No summary available.
የካቲት 11 ቀን 2006 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ አዳነ ንጉሤ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጠበቃ አውላቸው ደሣለኝ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ካፒቴን እንድሪያስ ጀምሬ ጠበቃ ዶ/ር ያሬድ ለገሰ ቀረቡ።
መዝገቡን ከሰ/መ/ ጋር አጣምረን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 እና ይህንኑ አዋጅ ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 494/1998 መሰረት የሥራ ስንብት ክፍያ የሚከፈልበትን ሕጋዊ አግባብ የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን፤ ከሣሽ የነበሩት የአሁኑ ተጠሪ ናቸው። ተጠሪ በአመልካች ላይ ክስ የመሰረቱት በአመልካች ድርጅት ውስጥ ከመጋቢት 10 ቀን 1987 ዓ.ም ጀምሮ በአውሮፕላን አብራሪነት የሥራ መደብ ተቀጥረው በወር ያልተጣራ ብር 91623.60 እየተከፈላቸው ሲሰሩ ቆይተው የአንድ ወር የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ሰጥተው የሥራ ውላቸውን ያቋረጡና ንብረቶቹን ያስረከቡ ቢሆንም አመልካች ድርጅት ሕጋዊ ክፍያዎችን ያልፈፀመላቸው መሆኑን ጠቅሰው ክፍያዎቹ እንዲከፈሐቸው እና የሥራ ምስክር ወረቀት እንዲሰጣቸው ይወሰን ዘንድ ዳኝነት በመጠየቅ ነው። አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስም ተጠሪ አመልካችን በገበያ ውድድር ለመጣል በሚታገሉት ድርጅቶች ተጠቂ በመሆን ሥራቸውን የለቀቁ መሆኑን፤ ይህ ደግሞ አመልካች አብራሪዎችን ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ለማሰልጠን ከሚያስብበት መሰረታዊ ዓላማና ከአጠቃላይ የአገር ጥቅምና ደህንነት ጋር የማይሄድ መሆኑን፤
እንዲሁም ለአመልካች ድርጅት ሕልውና አደገኛ መሆኑን ዘርዝሮ የተጠሪን የማስጠንቀቂያ መስጠትን እና ሥራ መልቀቅን ሕጋዊነት የተቃወመ ሲሆን፤ ክፍያዎችን በተመለከተም ክፍያ ለዘገዬበት ጊዜ የሶስት ወር ደመወዝ የሚከፍልበት አግባብ ያለመኖሩን፣ የዓመት ፈቃድ ደግሞ በይርጋ የታገደ ከመሆኑም በላይ ተጠሪ ያላቸው የዓመት እረፍት ቀናት ብዛት በጥቅሉ 64 ብቻ መሆናቸውን፤ የሥራ ስንብት ክፍያም ተጠሪ ከሚሰሩበት ለየት ያለ የሥራ ሁኔታ ላያገኙ ከነበረው ከፍተኛ ገቢ፣ ከአገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ አንፃር እና ሥራቸው በዓለም አቀፍ ዘርፍ ሳይቀር ካለው ተፈላጊነት አንፃር እንደሕጉ መንፈስ አሰሪው ላሞላው የሚገባው ክፍተት አለ የሚያስብል ካለመሆኑ አንፃር ጥያቄው ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክሯል።
ክሱን ያስተናገደው ፍ/ቤትም የሁለቱን ወገኖች ክርክር ከሰማ በኋላ የስንብት ክፍያን በተመለከተ ተጠሪ እንደሚገባቸውና መጠኑም ብር 253846.49 ክፍያ ለዘገዬበትም ላከፈል የሚገባ ክፍያ ደግሞ የአንድ ወር ተኩል ደመወዝ ብር 144935.40 የስልሳ አራት ቀናት የዓመት ፈቃድ ወደ ብር ሲቀየር ብር 206129.92 በድምሩ ብር 604911.81ስድስት መቶ አራት ሺህ ዘጠኝ መቶ አሥራ አንድ ብር ከሰማንያ አንድ ሣንቲም አመልካች ለተጠሪ ላከፍል ይገባል በማለት ወስኗል። በዚህ ውሣኔ የአሁኑ አመልካችም ሆነ ተጠሪ በከፊል ባለመስማማት ይግባኙን ለፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው የአመልካች ይግባኝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 የተሰረዘ ሲሆን፤ በተጠሪ ይግባኝ ላይ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን መርምሮ የስር ፍርድ ቤት ለሥራ ስንብቱ መሰረት ያደረገው ስልት ተገቢ ያለመሆኑን፣ ወጪና ኪሣራን በተመለከተም በስር ፍርድ ቤት የተወሰነበት አግባብ ሕጋዊ ተቀባይነት የልለው መሆኑን ፍርድ ቤቱ ደምድሞ የሥራ ስንብቱ በጠቅላላው ብር 517673.70 እንዲሆን። ወጪና ኪሣራን በተመለከተ ደግሞ የተጠሪ ዝርዝር የማቅረብ መብታቸውን ጠብቆ የስር ፍርድ ቤትን ውሣኔ በእነዚህ ነጥቦች ብቻ በማሻሻል ወስኗል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ተጠሪ 93 828ክፍያ እንዲከፈል መደረጉ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 39 እና አዋጅ ቁጥር 494/1998 አንቀጽ 2ሸ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ፤ እንዲሁም ስለድንጋጌዎች ከተሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ውጪ ነው ሲል፤ በዚህ ረገድ የተሰጠው ውሣኔ እንዲሻር ዳኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም ለተጠሪ የሥራ ስንብት ክፍያ እንዲከፈል መወሰኑ ስለሥራ ስንብት ክፍያ በፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከተሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም አንፃር ተገቢ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዳዩ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ የተደረገ ሲሆን፤ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበውም ግራቀኙ በጽሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን፣ ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዳዩ ለሰበር ችሎት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ በአመልካች ድርጅት ውስጥ ተቀጥረው በወር ያልተጣራ ብር 91623.60 ወርሃዊ ደመወዝ ሲከፈላቸው እንደነበር፤ ከቅጥር ጊዜው ጀምሮ ሥራውን እስከለቀቁበት ጊዜ ድረስ ያለው አገልግሎታቸውም ከአሥራ ሰባት ዓመታት በላይ መሆኑንና ሥራውንም በገዛ ፍቃዳቸው የለቀቁ መሆኑን ነው። ወደ ሕጉ ስንመጣ ቢያንስ አምስት ዓመት በአሰሪው ዘንድ የሥራ አገልግሎት ኖሮት በሕመም ወይም በሞት የሥራ ውሉ ሲቋረጥ፤ ወይም ሥራው ላይ የሚያስቆይ ከሥልጠና ጋር የተያያዘ ለአሰሪው የውል ግድታ ሳይኖርበት ሥራውን በገዛ ፈቃዱ ሲለቅ ከሥራ የተገለለ ሰራተኛ የሥራ ስንብት ክፍያ የማግኘት መብት እንዳለው በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 494/98 አንቀጽ 22ሸተመልክቷል። ይህ ከሕጉ በስተጀርባ ያለው ምክንያት ሲሆን፣ የሥራ ስንብት ክፍያ ጥያቄ ተቀባይነት የማያገኝበት አግባብ በሕጉ እንደተመለከተው ሰራተኛው ሥራው ላይ የሚያስቆይ ከሥልጠና ጋር የተያያዘ ለአሰሪው የውል ግድታ ያለበት ከሆነ ነው። ሕጉ የአገልግሎት ዘመኑ አምስት ዓመትና ከዚያ በላይ መሆኑ ግንዛቤ ውስጥ ሳይገባ ሰራተኛው ግድታውን ሳይወጣ የሥራ ስንብት ክፍያ መጠየቅ የማይችል መሆኑን በግልጽ ከሚያሳይ በስተቀር አንድ ሰራተኛ ከፍተኛ ደመወዝ ሲከፈል የነበረ ከሆነ የሥራ ስንብት ክፍያ አይገባውም በሚል ያስቀመጠው መለኪያ የለም። ሕጉ ግልጽ ከሆነ ደግሞ ሕጉን እንዳለ ከመተግበር ውጪ ትርጉም የሚሰጥበት አግባብ አይኖርም። አመልካች ድርጅት ከሰራተኞቹ ጋር ያለው ግንኙነት የሚገዛው በአዋጅ ቁጥር 377/1996 መሆኑ ግልጽ እስከ ሆነ ድረስ በአዋጁ የተቀመጡትን ድንጋጌዎች ተግባራዊ ማድረግ የግድ የሚል መሆኑን ከአዋጁ ጠቅላላ ድንጋጌዎች እና ከኢ.ፍ.ዲ.ሪፐብላክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 793 እና በሥነ ሥርዓት ሕጉ ስለዳኝነት አሰጣጥ ከተደነገጉት ድንጋጌዎች ይዘት የምንገነዘበው ጉዳይ ነው። ስለሆነም ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ የሥልጠና ግድታ ያለበት ሰራተኛ ግድታውን ሳይወጣ የሥራ ስንብት ክፍያ ጥያቄ ሲያቀርብ ተቀባይነት እንደማይሰጠው፤ በሰ/መ/ ደግሞ ስለሥራ ስንብት ክፍያ የሰጣቸው አስገዳጅ የሕግ ትርጉሞች የሥራ ስንብት ክፍያና የፕሮቪደንት ፈንድ አንድ ላይ ላከፈሉ የሚችሉበት አግባብ መኖር ያለመኖሩን ለማየት ይቻል ዘንድ የሁለቱን ክፍያዎች መሰረታዊ ዓላማ መመሳሰል ከማመላከቱ ውጪ የሰራተኛውን የደመወዝ መጠን ከፍተኛነት ግንዛቤ ውስጥ አስገብቶ የሥራ ስንብት ክፍያ የሚከፈልበትን አግባብ በተመለከተ አስገዳጅ የሕግ ትርጉም የሰጠ ባለመሆኑ በመዛግብቱ የተሰጠው ትርጉም ተጠሪ ከሥልጠና ጋር በተያያዘ ለአመልካች ግድታ ያለባቸው ወይም የፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ ስለመሆናቸው ያልተረጋገጠ በመሆኑ ለዚህ ጉዳይ ተፈጻሚነት ያላቸው አይደሉም። በመሆኑም አመልካች የተጠሪን የደመወዝ መጠን ከፍተኛነት መሰረት አድርጎ ያቀረበው ቅሬታም ሆነ የሰበር አጣሪ ችሎት ጉዳዩን ለሰበር ሰሚ ችሎት ለማስቀረብ የጠቀሳቸው መዛግብት ውስጥ አስገዳጅ የሕግ ትርጉም የተሰጠባቸው ምክንያቶች ተጠሪ የሥራ ስንብት ክፍያ እንዲያገኙ ለማድረግ የሚያስችሉ ሁነው ያላገኘን በመሆኑ፤ በዚህ ረገድ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት የውሣኔ ክፍል መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
ተጠሪ የሥራ ስንብት ክፍያ ይገባቸዋል ተብሎ በፍድራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ የካቲት 28 ቀን 2005 ዓ.ም የተወሰነውና በፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ሰኔ 11 ቀን 2005 ዓ.ም በትዕዛዝ የፀናው የውሣኔ ክፍል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
የሥራ ስንብት ክፍያ መጠኑን በተመለከተም በፍድራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ የካቲት 28 ቀን 2005 ዓ.ም ተወስኖ በፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ሐምል 02 ቀን 2005 ተሻሽሎ የተሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 3481 መሰረት ፀንቷል። በወጪና ኪሣራ ላይ የተጠሪን የወጪና ኪሣራ ዝርዝር በመጠበቅ በፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠው የውሣኔ ክፍል ክፍያ ለዘገየበትና ለዓመት ፈቃድ ክፍያ ደግሞ በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሙሉ በሙሉ የፀናው የውሣኔ ክፍል በዚህ ችሎትም አልተነካም።
በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።
ሐምል 18 ቀን 2005 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረው እግድ ተነስቷል። ለሚመለከታቸው ይጻፍ ብለናል።
No topics extracted.