No summary available.
መጋቢት 22 ቀን 2006 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ አዳነ ንጉሤ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- መተሃራ ስኳር ፋብሪካ ነ/ፈጅ አሉላ ድንቂሳ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ለራሳቸውና ለልሎች ወኪል ጥበቡ እሸቱ ቀረቡ።
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/1996ን መሰረት አድርጎ የቀረበን የሥራ ክርክር የሚመለከት ሲሆን፤ ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪዎች ባሁኑ አመልካች ላይ በምስራቅ ኦሮሚያ አሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የተጠሪዎች የክስ ይዘትም ባጭሩ፡- ከአመልካች ጋር መስርተው የነበረውን የሥራ ውል አዋጅ ቁጥር 714/2003 አንቀጽ 197 ድንጋጌን በሚቃረን ሁኔታ ከሥራ የተቀነሱ መሆኑን ጠቅሰው እርምጃው ሕገወጥ ነው ተብሎ ወደ ሥራ እንዲመልሳቸው ወይም ሕጋዊ ክፍያዎችን እንዲከፍላቸው ይወሰንላቸው ዘንድ፣ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስም የግል የሥራ ክርክር በመሆኑ በቦርዱ ላታይ እንደማይገባ፤ ክሱም በይርጋ የታገደ መሆኑን በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያነሳ ሲሆን፣ በፍሬ ነገር ደረጃም ተገቢ ነው ያለውን የክርክር ነጥብ አንስቷል። ቦርዱም ጉዳዩን መርምሮ የአንድ መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሰዎች ክስ ጥቅምት 09 ቀን 2005 ዓ.ም የተመሰረተ መሆኑን ጠቅሶና ጥያቄውም ከሥራ ያላግባብ ስለተቀነስን ወደ ሥራ ይመልሰን የሚል በመሆኑ፤ ቦርዱ ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን እንደአለው፣ ሆኖም እነዚህ ሰዎች ሐምል 25 ቀን 2005 ዓ.ም ከቀረበው የአሥራ አራት ሰዎች ክስ ጋር ተቀላቅሎ የሥራ ውሉ የካቲት 01 ቀን 2004 ዓ.ም ከተቋረጠ በኋላ መቅረቡ ተቀባይነት እንደልለውና ክሱም በይርጋ የታገደ መሆኑን፤ የ14 ሰዎች ክስ ግን ሐምል 27 ቀን 2004 ዓ.ም መቅረቡንና ጊዜውን የጠበቀ ቢሆንም ጥያቄው በክፍያ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ በቦርዱ ሥልጣን ስር እንደማይወድቅና የመደበኛ ፍርድ ቤት ሥልጣን መሆኑን ጠቅሶ መዝገቡን ዘግቷል። የአሁኑ ተጠሪዎች በዚህ የቦርዱ ብይን ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቅርበው ፍርድ ቤቱ ጉዳዩ ላይ ግራ ቀኙን ከአከራከሩ በኋላ መርምሮ በሰጠው ውሣኔ የተጠሪዎች ጥያቄ ከራሳቸው አልፎ ልሎች ሰራተኞችን የሚነካ ነው። ይህም የወል የሥራ ክርክር ያደርገዋል። ይርጋም ቢሆንም ክሱ መጀመሪያ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ላታሰብ የሚገባውና ጊዜውም ያላለፈ ነው ወደሚለው ድምዳሜ ደርሶ የቦርዱን ብይን ሽሮ ቦርዱ በፍሬ ጉዳዩ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ ዳኝነት ላሰጥበት ይገባል በማለት ጉዳዩን መልሶለታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ጉዳዩ የወል የሥራ ክርክር ነው። በይርጋው የሚታገድ አይደለም ተብሎ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት መወሰኑ ያላግባብ ነው የሚል ሲሆን፤ አቤቱታው ተመርምሮም በዚህ ችሎት እንዲታይ የታዘዘ ሲሆን፣ ተጠሪዎች ቀርበውም ግራ ቀኙ በጽሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን፤ ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም በቅድሚያ የችሎቱን ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ነጥብ ጉዳዩ በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት ለመታየት የመጨረሻ ፍርድ አግኝቷል ወይስ አላገኘም የሚለው ሆኖ ተገኝቷል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች ድርጅት በፍድራል መንግሥት አካል ቢሆንም ግራ ቀኙን የሚያከራክረው ጉዳይ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 መሰረት የተመሰረተውን የቅጥር ውል መነሻ ያደረገ ጉዳይ መሆኑን ነው።
በመሰረቱ የኢትዮጵያ ፍድራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብላክ በፍድራል መንግሥትና በክልሎች መዋቅሩን መሰረት በማድረግ የዳኝነቱም ሥልጣን በፍድራል መንግሥት እና በክልል መንግሥታት መካከል እንደተከፋፈለ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 50 እና 51 ሥር ተመልክቷል።
በኢ.ፍ.ዲ.ሪ. ሕገ መንግሥት በአንቀጽ 80 የፍ/ቤቶች ጣምራነትና ሥልጣን በሚል ርዕስ በፍድራል ጉዳዮች ላይ የበላይና የመጨረሻ የዳኝነት ሥልጣኑ በፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ በክልል ጉዳዮች ላይ በክልሉ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሥልጣኑ የተደነገገ ሲሆን፣ የክልል ፍ/ቤቶች በሕገ - መንግሥቱ የተሰጣቸው የውክልና ሥልጣን መሰረት ካልሆነ በቀር የፍድራልን ጉዳይ ለማየት፤ እንዲሁም የፍድራል ፍ/ቤቶች የክልልን ጉዳይ ለማስተናገድ የሚያስችል ሥልጣን የልላቸውም መሆኑን በዚሁ ድንጋጌ ስር የተቀመጡት ንዑስ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ያሳያል። አንድ ጉዳይ የፍድራል ነው ወይስ የክልል የሚለውን ለመለየትም መሰረቱ የአዋጅ ቁጥር 25/88 ሲሆን፤ በዚሁ ሕግ አንቀጽ 5 ሥር በተመለከቱት ጉዳዮች ላይ ብቸኛ ሥልጣን ያላቸው የፍድራል ፍ/ቤቶች ናቸው። በእነዚህ ጉዳዮች ላይ የክልል ፍ/ቤቶች ሥልጣን የሚኖራቸው በሕገ-መንግሥቱ በተሰጣቸው የውክልና ሥልጣን አግባብ ብቻ ነው። ይህ በግልጽ የሚያሳየው በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 5 መሰረት የፍርድ ቤቶች ሥልጣን በጉዳዩ ባለቤትነት Subject matter የሥልጣን ክፍፍል እንደተጠበቀ ሆኖ ክሱም መቅረብ ያለበት ጉዳዩን አይቶ ለመወሰን የሥረ -ነገር ሥልጣን ላለው ፍ/ቤት ስለመሆኑ ነው። የፍድራል ፍ/ቤቶችን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 8፣11፣14 እና 15 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ደግሞ አንዳንድ ጉዳዮች ላያስነሱ በሚችሉት የክርክር ባህርይ ምክንያት ለተወሰኑ ፍ/ቤቶች እንዲቀርቡ በሕግ ተለይተው ከተመለከቱት በቀር የሥረ - ነገር ሥልጣን የተደለደለው በክሱ በተመለከተው የገንዘብ ወይም የንብረት ግምት መነሻ እንደሆነ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 14 እና 15 ስር ከተመለከቱት ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ እና የክልል መንግሥታት ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ ሕጐች ያስረዳሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን አዋጅ ቁጥር 25/1988ን ያወጣው የፍድራል መንግሥት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ክርክሮች የሚመሩበትን ሥርዓት የዘረጋውን አዋጅ ቁጥር 377/1996 ከየካቲት 18 ቀን 1996 ዓ.ም ሥራ ላይ ያዋለ ሲሆን፤ በዚህ አዋጅ የሥራ ክርክር ሥልጣን ድልድል የተደረገው የግል የሥራ ክርክርና የወል የሥራ ክርክር የሚሉትን ጉዳዮችን መሰረት በማድረግ ሲሆን፣ የተከራካሪ ወገንን ማንነትን ግንዛቤ ውስጥ ባስገባ መልኩ አይደለም። በመሆኑም ክርክሮቹ ክልል የተነሱ ቢሆንም ጉዳዩን የክልል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ወይም አግባብነት ያላቸው የቋሚ ወይም ጊዚያዊ ቦርዶች ላመለከቱ እንደሚችሉ አድርጎ ሕጉን ሕግ አውጪው አውጥቷል። ይህ አዋጅ ከአዋጅ ቁ
No topics extracted.