No summary available.
ሐምል 14 ቀን 2006 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽላት ይመሰል አመልካች፡- ሙኒሽ ካፍ ድርጅት(ሙኒሽ ጀርመን ቤከር እና ካፍ) ጠበቃ ወርቁ ፉንታሁን ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ዳዊት ፀጋው - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዳዩ የአሰሪና ሰራተኛ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም በፍ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ ተጠሪ በአሁኑ አመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ ነው።በ15/05/2005 ዓ.ም.አዘጋጅተው ያቀረቡት ክስ ይዘትም ባጭሩ፡-ከሳሽ ከ24/01/2004 ዓ.ም.ጀምሮ በብር 900 የወር ደመወዝ በተከሳሽ ድርጅት ውስጥ በባሬስታ የስራ መደብ ተቀጥረው በመስራት ላይ እያሉ ተከሳሽ ድርጅት ከ30/04/2005 ዓ.ም. ጀምሮ የስራ ውላቸውን አላግባብ እንዳቋረጠ የሚገልጽ ሆኖ ስንብቱ ሕገ ወጥ ነው ተብሎ ተከሳሽ ድርጅት ከሕገ ወጥ የስራ ስንብት ጋር የተያያዙትን እና ልሎች ክፍያዎችን እንዲከፍላቸው ይወሰን ዘንድ ዳኝነት የተጠየቀበት ሲሆን ተከሳሽ ድርጅት በበኩሉ በ16/07/2005 ዓ.ም. በሰጠው መልስ ተከሳሽ ከስራ እንዲሰናበቱ የተደረገው ከ03/05/2005 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ዋናው መ/ቤት ተዛውረው እንዲሰሩ በ01/05/2005 በተጻፈ ደብዳቤ ተገልጾላቸው እያለ በተዛወሩበት ቦታ ከአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት በላይ በስራ ላይ ባለመገኘታቸው በሕጉ አግባብ መሆኑን ገልጾ ከዓመት ፈቃድ ክፍያ ብር 519 ውጪ ከሳሽ ጥያቄ ያቀረቡባቸው ሕገ ወጥ የስራ ስንብት የሚያስከትላቸው የክፍያ ዓይነቶች ጥያቄ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
ፍ/ቤቱም ክሱን እና የግራ ቀኙን ምስክሮች ሰምቶ አጠቃላይ ክርክሩን ከመረመረ በኋላ ከሳሽ እንዲሰናበቱ የተደረገው በተዛወሩበት ቦታ በመደዳው ከአምስት የስራ ቀናት በላይ ከስራ በመቅረታቸው ምክንያት እንደሆነ በማስረጃ በመረጋገጡ ስንብቱ ሕገ ወጥ ነው ተብሎ የተለያዩ ክፍያዎች እንዲፈጸሙላቸው አመልካች ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት የልለው መሆኑን፣ ላከፈላቸው የሚገባው የ17.5 ቀን የዓመት ዕረፍት ክፍያ ብር 525.00 ብቻ መሆኑን፣ተከሳሽ ተገቢውን የስራ ልምድ የምስክር ወረቀት አዘጋጅቶ ለከሳሽ መስጠት የሚገባው መሆኑን፣ከሳሽ ክፍያ ለዘገየበት የ3 ወር ደመወዝ እንዲከፈላቸው የጠየቁ ቢሆንም በእጃቸው የሚገኙ ንብረቶች ካሉ አስረክበው ክላራንስ ከያዙ በኋላ ክፍያ እንዲፈጸምላቸው ጠይቀው የዘገየ ክፍያ ስለመኖሩ ስላላስረዱ ጥያቄአቸው ተቀባይነት የልለው መሆኑን ገልጾ የተከሳሽን የወጪና ኪሳራ ዝርዝር የማቅረብ መብት በመጠበቅ ጭምር ውሳኔ የሰጠ ሲሆን በከሳሽ ጠያቂነት ይግባኙን የተመለከተው የፍ/ከ/ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የስር ፍ/ቤት ውሳኔን አሻሽሎ ልላውን የውሳኔ ክፍል ሲያጸና ክፍያ የዘገየበትን እና የወጪና ኪሳራ ዝርዝር የማቅረብ መብትን በተመለከተ ግን ውሳኔውን ሽሮ በአዋጁ አንቀጽ 36 መሰረት የዓመት ዕረፍት ክፍያውን ተከሳሽ በሰባት ቀናት ውስጥ መክፈል የሚጠበቅበት ሆኖ እያለ ከሳሽ ማስጠንቀቂያ ከሰጡበት ጊዜ ጀምሮ ክፍያውን ለመክፈል አዘጋጅቶ ከሳሽ በራሱ ጥፋት ሳይወስድ ያዘገየ ስለመሆኑ በማስረጃ አስደግፎ እንዳልተከራከረ ገልጾ በአዋጁ አንቀጽ 38 መሰረት ተከሳሽ ድርጅት ክፍያ ለዘገየበት የ3 ወር ደመወዝ ለከሳሽ እንዲከፍል በማለት እና ለተከሳሽ ተጠብቆ የነበረውን የወጪና ኪሳራ ዝርዝር የማቅረብ መብት በመሰረዝ ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች አቤቱታውን ለዚህ ችሎት ያቀረበው ይዘቱ ከላይ የተመለከተው የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ላታረም ይገባል በማለት ሲሆን የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ በዚህ ጉዳይ የስራ ውል ሲቋረጥ ለሰራተኛ ላከፈል የሚገባው ክፍያ ዘገየ የሚባልበትን እና ዘገየ ለተባለ ክፍያ እስከ ሶስት ወር ደመወዝ የሚደርስ ክፍያ እንዲፈጸም የሚወሰንበትን አግባብ ተጠሪው ባሉበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዳዩ ለሰበር ክርክር እንዲቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።
የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለክርክሩ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር መርምረናል።
በዚህም መሰረት ከስራ ውል መቋረጥ ጋር ተያይዞ ከአሰሪው ቁጥጥር ውጪ በሆነ ምክንያት ካልሆነ በቀር በአንቀጽ 36 በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ አሰሪው ለሰራተኛው መከፈል የሚገባውን ሂሳብ ካልከፈለ ክፍያው ለዘገየበት ጊዜ ለሰራተኛው እስከ ሶስት ወር ለመድረስ የሚችል ደመወዙን ያህል አሰሪው እንዲከፍለው የስራ ክርክር ችሎት ላወስን እንደሚችል በአዋጁ አንቀጽ 38 የተመለከተ ሲሆን ክፍያውን በአዋጁ አንቀጽ 36 በተመለከተው የሰባት የስራ ቀናት ጊዜ ውስጥ መክፈል ያልተቻለው ከአሰሪው ቁጥጥር ውጪ በሆነ ምክንያት በተለይም በአንቀጽ 36 እንደተገለጸው ሰራተኛው ከአሰሪው የተረከበውን ንብረት የማስረከብ ወይም የሚፈለግበትን ማንኛውንም ሂሳብ የማወራረድ ግድታውን ባለመወጣቱ ምክንያት ሆኖ ከተገኘ አሰሪው በአንቀጽ 38 የተጠቀሰውን ክፍያ የመክፈል ግድታ የልለበት መሆኑን ከድንጋጌዎቹ ይዘት መገንዘብ ይቻላል።
ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት አመልካች ክፍያ አዘግይቷል ከሚል ድምዳሜ ላይ የደረሰው የዓመት ዕረፍት ክፍያውን በሰባት ቀናት ውስጥ መክፈል የሚጠበቅበት ሆኖ እያለ ተጠሪ ማስጠንቀቂያ ከሰጡበት ጊዜ ጀምሮ ክፍያውን ለመክፈል አዘጋጅቶ ተጠሪ በራሱ ጥፋት ሳይወስድ ያዘገየ ስለመሆኑ በማስረጃ አስደግፎ አልተከራከረም በማለት ነው።
በመሰረቱ ተጠሪ በፍ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ ክፍያ ለዘገየበት የሶስት ወር ደመወዝ እንዲከፈላቸው በግልጽ ስለመጠየቃቸው ፍ/ቤቱ በውሳኔው ላይ አስፍሯል።አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስ በተጠሪው የተጠየቁ ልሎች መብቶችን እና የክፍያ ዓይነቶችን ክዶ የተከራከረ ሲሆን የዓመት ዕረፍት ክፍያውን በተመለከተ ግን በክፍያው መጠን ላይ ከመከራከር ውጪ ይህ ክፍያ የማይገባቸው ስለመሆኑ እና ይህ በአሰሪው የታመነው የክፍያ ዓይነትም በአዋጁ አንቀጽ 36 መሰረት በሰባት የስራ ቀናት ውስጥ ለሰራተኛው ሳይከፈል የቀረው ሰራተኛው ከአሰሪው የተረከበውን ንብረት የማስረከብ ወይም የሚፈለግበትን ማንኛውንም ሂሳብ የማወራረድ ግድታውን ባለመወጣቱ ምክንያት በመሆኑ ክፍያ ለዘገየበት በተጠሪ የተጠየቀውን ቅጣት የመክፈል ግድታ የልለበት ስለመሆኑ ገልጾ ያቀረበው ክርክር ስለመኖሩ የመዝገቡ ግልባጭ አያመለክትም።ተጠሪው የሚፈለግበትን ንብረት የማስረከብ እና ሂሳብ የማወራረድ ግድታ አልተወጣም የሚለውን የክርክር ነጥብ አመልካች በሰበር ደረጃ ከማቅረቡ በቀር በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤትም ቢሆን የዚህ ዓይነት ክርክር አቅርቦ የነበረ ስለመሆኑም መዝገቡ አያመለክትም።የታመነውን ክፍያ ያዘገየሁት ተጠሪው የበኩሉን ግድታ ባለመወጣቱ ነው በሚል አመልካች በሁለቱ የስር ፍ/ቤቶች አንስቶ ያልተከራከረበትን ነጥብ ደግሞ በሰበር ደረጃ በመከራከሪያነት ማንሳቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 329(1) ድንጋጌ የተመለከተውን የክርክር አመራር ስርዓት የተከተለ ባለመሆኑ ሕጋዊ ተቀባይነት ላሰጠው የሚችል ሆኖ አልተገኘም።አመልካች በዚህ ነጥብ ላይ በስር ፍ/ቤቶች ያቀረበው መከራከሪያ የለም በማለት ተጠሪ በሰበር መልሳቸው ያቀረቡትን ክርክርም አመልካች አላስተባበለም።እንዲህ ከሆነ ደግሞ አመልካች ክፍያ ላዘገየበት በአዋጁ አንቀጽ 38 መሰረት የሶስት ወር ደመወዝ ለተጠሪው በቅጣት መልክ እንዲከፍል በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔ ላነቀፍ የሚችልበት ሕጋዊ ምክንያት የለም።
ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት የፍ/ከ/ፍ/ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ ስላልተገኘ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
የፍ/የመ/ደ/ፍ/ቤት በመ.ቁ. 07894 በ11/11/2005 ዓ.ም. የተሰጠውን ውሳኔ በማሻሻል የፍ/ከ/ፍ/ቤት በመ.ቁ. 136017 በ10/06/2006 ዓ.ም. የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ፀንቷል።
የውሳኔው ቅጂ ለስር ፍ/ቤቶች ይላክ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ።
ውሳኔ ያገኘ ሰለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.