ ላከፈል የሚገባው የአካል ጉዳት ካሳ መጠን ግን መታሰብ ያለበት ተጠሪ ወደፊት ስልሳ አመት እስከሚሞላቸው ድረስ ላኖሩ ይችላሉ ተብሎ ላሆን ስለሚገባው ጉዳቱ ሲደርስ ተጠሪ የነበራቸውን እድሜ (28 አመት) መነሻ በማድረግ ወደፊት የሚቀራቸው 32 አመት መሰረት ተደርጎ ላሰሳ ይገባል ብለናል።በዚህም መሰረት የተጠሪ የተጣራ ወርሃዊ ገቢ ብር 1617 መሆኑ ስለተረጋገጠ ይኼው ገንዘብ በአስራ ሁለት ወራት እና በሰላሳ ሁለት አመታት ሲባዛ የሚመጣው ውጤት (1617×12×32×30%=186,278.40) አንድ መቶ ሰማንያ ስድስት ሺህ ሁለት መቶ ሰባ ሰምንት ብር ከአርባ ሳንቲም) ለተጠሪ ላከፈል የሚገባው የአካል ጉዳት ካሳ ነው ብለናል።ልሎች የክፍያ አይነቶችን በተመለከተ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ አልተነካም።ተጠሪ የዳኝነት መክፈል ያለባቸው በዚህ ችሎት በተወሰነው የካሣ መጠን ነው ብለናል።
በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።
በመዝገቡ ነሐሴ 09 ቀን 2005 ዓ/ም ተሰጥቶ የነበረው እግድ ተነስቷል።ለሚመለከታቸው አካላት ይፃፍ።
No topics extracted.