No summary available.
ሰኔ 06 ቀን 2006 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- ሉሃና አንጂነሪግ ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግል ማህበር - ጠበቃ ፍሬው ካሳሁን ቀረበ ተጠሪ፡- ማክሮ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ኃ.የተ.የግል ማህበር - ጠበቃ ሰለሞን በዳኔ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ይህ የሰበር ጉዳይ የተጀመረው በተጠሪ ከሣሽነት አመልካች በቼክ ቁጥር C-1469751 ብር 462,518.04 እንዲከፈለው ከሰጠ በኃላ ክፍያው እንዳይፈጸም አመልካቹ ለባንኩ ትእዛዝ ሰጥቶ እንዲታገድ ከመደረጉም በላይ ገንዘቡን አመልካቹ ላከፍል ፈቃደኛ አልሆነም በማለት ገንዘቡ በአመልካች እንዲከፈለው ይወሰን ዘንድ በተፋጠነ ስነ ስርዓት በፍድራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረተው ክስ መነሻ ነው።
አመልካች እንዲከላከል ተፈቅዶለት ባቀረበው መልስም ቼኩ በተጠሪ እጅ ላገባ የቻለው በአመልካችና በተጠሪ መካከል መስከረም 04 ቀን 2004 ዓ/ም በተፈፀመ የኮንስትራክሽን ንዑስ ስራ ተቋራጭነት ውል ስምምነት መሰረት አድርጎ ለሚፈጸመው ቅድመ ክፍያ ለዋስትና የተሰጠ መሆኑን ፣ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የስራ ውል ስምምነት ሲፈጸም አስቀድሞ እዳ አለብኝ ተብሎ የሚሰጥም ሆነ የሚገባ የውል ስምምነት የልለ መሆኑን ፣ ቼኩ በተጠሪ እጅ የገባው ለተባለው አላማ ስለሆነ ተጠሪ እንዲፈጸምለት ለባንኩም ሆነ ለፍርድ ቤቱ ጥያቄው ከማቅረቡ በፊት በውሉ አግባብ አመልካች ያልተወጣውን ግድታ አረጋግጦ መሆን ሲገባው በቀጥታ በቼኩ ላይ የተገለጸውን ክፍያ እንዲፈጸምለት የዳኝነት ጥያቄ ማቅረቡ ተገቢነት የልለው መሆኑን ፣ ቼኩ የተሰጠው ለተባለው ዓላማ ወይም በተጠሪና በአመልካች መካከል በነበረው የግል ግንኙነት ከሆነ ደግሞ ቼኩ እንደቀረበ የሚከፈል ሰነድ ሳይሆን ተራ ሰነድ መሆኑን ፣ አመልካች ወደ ስራው ገብቶ ስራውን እያከናወነ እያለ ያልታሰበ ድንገተኛ የተፈጥሮ አደጋ በመድረሱ ንብረቶች በመጎዳታቸው ምክንያት ለተጠሪ ቅድመ ሁኔታዎችን ሰጥቶ ስራውን በወቅቱ ለማቋረጥ መገደዱን ፣ ነገር ግን ተጠሪ ባለመስማማት ውሉን በራሱ ጊዜ ማቋረጡን ዘርዝሮ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል። የስር ፍርድ ቤትም የአመልካችን መከራከሪያ ነጥቦችን ውድቅ አድርጎ ለክሱ ኃላፊ ያደረገው ሲሆን የኃላፊነት መጠኑን በተመለከተም በክሱ ላይ የገለጸውንና ልሎች ወጪዎችን እንዲሁም የኮሚሽን ክፍያ እንዲከፍል ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም የበታች ፍርድ ቤቶች ቼክ ለኮንስትራክሽን ስራ ለመያዣነት የተሰጠ መሆኑን ሳይገነዘቡና የተሰራ ስራ ስለመኖሩ እንዲሁም ተጠሪም ለተሰራው ስራ ከስራው ባለቤት ክፍያ መውሰዱ እየታወቀ ይህንኑ አልፈው አመልካች ለክሱ መሰረት የሆነውን ገንዘብ እንዲከፍል መወሰናቸው ያላግባብ ነው የሚል ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በዚህ ችሎት ላታይ የሚገባው መሆኑ ታምኖ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦ ግራ ቀኙ በጽሁፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችሎትም ጉዳዩን ለዚህ ችሎት ያስቀርባል ተብሎ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር ጉዳዩን እንደሚከተለው መርምረናል። ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሲቀርብ የተያዘው ጭብጥ በአመልካችና በተጠሪ መካከል ያለው የኮንስትራክሽን ስራ ሁኔታ ሳይጣራ ቼኩ ለተጠሪ ለክፍያ መቅረብ አልነበረበትም በማለት ያቀረበው ክርክር ታልፎ በበታች ፍርድ ቤቶች ክፍያው እንዲፈጸም የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ተብሎ በመሆኑ በዚህ አግባብ ጉዳዩን ተመልክተናል።
በመሰረቱ ቼክ የንግድ ወረቀት ከሚባሉ አንዱ ሲሆን እንደቀረበ የሚከፈል ፣ በባንክ ተቀማጭ ሂሳብ ያለው ሰው ገንዘቡ ለራሱ ወይም ለልላ ወገን እንዲከፈል ሐተታ የልለው ትእዛዝ የሚሰጥበት ፣ ገንዘብን ተክቶ ክፍያን የሚያቀላጥፍ የንግድ ወረቀት ወይም ሰነድ ስለመሆኑ ከን/ህ/ቁ.732፣827፣828 እና 854 ድንጋጌዎች ይዘት የምንገነዘበው ጉዳይ ነው። ስለሆነም ቼክ እንደቀረበ የሚከፈል የገንዘብ ሰነድ በመሆኑ በቼክ ገንዘብ ለመክፈል አውጭው በባንክ ተንቀሳቃሽ ሂሳብ የተቀመጠ የቼኩን ዋጋ አጣርቶ የሚከፈል ፣ በቂ ስንቅ /ገንዘብ/ ላኖረው የሚገባ ስለመሆኑም እርግጠኛ መሆን እንዳለበት የን/ህ/ቁ. 830(2) ድንጋጌ ያስቀምጣል። ይህንኑ በህግ የተጣለበትን ግድታ ሳይወጣ የቀረ አውጪ በቼኩ ላይ የተጻፈውን ገንዘብ /እዳ/ ለአምጪው እንዲከፍል የሚገደድ ስለመሆኑ የህጉ ይዘትና መንፈስ የሚያስገነዝበን ጉዳይ ነው። ዕዳ ከፋዩ /አውጪው/ ግድታውን እንዲወጣ የማይገደደው በህጉ የተቀመጡትን መቃሚያዎች /መከራከሪያ ነጥቦችን/ በአግባቡ ሲያስረዳ ነው። በህጉ እዳ ከፋዩ በአምጪው ላይ ላያቀርብ ይችላል ተብለው የተቀመጡት መቃወሚያዎች በን/ህ/ቁጥር 717 ስር የተመለከቱት ናቸው። እነዚህም፡- በሁለቱ የግል ግንኙነቶች ላይ የተመሰረቱ ፣ በሰነድ አጻጻፍ ፎርምና በሰነዱ ላይ በተጻፉ ቃሎች ፣ እንዲሁም ፊርማን በማስመስል የተሰራ ፣ ችሎታ ወይም ሰነዱ ሲወጣ የውክልና ስልጣን ባለመኖሩ ወይም ክስ ለማቅረብ አስፈላጊ የሆኑት ሁኔታዎችን ባለመሟላታቸው የሚነሱ መቃወሚያዎችና አምጭው ይህን ሰነድ ባገኘበት ጊዜ እዳ ከፋዩን ለመጉዳት እያወቀ ያደረገው መሆን ስለመሆናቸው የሚያሳዩ እንደሆነ ህጉ አስቀምጧል።
No topics extracted.
እንግዲህ ቼክ እንደቀረበ የሚከፈል እንደመሆኑ መጠን አውጪው ለቼኩ መውጣት ምክንያት የሆነውን ነገር የማስረዳት እና የማስተባበል ሸክም ያለበት ስለመሆኑ ከህጉ ቅርፅ ፣ ይዘትና መንፈስ በቀላሉ የምንገነዘበው ጉዳይ ሲሆን በቼኩ የተጻፈውን ገንዘብ ለመክፈል አልገደድም የሚለው አውጪው ከላይ በን/ህ/ቁጥር 717 ስር የተመለከተቱትን ሁኔታዎች በበቂ እና አሳማኝ መንገድ ማስረዳት ግድታውን ሲወጣ ነው።
በተያዘው ጉዳይ በአመልካችና በተጠሪ መካከል የኮንስትራክሽን ስራን በተመለከተ ውል መኖሩ አልተካደም። ቼኩም ለዚህ ምክንያት የተሰጠ መሆኑን አመልካች ክርክርና ማስረጃ ያቀረበበት ጉዳይ ነው። እንዲህ ከሆነ አመልካች በውሉ መሰረት የሰራው ስራ መኖር፣ የስራው መጠን ምን ያህል እንደሆነና በዚሁ ስራ መነሻ ተጠሪ ከስራው ባለቤት ክፍያ ያገኘ መሆን ያለመሆኑ በዚሁ መዝገብ ክርክር ተደርጎ በማስረጃ የማይነጥርበት የሕግ አግባብ የለም።
የአመልካች እና የተጠሪ ግንኙነት የተመሰረተው በመሃከላቸው በተደረገው የግንባታ ውል ላይ ስለመሆኑ በአመልካች በኩል ክርክር ቀርቦ በተጠሪ እስካልተካደ ድረስ ተጠሪ በተፋጠነ ስነ ስርዓት ታይቶ ይወሰንለት ዘንድ ላቀረበው ክስ መሰረት ያደረገው ቼክ ቁጥር C-1469751 በግንባታ ውሉ መነሻ የተሰጠ ስለመሆኑ አመልካች የማስረዳት መብቱ በልላ መዝገብ ሳይሆን በዚህ መዝገብ የማይታይበት የህግ ምክንያት የለም። አመልካች እነዚህን ሁኔታዎች ግምት ውስጥ በማስገባት ክሱን ይከላከል ዘንድ እንዲፈቀድለት ያቀረበው ጥያቄ ፍ/ቤቱ ከተቀበለው በኃላ የመከላከያ መልሱንና እና ማስረጃዎችን ላታይለት ይገባል እንጂ በክሱ ቼክ በመጠቀሱ ብቻ ጉዳዩ ቼክን በሚመለከቱ የንግድ ህግ ድንጋጌዎች አንጻር ብቻ በማየት በቼኩ የተመለከተው ገንዝብ ለተጠሪ እንዲከፈል ለመወሰን የሚያስገድድ አይደለም። በዚህ ረገድ አመልካች አጥብቆ የተከራከረው ቼኩ ለተጠሪ የተሰጠው አመልካች በኮንስትራክሽን ንዑስ ስራ ስምምነት መሰረት በውሉ የገባውን ግድታ ለመወጣት ፣ በውሉ ለተመለከተው የቅድሚያ ክፍያ በተወሰነ መጠን በመውሰዱ ለዚሁ ለመያዣነት እንዲሆን ነው የሚሉትን ነጥቦች በማንሳት ነው። ለዚህ የአመልካች ክርክር ግራ ቀኙ መስከረም 04 ቀን 2004 ዓ/ም ተፈረመ የተባለው የግንባታ የውል ስምምነት ቀርቦ በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው ስምምነት ቀርቦ ይዘቱና መንፈሱ ላታይና የቼኩን መሰጠት ምክንያት ማጣራት የሚያስችል ነው። ተጠሪ ቼኩ የተሰጠው በቼክነቱ እንዲከፈል እንጂ ሁኔታ ላይ /ከአመልካች የውል ግድታ መወጣት ጋር እየታየ የሚከፈል አይደለም/ የተመሰረተው አይደለም የሚል ክርክር በማንሳት በአመልካች በኩል እንዲፈጸም በውሉ የተቀመጠውን ግድታ አመልካቹ ያለመወጣቱን እንዲያስረዳ አልተደረገም። የአመልካች ክርክር የግንባታ ውል ስምምነቱ እና የሲቪል ስራ ፕሮጀክቶች ግንባታ መደበኛ ሁኔታዎች /fidic/ ጋርም ተዛምዶ የማይታይበት ምክንያት የልለ ሲሆን የስር ፍርድ ቤቶች ጉዳዩን ከእነዚህ ሁኔታዎች አንጻር ያጣሩት አግባብ ያለመኖሩን ከክርክር ሂደት ተገንዝበናል።
በንግድ ህግ ቁ.717/1/ እንደተመለከተው ዕዳ ከፋዩ ሰነዱን /ቼኩን/ በያዘው ሰው ላይ በሁለቱ የግል ግንኙነቶች ላይ የተመሰረቱት ሁኔታዎች መነሻ በማድረግ መቃወሚያ ማቅረብ ይችላል።
በያዝነው ጉዳይም ከላይ እንደተገለፀው የግንባታ ውሉ የአመልካች እና የተጠሪ የግል ግንኙነት የሚመለከት ነው።
የግንባታ ውል ስምምነት ደግሞ ሁለቱም ወገኖች በውሉ ያገኙትን መብት እና ከውሉ የሚጠበቅባቸውን ግድታ የያዘ ሰነድ ስለሆነ የገንዘብ ክፍያ የሚጠይቀው ተዋዋይ ወገን ገንዘቡን ያገኝ ዘንድ የበኩሉን ግድታ ላወጣ ይገባል። ግራ ቀኙ በውሉ ያላቸው ግድታ ታይቶና ግድታውን የተወጣ ወገን መኖር ያለመኖሩ በማስረጃ ከነጠረ በኃላ የቼኩ ክፍያ እልባት ይገባል እንጂ ይኼው ታልፎ ተጠሪ ቼክን መሰረት አድርጎ ክስ በማቅረቡ ብቻ የአመልካች የመከላከያ ማስረጃ ሳይመዘን ውድቅ የሚሆንበትን አግባብ የን/ህ/ቁጥር 717፣732፣827፣828 እና 854 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ አያሳይም። የስር ፍ/ቤቶችም ለቼኩ መሰጠት መሰረት የሆነውን ውል እና ለጉዳዩ አወሳሰን ተገቢነት ያለውን ህግ ሳይመለከቱና በተገቢው የክርክር አመራር ስርዓት ፍሬ ነገሩን ሳያጣሩ ዳኝነት መስጠታቸው ተቀባይነት የሚሰጠው ሁኖ አልተገኘም።፡ አመልካች ለመከላከል ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ካገኘ በኋላ አመልካች ከተጠሪ ጋር ያለውን ግንኙነት እና ቼኩ የተወሰደበትን ምክንያት መሰረት አድርጎ ያቀረበው ክርክር ውድቅ ሆኖ ለገንዘብ ጥያቄው ኃላፊ መባሉ የአመልካች ማስረጃዎችን የስር ፍርድ ቤት ሳይሰማና የሰነድ ማስረጃዎችንም በሕጉ አግባብ ዝርዝር ምክንያት ሳይሰጥ ታልፎ መሆኑን ተገንዝበናል። በሕግ አግባብ የቀረበን ክርክርና የተቆጠረ ማስረጃ ደግሞ ያለ ሕጋዊ ምክንያት ሳይሰማና ሳይመዘን በዝምታ የሚታለፍበት፣ አግባብነት የልለው ሕግ ተጠቅሶ ውድቅ የሚሆንበት፣ የሰነድ ማስረጃው ቀርቦ ደግሞ ይዘቱ ሳይታይ በደፈናው ውድቅ የሚደረግበት የማስረጃ አቀባበል እና የዳኝነት አሰጣጥ ስርዓትና ተቀባይነት የልለው ሲሆን የክርክሩ ፍሬ ነገሮች አግባብነት ባላቸውና በሕጉ አግባብ በተቆጠሩ የተከራካሪ ወገኖች ማስረጃዎች እንዲሁም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ በፍርድ ቤቱ አነሳሽነትም ከሚመለከታቸው አካላት በሚቀርቡት ማስረጃዎች በተገቢው መንገድ ሳይጣሩ ዳኝነት መስጠት የዳኝነት አሰጣጥ ስርዓት የማይቀበለው ጉዳይ ሲሆን የክርክሩ አካሄድ ሳይሟላ የሚሰጥ ዳኝነት ደግሞ በውጤቱ የተከራከሪ ወገኖችን የመደመጥ መብት እጅጉን የሚጎዳ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው። ሲጠቃለልም፡-
በዚህም ምክንያት ውሳኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።